ማን ይሆን ብዬ ተደናገጥኩ!! ነገር ግን በእጅ ምልክት ድብቅ እዉልብልቢት የጠራኝን ሰዉ ተከትዬ ወደ መጸዳጃ ቤት ዘለቅኩኝ ሴት መሆኔን የዘነጋዉ መለሰኝ ሰዉዬዉ በቀጥታ ወደ ወንዶች ሽንት ቤት አመራ እኔ ግን ወደዛ መግባት ስለፈራዉ ባለሁበት ቆምኩ ከጥቂት ቆይታ ሰከንዶች በኋላ ተመልሶ ወጣ መካከለኛ ቁመትና ደንዳና ሰዉነት አለዉ ከላይ ጥቁር ጃኬት ደርቦ ጥቁር የጨርቅ ሱሪ ታጥቋል በስሱ ተመልክቶኝ በንገቱ ወደ መጸዳጃ ቤት አመላከተኝና ዘመመ አሁን ፈራሁ በርግጠኝነት የሆነ ነገር መጸዳጃ ቤት ጥሎ እንደሄደ ጥርጥር ብጤ ገባኝ ቢሆንም የሰዉዬዉ ሁኔታ አስፈራኝ ልክ እንደ ሌባ ወይም የሆነ ነገር እንደሚደበቅ ሰዉ ነበር ሁኔታዉ። እንደምንም እራሴን አበራትቼ ወደ ወንዶቹ ሽንት ቤት ዘለቅኩ ታዲያ ይህ ሰዉ አንዳች ነገር ጥሎ እንደሚሄድ በመጠራጠሬ አይኖቼን ዙሪያ አማተርኩ በትክክል ልክ ነበርኩ አንድ የተጤቀለለ ወረቅት በገፋሁት በር ሲንፏቀቀ ተመለከትኩ በቀጥታ ወረቀቱን አንስቼ ስወጣ ያዉ ወረቀቱን የወረወረዉ ግለሰብ እና ሌላ ሰዉ ሽንት ቤቱ በር ላይ ቆመዉ ተመለከትኩ እናም ” እህት አንዴ ቆይ! ” ተባልኩ እኔም ባለሁበት ቆምኩ ያዉ እራሱ ግለሰብ ወደኔ ጠጋ አለና ” ይህ የወንዶች ሽንት ቤት ነዉ ምን ታደርጊያለሽ ” አለኝ ” አረ እኔ! ተሳስቼ ነዉ። ደግሞ ሽንቴን ወጥሮኝ.. ስለነበር ” ብዬ ዝም አልኩ ” እሺ እዚህ አካባቢ ምን ታደርጊያለሽ ” አለኝ ” ማን! እኔ ” አልኩት ” አዎ! አንቺ ” ” እኔ የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አባል ነኝ!! እገሊት እባላለዉ ” አልኩት ” በጣም ጥሩ መታወቂያ ልታሳይኝ ትችያለሽ ” አለኝ አዎ! አልኩትና ሰጠሁት መታወቂያዬን እንዳየዉ ድንጋጤ ይነበብበት ጀመር እጁ እየተንቀጠቀጠ መልሶ ሰጠኝ ነገሩ ስለገባኝ ፈገግ ብዬ “” አታስብ አይዞን “” ብዬዉ ወደ መደበኛ ስራዬ አመራሁ።
ለግዜዉ ስሜ ይቆያችሁና ከሽንት ቤት የተገኘዉን ደብዳቤ ግን ለናንተ እንዲደርስ እንዲህ አሰብኩኝ
“” ይህን እዉነት ለሚያገኘዉ ሁሉ እዉነት በተወለደችበት እለት የእዉነት ጠላቶች እዉነት ነዉ ብለዉ የሚያምኑበትን የእኛን እዉነት የእነርሱን ዉሸት እንድንቀበል በሚደረግ ግብ ግብ መሐከል ስለሚንገላታ አንድ ግለሰብ እንዲያስብ ይሁንለት “” እኔ በምኖርበት ዘመን የተፈጠረዉ ትዉልዴ ልጅ ነኝ፣ አንዲት የምታሳዝን ሐገር ልጅ፣ አንዲት በጥቂቶች እጅ ወድቃ የምትንገላታ እናት ልጅ፣ አንዲት የልጅ ያለህ እያለች ለምትጣራ ደርባባ እናት የቃተትኩ ልጅ፣ ሽማግሌ ልጅ፣ አዛዉንት ልጅ፣ የእናቴ ልጅ ሆኜ ደግሞ ሌላ ልጅ ወደዚህ ምድር ያመጣሁ ስለነጻነትም ልጄን በበረሐ ላይ የወለድኩ ያሳደግኩ ፣ ለእርሷ ለእናቴ እዳ ሆኜ እንዳልቀር ለትዉልዴ ልስራ ያልኩኝ ነጻነት ተጠምቼ በነጻነት ምክንያት ተላልፌ የተሰጠዉ ልጅ እና የልጅ አባት’፤ አዛዉንት የነጻነት ጥመኛ የትዉልድ እረሃብተኛ።
እኔን ለማጥፋት ያልተቆፈረ አልነበረም እነ ይሁዳ አሳልፈዉ ሰጡኝ። ነገር ግን እኔ ብኖርም ባልኖርም የነጻነት ብርሐን አንድ ቀን ቦግ እንደሚል አዉቃለዉ!!! እጄ በእጃቸዉ ላይ ከወደቀበት እለት አንስቶ እኔ የምባል ሰዉ መሞቴን እወቁ!! በዚህ አለ!! እንዲህ ሆነ!! ይህን አደረገ!! ይህን ተናገረ!! ቢሏችሁ ሁሉ እኔ መሞቴን እወቁ!! የሞተን የተገደለን ሰዉ የተገደደን ሰዉ አትከተሉ እንዳሻቸዉ ሊያደርጉና ሊያደርጉብኝ ዛሬ በእነርሱ እጅ ላይ ነኝና እኔኝ እርሱኝ !! ለእናንተ በትግል ነጻ ለመዉጣት ለምትተባበሩ ሁሉ አደራዬን አስተላልፋለዉ ኢትዮጵያዬን አደራ! ህዝቤን አደራ! ነጻነትን አደራ! ከንግዲህ እያንዳንዳችሁ እስከሞት ድረስ የታመናችሁ ሁኑ በመሰዋትነት የሚገኝን ክብርና ሰላም ለሌሎች ስጡ! እነዚህን ግን ነቀርሳዎች ሳትነቅሉ እኝዳትተኙ እንዳታንቀላፉ ።
ደህና ሁኑ ድል ለመላዉ ህዝቤ !
No comments:
Post a Comment