Friday, 15 November 2013
ሰበር ዜና ወያኔ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችን አሰረ ሰልፉም እንዳይደረግ ከለከለ
ህዝብ መንግስት ከሳውዲ ጋር አበረ እያለ እያማረረ ነው፡፡
ከአዲስ አበባ ከሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ለተቃውሞ ሰልፉ በመዘጋጀት ላይ ከነበሩ አመራሮች መሃል ሶስቱን ፖሊስ አስሯቸው ወደ ጃንሜዳ ወስደዋቸዋል፡፡። በዚህም መሰረት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የፓርቲው ሊቀመንበር፡ አቶ ስለሺ ፈይሳ ምክትል ሊቀመንበርና ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ ህዝብ ግንኙነት ከደቂቃዎች በፊት ታስረዋል። በአሁኑ ሰዓት ሰዉ ሰልፉን ለመውጣት ተዘጋጅቷል። ሰማያዊ ፓርቲ ምንም ዓይነት ወከባና እስር ሰልፉን አያቆመውም ብሏል። እንዴት ነው ሰዎች? ወገኖቻችን በሰው ሀገር ሲገደሉና ደማቸው ሲፈስ እንኳን ሀዘን መግለጽ አይቻልም?
ዜጎች ክብ ክብ ሰርተው በሳውዲ ስለደረሰው በደል፣ ስለ ሰማያዊ ፓርቲ ታሳሪዎችና ስለ እርምጃው እያወሩ ነው፡፡ ፖሊሶቹ የታዘዙትን ብቻ የሚሰሩ መሆናቸውን የሚያሳየው ሰማያዊ ፓርቲ በር የተሰቀለውን ጥቁር አርማ አላነሱትም፡፡ የሰማያዊ ፓር አባላትንና ደጋፊዎችን አስረው እንኳ ፖሊስ ከቢሮው አካባቢ አልለቀቀም፡፡ ህዝቡ በሱቅ በረንዳዎች፣ ካፌና ሌሎች ምቹ አካባቢዎች ሆኖ እየተመለከተ ነው፡፡
source:_freedom4ethiopian
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment