Wednesday 30 April 2014

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ፡፡

 
  

 በሀገራችን ላይ የተንሠራፋውን አምባገነናዊ ሥርዓት ገርስሶ ለመጣል የመጨረሻ አማራጭ የሆነውን የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት በጠላት ላይ የሚወስዳቸውን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃዎች አጠናክሮ በመቀጠል በታህሳስ 23 ቀን 2006 ዓ/ም በሰሜን ጎንደር በላይ አርማጭሆ ወረዳ ልዩ ስሙ ገራርዋ ባምብላ ወንዝ በተባለው ቦታ መሽጎ የአካባቢውን ህብረተሰብ ሲያሰቃይና ሲያንገላታ ከነበረው የወያኔ 24ኛ ቴዎድሮስ ክ/ጦር እና ከፀረ-ሽምቅ ታጣቂ ኃይሎች ጋር ባደረገው ውጊያ 24 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 11 በማቁሰል የግንባሩ ሠራዊት አንፀባራቂ ድል አስመዝግቧል፡፡ በዚሁ ዕለትም በተደረገው እልህ አስጨራሸ ውጊያ የወያኔ 24ኛ ቴዎድሮስ ክ/ጦር ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት የሚደርስበትን የተኩስ ናዳ መቋቋም ተስኖት ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ እግሬ አውጪኝ በማለት መፈርጠጡን ታውቋል::

 ይህ በእንዲሀ እንዳለ የአካባቢው ነዋሪዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት በጠላት ላይ ባስመዘገበው ከፍተኛ ወታደራዊ ድል መደሰታቸውና ወደፊትም ሀገራዊና ሕዝባዊ አላማን አንግቦ የህብረተሰቡን እምባ በማበስ ግንባር ቀደም በመሆን ለሀገርና ለወገን ደራሽነቱን እያስመሰከረ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊትን በመደገፍ የቆመለትን አላማ ከግብ ለማድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀው ግንባሩ በተከታታይ ጊዜያቶች የሚወስዳቸው ወታደራዊ ጥቃቶችና የሚያስመዘግባቸው አንፀባራዊ ድሎች የወገንን አንጀት በማራስ በአንፃሩ ደግሞ የጠላትን አንገት በማስደፋቱ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም የአካባቢው ህብረተሰብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት የጀግና አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ከግንባሩ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ቆርጠው መነሳታቸውን አስታውቀዋል፡፡
                                                                       Posted by A.G

Saturday 26 April 2014

ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለሚዲያ ማህበረሰቡ የተላለፈ ጥሪ

ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለሚዲያ ማህበረሰቡ የተላለፈ ጥሪ

Ethiopia's Semayawi (Blue) party logoApril 26, 2014
ውድ የሚዲያ ማህበረሰብ አባላት፡- ባለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ በህገ መንግስቱ የሚዲያ ነጻነት እንደሚፈቀድ ቢደነግግም በተግባር ግን የራሱን ፕሮፖጋንዳ ከሚነዛባቸው ሚዲያዎች ውጭ ሌሎቹን ሲዘጋና ሲያሸማቅቅ ኖሯል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ህዝባችን ከገዥው ፓርቲ ፕሮፖጋንዳ ውጭ አማራጭ መረጃ ማግኘት አልቻለም፡፡ ጋዜጠኞች እየታሰሩ፣ እየተሰደዱ፣ ሚዲያዎች እየተዘጉም ቢሆን የተቻላችሁን ያህል ለህዝብ መረጃ ለማድረስ የሚዲያው ማህበረሰብ አባላት ለምታደርጉት ሁሉ ከፍ ያለ ክብር አለን፡፡ የታፈነውን የህዝብ ድምጽ ለማሰማት የምታደርጉትን ጥረትም እናበረታታለን፡፡ ሆኖም አሁንም ቢሆን በገዥው ፓርቲ አፋኝነት ምክንያት ህዝባችን የሚገባውን መረጃ እያገኘ አይደለም፡፡ እናንተም በሰበብ አስባቡ ጫና እየደረሰባችሁ እንደሆነ ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡
ገዥው ፓርቲ ላይ የሰላ ትችት የሚያደርሱ ጋዜጠኞች ‹‹አሸባሪ›› ተብለው ታስረዋል፡፡ ጋዜጦችና መጽሄቶች በስርዓቱ ተዘግተዋል፡፡ በርካታ ጋዜጠኞች አገራቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ድብደባ፣ ማስፈራሪያና ዛቻ ደርሶባቸዋል፡፡ እየደረሰባቸውም ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ በሚያደርስባቸው ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ጫና ከገበያ ወጥተዋል፡፡ በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት ለህዝባችን አማራጭ መረጃ የሚያደርሱ ሚዲያዎችና የሚዲያው ማህበረሰብ መብቶቻቸውን ተነጥቀው አደጋ ላይ ወድቀዋል፡፡
አማራጭ መረጃ ለዴሞክራሲና ለልማት ቀዳሚውን ሚና እንደሚጫወት የሚያምነው ፓርቲያችን ይህን የመብት ረገጣና አፈና ሲቃወምና ሲታገል ቆይቷል፡፡ አሁንም በጠነከረ መልኩ ይቃወማል፡፡
ፓርቲያችን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽን ጨምሮ የተነጠቁትን መብቶቻችን ለማስመለስ በመጣሩ አመራሮቹና አባላቱ በህገ ወጥ መንገደ እስር ቤት በሚገኙበት ተመሳሳይ ወቅት የዞን ዘጠኝ ወጣቶች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ከመቸውም ጊዜ በላይ ጭቆናው እንደመረረ እና ሁሉን ማህበረሰብ ያቀፈ ትግል እንደሚያስፈልግ ዋነኛ ማሳያ ነው፡፡ ከዚህ የመረረ ጭቆና ህዝባችንን ነጻ ማውጣት የምንችለው እኛ ህዝቡን ማደራጀትና ማንቀሳቀስ የሚዲያ ማህበረሰቡም መደረጃውን ለህዝባችን ማድረስ ሲችል ብቻ ነው፡፡
ፓርቲያችን ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ጨምሮ ገዥው ፓርቲ ከኢትዮጵያውያን የነጠቃቸውን መብቶች ለማስመለስ ተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ የሚዲያው ማህበረሰብ ይህን የተቃውሞ ሰልፍ ሂደት ለህዝብ በማስተላለፍ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የታመነ ነው፡፡ በመሆኑም መብቶቻችን በህዝብ ትግል ይመለሱ ዘንድ እናንተም የተለመደው የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡
መረጃ ኃይል ነውና በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ የህትመትም ሆነ የብሮድካስት ውጤቶች የተነጠቁትን መብቶቻችን፣ የሰላማዊ ሰልፉን ሂደት፣ በሂደቱ በፓርቲያችንና በህዝቡ ላይ የሚደርሰውን በደል እና ሰላማዊ ሰልፉን ለህዝብ በማድረስ ግዴታችሁን እንድትወጡ አደራ እንላለን፡፡ በተለይ ሌሎች ሚደያዎች በታፈኑበት በአንጻራዊነት የህዝብ ድምጽ በመሆን ላይ በሚገኘው ፌስ ቡክ በኩል መረጃዎችን ለህዝብ በማድረስ ቀላል የማይባል ጫና መፍጠር የሚቻል በመሆኑ አጋጣሚውን በመጠቀም መብታችን ለማስመለስ እንድንታገልና በሰልፉም እንድንገኝ አደራችን እናስተላልፋለን፡፡
ኑ ራሳችን ነጻ በማውጣት የአገራችን እጣ ፈንታ እንወስን!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
                                                                   Posted A.G

Bloggers and activists are arrested in Ethiopia

Bloggers and activists are arrested in Ethiopia

April 25, 2014
Six members of Zone Nine, group of bloggers and activists are arrested today late in the afternoon at 5:20 pm by Ethiopian security forces. Team members Befeqadu Hailu, Atnaf Berahane, Mahlet Fantahun, Zelalem Kiberet, Natnael Feleke and Abel Wabela are all under custody on arrest warrant.

The arrest comes immediately after the bloggers and activists notified their return to their usual activism on April 23, 2014 after their inactivity for the past seven months. On their return note the group has indicated that they have sustained a considerable amount of surveillance and harassment. They have indicated that one of their reasons for their disappearance from activism is the harassment they have been receiving from government security agents.

This one of the young souls currently locked up in makalwi Woyane notorious jail . Nathanael all our thoughts are with u :((((

We believe members and friends of Zone Nine have nothing to do with illegal activities and we request the government to release them immediately.
——————————–
ዛሬ አርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2006 አመሻሹ ላይ 11፡20 ገደማ ስድስት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን አባላት የሆኑት ጓደኞቻችን በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከያሉበት ተይዘዋል፡፡ እነርሱም ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ አጥናፍ ብረሀነ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ዘላለም ክብረት እና አቤል ዋበላ ናቸው፡፡ ጦማርያኑን ጓደኞቻችን ለማሰር የመጡት አካላት የማሰሪያና የመፈተሻ የፍርድ ቤት ፈቃድ የያዙ መሆናቸውን ሰምተናልአ መደበኛ የሆነው “ዞን 9” የጦማርያን ስብስብ አባላት ሚያዚያ 15፣2006 በዋጣነው መግለጫ ላለፉት ሰባት ወራት የዞኑ አባላት ከፍተኛ የሆነ ክትትል ሲደረግባቸው እንደነበር በጠቅላላው የተጠቆመ ሲሆን ክትትሉ የተወሰኑ የቡድኑን አባላትና የቅርብ ወዳጆችን ጭምር ያካተተ ነበር፡፡ አሁን በመንግስት የተወሰደው እርምጃ የዞኑን ተመልሶ ወደ ስራ መግባት ተከትሎ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ሆኖም የዞን 9 አባላትና ወዳጆች በምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው እነዳልነበር ለማረጋገጥ እንወዳለ፡፡ በመሆኑም የታሰሩ የዞኑ አባላትና ወዳጆች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን::
                                                                                     Posted A.G

Thursday 17 April 2014

ይድረስ ለብዙሃኑ የሠራዊቱ አባል ወገናችን!! Source,http://www.ginbot7.org /2014/04/17/

የመከላከያ ሚኒስትር በተሰኘው የውሸት ሥልጣን ላይ የተቀመጠው አድርባይ ሲራጅ ፈርጌሳ ለይስሙላው ምክር ቤት ባቀረበው ሪፓርት፣ “የመከላከያ ሚኒስትር የብሔር ተዋጽዖ የተመጣጠነ” እንደሆነ ገለፀ። እንደ ሰውየው ሪፓርት ከሆነ የመከላከያ ሠራዊቱ 29.46 በመቶ አማራ፣ 25.05 በመቶው ከደቡብ ብሔሮች የተውጣጣ፣ 24.45 በመቶ ኦሮሞ፣ 17.47 በመቶው ትግራይ እና የተቀሩት ክልሎች ድርሻ 4.17 በመቶ ነው። መረጃው የተቀናበረው በክልል ቢሆንም የቀረበው ግን በዘር ነው። “ተመጣጠነ” የተባለውም የክልሎች ተዋጽዖ ሳይሆን የዘር ተዋጽዖ ነው። ሠራዊቱን እንዲህ በዘር ሸንሽንኖ የስታትስቲክስ ጨዋታ መጫወት አሳዛኝም አሳሳቢም ነገር ነው። የሆነ ሆኖ ይህ መረጃ፣ መረጃ ነው ተብሎ ለሕዝብ ቀርቧል።
ይህንን መረጃ የሰማ ማሰብ የሚችል አዕምሮ ያለው ሰው የሚጠይቀው የመጀመሪያ ጥያቄ “የሠራዊቱ ስብጥር በተገለፀበት ዓይነት የመኮንኖቹም ስብጥር ለምን አልተገለፀም?” የሚል ነው። ይህ ጥያቄ በአስተዋይ ሰው አዕምሮ ውስጥ በተነሳነበት ፍጥነት ምላሽ ያገኛል፤ ምክንያቱም ምላሹ እዚያው እቁጥሮቹ ውስጥ አለ። የመኮንኖቹ ስብጥር ያልተነገረበት ምክንያት አብዛኞቹ መኮንኖች በ17.47 በመቶው በመሆናቸው ነው። ወደዚህ መምደሚያ የሚደርሰው አሳቢው ስለፈለገው ሳይሆን የመረጃው አቀራረብ አመክኖ (ሎጂክ) ወደዚያ ስለሚገፋ ነው። በዚህም ምክንያት በሲራጅ ፈርጌሳ አንባቢነት የቀረበው የህወሓት ሪፓርት በገዛ ራሱ ላይ ነው የተኮሰውም።
እኛ እንደ ሲራጅ ፈርጌሳ የዘር ስታትስቲክስ ውስጥ አንገባም፤ መልዕክታችን ለተገፋውና እየተበደለ ላለው ለመላው የሠራዊቱ አባል ነው።
ይድረስ ሹመትና ኃላፊነት ተነፈገህ፤ የጥቂቶቹን ሀብትና ዝና ጠባቂ እንድትሆን ለተፈረደብህ ወገናችን!!! እስከመቼ ለህወሓትና ጥቂት አጎብዳጅ መኮንኖች ባርነት ትገዛለህ? ይህ ውርደትህ የሚያበቃው መቼ ነው? የታጠቀው መሣሪያ የአገርህና የራስህ ክብር ማስጠበቂያ፤ ነፃነትህን መጎናፀፊያ የምታደርገው መቼ ነው? ለመሆኑ ለመኮንንነት የሚያበቃ ጭንቅላት፣ ልምድ ወይም እውቀት ከፓርቲ አባልነት ነው የሚገኘው? ህወሓቶችና አጋሮቻቸው በሠራዊቱ ያሉትን ቁልፍ ኃላፊነቶችን ሁሉ ጠቅልለው ይዘው “ጀሌዎቻችን እንዲሆኑ ፈቅደንላቸዋል” የሚል ሪፓርት የሚያቀርቡት ምንኛ ቢንቁን ነው? ይህንን ውርደት ኢትዮጵያዊው ወኔህ እንዴት ይቀበለዋል?
ኢትዮጵያዊው ወታደር ከሌላው ኢትዮጵያዊ በባሰ በአምባገነንና ዘረኛ አለቆቹ እየተዋረደ እንደሆነ በገሃድ የሚታይ ጉዳይ ነው። የህወሓት አባላት ቁልፍ የስልጣን ቦታዎችን ይዘው ጦር ሠራዊቱን እንደ ፓርቲ መዋቅር ሲመሩት ማየት የሠራዊቱን አባላት ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያንገበግብ ጉዳይ ነው። ሠራዊቱ አገርና ሕዝብን ሊጠብቅበት ይገባ የነበረውን መሣሪያ በንጹሃን ዜጎች ላይ እንዲያነሳ፤ ሰላማዊ ሰዎችን እንዲደበድብ፣ እንዲረግጥና እንዲገድል የሚያዙት እነዚህ የህወሓትና ጥቂት አጎብዳጅ አለቆቹ እንደሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቃል። ሆኖም የኢትዮጵያ ወታደር የታዘዘው ሁሉ የሚፈጽም ባርያ አይደለምና በእነዚህ ጥቂት ዘረኛ አለቆችህ ላይ እንዲነሳ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይጠይቃል።
ውድ የኢትዮጵያ ወታደር ሆይ!!! “ዘረኛነት በቃኝ” በል። ለነፃነት፤ ለእኩልነት፤ ለአገር ክብር በሚታገሉ ወገኖችህ ላይ ክንድህን አታንሳ። የጥቂት ዘረኞችን ሥልጣን በማራዘም ከሚመካብክ የኢትዮጵያ ድሃ ሕዝብ ጋር ዘላቂ ቂም ውስጥ አትግባ። በትእቢት “ሁልሽንም ረግጠን እንገዛለን” ብለው የሚፎክሩት አንተን ከወገንህ ጋር ደም በማቃባት ነውና “እምቢ!” በላቸው። ለዘረኞች ስልጣን ብለህ አትሙት! እንዲያውም ለገዛ ራስህ ክብር፣ ለቤተሰቦችህና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ቀደም አርበኛ ሁን።
ከላይ የተባለው ለፓሊስ አባላትም ይሠራል። በህወሓትና ህወሓት በየቦታው በፈጠራቸው ጀሌዎች የሚመራ በመሆኑ ከሕዝብ ፍላጎት በተፃፃሪ የቆመ ይምሰል እንጂ የኢትዮጵያ ፓሊስ የሕዝብ ወገን እንደሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች የታየ ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በፍትህ እጦት የሚሰቃየውን ያህል ብዙሃኑ ፓሊስ በፍትህ እጦት እየተሰቃየ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ የኑሮ ጫና እንዳዳከመው ሁሉ የኢትዮጵያ ፓሊስም ኑሮ ከብዶታል። እንደሌላው ሰው ሁሉ ፓሊስንም ዘረኝነት አስመርሮታል። ብዙሃኑ ፓሊስ አቅሙን በጥቂት አምባገነን አለቆቹ ላይ የሚፈትሽበት ጊዜ ደርሷል።
የስለላ ተቋማቱ ጉዳይ ለየት ይላል። “ደህንነት” ተብሎ በሚሞካሸው የጆሮጠቢዎች ስብስብ በሆነው መሥሪያቤት እና በኤክትሮኒክስ ብርበራ የተሠማሩ “ባለሙያ ጆሮ ጠቢዎች” ውስጥ ህወሓት በአለቃነትም በምንዝርነትም አብዛኛውን ቦታ ይዟል። ሆኖም እዚህም የሕዝብ ወገኖች እንዳሉ ይታወቃሉ። በእነዚህ ቦታዎች ያላችሁ የሕዝብ ወገኖች ሲቻል በገሃድ ሳይቻል በሚስጥር ተቋማቱን የማዳከም ሥራችዎችን መሥራት የህሊናና የዜግነት ግዴታችሁ ነው። ከእናንተ ብዙ፤ እጅግ ብዙ ይጠበቃል። የምታሾልኳት ትንሿ መረጃ የብዙዎችን ሕይወት ልትታደግ ትችላለች፡
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በህወሓት የጦር፣ የፓሊስና የስለላ መዋቅሮች ውስጥ የሕዝብ ወገኖች እንዳሉ ያውቃል። እነዚህ ወገኖቻችን እንደሌላው ሕዝብ ሁሉ – አንዳንዴም ከሌላው በባሰ ሁኔታ – በፍትህ እጦት፣ በኑሮ መክበድና በዘረኝነት እየተሰቃዩ መሆናቸው ያውቃል። እነዚህ ወገኖቻችን ጥለው እንዲወጡ፤ ይህ ካልተቻለም ከውስጥ ሆነው የወያኔን የጦር፣ የፓሊስና የስለላ መዋቅሮች እንዲያፈራርሱ ጥሪ ያደርጋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
                                                                                                             Posted A.G

Monday 7 April 2014

አንብባችሁ ሌሎች እንዲያነቡትና ውይይት እንዲያደርጉበት የተቻላችሁን ጥረት እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃችኋለን።


ማሳሰቢያ 

     ይህን አነስተኛ ሰነድ የተወሰደው ከ220 ገጾች በላይ ርዝማኔ ካለው የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የፖለቲካ ስልጠና ሰነድ ነው። ዋናው የስልጠናው ሰነድ እኔ፣ እኛና ህዝባዊ ሰራዊቱ፣ ሃገራችን ኢትዮጵያ፣ የፖለቲካና የፍልስፍና ጽንጸ ሃሳቦችና ንድፈ-ሃሳቦች በሚሉ 4 ምእራፎች የተከፋፈለ ነው። በዚህ ተቀንጭቦ በቀረበው ሰነድ ውስጥ የተነሱ ጉዳዮች አንዳቸውም ሳይቀሩ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል ድርጅትና አባላት ብቻ ጉዳዮች ናቸው ብለን አናምን። የሁሉም የሃገራችን የፖለቲካ ድርጅቶችና አባሎቻቸው፣ እንዲሁም የአጠቃላይ የማህበረሰባችን ጉዳዮች ናቸው ብለን እናምናለን። በዚህ ሰነድ ውስጥ በተነሱ ጉዳዮች ላይ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል አባላት የሚያደርጉትን ሰፊና ጥልቅ ውይይት በትንሹም ቢሆን በማህበረሰባችን ውስጥ እንዲደረግ ካስቻልን ለሁላችንም ጠቀሜታ የሚኖረው መስሎናል። በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ የምንፈልገው በዚህ ሰነድ ውስጥ የተነሱ ችግሮች በመሰረቱ ሊቃለሉ የሚችሉት ተገቢ የሆኑ የስርአት ለውጦችና ተገቢው የሆኑ ተቋማት ሲመሰረቱ እንደሆነ እናውቃለን። ቁልፍ የሆኑት ከፖለቲካው ጋር የተያያዙ የስርአትና የተቋማት ለውጦች ናቸው። ከዚህ አንጻር ነገሮችን ካየናቸው ይህን አይነቱ ሰነድ ወይም ሌላ ምንም አይነት ሰበካ፣ ትንታኔ፣ ውይይት፣ የንባብና የምርምር ጥረት መሰረታዊ የሆነውን ለውጥ ለብቻቸው ያመጣሉ ብለን አናምንም። ችግሩ ያለው የምንመኛቸውን መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ስርአቶችና ተቋማት በሃገራችን የሉም። እነሱን ደግሞ የምንፈጥራቸው እኛውየሃገሪቱ ዜጎች ነን። ይህ ሰነድ ሌላው ሁሉ ቢቀር በግለሰብ፣ በቡድንና በድርጅት ደረጃ ችግሮቻችን ምን ያህል ጥልቅና 
ውስብስብ እንደሆኑ መገንዘብ እንድንችል ያደርገናል የሚል እምነት አለን። ችግሮቹን ከተገነዘብን የመፍትሄዎቻቸውን ፍንጭ ለማየት አያዳግተንም። ስለሆነም ይህን ሰነድ ከግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ውጭ የሚገኙ ወገኖቻችን እንዲያነቡት በማሰብ በስፋት እንዲሰራጭ ወስነናል:: 

አንብባችሁ ሌሎች እንዲያነቡትና ውይይት እንዲያደርጉበት የተቻላችሁን ጥረት እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃችኋለን። 



የፖለቲካ ስልጠና 

ምእራፍ 1- እኔ 

የፖለቲካ ሥልጠና ትምህርታችን የሚጀምረው እኔ በሚለው ርዕስ ነው። ለምን ይህ ርዕስ ከሁሉም ርዕሶች ቀደመ? በዚህ ርዕስ ሥር ምን ጉዳዮች እናነሳለን? በመጨረሻም የዚህን ርዕስ ወይይት ስንጨርስ ምን መጨበጥ ወይም ማግኘት ይቻላል ብለን እናምናለን? የሚቀጥለው ሃተታ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ ይሆናል። 

1. ለምን እኔ በሚለው ርዕስ ጀመርን? 

    መልሱ ቀላል ነው። ሁላችንም ወደ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ስንመጣ በግላችን ነው የመጣነው። ከሌሎች ጓደኞቻችን ጋር ብንመጣም ሕዝባዊ ኃይሉን እንቀላቀል የሚለውን ውሳኔ የወሰንነው እያንዳንዳችን በተናጠል ነው። ብዙዎቻችን ከዚህ በፊት አንተዋወቅም። የመጣነው እያንዳንዳችን ከሌላው ጋር ሆነን፣ ድርጅት ፈጥረን፣ ወያኔን ተዋግተን እናስወግዳለን ብለን አስበን ነው። ከተሰባሰብን በኋላ ከተናጠል ወደ ብዙሃን ተቀይረናል። ከእኔ እኛ ሆነናል። የእኛነታችን መሠረት ግን እኔ ነው። የእኛነታችን መነሻ እኔ ሆኖ መድረሻችን ደግሞ እኛ ሆኗል። መነሻውን የማያውቅ መድረሻውን አያውቅም ይባላል። እኔን ሳናውቅ እኛን ማወቅና እኛን መሆን አይቻልም። በመሆኑም እኔ ማነኝ የሚለውን ጥያቄ በቅድሚያ በሚገባ ለራሴ መመለስ መቻል ይኖርብኛል። ከሌሎቹ ጓዶቼ የሚቀርብልኝ አንተ ማነህ የሚል ጥያቄ በሚገባ መመለስ የምችለው ስለራሴ ከሚኖረኝ ጥልቅ እውቀት በመነሳት ብቻ ነው። እውን ስንቶቻችን ነን እራሳችን በደንብ የምናውቅ? እኔ ማነኝ ለሚለው ጥያቄ የተሟላ መልስ ለመስጠት ትልቅ ድፍረትና ከራስ ጋር መፋጠጥን ይጠይቃል። ጀግንነትን ይጠይቃል። ከራስ ስሜት፣ ዝንባሌና ፍላጎት ጋር መሟገት ያስፈልጋል። የራስን አእምሮና ነፍስ መበርበር ያስፈልጋል። 

    እኔ ማነኝ ለሚለው ጥያቄ በሚገባ መልስ ስሰጥ ነው ነገ በጦር ሜዳ ጓዴን ጥዬ እንደማልሸሽ፣ ወንድሜን በሰላሳ ሽልንግ እንደማልሸጥ እርግጠኛ የምሆነው። ወያኔ እንዳደረገው ነፃ አወጣዋለሁ የምለውን ሕዝብ መልሼ ረጋጭ መሆን እንደማልችል የማውቀው። ዘራፊ፣ ገፋፊ፣ አስገድዶ ደፋሪ እንደማልሆን እርግጠኛ መሆን የምችለው። ሰለ ሀገሬ ስለወገኔ መዋረድ የማነበንባቸውን ቃላት፣ ጉልበቱ እድሉ ስልጣኑ ሲኖረኝ ወደ በጎ ተግባራት እንደምቀይራቸው እርግጠኛ የምሆነው ራሴን በሚገባ ሳውቅ ነው። ጽናት ኖሮኝ የምዘልቅ፣ ምንም ፈተናና ችግር ወያኔን ከመደምሰስ ሊያስቆመኝ እንደማይችል እርግጠኛ የምሆነው እራሴን በሚገባ ሳውቅ ብቻ ነው:: ለጓዴ፣ ለድርጅቴ ለሃገሬ ሰዎችና ለሃገሬ የገባሁትን ቃል የማላጥፍ እንደሆነ እርግጠኛ የምሆነው እኔ ማነኝ ለሚለው ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ስሰጥ ነው። 


     እኔ ማነኝ የሚለውን ጥያቄ በሚገባ ለራሴ ስመልስ ከጓዶቼ የሚቀርብልኝን አንተ ማነህ የሚል ጥያቄ በቀላሉና በእርግጠኛነት መመለስ እችላለሁ። እኔ፣ የእኛ የግንቦት 7 ሕዝባዊ አባላት ስብስብና ድርጅት፣ ከዛም አልፎ የማኅበረሰባችንና የሀገራችን የመሠረት ድንጋይ ነው። የመሠረት ድንጋይ ብቻ አይደለም። ድርጅታችንን፣ ማኅበረሰባችንና ሀገራችንን የምንገነባበት እያንዳንዱ ጡብ እኔ ነው። እኔ በደንብ ካልተገነባ፣ እኔ በደንብ ካልታነጸ፣ እኔ ነካ ሲያደርጉት የሚፈርስ፣ እፍ ሲሉት ብን የሚል ከሆነ፣ እኔ የሚያዝ የሚጨበጥ የሌለው ሙልጭልጭ፣ እኔ መርህ- የለሽ ልክስክስ፣ አከርካሪ የለሽ ልምጥምጥ ከሆነ እኛም የለንም። ድርጅት አይኖርም። ማኅበረሰብ መማቀቁ፣ ሀገር መውደሙ አይቀርም። 

    እንደ ወያኔ ድርጅት በሚያጭበረብሩ መሪዎችና ተከታዮች የተገነባ ድርጅት በለስ ቀንቶት ወያኔን ቢያስወግድ የሚፈጥረው ሀገራዊና መንግሥታዊ ሥርዓት የአጭበርባሪዎች ይሆናል። አድሎን፣ የድርጅትን ንብረት እንደራስ አድርጎ አለማየትን፣ ራስ ማስቀደምን፣ መስገብገብን፣ ወታደራዊ ፖሊስ ወይ ጓዶቼ አያዩኝም በሚል በጋራ ያጸደቁትን ሕግ ሥርዓትና ደንብ የሚጥሱ፣ ለጓዶቻቸው ደህንነትና ጤንነት የማይጨነቁ፣ እርስ በርስ የማይፋቀሩ፣ የግል ድሎትንና ምቾትን ብቻ ማሰላሰልን ሥራዬ ብለው የያዙ አባላት የተሰባሰቡበት ድርጅት ታግሎ አታጋይ መሆን አይችልም። እንደ ድርጅትም መዝለቅ አይችልም። ነጻ ወጥቶ ሌላውን ነጻ ማውጣት አይችልም። በአንድ ተአምር ወያኔን ማስወገድ ቢሳካለት ከወያኔ በላይ ሕዝብ አስመርሮ ወያኔ ማረኝ የሚል ዘመን እንዲመጣ ማድረጉ አይቀርም። በሀገራችን ታሪክ የሆነው ይህ ነው። ደርግን ያየ ሃይለስላሴ ማረኝ አለ። ወያኔን ያየ ደርግ ማረኝ አለ። እኛን ያየ ወያኔ ማረኝ የሚልበትን ሁኔታ ልንፈጥር አይደለም ትግል ውስጥ የገባነው። እኛ ትግል ውስጥ የገባነው መንግሥት ተቀይሮ መንግሥት በመጣ ቁጥር ካለፈው ሥርዓት አዲሱ እየባሰበት የሕዝብ ስቃይ የረዘመበትን የታሪክ ጉዞ ለመቅጨት ነው። 

    እያንዳንዳችን ወደ ትግል የገባነው የሕዝብ እሮሮና ስቃይን ለአንዴና ለመጨረሻው እልባት ወይም መቋጫ ልናበጅለት ነው። ይህ ማድረግ የምንችለው በምንገነባው ድርጅት አማካይነት ነው። የምንገነባው ድርጅት የሚሰራው ከሲሚንቶና ከአሸዋ ወይም ከሌሎች ቁሳቁሶች አይደለም። በሰው ነው። በእኔ ነው። ሰው እንደሸክላ እንደ ብሎኬት ከአሸዋና ከሲሚንቶ የሚሰራ ወይም እንደ እንስሳ የምናራባው ፍጥረት አይደለም። 

  ሰውን ሌላው ሰው አይሰራውም። ሰው ራሱን በራሱ ብቻ የሚሰራ ፍጥረት ነው። እኔ ፈቃደኛ ካልሆንኩ፣ ለመማር ዝግጁ ካልሆንኩ ሌላው ሰው ላስተምርህ፣ ልምከርህ ቢለኝ ዋጋ የለውም። 

  ዛሬ እኔነታችንን ወደፊት ለማምጣት ለምንፈልገው ሀገራዊና ማኅበረሰባዊ ለውጥ እንዲመች አድርገን በሚገባ እዚሁ ካላነጽነው መጨረሻችን አሳፋሪ ውድቀት ነው። የሀገር እጣ፣ የ90 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እጣ የሚወሰነው እዚህ እኛ መሃል እያንዳንዳችን በምንላበሰው ስብእና፣ በሚኖረን ሰብአዊ ሥነሥርዓትና ጥብቅነት፣ በምንገነባው የአብሮነትና የአንድነት ስሜት፣ በምንሸምተው እውቀትና ክህሎት ላይ ተመስረቶ ነው። እባብ ከሆነን የርግብ እንቁላል አንጥልም። የእባብ ፍልፈሎች እንጂ። ለዚህ ነው ከማናቸውም ጉዳዮች በላይ በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ውስጥ እኔ ማነኝ ለሚለው ጥያቄ ቅድሚያ የሰጠነው። እኔ ማነኝ ወይም አንተ ማነህ ለሚለው ጥያቄ በጣም ቀላል ከሆኑ ነገሮች ተነስተን መልስ መስጠት እንችላለን። የእኔ ማነኝ ጥያቄ ምላሽ ግን እንደምናስበው ቀላል እንዳልሆነ ቀጥለን እንመለከታለን። 

2. እኔ ማነኝ 

“አንተ ማነህ? 
“እኔ?” 
“አወን፣ አንተ” 
“እኔማ ከበደ አበበ ነኝ፣ እንደ ሰው በማልቆጠርበት ኢትዮጵያ በምትባል ሀገር የምኖር ሰው ነኝ” 
“ሰው መሆንክን አውቃለሁ። እሱ ምን ችግር አለው። ስምም የሁላችንም ነው። ሃገርም እንደዛው። ከዚህ ውጭ ሌላ ነገር ስለራስህ ንገረኝ።” 
“እንደምታየኝ ወጣት ኢትዮጵያዊ ነኝ። እድሜዬ 30 አመት ነው። የተወለድኩት ጎንደር፣ አዲስ ዘመን ነው። እስከ 12ኝ ክፍል ተምሬአለሁ። በውትድርና ሙያ ሰርቻለሁ። 3 ወንድሞች 2 እህቶች አሉኝ። እኔ የመጨረሻው ልጅ ነኝ። የመጀመሪያው ወንድሜ ታላቃችን አዲስ አበባ ውስጥ በምርጫ 97 ወቅት በወያኔ ተገድሏል። ሁለቱ እህቶቼ በሃገራቸው ስራ አጥተው አረብ ሀገር ሥራ ብለው ሄደዋል። እናቴ በውንድሜ ሞት ሃዘን የተነሳ ብዙም ሳትቆይ አርፋላች። አባቴ ነጋዴ ነው። በሕይወት አለ። ወያኔ ከምርጫ 97 በኋላ ተቃዋሚ ትደግፋለህ ብሎ አሰረኝ። ከዛም ከሠራዊቱ ተባረሃል ብሎ ፈታኝ። መጀመሪያውኑ የወያኔ ወታደር መሆን አልነበረብኝም። በሠራዊቱ ውስጥ ያየሁት የዘር አድሎና መጠቃቀም ቆሽቴን ያበግነው ነበር። የከፍተኛ መኮንኖቹ እጅግ የሚገርም በዘር ላይ የተመሰረተ የዘረፋና የቅንጦት ህይወትና የተራው ወታደር ሬት ሬት የሚል ህይወት አንገሽግሾኝ ነበር። መባረሩን በደስታ ነው የተቀበልኩት። ችግሩ ሌላ ሥራ ማግኘት አልቻኩም። በመንግሥት መስሪያ ቤት እንዳልቀጠር በጸረ_መንግሥትነት የሚፈርጅ ደብዳቤ ሰጥተው ነው ከሰራዊቱ ያባረሩኝ። ያንን ደብዳቤ እያየ ማንም የሚቀጥረኝ ጠፋ። በግል ሥራ እዛም እዚህም ሁሉን ነገር ሞከርኩት። ነገር ግን የኑሮ ውድነቱ፣ መተንፈሻ የነሳኝ የሰላዩ ብዛትና አፈናው፣ የወንድሜና የናቴ ደም መና ሆኖ መቅረቱ፣ በአ
ረብ ሃገር በእህቶቼ ላይ የሚደርሰው ውርደትና ስቃይ፣ ወያኔዎች ሲፋፉ እኔ እንደ ስልክ እንጨት መድረቄ ሌላውም ተደራርቦ ወያኔን መታገል አለብኝ ወደሚል መደምደሚያ አደረሰኝ። የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል መቋቋሙን ሰማሁ። መጣሁ። ተቀላቀልኩ። የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አባል ነኝ” 


     ከዚህ በላይ እንደተመለከትነው እኔ ማነኝ ወይም አንተ ማነህ የሚለው ጥያቄ በዚህ መልኩ ሊመለስ ይችላል። ይህ ምላሽ ግን ሁላችንም በየግላችን እንደማንነታችን የምንመልሰው ምላሽ ነው። ይህን አይነት ምላሽ ለመስጠት ሁላችንም ብዙ አይቸግረንም። ሁላችንም በየግላችን ስለራሳችን ታሪክ በቀላሉ የምናየው ጭብጥ ነው። ስማችን፣ የተወለድንበት ቦታ፣ እድሜያችን ወዘተ አይቀየርም። ስለወያኔም ሥርዓት የምንናገረው ጭብጥ እንዲሁ ለሁላችንም አንድ ነው። በወያኔ የደረሰብን በደል ይለያይ እንጂ ሁላችንም በደል ደርሶብናል። የምሬታችን ደረጃ ይለያይ እንጂ ሁላችንም መሮናል። ይህ ምሬት ሁላችንንም ወያኔን እንድንታገለው ገፍቶን በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ውስጥ አሰባስቦናል። ወደ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ስንመጣ ደረቅ ስማችን፣ የግልና የቤተሰብ ታሪካችንን፣ የግል ብሶታችንን ብቻ ግን ይዘን አልመጣንም። ቀጥለን እንደምንመለከተው ብዙ ነገር ይዘን መጥተናል። 

እኔ ማነኝ? 

    ወደ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ስመጣ ምን ይዤ መጣሁ? ስሜን ብቻ ነውን? በወያኔ ላይ ያለኝ ምሬትና ጥላቻ ብቻ ነውን? በደል የወለደው ምሬትንና መንገፍገፍ ብቻ ነውን? መንገፍገፍ የወለደው እልህና ቁጭት ብቻ ነውን? እነዚህ ብቻ አይደሉም። ሌሎችም ነገሮች ይዤ መጥቻለሁ። እያንዳንዳችን የተለያዩ ሙያዎቻችንን ይዘን መጥተናል። የወታደራዊ፣ የሂሳብ ሠራተኛነት፣ የጋዜጠኛነት፣ የሃኪምነት፣ የግንበኛነት፣ የገበሬነትና የአስተማሪነት ወዘተ የመሳሰሉትን ሙያዎች ይዘን መጥተናል። ግን እነዚህን ብቻ ነውን ይዘን የመጣነው? የለበስኩትን ልብስ ብቻ ነው ወይስ መቀየሪያ ጭምር፣ ገንዘብ፣ መሣሪያ፣ ሞባይል፣ መጽሃፍ ይዤ መጥቻለሁን? በሽታ፣ ህመምና ቁስል ይዤ መጥቻለሁን? የሲጋራ፣ የመጠጥ፣ የጫት ሱስ ይዜ መጥቻለሁን? ሌላም ጥያቄ ማንሳት ይቻላል። 

     ከዚህ በላይ የተጠቀሱት እኔ ወደ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ይዣቸው የመጣኋቸው ወይም ላመጣቸው የሚችሉ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ነገሮች የተለያዩ ጥቅምና ጉዳት አላቸው። ስሜ ታሪኬ ማንም አይጎዳም። ሙያዬ ይዤ የመጣሁት ንብረት ገንዘብ ወዘተ የኃይሉን አባላትና ድርጅታችንን ይጠቅማል። በሽታ፣ ህመም ቁስል ይዤ ከመጣሁ ቆራጥነቱና ጽናቱ እስካለኝ ድረስ ጤናዬንና አቅሜን የሚመጥን ተግባር እያከናወንኩ ለትግሉ የድርሻየን አበረክታለሁ። ከነህመሜ የጓዶቼ መመኪያ መሆን እችላለሁ። ይዤ የመጣሁት ሱስ ካለ ግን ምንም ጠቀሜታ የለውም። በዚህ ሱስ የተነሳ እራሴን እጎዳለሁ። ጓዶቼን እጎዳለሁ። የሱስ ምርኮኛ መሆን ሱስ ለማርካት ሲባል የማያመጣብኝ ፈተና አይኖርም። 

   ሱስ አላስፈላጊ የደህንነት አደጋ ያለበት ሁኔታ ውስጥ ይጨምረኛል። ሱስ ልመናን ውርደት ያስከትላል። ሱስ የድርጅትን የአደራን ገንዘብና ንብረት ማባከንንና ሌባ መባልን ያስከትላል። ሱሱ ምሱን ካላገኘ ማንቀላፋት፣ መንገላጀጅ፣ ትእግስት የሌለን፣ የምንነጫነጭ፣ የምንቀዠቀዠ ወይንም የምንደበት ያደርገናል። ሱስ ሰው እራሱ ጥሮ ግሮ ወይም ሌሎች ጓዶቹ ጥረው ግረው ላባቸውን አንቆርቁረው ያሰባሰቡትን ሃብት በከንቱ እንዲባክን የሚያስደርግ ነው። እንኳን ለትልቅ ዓላማ አባላት በተሰባሰቡበት ድርጅት ውስጥ ቀርቶ የግል ሕይወት በሚኖርበት ሁኔታ ይህ ብክነት አሳዛኝ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የተጠቀሱት ሱሶች በተለያየ ደረጃ በጤንነታችን ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ናቸው። ሲጋር በቀጥታ ከሳምባና ከልብ ጋር፣ መጠጥ ከልብ፣ ከጉበት፣ ከኩላሊት ወዘተ ጋር፣ ጫት ከሆድ ከአእምሮ ጋር የተያዙ የጤንነት ጉዳት አላቸው። ይህ ጉዳት እያንዳንዱ ሱስ ያለበትን ሰው በተለየ የሚጎዳ ቢሆንም የርሱ መጎዳት በሌሎች ላይ ጉዳት ያስከትላል። ጤና የሌለው፣ የአእምሮና የአካል ብቃት የሌለው ታጋይ ከሌሎች ጓዶቹ ጋር በእኩልነት መንቀሳቀስ አይችልም። በጉዞ መድከም፣ መፍዘዝ ይመጣል። እነዚህ ሱሶች የየግለሰቡ ናቸው ብለን የማንተዋቸው ለዚህ ነው። ሌሎችንም ጉዳት ላይ የሚጥሉ መዘዞች አላቸው። እኔ ማነኝ ስንል እነዚህ አይነት ሱሶች ካሉን እነዚህ ሱሶች ያ
ሉኝ ግለሰብ ነኝ የሚል ተጨማሪ ምላሽ ይኖረዋል። እኔ ማነኝ የሚለው ጥያቄ ግን በነዚህ ስለራሴ ባቀርብኳቸው ጭብጦች ብቻ የሚጠቃለል አይደለም። የተሟላ ምላሽ ለማግኘት ብዙ የሚቀረው ነጥቦች አሉ። 

እኔ ማነኝ? 

    እኔ ማለት ስሜ፣ ንብረቴ፣ ሱሶቼ፣ እድሜ፣ የትውልድ ቦታዬ፣ ጎሳዬ ዘሬ፣ ሃይማኖቴ ብቻ ናቸው ወይ? ወይንስ ሌሎች ጓዶቼ በቀላሉ ሊደርሱባቸው የማይቹላቸውና የማያዩዋቸው እኔ ግን ለብቻዬ የማውቃቸው ነገሮችም ይዤ መጥቻለሁ። እነዚህ ጓዶቼ በቀላሉ ለማየት የማይችሏቸው ነገሮች ግን እኔ የማውቃቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? 

ድፍረት፣ ጀግንነት፣ ቆራጥነት፣ ታማኝነት፣ ፍቅርን፣ ትእግስትን፣ ጽናትን ወዘተ ይዤ መጥቻለሁ? ሌሎችስ የነዚህ ተቃራኒ የሆኑ። ፈሪነትን መሠሪነትን፣ ክፋትን፣ ተንኮልን፣ መዋሸትን፣ ወላዋይነትን፣ ተራ ቅናትን፣ አሉባልተኛነትን ወሬኛነትን፣ አጭበርባሪነትን፣ ተላታሚነትን፣ ጠብ ጫሪነትን፣ መለገምን፣ መስገብገብንስ፣ ቱግ ማለትን ግብዝነትን ይዤ መጥቻለሁ? እየዋልን እያደርን መተዋወቅ ስንጀምር ለነዚህ ጥያቄዎች አንዳችን ስለአንዳችን የምንለው ነገር ይኖረን ይሆናል። ገና ሕዝባዊ ኃይሉን ስንቀላቀል ግን በነዚህ ጉዳዮች ላይ ስለእኔ ከኔ በስተቀር ማንም የሚያውቅ ሰው አይኖርም። ፈሪ ልሁን ደፋር፣ ሃቀኛ ልሁን አጭበርባሪ የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ። ደፋር፣ ሃቀኛ፣ ጀግና፣ ታማኝ፣ ጓዱን አፍቃሪ የሆኑ ባህሪዎቼ ለጎዶቼና ለድርጅቴ ጥንካሬዎች ናቸው። ሌሎች ባህሪዎቼ፣ ለምሳሌ መዋሸት፣ መወላወል፣ ተላታሚነት፣ አምባገነንነት፣ ሌብነት፣ ስግብግብነት ግለሰበኛነት፣ ወዘተ የሕዝባዊ አባላቱንና ድርጅቱን የሚጎዱ አደጋ ላይ የሚጥሉ መጥፎ ባህሪዎች ናቸው። ቀደም ብለን ከጠቀስናቸው ከሱስ ጋር ተያያዥነት ካላቸው ችግሮች እጅግ የከፉ ናቸው። ለምን ብለን እንጠይቅ። 

     አሉባልተኛ ሰው ድርጅት ያምሳል። በአሉባልታው የተነሳ ግለሰቦችና ቡድኖች እርስበርሳቸው ሊጋጩ፣ በመሃከላቸው መተማመን ሊጠፋ ይችላል። ብሎም ድርጅት እስከማፍረስ ሊደርስ ይችላል። የሲጋራ ሱስ ወይም የመጠጥ ሱስ ያለበት ሰው ራሱን በቅድሚያ ይጎዳል። ድርጅቱንም ይጎዳል ግን ድርጊቱ ድርጅት የሚያፈርስ አይሆንም። ሲጋራ የሚያጨስ ሰው በጀግንነት ሊዋጋ ይችላል። ወላዋይ ሰው ግን ጓዶቹን በጦር ሜዳ ጥሎ ሊፈረጥጥ ይችላል። ሌሎችም ጎጂ የሆኑ ባህርይዎቻችንና ባህሎቻችን እያንዳንዳንችን ቤተስብ፣ ሃብት፣ ቤትና ንብረት በትነን እዚህ የተሰባሰብንለትን ዓላማ እንዳናሳካ የሚያደርግ አቅም አላቸው። ዋናውን ጠላት ወያኔን ትተን እርስ በርስ እንድንባላ፣ ወያኔ እስካሁን ካደረሰብን በደል በላይ የከፋ በደል እንዲያደርስብን የሚያደርጉ ናቸው። ይህ የከፋ በደልና ጥቃት ምን ሊመስል እንደሚችል ሁላችንም በቀላሉ ልንገምተው የምንችለው ነው። 
ይህ በመሆኑም እያንዳንዳችን ወደ ሕዝባዊ ኃይሉ ስንመጣ ይዘናቸው የመጣናቸውን ጎጂ ባህሎችና ባህርይዎች ያለምንም መወላወል መጋፈጥና ከሁላችንም ውስጥ አጥበን ማውጣት ይኖርብናል። 

     የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል እነዚህን አይነት ጎጂ ባህሎች እንታገል ሲል የመጀመሪያው ድርጅት አይደለም። በሀገራችን የፖለቲካ ድርጅቶች ከተፈጠሩ ጀምሮ እነዚህ ጎጂ ባህሎች በየፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ተነግሮ የማያልቅ ውድመት አስከትለዋል። እየዋለ እያደረ በበርካታ የሀገራችን የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ የእነዚህን ጎጂ ባህሎች አውዳሚነት እየታወቀ መጥቷል። ሆኖም ግን ተገቢውን ትኩረት በመስጠት እነዚህ ባህሎች በየድርጅቱ ውስጥ እንዳይሳፋፉና ሥር እንዳይሰዱ ማድረግ የቻለ ድርጅት እስካሁን የለም። በየመድረኩ የተለያዩ ድርጅቶች መሪዎች እነዚህን ጎጂ ባህሎችና ባህሪዎች እንታገላላን በማለት ቃል ቢገቡም እስካሁን ግን አንድም የተሳካለት ድርጅት አልተገኘም። ይህ ትግል ቀላል ስላልሆነ ብዙዎቹ ድርጅቶች በገዛ አባሎቻቸው የውስጥ ሽኩቻ፣ የርስበርስ መጠላለፍ፣ ሲወድሙ ሲሰነጣጠቁ ሥራ የማይሰሩ በድኖች ሆነው ሲቀሩ አይተናል። 

     ከ1966ቱ አብዮት ጋር ብቅ ካሉት ድርጅቶች ጀምረን ታሪካቸውን መቃኘት እንችላለን። ኢህአፓ፣ ኢዲዩ፣ መኢሶን፣ ኢሰፓ፣ ኦነግ ወዘተ በራሳቸው ድርጅትና ከሌሎች ድርጅቶችጋር የገቡበት ሽኩቻና መጠላለፍ ነው ያወደማቸው ወይም ከሞት አፋፍ ላይ ያስቀመጣቸው። የወያኔ አይነት ድርጅት ዘረኛነትን መሰባሰቢያ በማድረጉና የሰዎችን ግንኙነት በዘር ሙጫ ለማጣበቅ በመቻሉ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ሲወዳደር ብዙም የውስጥ መጠላለፍ አልታየበትም። በሌሎችም ላይ የበላይነት ያገኘው ዘረኛ በሆነ ዓላማ ዙሪያ የተሰባሰቡት ከፍተኛ መሪዎች ለዘር አጀንዳቸው ቅድሚያ ሰጥተው አንድ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ በማስቻሉ ነው። ይህም ሆኖም ወያኔም ቢሆን የድርጅት ውስጥ ሽኩቻና ሴራ መጠላለፍ ያልነበረበት ድርጅት አይደለም። አሁንም ቢሆን መጠላለፉ የሌለበት ድርጅት ነው ማለት አይደለም። በቅረቡ እየታየ ያለው የወያኔ መዳከም በተቃዋሚ ጥንካሬ የመጣ አይደለም። የድርጅቱ ውስጣዊ መበስበስ፣ የቡድኖችና የግለሰቦች የሥልጣን፣ የጥቅም፣ የከንቱ ክብርና ዝና ሸኩቻ ነው። 

    በወቅቱ በሚገኙት የተቃዋሚ ድርጅቶች ጎራ ያለውን ጉድ ሁላችንም እናውቀዋለን። ዛሬ ትብብር፣ ቅንጅትና ኅብረት ፈጥሮ ነገ መበታተን የተለመደ ነው። በየቀኑ ድርጅት መፈልፈል ነው። ዛሬ ተመሥርተው፣ በማግስቱ መሰነጣጠቅ መፍረስ እጣቸው የሆነው የሀገራችን ድርጅቶች ይህን መራራ ጽዋ በመጎንጨት ላይ ያሉት በወያኔ የስለላ ችሎታና ሌላም ክህሎት አይደለም። የየድርጅቶቹ መሪዎችና አባላት ደካማና ጎጂ የሆኑ ባህሎቻቸውንና ባህሪዎቻቸውን በደንብ መገንዘብና ማስወገድ ስላልቻሉ ነው። ሃገርና ወገን የመሳሰሉ እጅግ ክቡር የሆኑ ነገሮችን ከተራ የግል ስም፣ ክብር ጥቅምና ፍላጎት በታች አድርጎ ለማየት የማይፈልጉ አባላት ድርጅቶች በማቀፋቸው እነዚህ አሳፋሪና አሳዛኝ የመሰነጣጠቅ ችግሮች ሲከሰቱ አይተናል። እኛስ? እነዚህን ከየአንዳንዳችን ማንነት የሚፈልቁትን ጎጂ ባህሎች አስወግደን የጓዶቻችን የወገናችን የሕዝባችን ተስፋ መሆን እንችላለን? የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ትልቁ ፈተና ይህ ነው። 

     አናሳ ቁጥራችንን በሂደት ማብዛት እንችላለን። ወታደራዊ ሙያ የሌላቸውን ጓዶቻችንን ከፍተኛ ወታደራዊ ሥልጠና እንዲወስዱ ማድረግ እንችላለን። የታሪክ፣ የፖለቲካና የሥነ መራር እውቀት የሌላቸውን እውቀቱን በቀላሉ እንዲላበሱ ማድረግ እንችላለን። የቀለም ትምህርት ለሌላቸው እዚሁ በረሃ ውስጥ ከየትኛውም የሀገራችን ት/ቤት ወይም ኮሌጅ በላይ ጥራቱ የጠበቀ ትምህርት መስጠት እንችላለን። ይህን ሁሉ ማድረግ መቻላችን ግን ጎጂ ባህሎቻችን ከሚያስከትሉብን ውድቀት አያተርፉንም። ብዙ የወታደራዊ ሳይንስ እውቀት የነበራቸው፣ ወታደራዊ መሪዎች የያዘ መንግሥት አነስተኛ ወታደራዊ እውቀትና ልምድ ባላቸው ግለሰቦችና መሃይሞች በሚመራ ጦር ሲፈታ አይተናል። በተለያዩ የእውቀት ዘርፎች ሊቃውንት ሊባሉና እንዲሁም በእድሜና በተመክሮ በከበዱ ምሁራን የታጨቁ ድርጅቶች ወያኔን የመሰለ የሀገር ተምች አስቀምጠው እንደ ባለጌ ኮማሪት በአደባባይ ሲዘላላፉ፣ ሲዘራጠጡ፣ ራሳቸውን አዋርደው የኛ ናቸው ያላቸውን ሕዝብ ሲያዋርዱ አይተናል። 

    ለድርጅቶች መዳከም ወይም መውደም ምክንያቶቹ ክህደት፣ ጭቅጭቅ፣ መጠላለፍ የመሳሰሉት በሰዎች መሃከል መልካም ግንኙነት እንዳይኖር እንቅፋት የሆኑ ባህሪዎች ብቻ አይደሉም ። አድርባይነት፣ አጎብዳጅነት፣ ዝርክርክነት፣ ተጨንቆና ተጠቦ አለማቀድ፣ የግብር ይውጣ አሰራር ፣ጀብደኛነትና ወዘተ የመሳሰሉት ባህሎቻችን ለድርጅቶች መዳከም መውደም የራሳቸው አስተዋጸኦ አድርገዋል።እኛስ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አባላት እስካሁን በሀገራችን ውስጥ ከበቀሉት ድርጅቶች የተሻለ እጣና ታሪክ እንዲኖረን ምን ማድረግ አለብን? መልሱ በሌሎች ጥያቄዎችና ምለሾች የሚገኝ ነው።

    በቅድሚያ ራሳችንን መጠየቅ የሚገባን፣ ቀደም ብለን የጠቀስናቸውና ሌሎችም ጎጂ እና አፍራሽ ባህርያት በተለያየ ደረጃም ቢሆን በውስጣችን እንዳሉ እንገነዘባለን ወይ? ለዚህ ጥያቄ የሉም የሚል ምላሽ መስጠት አንችልም። ምንም ያህል ብጹእና የበቃን ብንሆንም ህጸጽና ድክመት አያጡንም። የሰው መሆን አንዱ ትርጉሙ የሚሳሳት የሚያጠፋ የሚል ነውና። እነዚህ ጎጂ የምንላቸው የግለሰቦች የቡድኖች ባህርያትና ልምዶች ምንድን ናቸው? እውን በደንብ እናውቃቸዋለን? ለምንድነው እነዚህ ባህርያት ልምዶች በማኅበራችንና በሀገራችን ውስጥ ከሌላው ማኅበረሰብና ሀገር ውስጥ ከሚታየው በላይ ሥር ሰደውና ደንድነው የሚገኙት? የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ከዚህ የባህልና የባህርይ ነቀርሳ ለማምለጥ ምን ማድረግ አለበት? ለመሆኑ እነዚህን ጎጂ የምንላቸውን ባህርያትና ልምዶች በደንብ እናውቃቸዋለን? 

3. የግለሰብ እና የቡድን ጎጂ ባህሎችና ባህርያት የምንላቸው የትኛዎቹ ናቸው? 

     የእነዚህ ባህሎችና ባህርያት ዝርዝር ብዙ ሊሆን ይችላል። በሁሉም ላይ ስምምነት ላይኖር ይችላል። ብዙዎቹ ተመሳሳይነት ተወራራሽነት ሊኖራቸው ይችላል። በአንድነት ሰብሰበን ብናቀርባቸው በመሃከላቸው ያለውን ረቂቅ ልዩነት ማየት ያስቸግረናል። አብዛናዎቹ ከግለሰብ ባህሪዎች ጋር የተሳሰሩ ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ ከድርጅቶች ጎጂ ባህርያት ጋር የተሳሰሩ ናቸው። የምንችለውን ያህል ዘርዝረን ማቅረቡ ይጠቅማል ብለን ስላሰብን እንደሚከተለው እናቀርባቸዋለን። 

1. ገደብ የሌለው ተጠራጣሪነት፤ 
2. ታማኝነት የሌለው ሆኖ መገኘት፤ 
3. ንቀት፤ 
4. ከሚገባው በላይ ለስም ለክብር መጨነቅ፤ 
5. ትእግስት ማጣት፣ ቱግ ባይነት፤ 
6. ተነጫናጭነት፤ 
7. ውሸታምነት፤ 
8. ሁሉን አውቃለሁ ባይነት፤ 
9. ኩርፊያ፤ 
10. ንትርክ፣ ጭቅጭቅ፣ እሰጣገባ፤ 
11. ስድብ፣ ጠብ፣ አምባጓሮ፤ 
12. እኔ ያልኩት የፈለግሁት ካልሆነ ባይነት፤ 
13. ተላታሚነት፣ በአካል ጓድን ለመጉዳት መሽቀዳደም፤ 
14. ብልግናና ጋጠወጥነት የተሞላውን ባህርይ ከደፋርነትና ከቆራጥነት ጋር ማምታት፤ 
15. ጥላቻ፤ 
16. ጉልበተኛ፣ አስፈራሪ ፣አዋካቢ ሆኖ መገኘት፤ 
17. የመንፈስ ጩቅነት፤ 
18. አዋራጅነት፣ ቅስም ሰባሪነት፤ 
19. ወሬኛነት፣ አሉባልተኛነት ፤ 
20. ሴረኛነት፣ ተንኮለኛነት፤ 
21. ከኔ በላይ ነፋስ አመለካከት፣ከጓዶቼ በፊት እኔ ብቻ፤ 
22. አድሎኛነት፣ አንድን ቡድን ወይም ግለሰብን ለይቶ ጥቃት ማድረስ ፣ በመንፈስ በአካል በጥቅም በመብት መጉዳት፤ 
23. ሁሌም መጥፎ መጥፎውን ማየት፣ ሊሆን የሚችለውን በጎ ነገር ትቶ ላይሆን የሚችለውን መጥፎ ነገር እስከማሰብ መሄድ፤ 
24. ራስን አሳንሶ ማየት፣ እኔ ትልልቅ ነገሮች ለማከናወን አልተፈጠርኩም፣ እሱ የሌሎች ስራ ነው ማለት፤ 
25. የግልና የድርጅት ንብረትን አለመንከባከብ፤ 
26. አንፋቃቂነት፤ 
27. ድጋፍና እርዳታ ለሚያስፈልገው ድጋፍን እርዳታን መከልከል፤ 
28. ትልቁን የጋራ የሆነውን ነገር ረስቶ የግል ጉልትን፣ ግቢን፣ ቤትን መከላከል። ይህ የግል ጉልት ስሜት፣ ፍላጎት፣ ዝንባሌን መከላከል ሊሆን ይችላል፤ 
29. የማይገባንን ዝና ክብር ስም መውሰድ፣ በጋራ ለተሰራ ወይም በሌላ ግለሰብ ለተሰራ ሥራ፣ ክንውን፣ ግኝት፣ ሃሳብና ወዘተ በመውሰድ ሊሆን ይችላል፤ 
30. የአንድን ሰው አቋም አጣሞ ማቅረብ። አንድ ሰው ሲናገር አለማዳመጥ። ሰውየው ተናግሮ ሲጨርስ ተራ ጠብቆ የራስን ከውይይቱ ጋር ተያያዥነት ይኑረው አይኑረው ንግግር ብቻ ለማድረግ መዘጋጀት። ሳያዳምጡ የተባለውን ጭብጥ ሳይዙ መልስ ለመስጠት መሞከር፤ 
31. መልእክቱን ሳይሆን መልእክተኛው መቀጥቀጥ ወይ በመልክተኛው ላይ መተኮስ። የአንድን ሰው አመለካከት ወይም ሃሳብ እንደመተቸት ሃሳቡ ያቀረበውን ሰው ከሃሳቡ ጋር ግንኙነት በሌለው መንገድ መቀጥቀጥ። አንድ ሃሳብ ከየትም ይምጣ ማንም ያምጣው ሃሳቡ ላይ ብቻ ትኩረት ሰጥቶ የሃሳቡን ዋጋ በሚገባ አለመመዘን፤ 
32. ሌሎች በሚገባ ያቀረቡትን ተደጋጋሚ ሃሳብ እንደ አዲስ ሃሳብ አድርጎ መልሶ ያንኑ ማቅረብ ፤ 
33. አቅምና ችሎታን እያወቁ በማይችሉት የኃላፊነት የሥራ ቦታ ዝም ብሎ መቀመጥ፤ 
34. የማይገባ ሹመት እድገት መፈለግ፤ 
35. ለጥራት ደንታ የሌለው መሆን፤ 
36. ለዝርዝር ጥቃቅን ለሆኑ ነገሮች በቂ ትኩረት አለመስጠት፤ 
37. የግል ችግርና ጉዳይ የሥራ ቅልጥፍናን የኃላፊነት ስሜትን እስኪያስረሳ ድረስ ልቅ መልቀቅ፤ 
38. የራስ ወይም የቡድን ስሜቶችን፣ አመለካከቶችን፣ እምነትን፣ ዘርን ወዘተ በተለየ መንገድ መመልከት ለሌላው ሰው ክብር፣ ትእግስት፣ የሌለ
ው የሚያጣጥል ሆኖ መገኘት፤ 
39. ሥርዓት ለማበጀት ፈጽሞ አለመፈለግ፣ በደንብ በሕግ በሥርዓት ለመሄድ አለመፍቀድ፤ 
40. ከሚገባው በላይ ለሥርዓትና ደንብ እንደባሪያ ተገዥ መሆን፤ 
41. ተነሳሽነት ማጣት፣ የጠባቂነት መንፈስ፤ 
42. የሚነገረውን እንጂ ቁምነገሩን አለማድመጥ፤ 
43. ሚስጥር መቋጠር አለመቻል፤ 
44. ሥራ ሰሪ መስሎ መታየት/ አስመሳይ ሰራተኛነት/፤ 
45. ለግል ጥሩ በሆነውና ለድርጅት ጥሩ በሆነው መሃል ውዥንብር ውስጥ መውደቅ፤ 
46. መጥፎ መጥፎ ወሬዎችንና ዜናዎችን ብቻ ማናፈስ፤ 
47. ግዜ በከንቱ ማባከን፤ 
48. ሁሌ ስህተት እየፈጸሙ እግዚአብሄርን ወይም ጓዶችን ምስክርነት መጥራት። ፈጣሪ ምስክሬ ነው። እገሌ ምስክሬ ነው ወዘተ፤ 
49. ለመጋፈጥ አለመፈለግ፣ ሰውን ሁኔታዎችን ሊሆን ይችላል፤ 
50. ተገቢ ያልሆነ ከሚያስፈልገው ደረጃ ያለፈ ለውጥ መፍራት፤ 
51. ከሚገባው በላይ ፍጹምነትና ትክክለኛነትን መፈለግ፣ ከሚገባው በላይ ስህተት ላላመስራት መጨነቅና በስጋት ታስሮ አለመስራት፤ 
52. በወቅቱ በተደረሰበት የብቃት፣ ችሎታ፣ የድልና የሥልጣን ደረጃ ከሚገባው በላይ ረክቶ በእብሪት መወጠር ፤ 
53. ከሚገባው በላይ መኩራራት መንጠባረር፤ 
54. አላስፈላጊ የሆነ ሁሉን ነገር የበላይ አካል እንዲወሥነው እንዲሰራው ማሰብና መተግበር፤ 
55. ሲሰሩ ከመታየት በስተቀር ሥራውን በሚገባ እንዲሰራ አስቦ አለመሥራት፤ 
56. አላስፈጊ የሆነ ጥድፊያ ላይ ማተኮር፤ 
57. ምሁራዊ ዘረፈ ብዙነት ማጣት፤ 
58. እኩል እድል ከመስጠት ፈንታ እኩል ውጤት ላይ ማተኮር። እያንዳንዱ በተሰጠው እድል ለሚያበረክተው ግልጋሎት እውቅና አለመስጠት፤ 
59. ከአቅም በላይ ቃል መግባትና በተግባር አንሶ መገኘት፣ በቃልና በተግባር መሃከል ሰፊ ልዩ ነት ማሳየት፣ ግብዝነት፤ 
60. ጉራ፤ 
61. ባህሪያቸው አስቸጋሪ የሆኑ ሰዎችን እሹሩሩ በማለት ድርጅቱና ሌሎች ስራ መስራት የሚፈልጉ አባላት ሥራቸውን እንዳይሰሩ፣ ሥነምግባር እንዲሸረሸረ፣ የስራ ባህል በድርጅት ውስጥ እንዲቦረቦር ማድረግ፤ 
62. ትንተና ማብዛት፣ በትንተና ሽባ ሆኖ ወደ ተግባር መግባት አለመቻል፤ 
63. ድርጅቱ ምን ይፈልጋል ሳይሆን በአድርባይነት እየተነዱ ሰው ሁሉ ምን ይፈልጋል በሚል በግብር ይውጣ ሥራን መሥራት፤ 
64. ጓዳዊ ግንኙነት የሌለው ወይም መፍጠር የማይችል ሆኖ መገኘት፣ ሲቀርቡት የሚርቅ፣ ሲያፈቅሩት የሚጠላ፣ ሲስሙት የሚናከስ፤ 
65. በድርጅቱ ውስጥ ቀድሞ ሲሰራበት ወይም ሌሎች ሲሰሩበት የነበረን የቆየ ሃሳብ በየግዜው እንደ አዲስ ማቅረብ፤ 
66. ከሚገባው በላይ ውጤት ተኮር ሆኖ መገኘት፣ ከውጤት ውጭ ለተገኙ መልካም ክንውኖች ቦታ አለመስጠት፣ ከውድቀት ለተገኙ ትምርቶች ቦታ አለመስጠት፤ 
67. ዝግ ሩቅ ሌሎች የማይደሩስበት የማያውቁት ድፍን ሰው ሆኖ መገኘት፤ 
68. ለሁሉም የሰዎች ድርጊቶች፣ ንግግሮችና ሃሳቦች ግለሰቦቹን ውስጣዊና ድብቅ ዓላማ እንዳላቸው ዝም ብሎ መጠርጠር፣ ድብቅ እምነትና አላቸው በሚል መላ መምታትና መጠንቆል፣ የራስን እምነትና ፍላጎት መለጠፍ፤ 
69. ሃብትንና መረጃን መደበቅ። ሃብት የሰው ኃይል ገንዘብ ቁሳቁስ እውቀት ሙያ ሊሆን ይችላል፤ 
70. ትርጉም የማይሰጥ መዋቅራዊ ድርጅታዊ ለውጥ ማድረግ ሁሉንም ሰው በአንድ አይነት መንገድ ማስተናገድ፣ አቅምን እድሜን ችሎታን የአይምሮ ና የአካል ብቃትን እምነትን ባህልን ግምት ውስጥ ያላስገባ ሁሉንም በአንድ አይነት መንገድ ስሱ ሳይሆኑ መመልከት ፤ 
71. የሰዎችን ችሎታና አቅም ግምት ውስጥ ያላስገባ ኮታ ለማሟላት ብቻ ሲባል ለሰዎች ኃላፊነት መስጠት፤ 


4. ሥር የሰደዱ የጎጂ ባህሪዎቻችን፣ ልምዶቻችንና ባህሎቻችን ምክንያቶች ምንድን ናቸው? 

   ይህን ጥያቄ እጅግ ግዙፍ ነው። ምክንያቱም የአንድ ሰው ባህርይ፣ልምድ ወይም ባህል የሚያንጹት ጉዳዮች ብዙ ናቸውና። ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የመጡ ልምዶችና ባህሎች ተጽእኖ ሊያደርጉበት ይችላሉ። ቤተሰቦቹ፣ ማኅበረሰቡ፣ መንግሥታዊ ና የትምህርት ሥርዓቱ፣ ሃይማኖቱ የአደገበትና የኖረበት አካባቢ ተፈጥሮ፣ የእድሜ እኩዮቹ ወዘተ ተጽእኖሊያደርጉበት ይችላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ግለሰቡ ለማንም ያልነገራቸው በውስጡ አምቆ የየያዛቸው የራሱ ልዩ የሆኑ የሕይወት ተመክሮች ተጽእኖ ሊያደርጉበት ይችላሉ። አንዳንዶቹ ተመክሮዎች በረጅም ግዜ ተደጋጋሚ ሂደት ተጽእኖ ማድረግ የሚችሉ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ግን የአንድ ግዜ ብቻ ገጠመኝ ሊሆኑ ይችላሉ። የረጅም ግዜ ሂደት ላልነው የሚከተለው ምሳሌ ሊገልጠው ይችላል። በህጻንነቱ እናቱ ሞታበት እጅግ ጨካኝ በሆነች እንጀራ እናት ለረጅም ግዜ አሰቃቂ በደል የደረሰበት ወይም በየምሽቱ እየሰከረ እየመጣ በሰበብ አስባቡ ቤተሰቡን የሚያሰቃይ አባት አሳድጎት ይሆናል። 

የደግነትና የርህሩነት ባህርይ ይዞ ያደገ ሰው በአንድ ወቅት በደረሰበት ከፍተኛ ጭካኔ የተሞላ ድርጊት የተነሳ ወደ እጅግ ጨካኝ ሰው ሊቀየር ይችላል። በአንድ ወቅት አንድ ነገር እጅግ በሚያስፈራ መንገድ ያስደነገጠው ህጻን የፈሪነት ባህርይ ተላብሶ ሊያድግ ይችላል። ሰው ውስብስብ ፍጥረት ስለሆነ ማንነቱን፣ ባህርያቱን የቀረጹት እነዚህ ነገሮች ናቸው ብሎ መናገር ቀላል አይደለም። 2+2 ይሆናል 4 እንደሚለው የሂሳብ ስሌት አንድን ሰው አጭበርባሪ፣ አድርባይ፣ ንፉግ፣ ጨካኝ ወይም ፈሪ የሆንከው በነዚህ ምክንያቶች ነው ብሎ እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም። አንድን ሰው ለሁላችንም የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ማለትም ያደግንባቸው ትምህርታዊ ሃይማኖታዊ መንግሥታዊ ሥርዓቶች፣ እንደሁላችንም ተጽእኖ አድርገው ማንነቱን ሊቀርጹት ይችላሉ። ከአንድ ወንዝ ስለተቀዳንማለትም ማኅበረሰባችን፣ መንግሥታዊ ሥርዓታችን፣ እምነታችን ታሪካችን አንድ ስለሆነ ወይም ስለሚቀራረብ፣ በብዙ ባህሪዎቻችን ልንመሳሰል እንችላለን። በሌላ በኩል ደግሞ እያንዳንዳችን እራሳችን የቻልን ፍጥረቶች ነን። የመመርመር የማሰላሰል ተፈጥሮዎች ስላሉን የጋራ ተመክሮዎቻችን የምንተረጉምበት የራሳችን መነጽር ይኖረናል። አንድ አይነት አስተዳደግ ካላቸው ሰዎች መሃል አንዱ ግፍ ሲበዛበት ያምጻል። ሌላው ግፍ ሲበዛበት የበለጠ አጎብድዶ ለመኖር ይወስናል፡፡ ለምን ለሚለው ጥያቄ በቀላሉ መልስ መስጠት አይቻልም። ሃቁ ግን ሁለት ሰዎች አንድ አይነት አስተዳደግ ስላላቸው ብቻ አንድ አይነት ሰዎች ሆነው እንደማ
ይወጡ ነው። 

   የጋራ ሆነ ወይም የግል ጎጂ ባህርያትና ባህሎች ምንጭ ጥናት ጥልቅ የሆነ የታሪክ፣ የሥነልቦናና የሥነ ማኅበረሰብ እውቀት የሚጠይቅ ነው።ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርበው ሃተታ ላነሳነው ግዙፍ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አይደለም። አይቻልምም። ሙከራችን እያንዳንዱ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል አባል የራሱን ባህሪዎች ሊፈትሽባቸው የሚችሉ ፍንጮችን፣ መኮርኮሪያዎችን ማቀበል ብቻ ነው። ጎጂ ባህርያትና ባህል በማለት የዘረዘርናቸውን ነጥቦች አንዳንዶቹን በተናጠል አንዳንዶቹን በቡድን እያደረግን የነዚህ ባህርይዎችና ባህሎች መነሻ ምንጭ ምን ሊሆን እንደሚችል የሚመስለንን መግለጫ እናቀርባለን። ቀደም ብለን እንዳልነው የሚቀርበው መግለጫ እንደ ተሟላ መልስ መታየት የለበትም። ውይይት መጫሪያና ራስን በሚገባ ለመፈተሻ ብቻ የቀረበ ተደርጎ መወሰድ ይኖርበታል። 


ገደብ የሌለው ተጠራጣሪነት 

    ገደብ የሌለው ተጠራጠሪነት ከሚለው ጎጂ ባህርይ እንጀምራለም። ማኅበረሰባችን እጅግ ተጠራጣሪ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የተጠራጣሪነት ባህል ረጅም እድሜ አለው። ይህ የተጠራጣሪነት ባህል በሁሉም የሀገራቱ ክልል በአንድ ግዜ በአንድ አይነት ጥልቀት የተስፋፋ አይደለም።እንደታሪካችን፣እንደማኅበራዊ አኗኗራችን፣ አስተዳደራዊ ሥርዓታችን፣ የሃይማኖት አስተምህሮታችን፣ ከአካባቢ አካባቢ፣ ከማኅበረሰብ ማኅበረሰብ ይለያይ ይሆናል። ደረጃ በደረጃ በየግዜው እየተስፋፋ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ባህርይ ሆኗል ማለት እንችላለን። እዚህ ላይ የምናተኩረው ብዙዎቻችንን የሚመለከቱ ጭብጦች ላይ ይሆናል። 

  ማለቂያ የሌለው ከውጭ ወራሪዎች ጋር የተካሄዱ በርካታ ጦርነቶችና እነዚህ ጋር ተያይዘው የመጡ እልቂቶች መፈናቀሎች ማንንም የውጭ ሃገር ሰው በተለይ አረብንና ነጭን እንዲሁም እምነቱ የተለየ የሚመስለንን ሰው እንድጠራጠር አድርጎናል። እንደ ሀገር እንደ ሕዝብ እንደ መንግሥት የውጭ የሆነን ነገር እንጠራጠራለን። ለኢትዮጵያ በጎ የሚመኝ መንግሥት ይኖራል ብለን አናስበም። የውጭ ፖሊሲዎቻችን ለረጅም ዘመን ከዚህ ጥርጣሬ ጋር ተያይዞ የተቀረጸ ነው። ሁሉም ሊያጠቃን እንደሚፈልግ አድርገን ነው የምናየው። ይህ ደግሞ በተወሰነ ደረጃ እውነትነት አለው። 

   ከውጭ ወረራ ቀጥሎ ማኅበረሰባችን ማለቂያ በሌላቸው የውስጥ ጦርነቶች፣ የርስ በርስ ግጭቶች ተጠምዶ እስካለንበት ዘመን ደርሷል። እነዚህ ጦርነቶችም ሞትን፣ መዘረፍን፣ መፈናቀልን መፈንገልን፣ መገፈፍን በስፋት በማኅበረሰባችን ውስጥ ያስከተሉ ናቸው። ግጭቱ እስከ አውራጃ ወረዳ ድረስ ይወርዳል። እንኳን በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንደር ደረጃ መተማማን የለም። የአንዱ ወረዳ ሕዝብ የሌላውን አያምን። ዛሬ ከአንዱ ንጉስ ጋር ወይም መስፍን ጋር የነበረው ነገ በሹመት በሃብት በጋብቻ ተደልሎ ባላንጣ ሆኖ የሚገዛውን ሕዝብ አስከትሎ ይዘምትብሃል። መገበር ማስገበር፣ መክዳት ተመልሶ መግባት፣ እንዲሁ እንደአዙሪት ሲያዞሩት የኖረ ማኅበረሰብ ስለሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ መጠራጠር የተለመደ ነው። ዘርን ጎሳን እምነትን ጠርቶ እነሱ አይታመኑም። እነሱን ማመን ቀብሮ ነው የሚል አባባል የተለመደ ነው። አንዱ ባንዱ ላይ ይለዋል። 

ለረጅም ግዜ የዘለቀው አስተዳደራዊ ሥርዓት ገበሬን በመዝረፍ በመቀማት ላይ የተመሠረተ ነበር። ዛሬም አልተቀየረም። መንግሥትንና የመንግሥት ባላስልጣናትን መጠርጠር የተለመደ ነው። መንግስትና ባለስልጣናቱ ለጥፋትና ለዘረፋ እንጅ ለበጎ ነገር አይፈልጉንም ብሎ ሕዝብ ያስባል። ጌቶች መጥተው ማር፣ ሙክት፣ አጃ፣ ጌሾ አምጣ ይላሉ። ወታደሩ መጥቶ ነጭ ኑግ፣ ጥቁር ወተት ውለድ ይላል። ሚስቱን “ ይች እህትህ እንዴት ታምራለቸ “ ቁንጅናዋን አድንቆ ከገዛ ባሏ ፊት ይደፍራታል። ደስ ሲለውም ይዟት ይሄዳል።የሰው ልጅም እንደከብት ይዘረፋል። 
ለጦርነት ወጣቶች ጎልማሶች ይዘረፋሉ። ታዲያ ወታደር መጣ የመንግሥት ተወካይ መጣ ሲባል ጥርጥሬ ይሰፍናል። ወታደሮችና ጌቶች ያለህን የእህል ብዛትና የደበቅበትን ቦታ እንዳያውቁ፣ ማርና ቅቤ የቀበርክበትን ጉርጓድ እንዳይደርሱበት ጎረቤትህም ማዋቅ ስለሌለበት ከጎረቤትህ ተደብቀህ ተጠንቅቀህ ትደብቃለህ። ጎረቤቴ አይቶኝ ይሆን አይሆን እያለክ ትጠራጠለህ። በአጋጣሚ የደበቅክውን ይደርስበት ይሆን በሚል ስጋት ጎረቤትህን ትጠረጥራለህ። 

የመሬት ስሪቱ እንዲሁ በወረራ የሚያዝ፣ በተወላጅነት የመካፈልና የማካፈል መብትና ግዴታ የነበረበት ነበር። በባእድ የመወረር ስጋት ብቻ አይደለም የነበረው ዝምድና አለኝ ያለን ሁሉ መሬት ማካፈልን የግድ ይላል። የመሬት ክርክር ሙግት ግጭት የተስፋፋ ነበር። መሬት ይገባኛል ባዩ ብዙ ነው። ባላንጣ ብዙ ነው። ዘመድ ቤተሰብ ሆኖ ይጋብዝሃል። ብላልኝ ጠጣልኝ ይልሃል። ለመሬት ሲል በምግቡና በመጠጡ ውስጥ መርዝ ጨምሮ ይገልሃል። ሽባ ያደርግሃል። ከፍተኛ የአካል ጉዳት ያደርስብሃል። ወገን አይታመንም። እንጀራ ቆርሶ ወጥ ጠቅሶ ካልቀመስ አንተ አትበላም። ያቀረበልህን ጠላ ወይም ጠጅ እጁ ላይ ፈሰስ አድርጎ ቀድሞ ካልቀመሰው አንተ አትጠጣም። በድንበር ገፋህኝ የሚቀሰቅሰው ጭቅጭቅ ወደ ስድብ አምቧጓሮ ይቀየራል። ተሰደብኩ ተመታሁ ያለው የበቀል እርምጃ ይወስዳል። ደም መቃባት ይመጣል። ዘር ማንዘር እየተቆጠረ መፋጀት ነው። የጥርጣሬን ጠቀሜታ ለመግለጽ 

ግደሉ ግደሉ ሰው መግደል ይበጃል 
ሰው ያልገደለ ሰው ሲሄድ ያንጎላጃል። ተብሎ ይዘፈናል። 

  ሰው ገድሎ በጥርጣሬ እንደሚዳቋ እየደነበሩ እንደ ቆቅ እየበረገጉ መኖር የሚጥም ሕይወት ሆኖ ስንኝ የተቋጠረለት ጉዳይ ሆኗል። ኅብረተሰቡ የደረሰበትን የሥነልቦና ቀውስ ከእነዚህ ስንኞች በላይ መግለጥ አይቻልም። 

   ይህ ባህል የመሬት ስሪት ሥርዓቱ ከጠፋም ከ50 አመት በኋላም በገጠር ብቻ አይደለም በከተማም ይሠራበታል። ቀመስ አርጎ ገበታ ማቅረብ ዛሬም ይሰራበታል። ሁሉም፣ አንዱ ሌላውን የሚጠረጠርበት አጠቃላይ ሁኔታ በሰፈነበት ማኅበራዊና መንግሥታዊ ሥርዓት ለሽህ አመታት ተኖረ። መንግሥት አይታመንም። የመንግሥት ባላሟል አይታመንም። ጎረቤት አይታመንም። ዘመድ ወገን አይታመንም። ያልጠረጠረ ተመነጠረ። ሰውን ማማን ቀብሮ ነው። ጠርጥር፣ ካደረ ገንፎ አይጠፋም ስንጥር፣ የሚሉ አባባሎችና ሌሎችም የመጠርጠር ትክክለኛነት በማኅበሩ አባላት ሥነ ልቦና ውስጥ ሲያስፋፉ ኑረዋል። 

   የመሳፍንቱ ዘመንና የመሳፍንቱ የርስ በርስ ግጭት ካባቃ በኋላም ኢትዮጵያ የውጭ ወረራ ያልተለያት ሀገር ናት። ይህ የእንግሊዞች፣ የቱርኮች፣ የግብጾች፣ የጣሊያኖች፣ የሱማሌዎች ወረራ፣ የቅርቡ የኢትዮ ኤርትራያ ጦርነት የቅርብና የሩቅ ሃገሮችን መጠርጠራችንን እንድንቀጥል ያደረገ ነው። ሁለተኛው የጣልያን ወረራ ኅብረተሰቡን በከሃዲ ወይም በባንዳና በአርበኛ ከፍሎ፣የዘርና የእምነት ልዩነቶች አራግቦ፣አለመተማመን ጥርጣሬን የበለጠ ቆስቁሶ ነው ያለፈው። 

  ወራሪዎችን በጀግንነት እንደመመከታችን ሁሉ፣ ነገስታት በንጉሶቻቸው በራሶቻቸው በፊትአውራሪዎቻቸው ሲከዱ አይተናል። የክህደቱ ደረጃ ይለያይ እንጅ ይጠቅመኛል ብሎ ካሰበ ትልቁም ትንሹም ለመክዳት አይመለስም። ቴዎድሮስ በዮሃንስ፣ ዮሃንስ በምኒሊክ፣ ምኒሊክ በመንገሻ ወዘተ። መአከላዊ መንግሥት ተጠናክሮ የመንግሥትና የሕዝብ ግንኙነት መልክ ይዟል በሚባልባቸው ዘመናት የመሬት ስሪቱ እንደ መሳፍንቱ ዘመን መቀጠሉ የሥርዓቱን የገዥዎችን ሥልጣን ጥቅም የሚያስከብረው የነጭ ለባሽ፣ የጆሮ ጠቢ፣ የስለላ መዋቅር መስፋፋቱ በሰዎች መሃከል አለመተማመኑ እንደነበረ ቀጥሏል። በቅርብ ግዜም ቢሆን ይህ የመከዳዳት ባህል በጦር ጄነራሎቹ በፖለቲካ ሰዎች አካባቢ እንደተፈጸመ ነው። የመንግስቱ ነዋይ፣ የደርግ ዘመንና የወያኔ ዘመን ጸረ መንግስት የሆኑ የአመጽ ሴራዎች የከሸፉት በመከዳዳት ነው። በቅንጅትና በህብረት ሰዎች ፣ በራሳቸው በቅንጅትና በህብረት ድርጅቶች ውስጥ የተከሰተው ችግር ከመከዳዳት ጋር ይያያዛል።  

     በማኅበረሰባችን ውስጥ ለአጭር ግዜም ቢሆን ከጥርጣሬ በተወሰነ ደረጃ ነፃ የሆነ የማኅበረስብ ክፍል መፍጠር ተጀምሮ የነበረው በተማረው የሰው ኃይል መሃል ነበር። የምሁሩና የተማሪው ክፍል ዘር ሳይለይ እርሱ በርሱ ሳይፈራራና ሳይጠራጠር በማኅበረሰባችን ታስቦ የማያውቅ ብዙ ሽህ ሰዎችን በሀገርና በውጭ ሀገር በጋራ አሰባስቦ መንግሥትና ሥርዓት ለመቀየር የሚያስችል ንቅናቄ መፍጠር ችሎ ነበር። ለዚህ ለውጥ መፈጠር ምሁሩና ተማሪው የገበየው ዘመናዊ እውቀት የራሱ ድርሻ ነበረው። የተማሪው ከወጣትነት የመጣ ንጽህና በጥቅም በሥልጣን ወዘተ ሊያጋጭ የሚችል ነገር በመሃሉ አለመኖሩ ሌላው ምክንያት ነበር። ትምህርት ቤት ተማሪዎች በብዛት መገናኘት የሚችሉበት ቦታ መሆኑ ጥርጣሬን በመቀነስ መቀራረብና መተዋወቅ በማሳደግ ሁሉም በጋራ መምከር የሚችሉበትን ሁኔታ በማመቻቸት የራሱ አስተዋጽኦ አድርጓል። ለ1966ቱ አብዮት መፈንዳት ሊጠቀሱ ከሚገባቸው ዋና ምክንያቶች መሃል ከጥርጣሬ በአንጻራዊነት ነፃ የሆነ ትውልድ መምጣት መቻሉ አንዱ ነው። ይህ እርሱ በርሱ የሚተማማን ትውልድ ግን የጀመረውን እንዳይጨርስ ያደረገው ራሱን ከግለሰቦች፣ ከቡድኖችና ከድርጅቶች የርስበርስ ጥርጣሬና መካካድ ነፃ ማድረግ ባላመቻሉ ነው። ጥርጣሬና መካካድ ብቻ አይደለም። ያ ትውልድ ተመልሶ እራሱ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሥር ከ
ሰደዱ ጎጂ ባህርያት ነጻ ባላመሆኑ እንኳን ሕዝብንና ሀገርን ሊታደግ፣ ነጻ ሊያወጣ እራሱን ከአጠቃላይ ውድመት ማትረፍ ሳይችል ቀርቷል። 

     አብዮቱ ንጉሱን በልቶ ለሽህ አመታት የጥርጣሬ ምንጭ የሆነው የመሬት ስሪት አጥፍቶ ሲያበቃ ይዞት የመጣው መህበረሰብ ይበልጥኑ ርስ በርሱ ተጠራጣሪ ሆነ። ደርግ በራሱ ውስጥና ከሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ተላተመ። ተቃዋሚዎችም ከደርግ ጋር፣ ርስበርሳቸውና በራሳቸው ውስጥ የከፈቱት የመበላላትና የእልቂት ጦርነት ተቀጣጠለ። ሁሉም ድርጅቶች ያሰማሯቸው ስውር ነፍሰ ገዳዮችና ሰላዮች ብዛት ሰው እንኳን ጓደኛውንና ጎረቤቱን የራሱን ጥላ ማመን ከማይችለበት ደረጃ አደረሰው። እናት አባት ባል ሚስት ወንድም እህት ልጆች እርስ በርሳቸው የማይተማመኑበትና እርስ በርስ የሚጠራጠሩበት የከፋ ሁኔታ እንዲመጣ አደረገ። ቀደም ባሉት ዘመናት ማኅበረሰባችን የፈለገውን ያህል በጥርጣሬ የተሞላ ቢሆንም እናትና አባት ልጆቻቸውን፣ ባል ሚስቱን አንዱ በሌላው ላይ የሚሰልሉ፣ በሌላ ባእድ አካል ተልከው ሊገድሉን ይችላሉ ብለው አስበውት አልመውት አያውቁም ነበር። አብዮቱ ግን ይህ ሁሉ ጉድ የመጣበት ዘመን ሆነ። 

   አብዮቱ በመሬት ስሪቱ ላይ ያመጣው ለውጥ ገበሬውን ከባላባቱ ጢሰኛነት ወደ መንግስት ጢሰኛነት ቀየረው እንጂ ከመሬት ስሪቱ ጋር የቆየውን ጥርጣሬ አላስወገደውም። መሬት የሚከፋፈፈለው በደርግና በወያኔ ካድሬዎች በመሆኑ ለእነዚህ ስርአቶች ታማኝ ሆኖ አለመገኘት መዘዙ በመሬት ክፍያው መበደል ወይም ፈጽሞ መሬት እስካላማግኘት ሊደርስ ቻለ። አንዱ ገበሬ በሌላው ገበሬ ላይ እንዲሰልል የሚያስችል የፖለቲካ አደረጃጀት ተበጀ። ዛሬም እንደትናንቱ መንግስት ካዝናው ሲጎድል፣ ተቀናቃኝና ጠላት ሲነሳበት አሁንም የሚዘረፈው የፈረደበትን ደሃ ገበሬ ልጆችና ጎተራ ነው። ወታደር መጣ ካድሬ መጣ ያው እንደጥንቱ የሚታዩት በጥርጣሬ ነው። የአንዱ የአብዮቱና የተከተሉት ዘመናት ቅርስ የማኅበረሰቡን አንድነት የበለጠ አናግቶ ጥርጣሬን በማኅበረሰቡ ውስጥ ጥልቀት እንዲኖረው ማድረግ ነው። 

   ወያኔ እጅግ አናሳ የሆነ የኅብረተሰብ ክፍል ተወካይ ሆኖ ያለምንም ተቃውሞ ሥልጣን ሊይዝና ሊጠናከር የቻለው በአብዮቱ ወቅትና ከዛም በኋላ ሰዎች በጋራ እጣቸው ላይ በጋራ ተማምነው እንዳይሰባሰቡና እንዳይመክሩ የደርግ ሥርዓት ያስፋፋው የጥርጣሬ ባህል ከዋና ዋና ምክንያቶቹ አንዱ ነው። ሁሉም በየቤቱ እህህህ ይላል። ያርራል። ይቃጠላል። አንዱ ከአንዱ ጋር ግን በድፍረት አይመክርም። በዚህ ሀገራዊና ማኅበረሰባዊ ሁኔታ ላይ የመጣው ወያኔ ኅብረተሰቡ የበለጠ በጥርጣሬ እንዲሞላ የበለጠ እንዲሰነጣጠቅ የዘርና የሃይማኖት ልዩነት ቤንዚን አርከፈከበት። እሳት ለኮሰበት :: የስለላ መዋቅሩን ከደርግ ግዜ በላይ አስፋፋው። የህዝቡ በድህነት መራቆት፣ በደርግ ዘመን በተካሄደበት የሽብርና የሰቆቃ ትውስታ የገባበትን መሰቀቅ በመጠቀም የወሬ አቀባዮንና አሳባቂውን ቁጥር በገንዘብ በመደለልና በማስፈራራት አሳደገው። የመንደር ሰላይ፣ የቀበሌ፣ የአንድ ለአምስት ቤተሰቦችና፣ የቤተሰብ ውስጥ ሰላይ ሳይቀር አደራጀበት። ከመቼውም ዘመን በከፋ መልኩ በወያኔ ዘመን ሀገርና ሕዝብ በሚሰቀጥጥ ደረጃ ተዋርዶ፣ ሃገርና ህዝብ ከመቼውም በላይ ተዘርፈው፣ ሕዝብ በድህነት ተቆራምዶ፣ የተስፋ ጭላንጭል አልታይ ያለው በገፍ በስደት ሲጋዝና ሲያልቅ በወያኔና ላይ ሰብሰብ ብሎ ጠንካራ ተቃውሞ ለማደራጀት ያልተቻለው የዘመናት የተጠራጣሪነት ማኅበረሰባዊ ባህላችን የደርግን ክፉ ዘመን አልፎ በወያኔ ዘመን ፋፍቶ መገኘቱ ነው። 

    በወያኔ ዘመን ወያኔን ለመቃወም የተነሱ ተቃዋሚዎችም ምን ሳይፈይዱ ውልቅልቃቸው የሚወጣው፣ በጃቸው የሚገኝ ወያኔን የማስወገድ መልካም አጋጣሚ የሚያልፋቸው ከጥርጣሬ መስፈን ጋር የተያያዘ ነው። በምርጫ 97 ወያኔ ተሸንፎ ሥልጣን እንደማይለቅ ግልጽ በሆነበት ወቅት ቅንጅት ሕጋዊ በሆነ መንገድ ሊፈታ የማይችልን ችግር በሕግ ለመፍታት ከመሯራጥ ይልቅ ሕዝብን የወያኔን ፈቃድ ለማያስፈልገው ተቃውሞ እንዲነሳ፣ ለዚህ ተቃውሞ የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን በሚስጥርና በህቡእ ማደራጀት ያልቻለው ሃሳቡን ሰዎች ሳያስቡት ቀርተው አልነበረም። እንዲህ አይነቱን ሃሳብ ማን ማንን አምኖ ለውይይት ያቀርበዋል ?። ማን እንደሚከዳ ማን ለወያኔ ወስዶ እቅዱን ሊናገር እንደሚይችል ባልታወቀበት ሰአት ማን ለማን ደፍሮ ይናገራል?። እንደታየውም ይህ ሃሳብ ቀርቦ ቢሆን ኖሮ ወያኔ በቅንጅት ውስጥ ባሰረጋቸው ሰዎቹ ወይንም ይህን መረጃ ለወያኔ በመስጠት ጥቅም እናገኛለን ብለው በሚያስቡ ሰዎች ወይም ሊከዱኝ ስለሚችሉ ቀድሜ ልክዳቸው በሚል ስሌት በሚያስቡ ሰዎች አማካይነት ለወያኔ ይደርሰው ነበር። ቅንጅቶች እርስበርሳቸው ተፈራርተውና ተጠራጥረው በከፍተኛ ደረጃ ድጋፉን የሰጣቸውን ሕዝብ ለመብቱ እንዲታገል በቂ ዝግጅትና በዚህ ዝግጅት ላይ የተመሠረተ ጥሪ ሳያደርጉ ቀሩ። እነሱም ተሰብሰበው ወህኒ ወረዱ። ደጋፊያቸውም ገሚሱ ውድ ህይወቱ አለፈች። የተቀረው ተጋዘ፣ ታሰረ፣ ተሰደደ። 

    ኅብረተሰባችን በጥርጣሬ አሲድ ተበልቶ እያለቀ ነው። የወያኔ አይነቶቹ አናሳ አፋኝና ዘረኛ ሥርዓቶች ደግሞ ዋንኛዎቹ የዚህ አሲድ አምራቾች  ናቸው። አናሳ ሃይሎች በሥልጣን መቆየት የሚችሉት ብዙሃኑን ከፋፍሎ በመግዛት ነው።አንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ማኅበራዊ ለውጥ፣ እድገትና የመብት ማስከበር ትግል መካሄድ የሚቻለው በተናጠል በሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች አማካይነት አይደለም። አንድ ግለሰብ በግሉ ለብቻው ሥርዓት ልታገል ማላት ይችላል። ነገር ግን ከሥርዓቱ ጋር ከመላተምና ከመታሰር ወይም ከመሞት ሌላ ሥርዓት ሊቀይር አይችልም። የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት የሚተማመኑ በርካታ ሰዎችን፣ ዜጎችን ማሰባሰብን ይጠይቃል። በሀገራችን የተዘራው የጥርጣሬ ባህል በዚህ ባህል የተበከለው የዜጎች ሥነልቦና ቀላል አይደለም።ጓዳዊ ግንኙነት የሌለው ወይም መፍጠር የማይችል ፣ ሲቀርቡት የሚርቅ፣ ሲያፈቅሩት የሚጠላ፣ ሲስሙት የሚናከስ፣ዝግ ሩቅ ሌሎች የማይደሩስበት የማያውቁት ድፍን ሰው ሆኖ መገኘት በማለት ባለፉት ገጾች የዘረዘርናቸው ጎጂ ባህርያት በአንድ ገጻቸው የተጠራጣሪት ውጤቶች ናቸው። 
ባምነው ሊሸጠኝ ይችላል። ባምነው ሊከዳኝ ይችላል። ባምነው መገልገያ መረማማጃ ሊያደርገኝ ይችላል። የሚፈልገኝ ለጥቅሙ እንጂ ለኔ ወይም ለጋራ ዓላማችን ብሎ አይደለም። ለማስመሰል ነው የሚናገረው፣ ውስጥ ውስጡን ከጠላት ጋር ይገናኛል። ወዘተ የሚሉ በማስረጃና በምክንያት ላይ ያልተመሠረቱ የጥርጣሬ ስሜቶች ተገዥ እስከሆንን ድረስ በጋራ ተሰባስበን የሁላችንንም መብትና ጥቅም ጠላት በሆነው ኃይል ላይ በጋራ ልንዘምትበት አንችልም። 

    ጥርጣሬ የሚወስደን ወደ በለጠ አዘቅት ነው። በጋራ የጋራ ችግራችንን መፍታት ሲያቅተን፣ በገዛ ሀገራችን በሶስተኛ የዜግነት ደረጃ ለሚያዩን የወያኔ ወራሪዎች ተላላኪ ሆነን ማደር እንጀምራለን። መልካም ባህርያችንና ሥነምግባራችን አራግፈን ለመኖር ስንል ወደ ሌብነትና ሥርቆት እንገባለን። የሌለ ጠላት፣ የሌላ ሴራ በዙሪያችን እያየን በአእምሮ በሽተኛነት ሊያስመድብ የሚያስችል በርጋጊዎች እንሆናለን። የስንት ጀግኖችና አርበኞች ልጆች ሆነን ሳለ ወያኔ ሀገር ሲሸጥ የድርሻችንን እንጠይቃለን። በስንት መከራ ቀደምቶቻችን ያተረፉልን ሀገር ለባንዳ ርዝራዦች ትተን ዘመዶቻችንን ጥለን መድረሻንን እንኳን በውል ወደማናውቀው ቦታ የዘመናዊ ባርነት ሕይወት ለመግፋት እንሰደዳለን። ተሰደንም በምንገኝበት ቦታም ገደብ የሌለው የተጠራጣሪነታችን ጎጂ ባህል አብሮን ተሰዷል። የአላማ ልዩነት በሌላቸው በርካታ ድርጅቶች ተከፋፍለን ዋናውን የኢትዮጵያን ህዝብ ጠላት ወያኔን ትተን እርስ በርስ ስንባላ እንኖራለን። ይህ ሁሉ ጣጣ መቆም የሚችለው ጥርጣሬን ከመሃከላችን አስወግደን ርስበርስ መተማመን በጋራ መምከር የጋራ ችግራችንን በጋራ መፍታት ስንችል ብቻ ነው። 

   ባሁኑ ግዜ በማህበረሰባችን ውስጥ ሰውን ማመን ክፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል። ክህደትና ሸፍጥን የሚያስቆመው የሞራል ልጓም ጠፍቷል። በእንዲህ አይነቱ አሳዛኝ ዘመንም ከአለንበት የስቃይና የውርድት ማጥ መውጣት የምንችለው ለመተማመን እድል ስንሰጥ ብቻ ነው። መተማመን ዋጋ ያስከፍላል ብለን ካሰብን እስቲ ያለመተማመን እስካሁን ካስከፈለንና ወደፊት ከሚያስከፍለው ዋጋ ጋር እናወዳድረው። ባላመተማመን የደረሰብን ጥፋት አይተነዋል። ወደፊት የሚያስከፍለን ዋጋ ካላፈው የባሰ እንጅ ያነሰ አይሆንም። ያለመተማመን ግለሰቦችን ብቻ አያጠፋም። ውሎ አድሮ ማኅበረሰብንና ሀገርን ያወድማል። ባለመተማመን የምንጠፋ ከሆነ ለመተማመን እድል ሰጥተን ብንጠፋ ይሻላል። ከተሞክሯችን ተነስተን ባለመተማመን የሚመጣውን የጋራ ውርደትና ሞት በርግጠኛነት መናገር ችለናል። በመተማመን ግን ውርደትንም ሞትን ማምለጥ የምንችልበትን እድል ይዞ ይመጣል። ካልተማመንም የትም ነቅነቅ ማለት እንደማንችል አጠቃላይ ውድመታችን የግዜ ጉዳይ ብቻ እንደሆነ ነፍሳችን ይነግረናል። መጥፋታችን የማይቀር መሆኑን ከተገነዘብን ለመተማመን እድል ሰጥተን እንሞክረው። 

    መተማመን መስዋዕትነት እንደሚያስከፍል እናውቃለን። በረሃብ በስደት በውርደት መስዋዕትነት እየከፈልን ከማለቅ ለመተማመን መስዋዕትነት መክፈሉና ውጤቱን በተስፋ መጠበቅ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን የሚያመላክት ዘመን ላይ ደርሰናል።በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በሚኖሩበት ሀገር፣ መታፈኔ፣ መብቴ መገፈፉ፣ ወገኔና ሃገሬ መዋረዳቸው አንጀቴ ድረስ ዘልቆ የሚሰማኝ እኔ ብቻ ነኝ ማለት እራሱ ግብዝነት ነው። 

    ሌላው ቢቀር አንድ ሌላ ሰው ይጠፋል ብለን እንዴት ማሰብ ያቅተናል? እኛ ምን አይነት ልዩ ፍጥረቶች ብንሆን እንደ እኔ የሀገር ውርደት የሚሰማው፣ መረገጡ የሚንገፈግፈው ሌላ ሰው የለም ከሚል መደምደሚያ ላይ የምንደርሰው። እንደኔ የሚያስብና የሚሰማው ሁለተኛ ሰው ከተገኘ ሶስተኛ ሰው የማይገኝበት ምን ምክንያት አለ። እንዲህ እየተባለ መሰባሰብ ይቻላል። የድርጅት መሠረት መጣል ይቻላል። ሶስት አራት እየተሆነ ማደግ ይቻላል። 

   የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አባላት ከዚህ በላይ የተባለውን በጥሞና ተገንዝበን ጥርጣሬ የትም እንደማያደርሰን አውቀን ከማኅበረሰባችን ከግል ህይወታችንና ተመክሯችን ይዘነው የመጣነውን የተጠራጣሪነት ባህል አውልቀን ከመጣል ውጭ አማራጭ የለንም። መንግሥትን እንዳናምን ተደርገናል። የፖለቲካ ድርጅቶችን እንዳናምን ተደርገናል። የማኅበረሰባችን አባላት እንዳናምን ተደርገናል። ከዛም አልፎ ጓደኞቻችንን እንዳናምን ተደርገነል። ነገር ግን እዚህ የተሰባሰብነው በተወሰነ ደረጃ ቢሆን አንዳችን አንዳችንን አምነን ነው። እንደ እኔ የከፋቸው ሊኖሩ ይችላሉ ብለን ነው። ይህ እምነት ግን በየግዜው በትንሹም በትልቁም አጋጣሚ ሊፈተን ይችላል። ያለመተማመን ባህልና ባህርይ በማኅበረሰባችን ሥር በመስደዱ የተነሳ ይህ ጎጂ ባህል በጋራ ለመሰዋት በተሰባሰብነው ሃይሎችም ውስጥ ሳይቀር በቀላሉ አይጠፋም። 

      ለጥርጣሬ እድል መስጠት የወያኔን እድሜ ማራዘም ነው ። በኛ አለመተማመን ተጠቃሚው ወያኔ ብቻ ነው። ወያኔን ለመታገል ያውም በወታደራዊ ኃይል ለመታገል የቆረጡ አባላት ጥርጣሬን ከውስጣቸው ሙሉ በሙሉ ካላስወገዱ መድረሻቸው አይደለም መነሻቸውም አያምርም። 

      አንድ ታጋይ ወደ ኋላ የገዛ ጓዱን በጥርጣሬ እያየ እንዴት አድርጎ ወያኔን ለማጥቃት ጥይት እየዘነበበት ወደፊት መጓዝ ይችላል። አይችልም። ገደብ የሌለው ጥርጣሬ ሲጠፋ ሌሎች ከጥርጣሬ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ወይም ጥርጣሬን ተገን አድርገው የፋፉ መጥፎ ባህሪዎቻችን አብረው ይጠፋሉ። በኅብረተሰባችን ውስጥ የጠፋው የመተሳሰብ፣ የመዋደድ፣ የአንተን ክፉ አያሳየኝ፣ እኔ ካንተ ልቅደም ባህሎች መፋፋት ይጀምራሉ። የሚዋደዱ ሰዎች በትንሽ በትልቁ አይጣሉም። ጭቅጭቅ ንትርክ አይኖርም። ሴራ ማሴር ሸር መጠንሰስ ያበቃለታል። የሚተሳሰቡ ጓዶች በጥሞና ለመደማመጥ ይችላሉ። የተሻለውን ሃሳብ የጋራቸው አድርገው ተስማምተው ይሰራሉ። መጯጯህ ያበቃለታል። ያላቸውን ተካፍለው ይበላሉ ይጠጣሉ። ሁሉም የየግሉን በማሰብ የሚታዩ የስግብግብነት ባህርዮች ይጠፋሉ። አቅምና ጤና የሌለውን ይደግፋሉ። አንዱ ባንዱ ላይ አያሳብቅም። አንዱ ለሃለፊነት ቢታጭ ሌላው መጥፎ ቅናት ውስጥ አይወድቅም። የጥርጣሬ መወገድ እጅግ በርካታ የሆኑ በጋራ የሚሰሩ ሥራዎችን እንዳይሳኩ ሊያደርግ የሚችሉ ጎጂ ባህርይዎችን አስወግዶ ለበርካታ በጎ ባህርያት ማበብ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል። 

     ቀደም ብለን ከዘረዘርናቸው 72 ጎጂ ባህርይዎች መሃል ጥርጣሬ አንደኛ የሆነው ያለምን ምክንያት አይደለም። አሁን በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ መተማመን ማስፋት መጠራጠርን ማስወገድ የሀገራችን የማኅበረሰባችን ህልውና የማስከበር ወይም ያለማስከበር ያህል ክብደት የሚሰጠው ጉዳይ ስለሆነ ነው። 

    አንድ መጥፎ ባህርይ ማጥፋት የሚከፍታቸው መልካም እድሎች ብዙ ናቸው ብለናል። መጠርጠር አቆምን ማላት ልባችን አእምሯችን ለጓዳችን ክፍት አደረግን፣ አጸዳን ማለት ነው። በንጹህ ልብ ውስጥ ጥላቻ ቅናት ምቀኛነት፣ ጠብ ጫሪነት፣ ያዙን ልቀቁኝ ባይነት አይኖሩም። የሚበቅለውና የሚያብበው ፍቅር ነው። የማፍቀር አቅምና ጉልበት ያለው ሰው በውስጡ የሚሰማውን ፍስሃና ምሉእነት ማፍቀር የቻሉ ብቻ ናቸው የሚናገሩት። “ገሃነም ምን ይመስላል” ለሚለው ጥያቄ ማን ነበር “ለማፍቀር የማይችልን ልብ ይመስላል” ብሎ የመለሰው? በፍቅር ሰንሰለት የተሳሰሩን ጓዶች ምንም ምድራዊ ኃይል ሊለያያቸው አይችልም። ደስታቸውም ልባዊና የጋራ ሃዘናቸውም የጋራና ጥልቅ ይሆናል። ፍቅር የአንድነት መሠረቱ ነው። ፍቅር በሚፈጥረው አንድነት በጋራ ለምናከናውነው ሥራና ለምንደርስበት የውጤት ደረጃ ገደብ አይኖረውም። 

ከዚህ ቀጥሎ ሌሎችን ቀደም ብለን የዘረዘርናቸውን ጎጅ ባህርያት፣ ልምዶችና ባህሎች የሚያመነጩ ምክንያቶችን እንይ። 

     ከሚገባው በላይ ለስም ለክብር የመጨነቅ ከሚገባው በላይ ለስም ለክብር የመጨነቅ ባህርይ ብንወስድ ይህ ባህርይ ከውጭ ስለሚታየው ማንነቱ ከሚገባው በላይ የሚጨነቅ ሰው በሽታ ነው። የራሱ ማንነት መመዘኛ በራሱ ውስጥ ራሱ የሚሰማው ስሜት ሳይሆን ሌሎች ስለሱ ይሰማቸዋል ብሎ ከሚያስበው ግምት የሚነሳ ነው። ንጽህና አለኝ ወይ ሳይሆን ንጹህ መስዬ በሌሎች እታያለሁ ወይ? እውቀት አለኝ ወይ ሳይሆን በሌሎች አይን አዋቂ መስዬ እታያለሁ ወይ? ሃብት አለኝ ወይ ሳይሆን በሌሎች አይን ሃብታም መስዬ እታያለሁ ወይ? እነዚህ ናቸው ከሚገባው በላይ ለክብሩ ለስሙ የሚጨነቅን ሰው ሕይወት የሚገዙት። የነተበና የበከተ የውስጥ ሱሪ ለብሶ በጣም ውድ ካቦርታ ደርቦ መሄድ፣ እውቀቱ ሳይኖር ዲግሪውን ገዝቶ መያዝ፣ አቅምንና ችሎታን ግምት ውስጥ ያላስገባ ግብዣ ድግስ ማድረግ፣ ሰው ስላደረገው ብቻ የማያስፈልጉ ነገሮችን ማድረግ፣ የመሳሰሉት ልምዶችና ባህሎች በስፋት ከተስፋፉበት ሀገር በመብቀላችን የሚመጣ ችግር ነው። ይህ ችግር በራስ ካለመተማመን ከውስጣዊ ባዶነት ወይም ቀፎነት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ችግር ነው። አንድ ትልቅ ቦክሰኛ አንዲት ህጻን ልጅ ጋር በሆነ ጉዳይ ተጣልቶ ህጻኑ ለቡጢ ሲጋባዝ ቢያየው ንቆ እንዲያውም ስቆ ይሄዳል። ምክንያቱም በአቅሙ በችሎታው ይተማመናልና። አንድ አዋቂ በአንድ ያልተማረ ሰው አታውቅም ብሎ ቢነገረው ዝም ብሎ ሰምቶ ይሄዳል እንጂ እንዴት ደንቆሮ አልከኝ ብሎ ለመደባደብ አይነሳም። ወይም አዋቂ መሆኑን ለማሳየት እቤቱ ሄዶ የጻፋቸውን ትልልቅ መጸሃፍት በማምጣት አዋቂነቱን አያረጋግጥም ። 

     በጎጂ ባህሎች ዝርዝር ውስጥ ያካተትናቸው ከማስመሰል ጋር የተያያዙ ጎጂ ባህርያት እዚህ ሊጠቀሱ ይችላሉ። ሥራ ሰሪ መስሎ መታየት አስመሳይ ሰራተኛነት፣ሲሰሩ ከመታየት በስተቀር ሥራውን በሚገባ እንዲሰራ አስቦ አለመሥራት፣ከአቅም በላይ ቃል መግባትና በተግባር አንሶ መገኘት፣ ጉራና ሌሎችም በሙሉ ጥልቀት ያለው የግል ስብእና ለመገንባት ከመሞከር ይልቅ ሌሎችን በማጭበርበር የመኖር ጎጂ ልምድ የተጠናወተው ሰው ችግሮች ናቸው። 

    ለስማቸውና ለክብራቸው ከሚገባው በላይ የሚጨነቁ ሰዎች ከኅብረተሰቡ ከወረሱት ተብለጭላጭነት ላይ ካተኮረ ባህል በላይም በራስ መተማመን የሌላቸው ሰዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች ትእግስት አይኖራቸውም። ስማቸውንና ክብራቸውን በማይሰነጥር በጣም አነስተኛ ጉዳይ ሳይቀር ትእግስት ያጣሉ። ቱግ ይላሉ። ያኮርፋሉ። ይጣላሉ። ተላታሚዎችና ተጋጮች ይሆናሉ። ትእግስት ማጣት ቱግ ባይነት ተነጫናጭነት ኩርፊያ የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖራቸውም በዋንኛነት በራስ አለመተማን ጋር የተያያዙ ናቸው። የራሱንና የማኅበረሰቡን ታሪክ በሚገባ የማያውቅ ዜጋ፣ የትምህርት ጥራቱ በወደቀ ትምህርት የተሰጠው በእውቀቱናና በሙያው የማይተማመን ዜጋ፣ የወደፊት ህይወቱ ምን ሊሆን እንደሚችል በድፍረት መናገር የማይችል ዜጋ ፣ ሁልግዜ በመኖርና ባላመኖር ጠርዝ ላይ ነርቩ ተወጥሮ የሚኖር ዜጋ በራስ መተማማን ሊኖረው አይችልም። እንዲህ አይነቱ ዜጋ በሆነ ባልሆነው ከሚወዳቸው ከሚያቀርባቸው ሰዎች ጋር ሳይቀር ወደ ጠብ ግጭት ለመግባት ግዜ አይፈጅበትም።ስድብ ይቀናዋል። አምባጓሮ ያሥነሳል። አንድ ግለሰብ እንዲህ አይነት ባህርይ ይዞ የጤነኛ ማኅበረሰብና ድርጅት አባል መሆን አይችልም። በጋር አቅዶ በጋር ያቀደውን ከግብ ማድረስ አይችልም። ሌሎችን ጎጅ ባህርያት ቀጥለን እንመልከት። 

    ለራሳችን ያለን ጥላቻ እንዴት ሌሎች እንድንጠላ እንደሚያደርገን የከረረ ጥላቻን፣ አንድን ሰው በአካሉም ይሁን በመንፈሱ ክፉኛ እንዲጎዳ መፈለግ፣ ጉልበተኛ አሰፈራሪ አዋካቢ ሆኖ መገኘት፣ ቀናነት የጎደለው መሆን የመሳሰሉት ጎጂ ባህርያት፣ እንደሌሎቹ ሁሉ ባህርያት ከማኅበረሰባችን የምንወርሳቸው፣ ከአስተዳደጋችን ጋር፣ ከመንግሥታዊ ሥርዓቱ ጋር የተያያዙ ናቸው። መንግሥት ይገድላል፣ ያሥራል፣ ይገርፋል ሰቆቃ ይፈጽማል። አስተማሪም ተማሪውን ይቀጠቅጣል፣ ወላጅ ልጆቹን፣ ባል ሚስቱን፣ ትላቅ ታናሹን፣ የመንደርና የትምህርት ቤት ጉልቤ አቅም የሌላቸውን ይማታል። ያዋክባል። አህያው ከነሸክሙ በዱላ ይነረታል። 
በሬው ከነቀንበሩ ይገረፋል። ውሻው በድንጋይ ይወገራል። ለከት ገደብ ምክንያት የሌለው ጉልበተኛነት ስድ አመጽ (violence) ቀንም ማታም ይከተለናል። በአጠቃላይ ለሌሎች የአካልና የመንፈስ ስቃይ በሁሉም መልኩ ደንታ ከሌለው፣ ደካሞች ሁሌም የጥቃት ሰለባ ሆነው ከሚኖሩበት ማኅበረሰብ ወጥተን የተለየን ፍጥረቶች እንሆናለን ማለት አይቻልም። እኛም በተራችን እድል ስናገኝ፣ ጉልበትና አቅሙና ስልጣኑ አለን ብለን በምናስብበት ወቅት ወደ የለየት አዋካቢ አምባገነን፣ ገራፊ ወዘተ መቀየራችን አይቀርም። የሥነ አእምሮ ሳይንስ የሚያሳየው መረጃ ይህንኑ ነው። በሌሎች ላይ የአካልን የመንፈስ ሰቆቃ የሚፈጽሙ ጎልማሶችና አዛውንቶች ራሳቸው ባንድ ወቅት የአካልና የመንፈስ ጥቃት ሰለባ የነበሩ እንደሆነ ይህ ሳይንስ ይነግረናል። ይህ አይነት ባህርይ እርስ በርስ ሲያናክሰን ሲያፋጀን ከመኖር ሌላ የሚፈይደው ነገር አይኖርም። 

    በደንብ ካሰብንበትና በውል ከመረመርነው፣ በተለይ ተቀራርበው ለመሥራት ለመታገል በተሰባሰቡ ወይም በሚቀራረቡ ጓደኛሞች መሃከል የሚታይ የጥላቻ የቂም፣ የመጎዳዳት መንፈስ ለምንጣላው ሰው ካለን ጥላቻ በላይ ለራሳችን ካለን ጥላቻ የሚመነጭ ነው። የወያኔ የጥቃት ሰለባ የሆነ፣ እንደኛው የተገፋ የተዋረደ ሰው ስናይ በዚህ ሰው ላይ የደረሰበት በደል ከኛ ጋር ተመሳሳይነት ስላለው የበለጠ ሊያቀራርበን በተገባ ነበር። የሚሆነው ግን ይህ አይደለም። ከእንዲህ አይነት ሰው ጋር ከመቀራረብ ይልቅ ማንነቱን በደንብ ካላወቅነው ሰው ጋር መቀራረብ ይቀለናል። መቀራረቡ ጥልቀት ባይኖረውም ከእውነተኛ ግንኙነት ይልቅ በማስመሰል የተሞላን ግንኙነት እንመርጣለን። ይህን እንግዳ ሰው የምናውቀው በርቀት ስለሆነና ብዙም ስለእኛ የሚያውቀው ነገር ስለሌለ ከዚህ ሰው ጋር ብዙ አንቃቃርም። የሚያቃቅር ነገር ከተነሳም ብዙ አቧራ ሳናሥነሳ መለየያት ይቻላል። 

   እንደኛው የተጠቃ የተዋረደ የተገፋ የጋራ ሰለባ እጣችን ተመሳሳይ ከሆነ ሰው ጋር የምንፈጥረው ግንኙነት ፈተና የበዛው ነው። በቀላሉ እንጋጫለን፣ እናመራለን። ካለተገዳደልን እንላለን። ለምን? እኔ በወያኔ ተገርፌ፣ በወያኔ የተገረፈ ሰው ከፊቴ ሳይ፣ ሰውየውን እንደሌላ በራሱ ስቃይ እንደደረሰበት ሰው ሳይሆን የኔን ውርደት የሚያሳይ መስተዋት አድርጌ ነው የማየው። ከፊቴ የቆመው ሰው በኔ ላይ የደረሰ ውርደትና ሰቃይ ሰቆቃ ደርሶበት ከሆነ፣ በህይወቱ ያለማቸው ነገሮች እንደኔው ያልተሳኩለት ሰው ከሆነ፣ ከፊቴ በቆመ ቁጥር የኔ ውርደት፣ ስቃይ፣ በውድቀትና በሃፍረት የተጠናቀቁ የሕይወት ሙከራዎቼ መስተዋት አድርጌ ነው የማየው። ከፊቴ ቆሞ የውርደትና የስቃይ ታሪኬን መልሶ የሚያንጸባርቅልኝን መስተዋት መስበር ወይም ከፊቴ ማግለል እንጂ፣ መወልወል መንከባከን እንደማይታየኝ ሁሉ ከፊቴ የቆመውንም እኔን የመሰለ ሰው ሳላውቅ በከፍተኛ የጥላቻ አይን እንዳየው ያደርገኛል። በዚህ ወዳጄ ላይ ከሌላ የበለጠ የምጨክነው ለራሴ ካላኝ ጥላቻ እንጅ ከፊቴ ለቆመው ጓደኛዬ ካለኝ ጥላቻ ተነስቼ አይደለም። ለራሳችን ጥላቻ ካለን ሌላውን መውደድ የማይታሰብ ነው። ከራሳችን ጋር በቅድሚያ ሳንታረቅ ከሌሎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት ሰላም አይኖረንም። 
ሴረኛነት ተንኮለኛነት በብልግና እና በጋጠወጥነት የተሞላ ድርጊት፣ በራሳችን ውስጥ ካለ ሥነ አእምሮዋዊ ቀውስ ጋር የተያያዙ የባህርይ ችግሮች ናቸው። ቤተሰባችን አስተማሪዎቻችን የምንቀርባቸው ጓደኞቻችን የፖለቲካና የሃይማኖት መሪዎቻችን በቃልም በድርጊት የሚሉትና የሚፈጽሙ እኛንም የእነዚህ ጎጂ ባህርያት ተለባሾች አድርገውን ይሆናል። ጎጂ መሆናቸውን እስካወቅን ድረሰ ሁሌም ለነዚህ ባህርያት ተጠቂ ያደረጉን አካላት ሰበብ እያደረግን እኛም ሴረኛ ተንኮለኛ ባለጌና ጋጠወጥ ሆነን መቀጠል አንችልም። ችግሮች እንደሆኑ ተረድተን ልናቸንፋቸው ይገባል። ሰው እስከሆንን ድረስ ችግር ማቸነፍ አንዱ የማንነታችን መገለጫ መሆኑን መርሳት የለብንም። በአንድ ድርጅት ውስጥ አባላት በሴራና በተንኮለኛነት የተሞሉ ከሆነ ምን ሊከተል እንደሚችል መገመት ቀላል ነው። 

        የመንፈስ ጩቅነት፤ሁሌም መጥፎ መጥፎውን ማየት፤ ሊሆን የሚችለውን በጎ ነገር ትቶ ላይሆን የሚችለውን መጥፎ ነገር እስከማሰብ መሄድ፤ ድጋፍና እርዳታ ለሚያስፈልገው ድጋፍን እርዳታን መከልከል፤ አድሎኛነት፣ አንድን ቡድን ወይም ግለሰብን ለይቶ ጥቃት ማድረስ ጦርነት መክፈት፤ የአንድን ሰው አቋም አጣሞ ማቅረብ፤ አንድ ሰው ሲናገር አለማዳመጥ፤ ሰውየው ተናግሮ ሲጨርስ ተራ ጠብቆ የራስን ከውይይቱ ጋር ተያያዥነት ይኑረው አይኑረው ንግግር ብቻ ለማድረግ መዘጋጀት፤ ሳያዳምጡ የተባለውን ጭብጥ ሳይዙ መልስ ለመስጠት መሞከር፤ መልእክቱን ሳይሆን መልእክተኛው መቀጥቀጥ ፤ የአንድን ሰው አመለካከት ወይም ሃሳብ እንደመተቸት ሃሳቡ ያቀረበውን ሰው ከሃሳቡ ጋር ግንኙነት በሌለው መንገድ መቀጥቀጥ፤ ሃሳቡ የሌላ ሰው ቢሆንም ሃሳቡ ከየትም ይምጣ ሃሳቡ ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሃሳቡን ዋጋ በሚገባ አለመመዘን፤ መጥፎ መጥፎ ወሬዎችንና ዜናዎችን ብቻ ማናፈስ ጎጂ ባህርያትና ልምዶች ናቸው። ለምን ደግ ደጉን አያስብም? ጓደኛ ስህተት ቢሰራም ሳያውቀው ሳይረዳው ቀርቶ ነው እንጂ ሆን ብሎ አይደለም፣ የአገላለጽ ችግር ወይ ስህተት እንጂ ለማለት የፈለገው ሰው ለመጉዳት ወይም ለማስቀየም ብ
ሎ አይደለም፣ አቀራረቡ እንጂ ቁም ነገሩ እኔ ካልኩት ልዩነት የለውም፣ የተናገረው ስህተት ያለው ነገር ቢሆንም ስህተቱ ካቀረበው ትልቅ ቁም ነገር ጋር ሲወዳደር ኢምንት ስለሆነ ሃሳቡን ልቀበለው ይገባል በሚል መንፈስ ለምን አንቀርበውም? በማኅበረሰባችን ውስጥ በየትኛውም መልኩ በፖለቲካም ሆነ በሌላ ድርጅት በጋራ ተሰባስበን በምንሰራበት ወቅት ብዙ ከዚህ በላይ ያልናቸው ችግሮች በስፋት ይከሰታሉ። እነዚህና ሌሎችም ተመሳሳይነት ያላቸው ጎጂ ባህርያት ቀናነት በከፍተኛነት የጎደለው ሰው ባህርያት ናቸው። 

       ለምንድነው አንዳንዱ ሰው ቀና ባህርይ የሌለው? 

      የአሰተዳደግ፣ የትምህርት፣ የአሰተዳደር፣ የአኗኗር ሁኔታችን ከመረመርን ከላይ ለተቀመጠው ጥያቄ መልስ ለማግኘት አይቸግረንም። ቀናነት ማጣት በራስ ካላመተማን ችግር ጋር ሊያያዝ ይችላል። ከአቅም ማጣት ችግር ጋር ሊያያዝ ይችላል ። እውነቱን እንነጋገር ከተባለ የሚበላ፣ የሚጠጣ፣ የሚለበስ፣ ሰው ቢታመም ህክምና ፣ ቢበደል ፍትህ ሊያገኝባቸው የምችልባቸው ሁኔታዎች ባልተሟሉበት፣ ከረሃብ ከርዛት ከበሽታ ከበደልና ከጦርነት ጋር ተፋጦ ለዘመናት የኖረ፣ በእጦት፣ ሰቀቀንና በእብሪተኞች ለዘመናት የተቀጣ ማኅበረሰብ በመንፈሱ ደግ፣ ቀና፣ ዘና ያለ ዜጋ ባይፈጥር ሊገርመን አይገባም። በኢኮኖሚ በልጽገው ብዙ ነገሮች በተትረፈሩባቸው ማኅበረሰቦች እነዚህ ከመንፈስ ጩቅነት ጋር የተያዙ ጎጂ ባህርያት በከፍተኛ ደረጃ ቀንሰው ይታያሉ። መሬት ላይ ያለ የኑሮ ሰቀቀን የመንፈስ ጩቅነት ሊያስከትል ይችላል። ርህራሄ ደግነት እንዳይኖር የሚያደርግ ጨካኝ ማኅበረሰባዊ አስተዳደራዊና ከባባዊ ሁኔታ ሥነ አእምሯችንንም በዛው መልክ የመቅረጽ እድሉ ትልቅ ነው። ለምን ክፉ ክፉን 
እናያለን ለሚለው ጥያቄያችን ህይወታታችን የክፉ ነገሮች ቅጥልጥሎሽ ስለሆነ እንዴት ደግ ደጉን ማየት እንችላለን የሚል መልስ ቢመጣ መቃወም አስቸጋሪ ነው። የህይወታችን ሎጂክ የሚያሳየው ይህንኑ ነውና። ቁምነገሩ እያንዳንዳችን በአንድ ውይም በሌላ ምክንያት የእነዚህ ጎጂ ባህሎችና ባህርያት ሰለባ ሆነናል። ባህሎቹ ጎጂ መሆናቸውን ላይ ስምምነት እስካለ ሁላችንም በምንጫቸው ላይ አንድ አይነት ስምምነት ላይ መድረስ የለብንም። 

    ማኅበረሰባችን በከፍተኛ ደረጃ የተጎዱ፣ ጎደሎ ዜጎች የሚያመርት የሰው ኢንዱስትሪ መሆኑን ካወቅን፣ ጎዶሏችንን ሞልተን ጉድለታችንን አስተካከለን የበቃን ሰዎች ሆኖ መገኘት የየአንዳንዳችን የግል ኃላፊነት ነው። ይህን ኃላፊነት መልሰን ለኅብረተሰቡ መስጠት አንችልም:: ምክንያቱም መጀመሪያውኑ እንዲህ ያደረገን ማህበረሰቡ ነውና። ይህን ኃላፊነት ለሌሎች ጓዶቻችን መስጠት አንችልም። ምክንያቱም እነሱም እንደኛ የተበላሸው የሰው ኢንዱስትሪ ውጤቶች ናቸውና። ኅብረሰተስብ ልንቀይር ከተሰባሰብን ከኅብረተሰባችን ከወረስናቸው ጎጂ ባህርያት፣ልምድና ባህሎች በላይ ገነን መቆም ይኖርብናል። ያለበለዚያማ ምኑን የነፃነት ታጋዮች ሆንን ? የነፃነት ታጋይ የሆንነው በቅድሚያ በውስጣችን የበቀለውንና ያደገውን አሜከላ ህፀጽና እኩይ ሥነልቦናዊ መርዝ ከውስጣችን ጠርገን ኅብረተሰባችን እናድናለን ብለን ነው። እኛ ነፃ ሳንወጣ ነፃ የማውጣት የሞራል መብቱም አቅሙም አይኖረንም። እየአንዳንዳችን ይህን ማድረግ ከቻልን ድርጅታችን የእያንዳንዳችን ጥንካሬ ወደ እኛ ጥንካሬ ቀይሮ ሀገርና ማኅበረሰብ ለመቀየር፣ የሰነቀውን ህልም ለማሳካት አይቸግረውም። 

   በጣም በሚደንቅ መልኩ ሌሎችም በዚህ ሠነድ የተካተቱ ጎጂ የማይመስሉ ግን በአንድ ድርጅት ውድቀት ወይም ልማት ላይ ወሳኝነት ያላቸው ባህርያትና ልምዶች እስካሁን ስናያቸው ከመጣነው ጎጂ ባህርያት በቀጥታና በተዘዋዋሪ ከቆዩ ጎጂ ልምዶች ባህሎች አስተዳደግ ትምህርት ወዘተ ጋር የተያዙ ናቸው። የተለያዩ ምሳሌዎች እንውሰድ። 

ለጥራት (quality, excellence)ትኩረት አለመስጠት - 

     እራሳችን በደንብ ከመረመርን ማኅበረሰባችን ለጥራት ቦታ አይሰጥም። አንድ ነገር ለመሥራት ለምሳሌ ቤት ይሁን ቁሳቁስ፣ እውቀቱም የመስሪያ እቃውም እያለን ጥራት ያለው ነገር ለመሥራት ሙከራ አናደርግም። በምሁራዊ የሥራ ውጤቶችም፣ ጥራት ያላቸው የምሁራዊ የሥራ ውጤቶች ምን መመሰል እንደሚገባቸው እያወቅንም ብዙዎቻችን ለምሁራዊ ሥራዎቻችን ጥራት አንጨነቅም። የተሟላ መረጃ አለማሰባሰብ፣ ለእውነት ሳይሆን ለስሜት መገዛት፣ በይዘቱም ሆነ በቅርጹ የተሟላለት ጽሁፍ እንዲሆን አለመሞከር፣ ተራ የአርትኦት እርማት ሳይቀር በደንብ ማድረግ አለመቻል፣ በይድረስ ይድረስ በይለቅ ይለቅ ተቻኩሉ ቶሎ ለመገላገል በሚፈልግ ስሜት መጓዝ የተለመደ ነው። በኪነት ሥራዎቻችን ላይም ተመሳሳይ ነገር ይታያል። ግዜ ወስዶ በትእግስት ተሞልቶ መቀመጫ መጅ እስከሚያወጣ፣ ጀርባ እስኪጎብጥም ድረስ ቁጭ ብሎም ቆሞም መስዋእተነት ከፍሎ የተሻለ ጥራቱን የጠበቅ ሥራ ማውጣት ለባህላችን ባእድ ነው። እንዳውም ለዚህ ቃል አለን። ሥራችን ሁሉ የግብር ይውጣ አይነት ነው። እራሱ የግብር ይውጣ ቃሉ የግብር እዳ ከመክፈል ጋር የተያያዘ ነው። ለጌቶች ወይም ለመንግሥት በግብር መልኩ የሚከፈልን ነ
ገር እንደነገሩ ከፍሎ መገላገል ማለት ይመስላል። ስናጸዳ በደንብ አናጸዳም። ስንገነባ በደንብ አንገነባም። ስናመርት በደንብ አናመርትም። አንድ ዓላማ ይዘን ስንነሳ በደንብ አልመን አንነሳም። ስናቅድ በደንብ አንዘጋጅም። የሶስት ሽህ አመት እድሜ ባለው ጎጆ ዛሬም የምንኖረው፣ የሶስት ሽህ አመት እድሜ ባለው ማረሻ የምናርሰው፣ የሶስትሽ አመት እድሜ ያለው የነተበ ሸማ የምንለብሰው፣ የሶስት ሽህ አመት እድሜ ባለው አምባገነናዊ መንግሥታዊ ሥርዓት የምንተዳደረው፣ በሁሉም ረገድ በመንፈሳዊ በአካላዊ ህይወታችን ባላንበት የምንረግጥ እከሚመስል ደርቀን የቆምነው ከጥራት ጋር የተጣላን በመሆኑ ነው። በእንዲህ አይነት ማኅበረሰብ ውስጥ በራስ ተነሳሽነት ሥራ መሥራት የሚባል ነገር አይታሰብም። ሁሉም ጠባቂ ነው። ሌላው እንዲያጸዳው፣ እንዲሸከመው፣ እንዲገነባው፣እንዲሰበስበው፣ እንዲጽፈው እንዲያመርተው መጠበቅ ነው። 

     ለክብርና ለመብት የሚደረገውንም ትግል ሌላው እንዲታገለው እንዲሞተው መጠበቅ ነው። እስኪ ያቅሜን ልሞክር የለም። መጠበቅ! መጠበቅ! 

     ማኅበረሰባችን የማይቀየረው ወግ አጥባቂ ስለሆነ ነው ይባላል። እኛም ብንሆን ዝም ብሎ ለውጥ ለለውጥ ብቻ ይደረግ አንልም። ለውጥ ማንነታችንን ወጋችንን ባህላችን ታሪካችንን ጠብቆ የሚደረግ መሆን እንዳለበት እናምናለን። በዚህ ረገድ የሚታይ ወግ አጥባቂነት አዎንታዊ ነው። 

     ነገር ግን ወግ አጥባቂነትና ለመቀየር አለመፈለግና በጅ ያለን የራስን ነገር በጥራት አለመሥራት ሁለቱ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። በማኅበረሰባችን የሚታየው ችግር ከወግ አጥባቂነት ጋር የተያያዘ አይደለም። የኛ ወግ አጥባቂነት በተለይ በተማረው ክፍል ውስጥ የሚታየው የግድየለሽነት የስንፍና ውጤት እንጅ የማንቀይረው ነገር ጥሩ መሆኑን በሚገባ መርምረንና ተቀብለን አይመስልም። አንድ ነገር ከቀደምቶቻችን በዛሬው መልኩ ስለወረሥነው መቀየሩ የእኔ ኃላፊነት አይደለም ከሚል የሚገርም ስሜት ነው፣ የሳር ጎጆውም ማረሻውም እድሜያቸው የረዘመው። የኃላፊነት ስሜት ማጣት፣ የመንፈስና የአካል ድቀት፣ ለጥራት ለውበት ከዛም አልፎ ትእግስትን ለሚፈታተኑ ጥቃቅን ነገሮች ትኩረት ሰጥቶ ላለመሥራታችን ምክንያቶች ናቸው። 

   ለእንዲህ አይነቶቹ ዝንባሌዎቻችን ምክንያቶቹ ምንድን ናቸው?ጦርነት፣ የገነቡትን የማውደም፣ የመቀማት፣ የማፈናቀል እዳ ይዞ ይመጣል። የማያልቅ የጦርነት ታሪካችን ነገ ለሚፈርስ ለሚወድም ነገር ምን አታከተህ የሚል መልእክት ከትውልድ ትውልድ ሲያስተላልፍልን እንደቆየ ግልጽ ነው። አስተዳደራዊ ሥርዓቱም ያለህ ከመሰለው የሚቀማ መሆኑ ቤትህን ማሰማመር ፣ በረትህን ማስፋፋት፣ አጥርህን ጠበቅ፣ የማር ቀፎህን ማብዛት የዘራፊ አይን መሳብ ነው። የቤተ ክህነቱም ስብከት ተጽእኖው ቀላል አይደለም። የምድሩን ነገር ተወው እሱ አላፊ ነው ይላል። ከደከማችሁም ለነፍሳችሁ ነው ይላል። ቆንጆ ህንጻዎች አልባሳት ቁሳቁሶች የሚገኙት በየቤተክርስቲያኑና ገዳሙ ነው።ማኅበረሰባችን ውስጥ የማይታየው ብርሃን፣ ውበትና ጥራት ያለው ቤተክርስትያን ውስጥ ነው። እሱም ቢሆን በአንጻራዊነት ነው:: የሕዝብ ቀለም በቤቱም በልብሱ በመልኩ አንድ ቀለም ነው። ግራጫ፣ አፈር፣ አቧራ የመሰለ። 

    በግል ህይወታችንና ተመክሯችንም የግብር ይወጣ ሥራ እንድንሰራ ስንፍና እንዲጫነን ያደረጉ ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ደክሞ ጥሮ ግሮ በችሎታ ሳይሆን በዘመድ አዝማድ፣ በዘር፣ በፖለቲካ አሽከርነትና በታማኝነት፣ ሃብት፣ ሥልጣንና ማኅበራዊ ከበሬታ የሚገኝበት ማኅበራዊ ሁኔታ ውስጥ ተኑሮ ለጥራት መድከም የማይታሰብ ነው። ጥረትና ጥራት ተያዥነት ያላቸው ቃላት ናቸው። ጥረት የሚያመጣው ትርፍ ከሌለ ጥራት ከየት ይመጣል። ለጥረት ትኩረት እንዳንሰጥ ያደረጉ ጎጂ ባህሎቻችን ምክንያቶቻቸው ምንም ይሁን ምንም ቁምነገሩ በዚህ ለጥራት ትኩረት በማይሰጥ መንፈስ የታሰሩ ግለሰቦች ተሰባስበው እንኳን ሀገር መቀየር ቀርቶ እርባና ያለው ድርጅት ማቆም እንደማይችሉ ማወቁ ነው። 

   ስለጥራት ከላይ የተባለው ሁሉ ለጥቃቅን ነገሮች ትኩረት እንዳንሰጥ ለሚያደርገን ጎጅ ባህላችን መግለጫ ሊሆን ይችላል። ማንኛውም ተግባር ትልቅ ይሁን ትንሽ በሚገባ አቅደን አንሰራም። ብዙ ነገሮች ለግምት ለመላምት ለእድል እንተዋለን። መረጃ ባይኖረንምም ለግዜ ትልቅ ትርጉም በሚሰጥባቸው የምእራብ ሃገሮች ውስጥ ከሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበረሰቦች ውስጥ ለማንኛውም ቀጠሮ አርፍደን የምንደርስ፣ ዘግይተን ከቤት በመውጣት፣ ፓስፖርት በመርሳት ባቡር አይሮፕላን የሚያመልጠን እኛኢትዮጵያውያን ሳንሆን አንቀርም። የተዋጣለት የምንለውን ዝግጅት፣ በአል ይሁን ስብሰባ ሳይቀር በብዙ እንከኖች የተሞላ እንደሆነ እናውቃለን። አስቀድሞ በቀላሉ ሊታዩ የሚችሉ ቀላል ችግሮችን ለማየት ፈቃደኛ ባላመሆናችን እርባና የሌለው ተግባር ሳይቀር ግዜውን ጠብቆ በሰአቱ አይከናወንም።በተያዘለት በጀት አይከናወንም። በተመኘነው የጥራት ደረጃ አይከናወንም። ሥራችን ሁሉ ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ አይነት ነው። አንድ ነገር ለመተግበር ምን አይነት ቁሳቁስ ፣ ሙያ፣ ክህሎት፣ ገንዘብ፣ ግዜ የሰው ኃይል ያስፈልጋል? እነዚህ የሚያስፈልጉት ነገሮች በጃችን አሉ ወይ? የጎደሉት እንዴትና መቼ እናሟላለን? ሥራውን መቼ ጀምረን መቼ እንጨርሰዋለን? ሥራው በተያዘለት በጀት በቀረበለት ግብአት በተፈለገው ጥራት፣ በተቀመጠለት የግዜ ገደብ እየተሰራ እንደሆነና በመጨረሻው የሥራውን ስኬት ወይም ውድቀት መለኪያ ሳናስቀምጥ ሥራ እንሥራ ብለን እንነሳለን። ብዙ ግዜ ጉልበትና ሃብት ባክኖ የተሰራ
ው ሥራ ምን እንደሆነ እስከማይታወቅበት ደረጃ የሚደርስ ብክነት ይከሰታል። አንማርም። ደግመን ደጋግመን እንሰራዋለን። 

ለግዜ በከንቱ መባከን ደንታ ማጣት 

      ሰለ ግዜ ያለን አመለካከት ሌላው ጎጂ ባህላችን ነው። ማለቂያ የሌለው ሥራ ከፊታችን ተቀምጦ ግዜን ማባከን በኛ ማኅበረሰብ የተለመደ ነው። የግዜ ግንዛቤያችን እየተሽከረከረ በቀለበት መልኩ መልሶ መልሶ የሚመጣ እንጂ እንደጦር ላይመለስ ወደፊት የሚነጉድ አይደለም። እያንዳንዱ ደቂቃ ያለምንም ጠቀሜታ ሲያልፍ በሌሎች ማኅበረሰቦች ውስጥ የምናየውን ቅሬታ በኛ ማኅበረሰብ አናይም። በሚገባ ያልሰራንበት፣ ያልተዝናናንበት፣ ያልተማርንበት ሂሳብ አወራርዱ ቢባል የት እንዳጠፋናቸው ለመናገር የሚቸግሩን ደቂቃቃዎች፣ ሰአቶች፣ ቀኖች፣ ሳምንቶች፣ ወራቶችና አመታቶች አሉን። እንዴት ነው አንድ ማኅበረሰብ በአሥር ደቂቃ የሚያልቅን ጉዳይ 10 ሰአት ሲወስድ ሲያይ ጸጉሩን የማይነጨው? እንዴት ነው አንድ ግለሰብ በቀትር ዛፍ ሥር ቆማ ፍዝዝ ብላ እንደምታማነዥግ ላም ፍዝዝ ብሎ ማዶ ማዶ ሲያይ ወይም ቁጭ ብሎ ሲቆዝም በጀርባው ተንጋሎ ጣራ ሲመለከት ቀናት ሲያልፉ ዝም ብሎ የሚያይ? ጫት እያመነዠጉ ሲሻ እየመገመጉ የወጣትነት እድሜያቸው ሲነጉድ በምርቃናና በሰመመን የሚታዘቡ ወጣቶች፣ ማህበረሰብና መንግስት መፍጠር ችለናል። 

     እያንዳንዷ ደቂቃ ወደሞታችን የምትወስደን ናት። ሞት በአንድ ግዜ የሚከሰት ነገር አይደለም። እኛ በአግባቡ ሆነ ያለ አግባብ የምንገላቸው ደቂቃዎች ውጤት ነው። ለእያንዳንዱ ደቂቃ በከንቱ መባከን ደንታ ማጣት ፋይዳ የሌለውን ሞት ለመሞት ከመመኘት ልዩነቱ ምንድነው? ነገሩ ራስን በራስ ማጥፋት ሆኖ ግን ዘገምተኛ ራስን በራስ ማጥፋት መሆኑ ነው። ከሚገባ በላይ በመቀመጥ በመተኛት፣ ያለፈን ታሪክና ወሬ ደግሞ ደጋግሞ በማመንዠክ የምናባክነውን ግዜ ግላዊና ማኅበራዊ የሆኑትን ከሰው ልጅ ክበብ ያወጡን ችግሮቻችንን ለመፍታት እውቀት ሙያ አቅም ለምን አንሸምትባቸውም የሚል ጥያቄ አይነሳም ። ሥራን ከምሮ ምን አይነት የህሊና መቆርቆር ሳይሰማው ግዜው በወሬና በማንቀላፋት አጥፎቶ “ለምን አልሰራህም” ሲባል፣ መልስ ደግሞ ደጋግሞ የሚያጣ ሰው ለምንድነው ትንሽም የማያፍረው። የመንግሥት ኃላፊውም ነገ ተመለሱ ይላል። ነጋዴውም ነገ አደርሳለሁ ይላል። በማግስቱ ግን የሚደርስ ነገር የለም። በተመሳሳይም ሕዝብ ነፃ ለማውጣት እንታገላለን የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶችም ከሌላ ድርጅት ለቀረበላቸው መልስ በ24 ሰአት ውስጥ እነሰጣለን ይላሉ ለሳምንትም አይደርስም። ሠነድ ለማዘጋጀት 2 ቀን ይሰጠኝ ይላል በ2 ወር ሳይጨርሰው ይመጣል። ዝርዝሩ ብዙ ነው። ማኅበረሰባችንን ለኋላ ቀርነት የዳረጉት ከግዜ አጠቃቀም ጋር የተያዙ ጎጂ ልምዶች መሆናችቸውን የሚያውቅ ነፃ አውጭ ግዜን በተመለከተ ከማኅበረሰቡ የላቀ ቀልጣፋ የግዜ አጠቃቀም ሊኖረው ይገባል። እያንዳንዷ በግል ይሁን በጋራ የምናባክናት ደቂቃ የወያኔን እድሜ የምታራዝም የኛን እድሜ የምታሳጥር ናት። የወያኔን እድሜ ለማሳጠር የተነሳ ግለሰብና ቡድን ለሚባክን ግዜ መንገብገብ ይገባዋል። 

    እስቲ ከዚህ በታች ያሉትን ተቀራራቢነት ያላቸውን በርካታ ጎጂ ባህርያትና ልምዶች እንመልከት። - ከራስ በላይ ነፋስ፣ የጋራ ንብረትንና አካባቢን እንደራስ ጉዳይ አለመንከባከብ፣ ትልቁን የጋራ የሆነውን ነገር ረስቶ አነስተኛ የግል ስሜትና ፍላጎትን መከላከል፣የማይገባንን ዝና ክብር ስም መውሰድ፣ በጋራ ለተሰራ ወይም በሌላ ግለሰብ የተሰራን ሥራ የግል አድርጎ ማቅረብ፣አቅምና ችሎታን እያወቁ በማይችሉት የኃላፊነት የሥራ ቦታ ዝም ብሎ መቀመጥ፣ የማይገባ ሹመት እድገት መፈለግ፣ የግል ችግር የሥራ ቅልጥፍናን የኃላፊነት ስሜትን እስኪያስረሳ ድረስ ልቅ መልቀቅ፣ የራስ ወይም ለቡድን ስሜቶች አመለካከቶች እምነቶች ዘር ወዘተ በተለየ መንገድ መመልከት ለሌላው ሰው አመለካከት፣ እምነት፣ ዘር ከበሬታና ትግስት የሌለውና የሚያጣጥል፣ ሥርዓት ለማበጀት ፈጽሞ አለመፈለግ፣ በደንብ በሕግ በሥርዓት ለመሄድ አለመፍቀድ፣ በስምምነት ያወጡትን ደንብ ሥርዓት መጣስ፣ሃብትንና መረጃን መደበቅ (ሃብት የሰው ኃይል ገንዘብ ቁሳቁስ እውቀት ሙያ ሊሆን ይችላል)፣ መስማት እንጅ አለማድመጥ፣ መናገር እንጅ አለማድመጥ፣ - እነዚህ ባህርያት ሥር ከሰደደ ግለኛነት፣ ራስን መውደድ፣ የቅርቡን እንጂ የሩቁን ለማየት የሚያስችል ሰብአዊ አቅም ማጣትና ለሌሎች ሰዎች በጎ አመለካካት ካለመኖር ጋር የተያያዙ ናቸው። ብዙዎቹ ሌላውን ሰው ከመጠርጠር፣ ራሴን ቀና በሆነ መንገድ ከከፈትኩ እጎዳለሁ፣ ሁሉም ሊያጠቃኝ ስለሚፈልግ እኔም በተጠንቀቅ መቆም ማጥቃት አለብኝ ከሚል ሥር የሰደደ ማኅበራዊና ሥነልቦናው ችግር ጋር የተያያዘ ነው።ሁሉም እድል ቢያገኝ፣ ቢመቸው ሥርዓትና ደንብ ይጥሳል፣ ይዘረፋል፣ ይረግጣል ከሚል ለሰው ልጆች ባጠቃላይ በተለይ ደግሞ ለድርጅት አባላት የምንሰጠውን እጅግ የወረደ ደረጃ ያሳያል። ከሌሎች ጋር በስሜትም በሃሳብም ሆነ በተግባር ሊያያዝ የሚችልን ነገር ከመፍራት የሚመነጭ ነው። መቀራራብ ወደ መዋደድ መከባበር መፋቀር ይወስዳል። የኛን ድርጊት ስናጤነው ፍቅር የሚያሸብረን ያስመስልብናል። 

   ጥላቻን ዋናው መግለጫው ካደረገ ማኅበራዊና አስተዳደራዊ እውነታ ውስጥ ተቁሞ እንዴት አንድ ሰው ሌላው ሰው የሚለውን ያዳምጣል። ሃብትና መረጃ ያካፍላል:: ከተቻለ ከሌሎች መውሰድ እንጂ መስጠት ማካፈል የማይታሰብ ነው። ብልጥነት ባሁኑ ቋንቋ አራዳነት በተቻለ መጠን ከጋራ ሥራና ኃላፊነት መሸሽ፣ በጋራ ሥራ ለሚሰሩ ሥራዎች ቢቻል ምንም አለመሥራት፣ ካልተቻለ አነስተኛ የሥራ ድርሻ መውሰድ ማለት ነው። ብልጥ ሰው በጋራ መሥራት የሚቻልባቸውን መንገዶች ያፈላልጋል። እሱ ለሌሎች ከሚሰጠው ሥራ በላይ ይሸከማል። ይህ አድርጎ የተሰራው ሥራ በግሉ ከሚሰራው ሥራ የላቀ ሆኖ ካገኘው በደስታ ይሞላል። ሌሎች ተጠቅመው ራሱን በመጥቀሙ ይረካል። የግለኛነት ጎጂ ባህርያት የተላበሰ ሰው ግን የጋራ ጥረት ጥቅም ይኑረው አይኑረው በቅድሚያ ከልቡ አይሳተፍበትም። ከተሳተፈም በሌሎች ኪሳራ እርሱ ከፍተኛ ጥቅም ካላገኘበት አይሆንም። የአንድ ድርጅት አባላት በሙሉ አንዱ በአንዱ አባል ስም፣ ድካምና ኪሳራ የራሳቸውን ትርፍ እያሰሉ የሚንቀሳቀሱ ከሆነ ድርጅት የላቸውም ማላት ይቻላል። ሰአት ቆጥሮ የሚፈነዳ ቦምብ በመሃከላቸው ቀብረዋል ማለት ነው። ይህ ቦምብ ደግሞ ግዜውን ጠብቆ ሁሉንም ማውደሙ አይቀርም። 


አድርባይነት 

ሌላው በርካታ ጎጂ ባህራያቶቻችን ሊገልጽ የሚችል ጽንሰ ሃሳብ አድርባይነት ነው። ብዙ ግዜ ሰዎች አድርባይነት ለአለቃ፣ ለባለሥልጣን፣ ለጓደኛ ማጎብደድ አድርገው ያዩታል። በዚህ ጽሁፍ አድርባይነት ሰፊ ትርጉም አለው። አድርባይነት ለሰው ብቻ ሳይሆን ለሁኔታዎች ማደርን ጭምር ይመለከታል። ድርጅቱ ምን ይፈልጋል ሳይሆን ግለሰሰቡ ምን ይፈልጋል በሚል ሥራን አለመሥራት ሊሆን ይችላል። ሰውን ሁኔታዎችን ለመጋፈጥ አለመፈለግ ሊሆን ይችላል። ተገቢ ያልሆነና ከሚያስፈልገው ደረጃ ያለፈ ለውጥ መፍራት ሌላው መገለጫው ነው። ባህሪያቸው አስቸጋሪ የሆኑ ሰዎችን እሹሩሩ በማለት በድርጅት ውስጥ ሌሎች ሥራቸውን እንዳይሰሩ ማድረግ፣ የሥራ ባህል የሥነምግባር ባህል በድርጅት ውስጥ እንዲቦረቦር ማድረግ፣ አላስፈላጊ የሆነ ሁሉን ነገር የበላይ አካል እንዲወሥነው እንዲሰራው ማሰብና መተግበር፣ ትንተና ማብዛትን በትንተና ሽባ ሆኖ ወደ ተግባር መግባት አለመቻል፣ ከሚገባው በላይ ለሥርዓትና ደንብ እንደባሪያ ተገዥ መሆንና የመሳሰሉት ሌሎች ጎጂ ባህርያት የአድርባይነት መገለጫዎችና ውጤቶች ናቸው። በጥቅሉ መፈታተንን፣ መግደርደርን መለወጥንና መቀየርን መፍራት በራስ ተነሳሽነት ሥራን አለመሥራት፣ ኃላፊነትን አሳልፎ መስጠት የመሳሰሉት ችግሮቻችን ከአድርባይነት ጋር ማያያዝ ይቻላል። አድርባይነት ለጥቅም ብቻ የሚደረግ ማጎብደድ አይደለም። ሰው ተራ በሆነ መንገድ ክብሩን ስሙን ለማስጠበቅ አድርባይ ይሆናል። የባለጌን ስድብ ፈርቶ የሚያውቀውን አይናገርም። ሥራን ድካም ውጣ ውረድን ፈርቶ ሰው አድርባይ ይሆናል። ኑሮን ሕይወትን ማኅበረሰብን ድርጅትን አካካባቢን ማሻሻል እየቻለ በነበሩበት በተበላሹበት መንገድ እንዲቀጥሉ ማድረግ ለሁኔታዎች ማደር ነው። “የመጣውን እወጣዋለሁ ይህን ጎጆ አፍርሼ በተሻለ መንገድ እገነባዋለሁ፣ ይህን ድርጅት አስተካክለዋለሁ ይህን ሃገር እቀይረዋለሁ” ብሎ ደፍሮ አለመነሳት ለሁኔታዎች ማደርን ነው የሚያሳየው። በማኅበረሰባችን ውስጥ አድርባይነትን ሥር እንዲሰድ ያደረጉ ምክንያቶች ቀደም ብለን ለሌች ጎጂ ባህርዮቻችን ካቀረብናቸው ምክንያቶች የተለዩ አይደሉም። ግዜን በክብ መልኩ እየዞረ የሚመጣ፣ ነገሮች እራሳቸውን ከኛ ቁጥጥር ውጭ የሚደግሙ፣ ሁሉ ነገር አስቀድሞ የተጻፈ የተደነገገ በኛ ጥረት የሚቀየር ነገር የለም የሚል እምነታችን ለአድርባይነት ሥር መስደድ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። የተግደረደረን፣ የጠየቀን፣ የተመራመረን አናት አናቱን የሚል የአስተዳደር የትምህርት የቤተሰብ ሥርዓት አድሮ መኖርን ሥር እንዲሰድ አድርገውታል። አድርባይነት ከልክ ያለፈ ወግ አጥባቂነትን ያበረታታል። የስንፍና ወዳጅ፣ የፈጠራና የራስ ተነሳሽነት ባህሎች ደመኛ ነው። አድርባይ ሰው አይተጋም፣ ከፊት አይቀድምም፣ አያስብም፣ አይፈጥርም። ነግቶ መምሸቱን እንጂ እንዴት እንዳደረ ግድ የለውም። ዝም ብሎ መሰንበትን መኖር መንከላወስን እንጂ ለህይወቱ ጥራትና ውበት አይጨነቅም። በማኅበረሰባችን ውስጥ ስለግዜ መባከን ደንታ የሌለን የሆንበትንም እውነታ ከአድርባይነት ጋር ማያያዝ ይቻላል። ቃሉን በደንብ ስናየው አድር ባይ ማላት ለማደር ብቻ ለመሰንበት ብቻ ለመኖር ብቻ ሲል ምንም አድርጎ፣ ዝም ብሎ የሚኖር ማለት ነው። 

        በአንድ ሀገር ላይ ትልቅ ለውጥ አመጣለሁ፣ የአንድን መከረኛ ሕዝብ ሕይወት በሰላምና በብልጽግና ወደተሞላ ሕይወት እቀይራለሁ ብለው የተሰባሰቡ ሰዎችን አድርባይነት መልካም ህልማቸው እንዳይሳካ የሚያደርግ ጎጂ ባህል ነው። አድርባይነት ልክ እንደተጠራጣሪነት ውሎ አድሮ የአንድን ድርጅት መኖር ወይም አለመኖር የሚወሥነው ጉዳይ ስለሆነ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠውና ሊወገድ የሚገባው ጎጂ ባህል ነው። አድርባይነትና ነፃ አውጭነት አንድ ላይ አይሄዱም። 

     ከዚህ በላይ ካነሳናቸው ጎጂ ባህርያት ጋር በቀጥታ ተመሳሳይነት ያላቸው የማይመስሉትም እንደ - ሌሎች በሚገባ ያቀረቡትን ተደጋጋሚ ሃሳብ እንደ አዲስ ሃሳብ አድርጎ መልሶ ያንኑ ማቅረብ፣ ከሚገባው በላይ ፍጹምነት ትክክለኛነት ስህተት አስወጋጅነት፣ ምሁራዊ ዘረፈ ብዙነት ማጣት፣ አላስፈላጊ የሆነ ጥድፊያ ላይ ማተኮር፤ እኩል እድል ከመስጠት ፈንታ እኩል ውጤት ላይ ማተኮር፣ ከሚገባው በላይ ውጤት ተኮር ሆኖ መገኘት፣ ውጤት ላይ ብቻ ማተኮርና ከውድቀት ለተገኙ ትምርቶች ቦታ አለመስጠት፣ ትርጉም የማይሰጥ መዋቅራዊ ድርጅታዊ ለውጥ ማድረግ፣ ሁሉንም ሰው በአንድ አይነት መንገድ ማስተናገድ፣ አቅምን እድሜን ችሎታን የአይምሮ ና የአካል ብቃትን እምነትን ባህልን ግምት ውስጥ ያላስገባ ሁሉንም በአንድ አይነት መንገድ ስሱ ሳይሆኑ መመልከት ፣የሰዎችን ችሎታና አቅም ግምት ውስጥ ያላስገባ ኮታ ለማሟላት ብቻ ሲባል ለሰዎች ኃላፊነት መስጠትና ወዘተ፣ አንድን ድርጅት ጤናማ በሆነ መንገድ እንዳይንቀሳሰ የሚያደርጉ ድርጅታዊ ጎጂ ባህርያት ናቸው። ድርጅታዊ ስንል ግን መሳሳት አይኖርብንም። የድርጅቶቹ ፈጣሪዎችና ኃላፊዎች ሰዎች ናቸውና ድክመቶቹ የድርጅቱ አባላት ድክመቶች ናቸው። ድርጅትን እራሳችን ፈጥረን ድርጅቱ እያልን እኛው የፈጠርነውን አካል በራሱ ነፍስ እንዳለውና እራሱን እንደፈጠረ አድርገን ከማየት አደገኛ ባህል እራሳችንን መከላከል ይኖርብናል። 

      ይህ ከግል ሃላፊነትና ተጠያቂነት ለመሸሽ ሲባል በሃገራችን የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ የተስፋፋ ድርጅትን በባእድ አምሎኮ ደረጃ ከሚያስቀምጥ አደገኛ ባህል ጋር ከምር መታገል ይኖርብናል። የድርጅት ወንጀል ወይም የድርጅት ጥፋት ብሎ ነገር የለም። ወንጀልም ጥፋትም ካለ በወንጀሉና በጥፋቱ የተሳተፉ ግለሰቦች ነው። ከላይ የተጠቀሱት ጎጂ ልምዶች እንደሌሎች ልምዶች የትኛዎቹ አባላት እንዳመጧቸው ሳይታወቅ በድርጅት ውስጥ እንደሃረግ በሁሉም ቦታ ተስፋፍተው የሚገኙ መሆናቸው ነው። በመሆኑም አንድ ድርጅት በቋሚነት እነዚህ ጎጂ ባህሎች ሥር ሰደው አንቀው እንዳይገሉት አባላቱ ነቅተው መጠበቅ ይገባቸዋል። እነዚህን አይነት ልምዶች ለምን ጎጂ ተብለው እንደተዘረዘሩ በየነጥቦቹ ዙሪያ በሚደረጉ ውይይቶችና በሚሰጡ ምሳሌዎች የበለጠ ሊብራራ ይገባዋል። ከላይ የተዘዘሩ ከ70 በላይ የሚሆኑ ጎጂ ባህርያት በተግባር ምን እንደሚመስሉ የሚያሳይ ከሕዝባዊ ኃይሉ የቀን ተቀን ሕይወት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች ወደፊት በአባሪ ሠነድነት በስልጠና ሰነዱ ውስጥ ማካተት ይገባል። 

     እያንዳንዳቸውን ጎጂ ባህርያት ሁላችንም ታግለን ለምን ማሸነፍ እንደሚገባን እንደሚያስፈልግ በደንብ ግንዛቤ መጨበጥ የምንችለው የነዚህ ጎጂ ባህሎች ማስረጃ የሚሆኑ የግልና የቡድን ድርጊቶቻችንን በሚገባ መመርመር ስንችል ብቻ ነው። (በዚህ ሰነድ አማካይነት ውይይት ለማድረግ የወሰኑ ሌሎች አካላትም ከራሳቸው ተመክሮዎች ጋር የተባለውን በማዛመድ የተሻለ ግንዛቤ ማዳበር ይችላሉ።) 

ማጠቃለያ 

እኔ ማነኝ የሚለው ቀላል የሚመስል ጥያቄ ወደኋላ ተመልሰን ከሽህ ዓመታት በፊት ከነበሩ ቀደምቶቻችን ጋር እንድናወጋ አድርጎናል። እኔ የዛሬ ብቻ ውጤት አይደለሁም። የረጅም ዘመን የታሪክ፣ የባህልና የልምድ ውጤት ነኝ። እራሴን ለመረዳት ከፈለግሁ ብዙ ነገሮችን ማወቅ እንዳለብኝ ተረድቻለሁ። ተራ የሚመስሉ ፍላጎቶቼ፣ ስሜቶቼና ዝንባሌዎቹ ጥልቀት ካላቸው ማህበራዊና ሥነልቦናዊ ጉዳዮች ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን አይቻለሁ። እኔ፣ ስሜን ብቻ ሳይሆን ፣ ወይም በፌስታል የሸከፍኳትን ኮተቴን ብቻ ሳይሆን ከዛ በላይ የገዘፉ ነገሮችን ይዤ ነው ወደ ግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል የመጣሁት። እነዚህን ግዙፍ ነገሮች፣ እንኳን ሌሎች ጓዶቼ ራሴም በቀላሉ ላያቸው የማልችላቸው መሆናቸውን ተረድቻለሁ። 

እኔ በሚለው ርዕስ፣ እኔ ማነኝ በሚለው ጥያቄ ጀመርን:: ለምን በእኔ ማነኝ ጥያቄ ጀመረን? እኔነቴን፣ ማንነቴን በሚገባ ሳላውቅ፣ ምን እንደምፈልግ ምን እንደምመኝ፣ ያሉኝን ፍላጎቶችና ምኞቶች ለማሳካት የሚያስችሉ ባህርያት፣ ሙያ፣ እውቀት፣ክህሎት እንዳለኝ ወይም እንደሌለኝ ማወቅ አልቻልም። በዚህ ታሪካዊ ወቅት ማንነቴን በደንብ ማወቅ የምፈልገውን ዝም ብዬ ለማወቅ ብቻ አይደለም። ላሳካው እፈልጋለሁ ብዬ ካሰብኩት ዓላማ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ስለሆነ ነው። ይህ ዓላማ የወያኔን የአመጽ እብሪት በአመጽ ሰባብሮና ወያኔን አስወግዶ በቦታው ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ማየት ነው። ለእኔ ማነኝ ጥያቄ የሰጠሁት ምላሽ፣ ወደምፈልገው ዓላማና ግብ ለመድረስ የሚገጥሙኝን ተግዳሮቶች ለመቋቋም ያለኝን የመንፈስ ጽናት፣ ቁርጠኛነት፣ እልህ፣ እውቀት፣ሙያ የሚጎድሉኝን ክህሎቶች ማወቅ ብቻ ሳይሆን ወደ ማራኪው ራዕይ ለመድረስ የሚጎድሉኝ ባህሪያትና ክህሎቶች ማሟላት እንድችል ያደርጉኛል። ለእኔ ማነኝ ጥያቄ በቅድሚያ የሰጠሁት መልስ ሰው ነኝ የሚለውን ነው። ሰው ስለሆንኩ እንደሰው በፈጣሪ በተፈጥሮ የተሰጡኝ መብቶች አሉኝ። ነፃ ሆኘ ነው የተፈጠረኩት ማንም ባሪያ ሊያደርገኝ አይገባም። እኩል ሆኘ የተፈጠርኩት ማንም የበታቹ አድርጎ ሊያየኝ አይገባም።በሰው ልጅነቴ ብቻ ማግኘትና ሊኖሩኝ የሚገቡ መብቶቼን ማንም ሊነካብኝ አይገባም ብያለሁ። እኔ ማነኝ የሚለው ጥያቄ ሰው ነኝ ከሚለው ምላሽ አልፎ ኢትዮጵያ ብዬ የምጠራት ሀገር ዜጋ መሆኔን የሚያስረግጥ ሌላ ምላሽ አግኝቷል።ኢትዮጵያዊ ከሆንኩ በዜግነት ከማንም የማያንስ የማይበልጥ የእኩልነት መብት ያለኝ፣ እንደዜጋ የሲቪል፣ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊና የኢኮኖሚ መብቶቼ ሊከበርሉሉኝ እንደሚገባ ግልጽ አድርጎልኛል። እኔ ማነኝ የሚለው ጥያቄ ሌላ ተጨማሪ መልስ ይዞ መጥቷል። እኔ የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል አባል ነኝ የሚለውን። የግንቦት7 አባል ነኝ የሚለው ምላሽ ግን ሰው ነኝ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነኝ ከሚለው ምላሽ የተለየ ነው። ለምን? 

    ሰው ሆኘ ስፈጠር በራሴ ምርጫ አይደለም። ኢትዮጵያዊ ሆኜ ሰወለድም በኔ ምርጫ አይደለም። የግንቦት7 ሕዝባዊ አባል ስሆን ግን በኔ ምርጫ ነው። ስለሆነም ለምን የግንቦት 7 ኃይል አባል ሆንኩ የሚል ጥያቄ አንስቻለሁ። የግንቦት 7 አባል ነኝ ስል ምን ማለቴ ነው? የግንቦት ሰባት አባል ያደረገኝ በሰውነቴ በዜግነቴ ማግኘት የሚገባኝን መብት እንደኔው ሰዎችና ዜጎች በሆኑ እብሪተኞች ሰለተቀማሁ ነው። ስለተገፋሁ ስለተዋረድሁ፣ ቤተሰቦቼ ፣እውቆቼ ወገኖቼ በሙሉ ይህን መብት ስለተቀሙ ነው። የሃገሬ ዜጎች በሙሉ ይህን መብት ስለተቀሙ ነው።የግንቦት 7 ሕዝባዊ አባል ያደረገኝ ይህንን መብቴን በእብሪት የቀማውን ወያኔን በማስወገድ ለማስከበር ነው። የግንቦት 7 ሕዝባዊ አባል ስሆን ለራሴ ብቻ ሳይሆን ከራሴ አልፎ ለቅርብና ለሩቅ ወገኖቼ የሚተርፍ መብት የማስከበር የተቀደሰ ዓላማ ለማሳከት ነው። ይህን ዓላማ ለማሳካት ደግሞ ለብቻዬ የምወጣው ስላልሆነ እንደኔው ከተገፉ ከተዋረዱ ከሚቆረቆሩ ከቆረጡ ለምን እንደሚታገሉ ለምን እንደሚደሙ እንደሚሞቱ ዓላማቸውን ጠንቅቀው ካወቁ ሌሎች የሃገሬ ሰዎች ጋር በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ውስጥ በመሰባብ እንደሆነ አውቂያለሁ። እኔ ብቻየን አይደለሁም። እኛ ነን። ከራሴ ተነስቼ እኔ ማነኝ የሚለውን ጥያቄ በዝርዝር እንደመለስኩት ይህ ሂደት እኛ ማነን የሚለውን ጥያቄ እንዳነሳ አድርጎኛል። 


የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል የፖለቲካ ጉዳዮች ዘርፍ 

ሚያዝያ 2005 
www.ginbot7pf.org 

                                                                                         Posted by A.G