በዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ስታቫንገር ቅርንጫፍ አዘጋጅነት መስከረም 5 2015 በኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይና በሰብዓዊ መብት አያያዝ በተመለከተ ታላቅና የተሳካ ውይይት ተካሄደ::
በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ የነፃነት ተምሳሌቱና የጀግናው አንዳርጋቸው ፅጌ ወ/ሮ ብዙሃየው ፅጌ ፣ የአበኞች ግንቦት 7 አመራር ዶ/ር ሙልዋለም አዳምና ፣ የዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሊቀመንበር አቶ ዩሀንስ አለሙ በተጋባዥ እንግድነት የተገኙ ሲሆን
ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ከተለያዩ የኖርዌይ ከተማ የመጡ አገር ወዳድ ታዳሚዎች በስብሰባው ተገኝተዋል::
በመጀመርያ የዲሞክራሲያዊ ለለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ስታቫንገር ቅርንጫፍ አቶ አብዩ ጌታቸው በኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ አረመናዊ ስርአት በጭካኔ በግፍ ለተገደሉ እና በተለያዩ አስር ቤቶች በፖለቲካ ኣስተሳስባችው ምክንያት ያለወንጀላችው ለታሰሩ ውድ ኢትዮጵያዊን ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማስደረግ ስብሰባውን ያስጀመሩት ሲሆን በመቀጠል የዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሊቀመንበር አቶ ዩሀንስ አለሙ ስለ ድርጅቱ እንቅስቃሴና ከዚህ ቀደም ሲደግፋቸው የነበሩት የቀድሞው ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሰማያዊ ፓርቲ ጋር ባሁን ሰሃት የወያኔ ሥርሃት ባደረገው አፈና ምክንያት መገናኘት እንዳልተቻለና የቀረው አርበኞች ግንቦት 7 በመሆኑ ሙሉ ድጋፋቸውን እያደረጉ እንደሆነ የገለፁበት ንግግር አድርገዋል።
በቀጣይም የነፃነት ተምሳሌቱና የጀግናው አንዳርጋቸው ፅጌ ወ/ሮ ብዙሃየው ፅጌ ስለ ወንድማቸው ያለበት ሁኔታና አንዳርጋቸውን ለማስፈታት በዲያስፖራ ኢትዮጵያን እየተደረገ ያለው ተቃውሞ ፍሬ አፍርቶ ባሁን ጊዜ በተባበሩት መንግስታት፣ በአሜሪካንና በእንግሊዝ መንግስት የነፃነት ታጋዩን አንዳርጋቸው ፅጌ ይፈታ ዘንድ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ መሆኑንና ይህም የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የዲያስፖራው ትልቅ ተጋድሎ መልስ መሆኑንና ትግሉም አንዳርጋቸው ፅጌ ማስፈታት ብቻ ሳይሆን ነፃነት ያጣውን የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ ስርሃት እስኪፈቱ ድረስ ትግሉ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
በኖርዌይ ለሚገኙ ኢትዮጵያን ያላሰለሰ ድጋፍ ያደርጉ ለነበሩት የኖርዌይ ስታቫንገር ማህበራዊ ተቃውማት የምስጋና ሰርተክፌት የተሰጠ ሲሆን
ከዚያ በማስከተል መድረኩን የተረከቡት የአበኞች ግንቦት 7 አመራር ዶ/ር ሙልዋለም አዳም ሲሆኑ ባሁን ሰሃት የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች በኤርትራ በረሃ ላይ እያደረጉ ያለውን እንቅስቃሴና ወሳኝ ምህራፍ ላይ ስላለው ትግል እንዲሁም አርበኞች ግንቦት 7 ከየትኛውም አይል ጋር አብሮ የሚሰራና ለመስራትም የሚጥር እንደሆነ እንደምሳሌም ከትህዴን/የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲ ንቅናቄ/ ፣ ከአፋርና ከጋምቤላ ነፃ አውጪ ድርጂቶች ጋር ተባብሮ በመስራት ላይ እንደሆነ ገልፀው አሁን የውይይትና የወሬ ጊዜ አይደለም እንቅስቃሴውን ሰምታቹዋል በየቀኑ ከወያኔ ሃይል ጋር ትንቅንቅ እያደረጉ ነው ስለዚህ ይህን ትግል ለመደገፍ የእናንተን ድጋፍ ይፈልጋልና ትግሉን ለመደገፍ እንነሳ ብለዋል።
በመጨረሻም ከታዳሚ ለሚሰነዘሩ ጥያቄና አስተያየት መልስ የሚሰጥበት ሆኖ በግልፅነትና በጨዋነት ለተነሱ ጥያቄዎች ከመድረክ መልስ እየተሰጠባቸው የሰከነ ውይይት ተደርጎ በዝግጂት ክፍሉ ሰብሳቢና በዲሞክራሲያዊ ለለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ስታቫንገር ቅርንጫፍ አቶ አብዩ ጌታቸው የመዝጊያ ንግግር ተደርጎ በአበኞች ግንቦት 7 መዝሙር በመዘመር የተሳካ ውይይት ተደርጎ ተጠናቅዋል።
ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ!!!!!
በዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ስታቫንገር!!!!
No comments:
Post a Comment