Tuesday 30 December 2014

የኢንተርኔት እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መረጃዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር የሚያደርግ አዋጅ ተረቀቀ

ኢሳት

በሥራ ላይ ያለውን የብሮድካስት አዋጅ የሚሽርና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ስልክን በመጠቀም የሚቀርብ የብሮድካስት አገልግሎቶችን ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል፡፡

የኢትዮጵያ የብሮድካስት ባለስልጣን ያዘጋጀውና በዚህ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህው የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ አሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃን ማለትም ራዲዮ፣ቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም የሕትመት ሚዲያውን የሚመለከት ነው፡፡ በዚህ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንተርኔት ድረገጾች ፈቃድ ማውጣት የግድ መሆኑን ደንግጎአል፡፡ 



በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል የመረጃ መረብ አማካኝነት ለስርጭት የሚቀርብ ማንኛውም ፕሮግራም በአገር አንድነትና ሉአላዊነት ላይ አደጋ የሚጥል ፣በአገር ደህንነት፣ ክብርና ጥቅም ላይ ጉዳት የሚያደርስ ፣የአገር ሚስጢርን የሚገልጽ ፣ አመጽና ጦርነትን የሚቀሰቅስ፣ የሰው ልጆችን ስብዕና ፣ነጻነት ወይንም ስነምግባር የሚጻረር ፣የሌሎችን እምነት የሚያንኳስስ መሆን እንደሌለበት ደንግጎአል፡፡



በተጨማሪም ሥራዎቹ ማንኛውንም የህብረሰተብ ክፍል፣ ብሔር፣ጎሳ፣ቀለም፣ጾታ፣ዘር፣ቋንቋ፣ሃይማኖት፣ማህበራዊ አመጣጥ፣ ወይንም ሌላ መሰል አቋምንና ክብርን የሚነካ ወይም የሚያዋርድ፣ በህዝቦችና በሃይማኖቶች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት የሚቀሰቅስ ወይንም ጥላቻ የሚያስፋፋ፣ የግለሰብን ስም የሚያጠፋ፣፣ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን አመለካከት ስሜት የሚጎዳና ወደአልተፈለገ አቅጣጫ እንዲያዘነብሉ የሚገፋፋ፣ የህብረሰተቡን ሞራል የሚጥስ ወይንም በሕግ የተከለከለ ማንኛውንም ድርጊት የሚፈጽም መሆን የለበትም ይላል፡፡

Wednesday 24 December 2014

አየር ሃይል እየታመሰ መሆኑን ምንጮች ገለጹ

  የአየር ሃይል ባልደረባ የሆኑት ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ ከበረራ ቴክኒሻኑ ጸጋ ብርሃን ግደይ ጋር በጋራ በመሆን የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ከጠፉ በሁዋላ የአየር ሃይል አዛዦች አስቸኳይ ግምገማ ከተጠሩ በሁዋላ እርስ በርስ እየተገማገሙና ከእነዚህ ሰዎች ጋር ግንኙነት አላቸው ብለው የሚያስቡትን የአየር ሃይል አባላት ለማሰር እንቅስቃሴ መጀመራቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በተለይም የትግራይ ተወላጅ ከሆኑት ሻምበል ሳሙኤል ግዴይና ቴክኒሻኑ ጸጋ ብርሃን ጋር የቅርብ ግንኙነት አላቻው የተባሉ ሰዎች እየተጠሩ በመጠየቅ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሎአል። የመከላከያ ሚኒስትር ሻምበል ሳሙኤል ግደይን ከሃዲ ሲል ሲፈርጀው፣ መቶ አለቃ በልልኝ ደሳለኝንና ቴኒኪሻን ጸጋ ብርሃንን ደግሞ ተገደው መብረራቸውን ገልጿል። ፋሲል የኔአለም ዝርዝር አለው።
የኢሳት ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት ከፍተኛ የበረራ ልምድ ያላቸው ሻምበል ሳሙኤል የህወሃት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ አየር ሃይል ላይ የሚያደርሱትን ጥፋት ከሚቃወሙት የትግራይ ተወላጆች መካከል አንዱ ነው። መቶ አለቃ ቢልልኝ ደግሞ በአየር ሃይል ውስጥ የተስፋፋውን ዘረኝነት ከሚኮንኑ አብራሪዎች መካከል መሆኑ ታውቋል። በ2 ሺ ዓም አየር ሃይልን የተቃለቀለው መቶ አለቃ ቢልልኝ ሱዳን ውስጥና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሄሊኮፕተር በማብረር ብቻውን የተለያዩ ግዳጆችን መወጣቱን ምንጮች ገልጸዋል። ሁሉም ስርዓቱን በመቃወም ጥለው የጠፉ እንጅ፣ መንግስት እንዳለው አንዱ ሌላውን አስገድዶ እንዲጠፋ አለማድረጉን ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁት ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። 

በሌላ በኩል መንግስት አብራሪዎቹ ሄሊኮፕተሩን ኤርትራ አሳርፈውታል የሚል መግለጫ ቢሰጥም፣ የኤርትራ መንግስት ምንም መግለጫ አልሰጠም። ኢሳት ሄሊኮፕተሩ የት እንዳረፈ ለማወቅ ያደረገው ሙከራም እስካሁን አልተሳካለትም።


በአየር ሃይል አዛዦች ውስጥ የተፈጠረውን ትርምስ ተከትሎ ኮሎኔል አበበ ተካና በብርጋዴር ጄኔራል ማሾ ሃጎስ እርስ በርስ መወነጃጀል ጀምረዋል። 
ኮሎኔል አበባ ተካ በህወሃት መሪዎች ዘንድ የሚወደዱ በመሆናቸው አየር ሃይልን ከጀርባ ሆነው እስካሁን ሲመሩት ቆይተዋል። አለቃቸው ብርጋዴር ጄኔራል ማሾ ሃጎስ ደግሞ ከህወሃት ባለስልጣናት ጋር በሚፈጥሩት አለመግባባት የተነሳ ስልጣን ሳይኖራቸው በስም ብቻ ተንሳፈው የሚኖሩ ናቸው። ብርጋዴር ጄኔራል ማሾ ቀደም ብሎ ከአየር ሃይል አዛዡ ሞላ ሃይለማርያም ጋር ከፍተኛ ጸብ ውስጥ ገብተው የነበር ሲሆን፣ ከኢታማጆር ሹሙ ሳሞራ የኑስ ጋርም ያላቸው ልዩነት እየሰፋ ሄዶ እርስ በርስ ማውራት ማቆማቸው ይነጋራል። ከጄ/ል ማሾ ጋር በእኩል ደረጃ የነበሩ ወታደራዊ አዛዦች ቀድመዋቸው የጄኔራልነት ማእረግ ሲሰጣቸው እርሳቸው ግን ከሁለት ጊዜ በላይ እንደታለፉና በቅርቡ በተደጋጋሚ ባሰሙት ቅሬታና ህወሃትን ከመከፋፈል ለማዳን በሚል ምክንያት የብርጋዴር ጄኔራልነት ማእረግ እንዲሰጣቸው ተደርጓል። 


ጄ/ል ማሾ በሲነየርቲ ከፍተኛ የማእረግ ደረጃ ላይ መድረስ የነበረብኝ ቢሆንም፣ ከጓደኞቹ እንዳንስ ያደረገኝ ጄ/ል ሳሞራ በሚያደርስብኝ በደል ነው በሚል በተደጋጋሚ ቅሬታ እንደሚያሰሙና ከስራቸው እየቀሩ በተለያዩ ሱሶች ተጠምደው እንደሚውሉ የቅርብ ምንጮች ይገልጻሉ። ጄ/ል ማሾ ቦታውን በስም ብቻ እንዲይዙ ተደርጎ ዋናውን የበረራ ስምሪት የሚያካሂዱት ኮ/ል አበበ መሆናቸው ፣ ኮሎኔል አበበን በሚደግፉት በእነ ሳሞራ እና በጄ/ል ማሾ መካከል ያለው ውዝግብ እንዲሰፋ ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል። 


ኮ/ል አበባ ተካ አየር ሃይልን በተለይም የድሬዳዋን አየር ምድብ ማዘዝ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ አየር ሃይሉን ጥለው የሚጠፉ አብራሪዎች ተበራክተዋል። ባለፉት 6 ወራት ብቻ 11 አብራሪዎች አየር ሃይልን ጥለው በመጥፋት ግንቦት7ትና አርበኞች ግንባርን ተቀላቅለዋል። አብዛኞቹ ለመጥፋታቸው ከሚሰጡዋቸው ምክንያቶች መካከል ዘረኝነት፣ የተበላሸ አስተዳደራዊ አሰራር መኖርና በአገሪቱ የሚታየው የመብት አፈና የሚሉት ናቸው።


የአየር ሃይል ምንጮች እንደሚሉት ኮ/ል አበበ ተካ የውቅሮ ተወላጅ ሲሆኑ፣ በድሬዳዋ ምድብ ውስጥ ያሉ የሃላፊነት ቦታዎችን በውቅሮ ልጆች ብቻ እንዲሞሉ አድርገዋል። ቀደም ብሎ የአየር ሃይል አዛዥ የነበሩት አበበ ተክለሃይማኖት በተመሳሳይ የውቅሮ ልጅ ሲሆኑ፣ ኮ/ል አበበን አሁን ላሉበት ደረጃ ያደረሱዋቸው እርሳቸው መሆናቸውንም ምንጮች ይገልጻሉ። ኮ/ል አበበ አየር ሃይል እንዲዳከም ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን የተለያዩ አብራሪዎች ቢናገሩም፣ እስካሁን ድረስ ማንም ደፍሮ እርምጃ አልወሰደባቸውም። እርሳቸው ሃላፊ ሆነው ከተሾሙ ወዲህ በ2001 ዓም ሃምሌ ወር ላይ 2 ኤፍ ኤፍ 260 የመሰረታዊ በረራ ማስተማሪያ ሄሊኮፕተሮች ተጋጭተዋል። እርሳቸው በሰጡት የተሳሳተ አመራር 2 ኤም አይ 35 ሄሊኮፕተሮች በአየር ላይ ተጋጭተው 6 አብራሪዎች አልቀዋል። አንድ ኤፍ ኤፍ ሄሊኮፕተር ደግሞ ሁርሶ ላይ ሞተር ጦፍቶበት የወደቀ ሲሆን፣ አብረራዎቹ እንደ እድል ተርፈዋል። እነዚህ ሁሉ ችግሮች የኮ/ል አበበ የአመራር አሰጣጥ ድክመት የፈጠራቸው መሆናቸው ቢታመንም፣ ለረጅም ጊዜ ጄ/ል ሞላ እንዳይገመገሙ አድርገዋቸው እንደቆዩ ጄ/ል ሞላ ሃላፊነቱን ከለቀቁ በሁዋላ ደግሞ ጄ/ል ሳሞራ እየተከላከሉላቸው ይገኛሉ።


ኮሎኔሉ አበበ በጦር ሄሊኮፕተሮች የኮንትሮባንድ እቃዎችን ወደ ድሬዳዋ እየጫኑ ከጄ/ል ሞላ ሃይለማርያም ጋር በመሆን ሲነግዱ እንደቆዩና ከፍተኛ የሆነ ሃብት እንዳከማቹ የቅርብ ምንጮች ይገልጻሉ። በድሬዳዋ፣ አዲስ አበባና መቀሌ ሰፋፊ ቦታዎችና በአዲስ አበባም አንድ ትልቅ ፎቅ አሰርተዋል በማከራየት ላይ ናቸው። እነዚህ ሁሉ ቸግሮች ጄ/ል ማሾ ኮሎኔል አበበን ለመክሰስ በቂ ምክንያቶች ቢሆኑላቸውም፣ ከላይ ባሉ ባለስልጣናት ድጋፍ በማጣታቸው እስካሁን ውጤታማ ሊሆኑ አልቻሉም። ሰሞኑን የጠፉትን አብራሪዎች ከጄ/ል ማሾ ጋር ለማያያዝ የእነ ኮ/ል አበበ ደጋፊዎች ጥረት እያደረጉ ሲሆን፣ ከጄ/ል ማሾ ጋር ግንኙነት አላቸው ወይም አላማቸውን ይደግፋሉ ያሉዋቸውን ሁሉ ለመምታት እየተንቀሳቀሱ ነው። 


ኮ/ል አበበ ኢሳት ሊያነጋግራቸው ቢሞክርም ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ይታወቃል። ብርጋዴር ጄነራል ማሾን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።


ምንጭ የህዝባችን አይንና ጆሮ የሆነው ኢሳት

Saturday 20 December 2014

ESAT Breaking News ሁለት የኢትዮጵያ አየር ሀይል ኤም አይ 35 ሄሊኮፕተር አብራሪዎች የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ጠፉ


ሰበር ዜና

ሁለት የኢትዮጵያ አየር ሀይል ኤም አይ 35 ሄሊኮፕተር አብራሪዎች የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ጠፉ። የት እንደገቡ እስካሁን አልታወቀም።



ለኢሳት በደረሰው መረጃ የ ኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አብራሪዎቹ ሻምበል ሳሙ ኤል ግደይ እና መቶ አለቃ ቢልልኝ መኮንን ትናንት ጧት ለልምምድ እንደወጡ ነው ጠፍተው የቀሩት።

አብራሪዎቹ ከ 30 ደቂቃ በላይ እንዲቆዩ ከማይፈቀድላቸው የበረራ ራዲየስ በመውጣት የሚያበሯቸውን ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች ይዘው መጥፋታቸው ተረጋግጧል ይህ ሪፖርት እስከተጠናቀረበት ድረስ አብራሪዎች የት እንዳሉ አልታወቀም ሁለቱ ከፍተኛ የ ኢትዮጵያ አየር ሀይል አብራሪዎች በስልጣን ላይ ያለውን ስር ዓት በመክዳት ከጎረቤት ሀገሮች በአንድኛቸው ሳያርፉ  እንዳልቀረ ግምት አለ።

ኢሳት ራዲዮና ቲቪ ጉዳዩን በመከታተል ተጨማሪ መረጃዎችን ያቀርባል።

Source ESAT

ዛሬም በዋልድባ እሥራቱ እንደቀጠለ ነው “አባት ሆይ ይሄ ሁሉ ግፍና በደል የሚቆመው መቼ ይሆን?"

ሁለት ታላላቅ ሊቀ አበው ባለፈው ሳምንት ወደ ማይጸብሪ ፖሊስ ተወስደው ታስረው ተፈቱ
የእነ አባ ገብረ ሕይወት መስፍን ስልታዊ የመንግሥት ተወካይነታቸው ቁልጭ ብሎ ታውቋል
ወታደሮች ዛሬም ድረስ በገዳሙ እንደሚገኙ አባቶች ይናገራሉ፣ ምክንያታቸው ግን ምን እንደሆነ አይታወቅም
የግድቡ ሥራ ከየትም ሊደርስ ባለመቻሉ የመንግሥት ሰዎች ዓይናቸውን ወደ ሌላ ለማዞር እየሞከሩ ነው
በመስከረም ወር ላይ በችግኝ ማፍያ አካባቢ የተነሳውን የአንበጣ መንጋ ለማጥፋት በሚል መንግሥት የሚረጨው መድሃኒት በርካታ የወልቃይት አውራጃ ነዋሪዎችን ከብቶች ፍጅቶባቸዋል
መንግሥት አሁንም 3900 የሚሆኑ አባወሮችን ከመዘጋ ወልቃይት እንደሚያስነሳ እየተነገረ ነው
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ ነው ከማይጸብሪ ፖሊስ ጣቢያ የመጡ ታጣቂዎች እንደተለመደው ወደ ገዳሙ ዘልቀው በመግባት ሁለት ሊቃነ አበውን ምክንያት በሌለው ነገር እንደ ወንጀለኛ አስረው ወደ ማይጸብሪ አውራጃ ፖሊስ ጣባያ በመውሰድ በእስር ቤት አጉረው ከወንጀለኛ ጋር አሳድረው ለቀዋቸዋል፡፡ በሁኔታው ያዘኑ በርካታ መነኮሳት ምን በድለው ነው? ምን ጥፋት ተገኝቶባቸው ነው? በማለት ቢወተውቱም መልሱ ግን ግልጽ ነው። እንደሚታወቀው ዓመት ከመንፈቅ በፊት በአቶ ሲሳይ መሬሳ የሚመራው የአውራጃው አስተዳደር በአበንታንት ዋልድባ ገዳም ያለውን የነበረውን የአበውን ትውፊት ወደጎን ብለው፥ በጉልበታቸው እና በሥልጣናቸው የእግዚአብሔርን ቦታ እና ቤተመቅደስ የሚያስተዳድሩትን አባቶች በጉልባቱ መርጦ በማስቀመጥ
1ኛ/ አባ ገብረዋሕድ መምሕር የአበረንታንት መድኃኒዓለም ገዳም አበመኔት
2ኛ/ አባ ገብረሕይወት መስፍን (የቀድሞ ታጋይ) እቃ ቤት አድርጎ ከሾመ በኃላ ነው ችግሮች እየበዙ እና እየጠነከሩ የመጡት። በዚህም መሰረት በተለይ የቀድሞው ታጋይ እያንዳንዷን በገዳሙ ውስጥ የሚደረጉትን እና የሚታሰቡትን በሙሉ በመቅረጸ ድምጽ በተደገፈ ማስረጃ ለመንግሥት በማቀበል፥ በእነሱ አመለካከት “ጸረ ልማት” ወይም “ጸረ ሰላም” ናቸው ብለው የሚሏቸውን መናንያን፣ መነኮሳት እንዲሁም ባሕታውያን ጭምር በፈለጉ ጊዜ ወደ እስር እንዲጋዙ፣ በድብደባ፣ እና ለስደት እንዲዳረጉ ከኃላ ሆነው መመሪያውን እየሰጡ ያሉት እኒሁ በውስጣቸው ተቀምጠው ያሉት ጉዶች እንደሆኑ አባቶች በሐዘን ይናገራሉ። “መድኃኒዓለም ጥዋው የሞላለት . . . ወይውላቸው” ነበር ያሉት አንድ የገዳሙ አባት።
ይህ ሁሉ መከራ እና ግፍ የሚፈጸምባቸው ፍቅረ ክርስቶስ ይዟቸው ይህን ጣፋጭ ዓለም ትተው እራሳቸውን ከዓለም ደብቀው በጸሎት፣ በስግደት ባሉበት ቦታ መጥተው እንዲህ ያለ ግፍ ሲፈጽሙባቸው እጅግ ያሳዝናል። በፍልሰት ከሚኖሩበት ተጎትተው ለእስር የበቁት ሁለቱ አባቶችም ይህው ነው የደረሰባቸው፥ እንደ ምክንያት የተሰጣቸውም
- ከቤተ ጣዕመ አባቶች ጋር በአንድነት አትሰሩም፣ አትጸልዩም
- መስቀላቸውንም አትስሙም
- በፍልሰት መቀመጥ አትችሉም (ዘግተው በጸሎት እና በስግደት ተወስነው መቀመት አትችሉም) ነበር ምክንያታቸው፤ እውን ይሄ ለእስር የሚያበቃ ጥፋት ነው? አምላከ አበው ፍርዱን ይስጥ
በማይጸብሪ ፖሊስ ጣቢያ ታጉረው የነበሩት ሁለት ሊቃነ አበው አባ ገብረ ኪዳን እና አባ ገብረ መስቀል ይባላሉ
በዋልድባ ገዳም ከሦስት ዓመት በፊት የወልቃይት ሥኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት ከተጀመረ ወዲህ በርካታ የመንግሥት ታጣቂ ወታደሮች በገዳሙ አካባቢ መታየት ጀምረው ነበር፥ አሁንም ድረስ ከሦስት አበመት በላይ በገዳሙ የተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ታጣቂዎች ሰፍረው ይገኛሉ፣ ገዳማውያኑም የተለመደ የቀን ተቀን ተግባራቸውን ይፈጽማሉ ሥራ የሚሰራውም ሥራዎን በጸሎትም ያሉት ጸሎታቸውን። ነገርግን ሁልጊዜም ጥያቄ ይፈጠራል እነኝህ ወታደሮች እኛን ነው የሚጠብቁት ወይንስ ? ጥያቄው መልስ ባያገኝም ዘወትር የሚያልፉት የሚያገድሙት ሁሉ እነሱን ሲመለከት ጥያቄ ማንሳቱ አይቀሬ ነው መልስ ባይኖረውም። ባለፉት ጥቂት አመታት መንግሥትም ይሄን አካባቢ በዓይነቁራኛ ከሚጠብቃቸው ጥቂት ቦታዎች አንደኛው እነመሆኑ መጠን ጥበቃው ያንን ፍራቻ ሊሆን ይችላል የሚሉም ብዞዎች ናቸው። ከአንድ አመት በፊትም የጃናሞራና የወልቃይት አርሶአደሮች በገዳሙ ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር ለመንግሥት ተወካዮች ቢያሳስቡ እናንተ ጸረ ልማቶች ተብለው ሲወነጀሉ ጥቂት የማይባሉ የአካባቢው አርሶ አደሮች ሸሸተው ጫካ መግባታቸውን እና አልፎ አልፎ መንግስም ስጋቱን በተለያየ ጊዜ ሲገልጽ ቆይቷል፣ በዚህም ይሁን ወይም በሌላ በገዳሙ ክልል ውስጥ ያሉት ወታደሮች ለበረከት የመጡ ሳይሆን ለቅስፈት እግዚአብሔር ያውቃል።
ከዚሁ የዋልድባ ዜና ሳንወጣ ላለፉት ወደ አራት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀሩት ጊዜ ውስጥ የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ጋር ተያይዞ የዛሬማ ወንዝን ገድቦ ወደ 40 ሄክታር የሚገመት መሬት ከአበረንታንት መድኃኒዓለም ገዳም ቀምቶ ሊገደብ የታሰበው ግድብ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ እንኳንስ ግድብ ቀርቶ፥ ጥቂት ውሃን እንኳን ሊያቁር የሚችል ነገር ለመስራት አለመቻላቸው መንግሥትንም ሆነ ለስራው ቅርበት ያላቸውን ሰዎች እራስ ምታት ሆኖባቸው ቀርቷል፣ ለዚህም ይመስላል የኢትዮጵያ ስኳር ልማት ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር የነበሩት አቶ አባይ ጸሐዬ እራስ ምታቱ እንደ ትግል አጋራቸው ይዟቸው እንዳይሄድ በመስጋት ይመስላል የስኳር ኮርፖሬሽን ሃላፊነታቸውን ጥለው ወደ ሌላ ቦታ የተዘዋወሩት። በርካታ ባሕታውያንም ገና ከጅምሩ ሲናገሩ እንደነበሩት ዛሬም ድረስ “በመድኃኒዓለም ቦታ ላይ ማንም ምንም አይሰራም” እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው በማለት ዛሬም ድረስ በልበ ሙሉነት አባቶች ይሄን ሲናገሩ መስማት እጅጉን ያስደስታል። ዛሬ ዛሬ እንደውም እስከዛሬ ከተቋራጭ ተቋራጭ እየተቀያየረ በመምጣት በዛሬማ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገደብ የሞከረም፣ ያሰበም፣ የስራ ተቋራጭ ሆኖ የሰራም በመድኃኒዓለም በትር ያልተቀጣ የለም። ያም ቁንጥጫው ነው በአግባቡ የሰሙ ፈጥነው ወጥተዋል አልሰማም ያሉትም ቀስ ብለው የሰሙታል፣ ያም ሆነ ይህ ግን ዛሬም ድረስ የስኳር ልማቱ የሚሆን የመስኖ ውሃ ለማዘጋጀት ግድቡ ወሳኝ ነው፣ ነገር ግን ግድቡም ሆነ ልማቱ ዋልድባን በሚያክሉ ታላቅ የቅዱሳን በፍለቂያ በሆነ ሳይሆን ሃገራችን ዓመቱን ሙሉ ሲፈሱ የሚኖሩ የበርካታ ወንዞች ባለቤት ናት ነገር ግን በእልህ እና በተልዕኮ የምነት ቦታችንን፣ ታሪካችንን፣ የቤተክርስቲያናችንን ይዞታ የሚነኩ ግን ይዋል ይደር እንጂ ከምድራዊውም ሆነ ሰማያዊው ፍርድ እንደማያመልጡ እምነታችን ነው።

በወልቃይት ተከስቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ ይህን ይመስል ነበር?

ሌላው ከወደ ዋልድባ የመጣልን ዜና እንደሚያመለክተው ባሳለፍነው መስከረም ወር አካባቢ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ብዙ ውድመትን አድርሷል። ከዚህም መካከል የስኳር ልማት ኮርፖሬሽኑ ከታሊማ ወንዝ የተጠለፈ ውሃን ገድበው ወደ 30 ሄክታር የሚሆን መሬት ላይ የሸንኮራ ችግኝ ለማፍላት ሙከራ እየተደረገ ነበር። ከትቂት ወራት በፊት በግንቦት እና ሰኔ አካባቢ በአንዳንድ የአካባቢው ገበሬ መኅበር ታይቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ ጊዜውን ጠብቆ በመስከረም እህል በሚያፈራበት ጊዜ ጠብቆ በመምጣት በ30 ሄክታር ላይ የተፈላውን የሸንኮራ ችግኝ እንዳልነበረ አድርጎታል፤ መንግሥትም በምላሹ በአካባቢው ላይ በርካታ ሰዎችን በማሰማራት መድኅኒት በመርጨት ወራሪን የአንበጣ መንጋ ለመዋጋት ሙከራ በሚያደርጉበት ጊዜ፥ በርካቶች የአባቢው ቀበሌ ገበሬ ማኅበር አባላት ከብቶቻቸው ግጦሽ በሚወጡበት ጊዜ ብዙ የመርዝ ክምችት ያለባቸው ቦታዎች ከብቶቻቸው እዛው በመብረቅ እንደተመታ እየሆኑ ወድቀው ተገኝተዋል፣ ደጋግመው አቤቱታቸውን ቢያሰሙም እንደከዚህ ቀደሙ ሰሚ ጆሮ ሳያገኙ ቀርተዋል። ለከብቶቻቸውም ካሳ ቀርቶ በአግባቡ አቤቱታቸውን ሊያዳምጥ የሚችል የመንግሥት አካል ሊገኝ አለመቻሉ በርካቶችን በእጅጉ አስቆጥቷል። የሆኖ ሆኖ በመንግሥት ላይ የደረውም ከባድ ኪሳራ ባያስደስትም ብዙዎችን ግን ትንሽ ሳያስፈግግ አልቀረም፣ ቀያችንን ለቀው ይሄዳሉ በማለት ነበር። ያም እንደታሰበው ሳይሆን የመንግሥት ሰዎች ላለፉት ጥቂት ወራት በእጅጉ ተያይዘው ያሉት በሌላ ጉዳይ በመሆኑ ችግሮችን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሳይሆንባቸው እንዳልቀረ ብዙዎች በምሬት ተናግረዋል።
ባለፈው ዓመት አካባቢ በዚሁ በልማት ሰበብ በርካታ ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቀው በምትኩ ሌላ ቦታ ይሰጣችኃል በማለት የትም ሜዳ ተበትነው እንደሚገኙ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። አሁንም የመንግሥት ሰዎች በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ 3900 አባወራዎችን ሊያነሳ እና ቦታቸውን ሊወስድ እንደሆነ በሰፊው እየተነገረ ነው። ነዋሪዎችም ከዚህ በፊት ተነስተው የት እንደደረሱ ያልታወቁት በርካታ ነዋሪዎችን እጣ ፈንታ በእነሱም ላይ ሊደርስ እንደሚችል በመገመት በርካቶች በከባድ ስጋት ላይ እንደሚገኙ ለመረዳት ችለናል። የሸንኮራው ጉዳይ አልሳካ ያላቸው የመንግሥት ሰዎች በርካታ የአውራጃውን ነዋሪ ካስነሱ በኃላ ሰሊጥ፣ ነጭ አደንጓሬ፣ እና ጥጥ የመሰሳሰሉትን እያለሙ እንደሚገኙ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በመጣ መረጃ ለመረዳት ችለናል። እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ከሚያስገኙ ምርቶች መካከል ከቡና ቀጥሎ ሰሊጥ እና ጥጥ እንደሆነ ይታወቃል። ቻይና ብቻ ከኢትዮጵያ 30 እስከ 40 ሜትሪክ ቶን ሰሊጥ እና ጥጥ ወደ ሃገሯ እንደምትወስድ ቻይና ዴይሌ የተባለው በቻይና በየቀኑ የሚታተም ጋዜጣ ዘገቦ ነበር።
አሁንም የበርካቶች ስጋት የነዚህን ምርቶች በአካባቢው በማምረት ውጤት ካመጣ በዚህ ሰበብ ለበርካታ ነዋሪዎች መፈናቀል እና ለዋልድባ ገዳምም ይበልጥ አደጋው ከፍተኛ እንደሆነ ይገመታል። በተለይ በገዳሙ ሞፈር ውሃ በሚባለው አካባቢ በርካታ የእርሻ ቦታዎችን በመውሰድ ለእነዚህ እራዎች እንደሚያደርገው ስለታወቀ ስጋታችን ይበልጥ ጨምሯል በማለት ነዋሪዎች ይናገራሉ። መናንያኑም በበኩላቸው እንደ ከዚህ ቀደሙ፤ በዋልድባ ምድር ላይ ምንም ነገር ቢመጣ ሊሰሩም ሆነ ሊያደርጉ የሚችሉት ነገር እንደማይኖር ደጋግመው ይናገራሉ። “እኛ አፈር ጠባቂዎች ነን፥ ቦታው የመድኃኒዓለም ነው” ስለዚህ እርሱ ይጠብቀዋል ከእኛ የዘውትር መወድስ፣ ፀሎት እና ልመና ብቻ ነው የሚፈልገው፥ እኛም ጸሎታችንን ልመናችንን አናቆምም፤ እነሱም በሃይላቸው ተመክተው የክርስቶስን ቦታ ለመውሰድ በሚያደርጉት ተግዳሮት ቀስ በቀስ እየተቀሰፉ ስራውን እስኪያቆሙ ይቀጥላል ይላሉ ያነጋገርናው አባቶች።

ኢህአዴግ በባህር ዳር ግድያ ፈጸመ! በባህርዳር ዋይታ ሆነ!


bahirdar


በእምነት ቦታ ይገባኛል ነዋሪዎች ባሰሙት ጥያቄ ኢህአዴግ የጥይት መልስ ሰጠ፡፡ ድርጊቱን በምስል በማያያዝ በተለያዩ ማኅበራዊ ገጾች ያሰራጩት ክፍሎች አዛውንትና መነኮሳት ሳይቀሩ መደብደባቸውንና መቁሰላቸውን በምስል አስደግፈው አመልክተዋል፡፡
አኻዙ በትክክለኛው ባይታወቅም አምስት የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ በማኅበራዊ ገጾች የተበተኑት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ አንዳንድ የድረገጽ ዜናዎችም በአኻዝ ከመለያየት በስተቀር የግድያውንና የድብደባውን መጠን በመግለጽ ዜናቸውን አስፍረዋል፡፡
ድርጊቱን የፈጸመው ኢህአዴግ ስለሞቱትና ስለተደበደቡት መነኮሳትና አዛውንት እንዲሁም ሌሎች ወገኖች ይህንን መረጃ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ይፋዊ ማስተባበያ አልሰጠም፡፡ ይልቁንም ከሁለት ሳምንት በፊት ኢህአዴግ የፌዴራል ምክት ሚ/ሩን በፖሊስ ፕሮግራም በማቅረብ የፌስቡክ ዜናዎችን አትመኑ በማለት ማሳሰቢያ ሲሰጥ ነበር፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ” የተሰኘው የፌስቡክ ገጽ ቀበሌ፣ ወሰንና የምክርቤት ስም ጠቅሶ የተፈጠረውን ሁኔታ ከዚህ እንደሚከተለው አስፍሮታል፡፡
“የአማራ ክልል አስተዳደር የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን የታቦት ማደሪያ ለመንገድና ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች መስሪያ እንዲነጠቅ ማዘዙን ተከትሎ በቤተ ክርስቲያን የተጠራው ተቃውሞ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከታቦት ማደሪያው 9 ሜትር ገብቶ መንገድ እንዲሰራ እንዲሁም ቀሪው ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች እንዲሰጥ አስተዳደሩ ማዘዙን ተከትሎ ታቦት ማደሪያውን ከነገ ህዳር 10/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሊፈርስ እንደነበር መረጃው የደረሳት ቤተ ክርስቲያን ለህዝበ ክርስቲያኑ አስቸኳይ ጥሪ ማስተላለፏ ታውቋል፡፡ ህዝቡም “በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተገናኝተን በእግዚያብሄር ስም በአስቸኳይ ጠርተንዎታል” በሚል በቀረበለት ጥሪ መሰረት ዛሬ ጠዋት ተቃውሞውን የጀመረ ሲሆን አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ተገልጾአል፡፡ ህዝቡ ቀበሌ 10 በሚገኘው አዲሱ ምክር ቤት እንዲሁም በዚሁ ቀበሌ በሚገኘው የቀድሞው ምክር ቤት በመገኘት ተቃውሞውን እየገለጸ ይገኛል፡፡ በተለይ በአዲሱ ምክር ቤት ተገኝቶ ተቃውሞውን እያሰማ የሚገኘውን ህዝብ በኃይል ለመበተን ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡”
ግድያውንና ድብደባውን በተመለከተ “የክልሉ መስተዳድር ድርጊቱን እንደፈጸመ አድርገው የሚወጡት ዘገባዎች ትክክል አይደሉም፤ መስመርም ያስታሉ፤ ዋንኞቹን ወንጀለኞች ከደሙ የነጹ ያደርጋቸዋል” በማለት ቅሬታቸውን ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የሰጡ ወገኖች “በየትኛውም የአገሪቱ ክልሎችም ሆነ ከተሞች ለሚፈሰው ደምና ለሚጠፋው ሕይወት ግምባር ቀደም ተጠያቂው ህወሃት/ኢህአዴግ እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል” ሲሉማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ “በቁጥጥር ሥር ውሏል” የተባለው የሙስሊሙ ተቃውሞ በድንገት መካሄዱ ታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ኑር መስጊድ የተካሄደውን ተቃውሞ አስመልክቶ የተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች በተለይም የሙስሊሙን ጉዳይ በመከታተል ይፋ የሚያደርጉ መገናኛዎች እንዳስታወቁት ተቃውሞው የተካሄደው ኢህአዴግ ከሚጠብቀውና ከሚገምተው ውጪ ነበር፡፡ እንደወትሮውም የጥሪ ማስታወቂያና ቅስቀሳ አስቀድሞ አልተካሄደም በማለት ዘግበዋል፡፡ ተቃውሞው ውጤታማ፣ ግቡን የመታና የተጠናከረ ቅንብር እንደነበረው የታዘቡ ይናገራሉ፡፡
ኢህአዴግ በእሁድ የፖሊስ ፕሮግራሙ የሚሰጠው “ልማት ተኮር” የፖሊስ ማስተባበያ “ምርመራ ውጤት በተስፋ” ይጠበቃል፡፡ ከተለያዩ የማህበራዊ ገጾች ያገኘናችው ምስሎች ከዚህ በታች ሰፍረዋል::
bahirdar3bahirdar5bahirdar10bahirdar11bahirdar7bahirdar15bahirdar16bahirdar17bahirdar14bahirdar6bahirdar8bahirdar9nur mesjid addisbahirdar1bahirdar13

Wednesday 17 December 2014

‹‹በሰላማዊ ሰልፈኛ ላይ ዱላ መሰንዘር ሽንፈት ነው›› እስክንድር ነጋ

ሰማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች በትብብሩ ውስጥ የታቀፉ ፓርቲዎች በጠሩት የአዳር ሰልፍ ላይ የወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተወሰደውን አሳፋሪ እርምጃ ሰምቻለሁ፡፡ እርምጃው ሁለት ነገሮችን በጉልህ ያሳዬ ነበር፡፡ አንደኛ የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ሽንፍትን ያሳየ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ ሰላማዊ ትግሉ እየተጠናከረ መምጣቱን ያመላከተ ነው፡፡
አንተ ባዶ እጅህን መብትህን ለመጠየቅ ስትንቀሳቀስ፣ መሳሪያ ወደታጠቀ አካል በሰላም ስትገሰግስ ባለመሳሪያው ዱላውን ከሰነዘረብህ አሸናፊው አንተ ሰላማዊው ታጋይ ነህ፡፡ በትብብሩ ሰልፍ ላይ የሆነው ይኸው ነው፡፡ አሁን ሰላማዊ ትግሉ ፍጹም ሰላማዊነቱን እንደጠበቀ መጠናከር ነው ያለበት፡፡ ሰላማዊ ትግል ላይ ልብ ማለት ያለብን ነገር አለ፤ እሱም ሰላማዊ ሆኖ መዝለቅ የሚለው ጉዳይ ነው፡፡
ሰላማዊ ታጋይ ይሰደባል፣ ይደበደባል፣ ይሞታልም፡፡ ግን ደግሞ ሰላማዊ ታጋይ አይሳደብም፣ አይደባደብም፣ አይገድልም፡፡ ይህ ከሆነ ሰላማዊ ትግል ያሸንፋል፡፡ አምባገነኖች ሰላማዊ ታጋዮችን በተለያየ መንገድ ከሰላማዊነታቸው እንዲወጡ ሊገፋፏቸው ይሞክራሉ፤ ስሜት ውስጥ በመክተትም የኃይል በትራቸውን ለማሳረፍ ይቋምጣሉ፡፡ ይህ ሴራ ሰላማዊ ታጋዮችን ሊያዘናጋቸው አይገባም፡፡
በቀደም በተደረገው ሰልፍ ላይ ድብደባው በሰላማዊ ሰዎች ላይ መፈጸሙ ለተደብዳቢዎቹ ሳይሆን ሽንፈቱ ለደብዳቢዎቹ ነው፡፡ በደረሰው ድብደባ ባፍርም፣ ባዝንም በውጤቱ ግን ደስተኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ሰላማዊ ሰልፈኞች ሰላማዊነታቸውን አሳይተዋልና! በሰልፉ ወቅት ድብዳባ እና እስር የደረሰባቸውን የመብት ጠያቂዎች ሁሉ በርቱ ልላቸው እፈልጋለሁ፡፡ ባደረጉት ሰላማዊ እንቅስቃሴ በጣም ኮርቻለሁ፡፡ ሰላማዊና ህጋዊ ትግላችሁን ቀጥሉ ማለትም እፈልጋለሁ!

‹‹አሸናፊው ህዝብ ነው›› አንዱዓለም አራጌ

ግለሰቦች የለውጥ ሐዋርያ ሊሆኑ ይችላሉ፤ በዚያው ልክ የሚሳሳቱትም ግለሰቦች ናቸው፡፡ የግለሰቦች አስተሳሰብ ህዝባዊ ከሆነ ግን በአሸናፊው ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ይኖራቸዋል፡፡ ምክንያቱም አሸናፊው ህዝብ ነው፤ አሸናፊው ሀገር ነው፡፡ የሁላችንም አሸናፊነት የሚገለጸው ሀገር ከፍ ከፍ ስትል ነው፡፡ ስለዚህ ስራችን ሁሉ ሀገርን ከፍ ለማድረግ መሆን አለበት፡፡
በትብብሩ ፓርቲዎች በተጠራው ሰልፍ ላይ የሆነውን ሰምቻለሁ፡፡ በሆነው ነገር አዝኛለሁም፤ ኮርቻለሁም፡፡ ያዘንኩት በደረሰው ድብደባ እና እስር ነው፡፡ የኮራሁት ደግሞ መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ ሊጠይቁ በድፍረት አደባባይ በወጡት ታጋዮች ነው፡፡ በእነዚህ ታጋዮች የእውነት ኮርቻለሁ፡፡
በቀጣይ ፓርቲዎች በአጋርነት መስራት አለባቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ በተለይ በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ፓርቲዎች ከእጩ አቀራረብ ጀምሮ ተቀራርበው መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ በተለይ ሰማያዊ እና አንድነት ተቀራርበው ቢሰሩ የበለጠ ውጤታማ የሚሆኑ ይመስለኛል፡፡ በተረፈ ግን በትብብሩ ሰልፍ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ ጥንካሬን እንዲሰጣቸው እመኛለሁ፡፡ ትግላቸውንም አጠናክረው እንዲቀጥሉ አደራ እላለሁ፡፡

‹‹ቃላችሁን ጠብቃችኋልና ክብር ይገባችኋል፣ ኮርቸባችኋለሁም!›› የሺዋስ አሰፋ

ሰማያዊ ፓርቲ መርህ አለው፡፡ ያመነበትን ነገር ህጋዊና ሰላማዊነቱን ጠብቆ እንደሚፈጽም አውቃለሁ፡፡ ትብብሩ በጠራው ሰልፍ ላይም የሰማያዊ ወጣቶችና ሌሎችም ቃላቸውን ጠብቀው ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ በእውነት በጣም ኮርቸባቸዋለሁ፡፡ እንደሁሌውም ቃላቸውን ጠብቀው ለህዝቡ መብት መቆማቸውን አይቼ ደስ ብሎኛል፡፡ እኔ በእስር ላይ ብሆንም ሌሎች የትግል ጓዶቼ ባደረጉት ነገር በጣም ነው ደስ የተሰኘሁት፡፡
ድብደባውና እስሩ የፈሪ ዱላ ነው፡፡ ኢህአዴግ በህዝብ ፊት ኪሳራን ነው ያተረፈው፡፡ ሰላምን እና ህግን ማስጠበቅ የሚቻለው በልምምጥ ሳይሆን ትክክለኛ መስመርን በመከተል ነው፡፡ በዚህ መሰረት የትግል ጓዶቼ ትክክለኛ መስመር ላይ እንደሆኑ ይገባኛል፡፡ በርቱልኝ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ በዚህ መሰል ሰላማዊነት ነው አምባገነኖችን ማሸነፍ የሚቻለው፡፡

Top 10 worst Jailers. Ethiopia became the second worst jailer of Journalists in Africa and the 4th in the world.

More than 200 journalists are imprisoned for their work for the third consecutive year, reflecting a global surge in authoritarianism. China is the world’s worst jailer of journalists in 2014. A CPJ special report by Shazdeh Omari
An Egyptian protester calls for the release of freelance photographer Mahmoud Abou Zeid, also known as Shawkan, who has been imprisoned since August 2013. (AP/Amr Nabil)
An Egyptian protester calls for the release of freelance photographer Mahmoud Abou Zeid, also known as Shawkan, who has been imprisoned since August 2013. (AP/Amr Nabil)
Published December 17, 2014
The Committee to Protect Journalists identified 220 journalists in jail around the world in 2014, an increase of nine from 2013. The tally marks the second-highest number of journalists in jail since CPJ began taking an annual census of imprisoned journalists in 1990, and highlights a resurgence of authoritarian governments in countries such as China, Ethiopia, Burma, and Egypt.
China’s use of anti-state charges and Iran’s revolving door policy in imprisoning reporters, bloggers, editors, and photographers earned the two countries the dubious distinction of being the world’s worst and second worst jailers of journalists, respectively. Together, China and Iran are holding a third of journalists jailed globally—despite speculation that new leaders who took the reins in each country in 2013 might implement liberal reforms.
The 44 journalists in Chinese jails are a jump from 32 the previous year, and reflect the pressure that President Xi Jinping has exerted on media, lawyers, dissidents, and academics to toe the government line. In addition to jailing journalists, Beijing has issuedrestrictive new rules about what can be covered anddenied visas to international journalists. Coverage of ethnic minority issues continues to be sensitive; almost half of those jailed are Tibetan or Uighur, including academic and blogger Ilham Tohti and seven students imprisoned for working on his website, Uighurbiz. Twenty-nine of the journalists behind bars in China were held on anti-state charges. (Read detailed accounts of each imprisoned journalisthere.)
The administration of Iranian President Hassan Rouhani has also maintained repressive measures against the press. This year, Iranian authorities were holding 30 journalists in jail, down from 35 in 2013 and a record high of 45 in 2012. CPJ’s 2014 International Press Freedom Award winner Siamak Ghaderi was released from prison in July, but that same month, Iranian authorities jailed Jason Rezaian, a Washington Post reporter. By late 2014, the government had still not disclosed the reason for Rezaian’s arrest or the nature of charges against him.
(Maha Masud)
(Maha Masud)
The list of the top 10 worst jailers of journalists was rounded out by Eritrea, Ethiopia, Vietnam, Syria, Egypt, Burma, Azerbaijan, and Turkey. The prison census accounts only for journalists in government custody and does not include those in the captivity of nonstate groups. For example, CPJ estimates that approximately 20 journalists are missing in Syria, many of whom are believed held by the militant group Islamic State.
Turkey, which was the world’s worst jailer in 2012 and 2013, released dozens of journalists this year, bringing to seven the number of journalists behind bars on the date of CPJ’s census. However, on December 14, Turkey detained several more journalists—along with television producers, scriptwriters, and police officers—and accused them of conspiring against the Turkish state, according to news reports. The detentions were born of a political struggle between President Recep Tayyip Erdoğan and the ruling party and the movement led by U.S.-based cleric Fethullah Gülen, and included the editor-in-chief of one of Turkey's largest dailies, Zaman, which is aligned with Gülen.
In Eritrea, which has consistently ranked among the world’s worst jailers and is ranked third this year, authorities are holding 23 journalists, all without charge, and have refused to disclose the prisoners’ health or whereabouts. In 2014, CPJ conducted a fresh investigation into the status of long-held prisoners in the extremely repressive country; the probe led to the addition or removal of a handful of cases but yielded little information about many of those long jailed.
A state crackdown on independent publications and bloggers in Ethiopia this year more than doubled the number of journalists imprisoned to 17 from seven the previous year, and prompted several journalists to flee into exile, according to CPJ research.
For the first time since 2011, Burma had journalists in jail on the date of CPJ’s census: at least 10 were imprisoned, all on anti-state charges. In July, five staff members of the Unity weekly news journal were sentenced to 10 years in prison each under the 1923 Official Secrets Act. Rather than reforming draconian and outdated security laws, President Thein Sein’s government is using the laws to imprison journalists.
Burmese journalists release birds outside a pagoda in solidarity with five journalists who were handed 10-year prison terms of hard labor in July. (AP/Khin Maung Win)
Burmese journalists release birds outside a pagoda in solidarity with five journalists who were handed 10-year prison terms of hard labor in July. (AP/Khin Maung Win)
In Azerbaijan, authorities were jailing nine journalists, up one from the previous year. Amid a crackdown on traditional media, some activists took to social networking sites in an attempt to give the public an alternative to state media. CPJ’s list does not include at least four activists imprisoned in Azerbaijan this year for creating and managing Facebook groups on which they and others posted a mix of commentary and news articles about human rights abuses and allegations of widespread corruption.
Egypt more than doubled its number of journalists behind bars to at least 12, including three journalists from the international network Al-Jazeera.
In recent years, journalist jailings in the Americas have become increasingly rare, with one documented in each 2012 and 2013. This year, the region has two: a Cuban blogger was sentenced to five years in prison in retaliation for his critical blog, and in Mexico, an independent journalist and activist for Mayan causes has been charged with sedition.
Other trends and details that emerged in CPJ’s research include:
  • The 220 journalists jailed around the world compares with the 211 CPJ documented behind bars in 2013. The 2014 tally ranks the second highest behind 2012, when CPJ documented 232 journalists jailed in relation to their work.
  • Worldwide, 132 journalists, or 60 percent, were jailed on anti-state charges such as subversion or terrorism­. That is far higher than any other type of charge, such as defamation or insult, but roughly in line with the proportion of anti-state charges in previous years.
  • Twenty percent, or 45, of the journalists imprisoned globally were being held with no charge disclosed.
  • Online journalists accounted for more than half, or 119, of the imprisoned journalists. Eighty-three worked in print, 15 in radio, and 14 in television.
  • Roughly one-third, or 67, of the journalists in jail around the world were freelancers, around the same proportion as in 2013.
  • The number of prisoners rose in Eritrea, Ethiopia, China, Bangladesh, Thailand, Azerbaijan, Bahrain, Egypt, Israel and the Occupied Palestinian Territories, and Saudi Arabia.
  • Countries that appeared on the 2014 prison census after jailing no journalists in the 2013 survey were Cameroon, Swaziland, Mexico, Cuba, Burma, and Belarus.
CPJ defines journalists as people who cover the news or comment on public affairs in media, including print, photographs, radio, television, and online. In its annual prison census, CPJ includes only those journalists who it has confirmed have been imprisoned in relation to their work.
CPJ believes that journalists should not be imprisoned for doing their jobs. The organization has sent letters expressing its serious concerns to each country that has imprisoned a journalist. In the past year, CPJ advocacy led to the early release of at least 41 imprisoned journalists worldwide.
CPJ’s list is a snapshot of those incarcerated at 12:01 a.m. on December 1, 2014. It does not include the many journalists imprisoned and released throughout the year; accounts of those cases can be found at www.cpj.org. Journalists remain on CPJ’s list until the organization determines with reasonable certainty that they have been released or have died in custody.
Journalists who either disappear or are abducted by nonstate entities such as criminal gangs or militant groups are not included on the prison census. Their cases are classified as “missing” or “abducted.”
Shazdeh Omari is CPJ's news editor. She was the former copy chief for The Village Voice and has worked as a reporter and editor in the United States and Greece.

Tuesday 16 December 2014

በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ ኢሳትና የግንቦት 7 ፣ በፕሮቴስታንት ደግሞ የኦነግ ሰዎች አሉ ሲሉ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ተናግሩ

ታኀሳስ (ሰባትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የፌደራልና የክልል የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች በባህርዳር በተሰባሰቡበት ወቅት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ፣ ይህን የተናገሩት የሃይማኖት ተቋም የፖለቲካ ፍላጎት ማራመጃ መሆኑን ለማስረዳት ነው። ዶ/ር ሽፈራው ከአፋር የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ” መንግስት ለምን በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ይገባል? ለምንስ በአገራችን የሌለ ችግር ያመጣብናል?” በሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ዶ/ር ሽፈራው ይህንን ለማስረዳት ይጠቅማል ያሉዋቸውን ምሳሌዎች አቅርበዋል።  በጥቅምቱ የሲኖዶስ ጉባኤ የኢሳት ሬዲዮና ቴሌቪዥን የሲኖዶሱን ውሎ በእየለቱ ሲዘግብ የነበረው በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ በሚገኙ አባላት አማካኝነት ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፣ ግንቦት7 እና ኢሳት ሃይማኖትን ለፖለቲካ እምነት ማራመጃ ለመጠቀም እንደሚፈልጉ ዋናው ማሳያ ነው ሲሉ ደምድመዋል

ፕሮቴስታንት ሃይማኖት ለኦነግ አላማ ማስፈጸሚያ እያገለገለ መሆኑን  የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ ኦነግ ከፕሮቴስታንት አልፎ ዋቄ ፈታንም እየተጠቀመ ነው ብለዋል አክራሪነት ስልቱን ቀየረ እንጅ አልተሸነፈም ያሉት ዶ/ር ሽፈራው፣ በሚቀጥሉት ወራት በሃይማኖት ተቋማት ላይ፣ በትምህርት ቤቶች፣ በወጣትና ሴቶች ማህበራት ሰፊ ዘመቻ እንዲጀመር መክረዋል። በተለይ አዲስ አበባ ስራዎች ቢሰሩም ተመልሶ ማጥ የሚገቡበት በመሆኑ፣ የአዲስ አበባ መዋቅራችን አክራሪነትን አሸነፍኩ ብሎ ሊዘናና እንደማይገባው አሳስበዋል።
ማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን በተለይም ፌስቡክና ትዊተር ትልቅ ችግር እየፈጠሩ ነው  ያሉት ሚኒስትሩ፣ እነዚህን የመገናኛ ብዙሃን ለመጠቀም እቅድና ስትራቴጂ ተነድፎ በሙሉ ጊዜና ሃይል የሚሰራ ሰው መድቦ መንቀሳቀስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህን ተግባራዊ ማድረግ የትግሉ ዋናው አካል መሆን ይገባዋል ብለዋል
መጪውን ምርጫ በተመለከተ በሁዋላ ላይ ችግር ሳይፈጠር ከአሁኑ እርምጃዎችን በመውሰድ መንቀሳቀስ እንደሚገባም አክለዋል። በአገሪቱ ያሉ የጸጥታ ሃይሎች በምርጫው ላይ መውሰድ ስለሚገባቸው እርምጃም ውይይት አድርገዋል። የውውይቱ ውጤት እንደደረሰን ለህዝብ የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ማህበረ ቅዱሳን ከቀኖና ጋር በተያያዘ ለመክሰስ የተዘጋጁ የደህንነት መስሪያ ቤት ያደራጃቸው ሰዎች ምክክር እያደረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። ሰዎቹ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ስልጠና እየወሰዱ ሲሆን፣ ከተወሰኑ ጊዜያት በሁዋላ በማህበረ ቅዱሳን ላይ በሃሰት በመመስከር ማህበረ ቅዱሳን የእኛ ነው በሚል ነባሩን ድርጅት ለማሳገድ እና ለገዢው ፓርቲ ተለጣፊ የሆነ ማህበረ ቅዱሳን ለማቋቋም እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል። በማህበረ ቅዱሳን ስም ማህተም ከማስቀረጽ ጀምሮ የተለያዩ ህገደንቦችን እያረቀቁ መሆኑን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

Monday 15 December 2014

አቶ ሽመልስ ከማል ከአቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር በመጋጨታቸው አኩርፈው ቤት መቀመጣቸው ተሰማ

December 15,2014

የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ከ ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን ጋር መግባባት ባለመቻላቸው አኩርፈው ቤት በመቀመጥ መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ አለመሆኑን  ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሽመልስ ከደባል ሱስ  ጋር በተያያዘ በመደበኛ የስራ ሰዓታቸው ሊገኙ ባለመቻላቸው ሚኒስትሩ ይህን ባህሪያቸውን እንዲያስተካክሉ ቢነግሩዋቸውም ሊያስተካክሉ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተፈጠረ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ። የአቶ ሽመልስን   ሃላፊነት ደርበው እየሰሩ ያሉት በቅርቡ ከዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተርነት ተነስተው የመንግስት ኮምኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን የተሾሙት አቶ እውነቱ ብላታ ናቸው።

አቶ ሽመልስ በቅርቡ የታዩት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ ሊቀመንበር በመሆናቸው በድርጅቱ ስብሰባ ላይ ብቻ ነው፡፡ የፕሬስ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ሰብስቤ ከበደ ከአቅም ማነስና የመልካም አስተዳደር ችግር ጋር ተያይዞ በድርጅቱ ጋዜጠኞች እየቀረበባቸው ያለውን ግልጽ ትችትና ቅሬታ በተደጋጋሚ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ከማስተባበላቸውም በተጨማሪ ጥያቄውን የሚያነሱ ጋዜጠኞችን እስከማስፈራራት የደረሰ ንግግር ሲያደርጉ የተሰሙት አቶ ሽመልስ፣  መደበኛ ስራቸውን መተዋቸው በኮምኒኬሽን መ/ቤቱ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖአል፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል በአቶ በረከት ስምኦን ደጋፊነት የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ስራአኪያጅ የነበሩ ሲሆን፣  የ97 ምርጫን ተከትሎ የቅንጅት አመራሮችና ጋዜጠኞች በተከሰሱ ወቅት አቃቤ ሕግን ወክለው ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲቀርቡና ሐሰተኛ ምስክሮችን በገንዘብ በመግዛትና በመደለል ለኢህአዴግ ውለታ ለመስራት የጣሩ ሰው መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጅ አቶ በረከት ከጤና ጋር በተያያዘ ስራቸውን እየተዉ በመምጣታቸው አቶ ሽመልስ ብቸኛው ደጋፊያቸውን አጥተዋል። አቶ ሽመልስ አቶ በረከትን የመተካት ህልም ቢኖራቸውም ሳይሳካላቸው አቶ ሬድዋን ቦታውን እንዲወስዱ ተደርጓል። በሁለቱ ባለስልጣኖች መካከል ባለው ልዩነት የተነሳ፣ አቶ ሽመልስ ከስራቸው የሚባረሩበት ቀን እሩቅ ላይሆን እንደሚችል ወይም በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን በመልቀቅ ከአገር ለመውጣት ሙከራ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ታዛቢዎች ይገልጻሉ። የአቶ ሽመልስ የስልጣን ቆይታ በከፍተኛ ህመም ከሚሰቃዩት ከአቶ በረከት ስምኦን ህልውና ጋር የተያያዘ መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ።

ምንጭ ኢሳት ዜና

Ethiopian Air Lines allegedly fired member of opposition

December 15,2014
Worotaw Wassie Source - Negere Ethiopia
Worotaw Wassie
Source – Negere Ethiopia
Addis Ababa – Negere Ethiopia, newspaper close to Semayawi party, reported that Worotaw Wassie who is serving as head of financial affairs within Semayawi party is fired from his job at Ethiopian Air Lines.
According to the report, while Worotaw is fired for alleged inaction in taking disciplinary administrative measures, the very employee whose case has caused dismissal of Worotaw is back to work at Ethiopian Air Lines.
The source cited Woretaw as saying that member of the management who is immediately responsible for taking administrative action against the employee got only deductions of five days of pay. Woretaw thinks that his dismissal is rather a political case possibly related to his activity in one of the active oppositions in the country – Semayawi party.
It’s , however, clear that Ethiopian Air Lines is under tight control of the dominant entity in the ruling coalition, TPLF, as are many institutions in the country including religious institutions . Board members of Ethiopian Air Lines are mainly from TPLF party. And there is much discontent in the ranks of Ethiopian Air Lines employees.

In February 2014, co-pilot of Ethiopian Air Lines, Hailemedhin Abera, hijacked Rome bound Ethiopian Air Lines jet and diverted it to Switzerland.
borkena will publish updated news should Ethiopian Air Lines responds on this matter.

አየር መንገድ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራርን ከስራ አባረረ

• ‹‹በፖለቲካ አመለካከቴ ምክንያት ሁልጊዜም እኔን ማባረር ይፈልጋሉ›› አቶ ወሮታው ዋሴ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ወሮታው ዋሴን ከስራ አባረረ፡፡ አቶ ወሮታው ከስራ የተባረሩት ጥፋት ያጠፋን ሰራተኛ አልቀጣህም በሚል ሲሆን በእሳቸው ስር የነበረውና አጠፋ የተባለው ሰራተኛ ጉዳይ ተመርምሮ ወደ ስራ መመለሱ ታውቋል፡፡
አቶ ወሮታው ከእሳቸውም በላይ ጉዳዩ የሚያገባው የማኔጅመንት አባል በተመሳሳይ ጉዳይ የአምስት ቀን ደመወዝ ብቻ ሲቀጣ እሳቸው ከስራ መባረራቸው በፖለቲካ አመለካከታቸው ላይ የተመሰረተና ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሆነ ያሳያል ብለዋል፡፡ ከስራቸው ይሰራ የነበረው ሰራተኛ ጥፋተኛ አለመሆኑን የገለጹት አቶ ወሮታው ‹‹በፖለቲካ አመለካከቴ ምክንያት ሁልጊዜም እኔን ማባረር ይፈልጋሉ›› ሲሉ የተባረሩት በፖለቲካ አመለካከታቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
አቶ ወሮታው ዋሴ ከሁለት አመት በፊት በኢሜል ለህዳሴው ግድብ ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ለተላከው የኢሜል መልዕክት አልከፍልም ብለው በመመለሳቸው ‹‹ሰራተኛ በማሳመጽ፣ የኢንዱስትሪ ሰላም በማናጋት›› በሚል ተከሰው ተባርረው ከሁለት አመት በኋላ በፍርድ ቤት ወደ ስራ መመለሳቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በወቅቱ አየር መንገድ አቶ ወሮታው ዋሴ ካሳ ተከፍሏቸው እንዲለቁ ይግባኝ ጠይቆ የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለሁለት አመት ካራዘመ በኋላ ወደ ስራ እንዲመለሱ አዝዞ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ጥፋተኛ ነው ብሎ ያባረራቸው አየር መንገድ ወደ ስራ በተመለሱ በ15 ቀናት ውስጥ ሰርተውበት ወደማያውቁት ክፍል በማዘዋወር እድገት አግኝተው የማኔጅመንት አባል እንደሆኑ እንደገለጸላቸው የሚናገሩት አቶ ወሮታው እድገቱ ሰራተኛ ሲባረር የመክሰስ መብት ስላለው፣ በተቃራኒው ግን ሳይፈልጉት በእድገት የማኔጅመንት አባል እንዲሆኑ የተደረገው የማኔጅመንት አባል የሆነ ግለሰብ ቢባረርም የመክሰስ መብት የሌለው በመሆኑ ሆን ተብሎ ለማባረር የተደረገ ስልት ነው ብለዋል፡፡ አቶ ወሮታው በወቅቱ ይህን እድገት አልቀበልም ብለው እንደነበርም ገልጸውልናል፡፡
አቶ ወሮታው ዋሴ አሁን ከስራ ባባረራቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለ14 ዓመታት ያህል ማገልገላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡



Sunday 14 December 2014

ኘሮፌሰር አሥራት ታህሳስ 11/1985 በደብረ-ብርሃን ከተማ መስቀል አደባባይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ

የኢትዮጵያን አንድነት በመደገፍ በዚህ ስብሰባ ላይ የተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፣
የዚህ መከረኛ ትውልድ ነፃ አውጭ የሆናችሁ ወጣቶች
ክቡራትና ክቡራን ወገኖቼ
ከሁሉ በፊት በእናንተ ውድ ወገኖቼ መካከል በዚህ አደባባይ ላይ ተገኝቼ ስለውድ ሀገራችሁ ስለኢትዮጵያ ህልውና እንዲሁም በየቦታው በግፍ በመጨፍጨፍ ላይ ስለሚገኘው ወገናችን ስለዐማራው ሕዝብ የወደፊት መኖር ወይም አለመኖር ጉዳይ፣ ለመወያየት ላበቃኝ ሁሉን ማድረግ ለሚችለው አንድ አምላካችን ምሥጋና አቀርባለሁ፡፡
የተወደዳችሁ ወገኖቼ!
ይህ የአለንበት ዘመን ሀገራችን ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ በከፍተኛ ችግር ላይ የወደቀበትና ፈታኝ ከሆነ የጥፋት ማዕበል ውስጥ የተገባት ወቅት ነው፡፡
በተለይም የኢትዮጵያ የታሪክ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማጥፋትና ለማዳከም ሲያውጠነጥኑ የኖሩት ዕቅድና ስልት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆን የጀመረበት ወቅት ስለሆነ በኢትዮጵያዊነታችን ለምናምን ሁሉ አሳሳቢ ብቻ ሳይሆን እጅግ ፈታኝ የሆነ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡
ይህ ሀገራችንንና ሕዝቡን ከጥፋት ማዕበል ውስጥ ያስገባ ችግርና ወጥመድ በኢትዮጵያዊያኖች የተጠነሰሰና የተፈጠረ ሳይሆን በውጭ ጠላቶቻችን የታቀደና ለተግባራዊነቱም ገንዘብ ዕውቀትና ቁሳቁስ ተመድቦለት በከፍተኛ ደረጃ ክትትል የሚደረግበት ከመሆኑም በላይ፣ ዓለም በአንድ ኃይል መዳፍ እጅ የመግባቷን ሁኔታ ሲያበስር የኢትዮጵያ ጉዳይ ደግሞ ከራሷ ሕዝብ በቀር ሌላ ዳኛና ተቆርቋሪ የሌላት መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡
የኢትዮጰያ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሲያቅዱና ሲዘምቱ ለረጅም ጊዜ የኖሩ ቢሆንም እንደዛሬው ኢትዮጵያን ባዶውን ያገኙበት ጊዜ በታሪክ አልታየም፡፡ ይህ የሀገራችን ባዶነት ሊከሰት የቻለው ከረጅም ጊዜ የጠላቶቻችን የውስጥ ቡርቦራ በኋላ ሕዝቡ እንዲከፋፈል፣ በራሱ ልጆች ላይ ዕምነት እንዲያጣ፣ ሞራሉንም፣ ታሪኩንም፣ ሃይማኖቱንም በአጠቃላይ ሁለንተናውን ሁሉ እንደምሰጥ ውስጥ ውስጡን ሲበሉት የቆዩ በመሆናቸው ነው፡፡
ከዚህ በቀር በአሁኑ ወቅት በድንገት በዓለም ላይ የተከሰተው የፖለቲካ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ ይታያል፡፡
ከዚህ የተነሳ፣ የዓለምን ሕዝብ የጋራ ሕልውናና የታናናሽ ሀገሮችን ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ፣ ከፍተኛ ሀላፊነት የሚጠበቅበት የተባበሩት መንግሠታት ድርጅትም፣ የዓለም ታላላት ኃይሎች ሚዛን ባልታሰበ ሁኔታ በድንገት ስለተዛበ በአንድ ኃይል አመራር ሥር ወድቆ ለዳግመኛ የታሪክ ትዝብት ተጋልጦ ይገኛል፡፡
የራሱ ሚዛን በመዋለል ላይ የሚገኘው የዓለምን ሁኔታ በብቸኛ ኃያልነት የሚመሩት ወገኖች፣ በየትኛውም አካባቢ ያለውን ፍላጐታቸውን ለማርካትና ጥቅማቸውን ለማመቻቸት የሚችሉ ቡድኖች በሥልጣን ላይ እንዲቆናጠጡ ከማድረግ ባሻገር የሀገሩን ሕዝብ ጩኸት የሚሰሙበት ጆሮአቸውን ይሁነኝ ብለው ደፍነውታል፡፡
ስለሆነም በማንኛውም አገር ውስጥ ምንም ዓይነት ችግርና በሕዝብ ላይ የሚፈፀም ዕልቂት ቢከሰት፣ ከነሱ ስልትና ጥቅም አንፃር የሚያሳስባቸው ሆኖ እስካላዩት ድረስ ስሜት ሊሰጣቸውና የዕልቂቱም ሰቆቃ የሚቀሰቅሳቸው አይደለም፡፡
ይህ የውጭ ሀይሎች ስልት፣ ይህች የምንኖርባትን ክፍለ ዓለም ማለትም የአፍሪካን ቀንድና እንዲሁም በአውሮፓና በዩጐዝላቢያም ምድር ሕዝብን እርስ በርሱ በማፋጀት የሚፈጽሙት ደባ በገሀድ እየታየ ነው፡፡
በማስታጠቅና የነሱ ደጋፊ ትከሻ በመሆን በሌላ በኩል ደግሞ የመሳሪያ ፋብሪካቸው ገበያ እንዲያገኝ፣ የጦር መሳሪያዎችን በግፍ በማቅረብ ሕዝቡን እርስ በርሱ በማፋጀት ረገድ ወኪሎቻቸው የነሱን ዓላማ ለማራመድ የሚችሉበትን በረቀቀ ጥናት የተደገፈ ተክህኖ ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ እርስ በርስ የማፋጀት ስልታቸውም ትኩረት የሚያደርገው በረጋው ማህበረሰብ ውስጥ ጐሳን፣ ቋንቋንና ሃይማኖትን ለሕዝቡ አጉልቶ በማሳየተና በዚህ አንፃር በመከፋፈል ነው፡፡
በኢትዮጵያ ላይ የውጭው ኃይል ትኩረት ማድረግ ከጀመረ ብዙ ምዕተ-ዓመታት ያለፈ ቢሆንም በይበልጥ ስልታዊ ዕቅዱን በተጠና ሁኔታ ማራመድ የተጀመረው በታላቁ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት በዳግማዊ ምኒልክ መሪነት ኢትዮጵያ በአድዋ ላይ ካስመዘገበችው ድል በኋላ ነበር፡፡
በነጮች ዕውቀት የተገነባውን የወቅቱን ኃይል ሀገር ጦር በአፍሪካ ምድር የሚቋቋመው ኃይል የለም በሚባልበት በዚያ ጨለማ ዘመን ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው የጦር ሜዳ ድል ወደ አፍሪካ ያጣጠረውን የውጭ ኃይል እንደገና እንዲያሰላስልና እንዲያስብ ስላደረገው ሕዝብን ማሸነፍና መያዝ የሚችለው በጦርነት ብቻ ሳይሆን እራሱን በራሱ እንዲጐዳና እንዲከፋፈል በማድረግ የሕዝቡ ኃይል በቀላሉ ሊፈራርስ የሚችልበትን ስልት በመቀየስ ጭምር መሆኑን እንዲያምኑበት አድርጓቸዋል፡፡
ስለሆነም ኢጣሊያ በአድዋ ላይ የደረሰባትን አሳፋሪ ሽንፈት መነሻ በማድረግ 40 ዓመት ሙሉ ሲጠና ሲታቀድና ከሞላ ጐደል ከሰሜን ኢትዮጵያ በተወሰደው የኢትዮጵያ አካል የሆነውን የኤርትራን መሬት መቆናጠጫ በማድረግ የኢትዮጵያ ሕዝብ እርስ በርሱ የማባላቱ ተግባር በግንባር ቀደምነት ተጀምሮ ነበር፡፡
የተወደዳችሁ ወገኖቼ!!
የወገንና የሀገር ጉዳይ በመሆኑ ብዙ በመናገር ጊዜያችሁን እንዳባከንኩ ይሰማኛል፡፡
ሆኖም የአባቶቻችንን የሚያኮራ ታሪክ በማስደፈርም ሆነ ባለማስደፈር በውርደትም ሆነ በኩራት ለማስረከብ ባለብን የዜግነት ግዴታ አነፃር በአሁኑ ጊዜ በታሪክ ፊት ተጋልጠን የምንገኝበትን እንደገና ላስታውሳችሁ እገደዳለሁ፡፡
በጠላት ወረራ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝብ በ3 ተከፍሎ እንደነበር አስታውሱ አንደኛው ወገን ውርደትን በመጥላት በነፃነቱና ለክብሩ ሲል ቤት ንብረቱን ትቶ ወደ አርበኝነቱ በመግባት የዱር ገደሉን ኑሮ በመጀመር ታራክ ሠርቶ ያለፈና የኖረ፣ ሁለተኛው አገር ሲረጋ እመለሳለሁ ብሎ ሕይወቱን ለማዳን ሲል የተሰደደ፣ ሦስተኛው ለሆዱ አድሮ የጠላት መሳሪያ በመሆን ወገኑን ከሚጨፈጭፈው የኢጣሊያ ጦር ጋር ያበረ ነበር፡፡
ሆዱን ለመሙላትና የማይቀረውን ሞት ለጊዜው ለማዘግየት ሲል የውርደትን መንገድ የመረጠው በትዝብት ውስጥ ወደቀ እንጂ የኢትዮጵያ አርበኞች ድል አድራጊነት አልቀረም፡፡
ለሀገሩና ለወገኑ ክብርና ደህንነት ደረቱን ለጥይት በመስጠት የቆረጠው አርበኛም ያለቀኑ አልወደቀም፣ አልሞተም እንዲያውም ከተፈጥሮ ሞቱ በኋላም ቢሆን በታሪክ ውሰጥ እየኖረና ኢትዮጵያንም በታሪክ እያኖረ ነው፡፡
ወገኑን የከዳውና ለሆዱ ያደረው ባንዳም ከውርደት በቀር ትረፍ ሕይወትና ትርፍ ኑሮ አልኖረም፡፡ ዛሬም እንደነዚህ ያሉ የሕዝብ ጠላቶች ለማንም የማይበጁ ማንኛውንም የሀገርና የወገን ጉዳይ ለጥቃቅን ጥቅማቸው የሚሸጡ፣ የትውልድ አተላ ስለሆኑ እግዚአብሔር በቸርነቱና በኃይሉ ቀናውን አስተሳሰብ እንዲሰጣቸው እየተመኘን ይህን ከመሰለው የትውልድና የታሪክ አተላነት የሚላቀቁበትን ልብ ለማግኘት በቂ ጊዜ ስላላቸው ማሰብና ደጋግመው ማሰላሰል ከዚያም ስለአቋማቸው መወሰን የኖርባቸዋል፡፡
በዚህም መሠረት ለወገን ውድቀትና መጠቃት ለሀገር መዋረድና መበታተን ለዲሞክራሲና ለሰብአዊ መብት መታፈን መሳሪያ የሚሆኑ ሆዳም ዐማሮች ካሉ አጥበቀን እንመክራቸዋለን፡፡
በተለይ ወጣቱ የአባቶቹን ዓላማ ያለጥርጠር እንደሚያነሳ ሙሉ ዕምነት አለኝ፡፡
መዐሕድ ለዐማራው ሕዝብ ሕጋዊ መብት መጠበቅ ለኢትዮጰያ አንድነትና ሉዓላዊነት መከበር የሚያደርገውን ትግል በቆራጥነት መቀጠሉን ይገፋበታል፡፡ የተቋቋመበት ዓላማው ስለሆነ በማንኛውም ቦታ የሚፈጽሙትን ኢ-ዲሞክራሲያዊ ድርጊቶች በማጋለጥና በመቃወም ቻርተተ በፈቀደው መሠረት የሕዝቡን ሠላማዊና ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ በግንባር ቀደምትነት ማስተባበሩን ይቀጥላል፡፡
በመጨረሻም ላሳሰባችሁ የምፈልገው ዛሬ ዓለም በሥነ ጥበብ መጥቃ በመሄድ ሀገረን በማልማት የሕዝብን የማህበራዊ ፍላጐት በመርካት ከፍተኛ እርምጃ የሚካድበት ጊዜ መሆኑን ነው፡፡ በዚህም መሠረት ሀገራቸው ምድረ በዳ የሆኑ አገሮች እንኳ በሠላም በመሥራታቸው ለሕዝባቸው ብዙ ጥቅም እያስገኙ ናቸው፡፡ ኢትዮጰያ ሀገራችን በምድር ላይ ያለች ገነት መሆኗን ሙሶሎኒ ሳይቀር ሲመሰክር ለወታደሮቹ ባደረገው ንግግር “ይህችን የምድር ገነት ውረሱ” ነው ያላቸው፡፡ ስለዚህ ሁላችንመ ሕዝብም ሹማምንትም በሰላምና በእኩልነት ተፈቃቅሮ መሥራቱ፣ ጥቅሙ የሁላችንም መሆኑን ተገንዝበን በመሐላችን ያለውን ልዩነት ከማስፋፋት ይልቅ በመሐላችን ሊጐለብት የሚችለውን ስምምነታችንን እንዲጠናከር በማደርግ አርቀን እንድንመለከት ጥሪ አቀርባለሁ፡፡
ኢትዮትጵያ በልጆቿ መሰዋዕትነት አንድነቷና ነፃነቷ ተከብሮ ለዘለዓለም ይኖራል