#Ethiopia #ESAT #ESAT_Norway በኖርዌይ በኦስሎ ከተማ ቅዳሜ 14/10/2017 በተዘጋጀው አዝናኝ እና ትምህርት ሰጭ 7ኛው የኢሳት ክብረ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሮል᎓᎓ ዝግጅቱን ካደመቁት እንግዶች መሃከል የኢሳት ጋዘኛ ፋሲል የኔአለም ከአምስተርዳም እንዲሁም ከለንደን ከተማ የመጣችው ታዋቂ ዘፋኝ ሃነሻ ሰለሞን የኢሳት 7ኛ ዓመት ክብረ በዓል ልዩና ትምህርት ሰጭ ፣ አዝናኝ እና በተለይ የኢሳት ሚዲያ ከተቋቋመ ጀምሮ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ የተገፀበት ነበር᎓᎓ የህዝባችን አይን፣ ጆሮ እና ድምፅ ለሆነልን ኢሳት በተዘጋጀውና ትልቅ ፉክክር የታየበት የገቢም ማሰባሰቢያ ጨረታም በስታቫንገር ከተማ የኢሳት ደጋፊ ነዋሪዎች አሸናፊነት የተዘጋጀውን ሽልማት ከጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ተቀብለዋል᎓᎓ በዝግጅቱም ከትኬት፣ከተለያዩ የገቢማሰባሰቢያዎች፣ ከምግብና ከመጠጥ እና ከጨረታ ጥሩ ድጋፍ ተደርጎአል ᎓᎓ በዚህ አጋጣሚ የእስታቫንገር ከተማ ከሌሎች ከተሞች በበለጠ በትኬትም ሽያጭ ሆነ ጨረታውንም ለማሸነፍ ላደረጋችሁት ትብብር ታልቅ ምስጋና ይድረሳችሁ᎓᎓ ከጎናችንም በመሆን ትብብር ላደረጋችሁልና ለማድረግ እየፈለጋችሁ በተለያየ ምክንያት ያልተመቻችሁ በሙሉ ወደፊት በምናዘጋጀው ዝግጅቶች ቅንነታችሁ እና ድጋፋችሁ አይለየን !
በአብዩ ጌታቸው ከስታቫንገር
16/10/2017