ሮዚና አለም ተስፈዬ የተባለች አትዮጵያዊት ከደርባን በሜሴንጀር በላከችልኝ መልዕክት መሠረት እነዚህ በአንገታቸው ላይ ጎማ የተጠለቀባቸው ሦሥት ወጣቶች ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡የሮዚና መረጃ ትክክል ከሆነ የዛሬ ሳምንት በሱቃቸው እያሉ የእሳት ጥቃት የተፈፀመባቸውን ሁለቱን ኢትዮጵያውያን ስንጨምር ቁ ጥሩ ወደ 5 ከፍ ይላል፡፡ከነዚህ ውስጥ አነዚህ ሶስቱና ሳምንት ከተጠቁት ሁለቱ አንዱ ስለሞተ የሟቾች ቁጥር 4 ነው፡፡
በፅኑ የቆሰለው አንደኛው ሆስፒታል ሕክምና ላይነው፡፡ ትናንት ተጠልፈው የተወሰዱና ይሙቱ ይዳኑ ያልታወቁ ሶስት የጠፉ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ይህ ብቻ እንኳ የአትዮጵያንን ቀጥተኛ ጥቃት ወደ 8 ያደርሰዋል፡፡በዐለም አቀፍ ሚዲያ የሚገለጸው ሊገባኝ አልቻለም፡፡ትናንት በሲኤን ኤን ዘገባ ድንበር ላይ ያነደዱትን ዚምባብዌያዊ አይቻለሁ፡፡ሌላ አንድ ሞተረኛን፣አንድ ደግሞ እላዩ ላይ እሳት ጭረውበት የሚያደርገው ጠፍቶት እንደ እብድ ወዳገኘበት ሲሮጥና ተከታትለው በጠረባ በመጣል ጎማ በአንገቱ አስገብተው ሲያነዱት አይቻለው፡፡እሱ የነደደበት ቦታ ላይ ነው ሞተረኛውን ከነሞተሩ የጣሉትና ያጋዩት፡፡እዛው የነበረና ቀይ ሹራብ የለበሰ ወጣት ድንገት ተናነቁት፡፡
አምልጬ እሔዳለሁ ሲል አንዱ በጣውላ አናቱ ላይ መታው ፤እነሳለው ሲል አንዱ ፊቱን ረገጠው፤ሌላው በጣውላው ደገመው ፡፡ከዛ እሳቱ ውስጥ ማገዱት፡፡ብዙ ደቂቃ እንደእንጨት ሲቃጠሉ በሕይወት ነበሩ፡፡
ሌሎች ዕድሜያቸው ከ14 21 ሊሆኑ የሚችሉ ሶስት ወጣቶች ሢቃጠሉ አይቻለሁ፡፡ሌሎች ሁለት እንደ አይጥ አሰፈልት መሐል በድንጋይ ተጨፍልቀው ፣በአጠና ተጨጭፈውና በእግር ተረጋግጠው ሢሞቱ አይቻለሁ፡፡አለም አቀፍ ሚዲያዎች የሚሠጡን ቁጥሮ ግን አስቂኝ ነው፡፡እስካሁን አምስት ሰዎች ተገደሉ ይሉናል፡፡በቂ መረጃ እያገኘን አይደለም፡፡
አለምነህ ዋሴ
No comments:
Post a Comment