ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለምን አጋነኑት ድሬቲዩብ እሳት ፈጠረለት
ግሩም ተ/ሀይማኖት
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሀኖም የመን ያለው ኤምባሲ ተመታ ብለዋል፡፡ ይህንኑ ዜና ድሬ ቲዩብ በእሳት የጋየ ምስል በመጨመር ውሽቱን በውሸት አዳምቋል፡፡ ለካ ሚኒስትርም ይዋሻል ያሉኝ ሰዎች ሄደው ኤምባሲውን ካዩ በኋላ ነው፡፡ አንድም ቦታ አልተመታም፡፡ ወደላይ ሲተኮስ በርዶ የተመለሰ ይሁን በቀጥታ የተተኮሰ አንድ ጥይት ጎማ ነገር መቷል፡፡ ይሄን ፍንጭ ይዘው እንዴት ይዋሻሉ ሲሉኝ እስኪ እናጣራ ብለው የሄዱ ሁለት ልጆች አገኘሁ፡፡ ዘ-ይገርም ውሸት ያስባለ ምንም ነገር የሌለ ውሸት መሆኑን ሲነግሩኝ ድንገት እዚሀ ያሉት ሰዎች ዋሽተው አስዋሽተዋቸው ይሆን? የሚል ጥያቄ ውስጤ ተላወሰ፡፡
ግና በዚህ ምክንያት ነው ስደተኞቹን ያላወጣነው ሊሉ ሰበብ ማዘጋጀታቸው መሆኑም አንዱ ምክንያት ነው፡፡ ለማጣራት ባደረኩት ሙከራ ራሳቸው ኤምባሲ አካባቢ ያሉ ስደተኛውን ሲመዘግቡ እና ሲያስተናግዱ የነበሩ ሰዎች በዚህ ውሸት ሲናደዱ ተሰምተዋል፡፡ በአርቡ ቀን ሰላም ሆነው እየመዘቡ ሳለ ተመታ መባሉ ለምን አያናድዳቸው? በሌላ በኩል ዲፕሎማቶቹ ዜጎቻችንን ሳናወጣ አንወጣም ብለው የሚለውን ሳይ ሆነ ተብሎ የተዋሸ እንደሆነ ገባኝ፡፡ ለመሆኑ ዲፕሎማቶቹ አሉ እንዴ? እኔ እንደሚመስለኝ ወይም ከወጡ ቆየት ብለዋል፡፡ ጊቢው ውስጥ ያሉት ተራ ሰራተኞች እንጂ ዲፐሎማቶች አይደሉም፡፡
ለመሆኑ እስከዛሬ ለምን ዝም ብለው ከረሙ ለህዝቡ ስላሰቡለት? ሌሎች ሀገራት ዜጎቻቸውን ሲያወጡ ይት ነበሩ? እስከዛሬ አገልግሎት ፍለጋ የሄደውን ኢትዮጵያዊን በአግባቡ አስተናግደው ያውቃሉ?..አሁንም ቢሆን እንደ እኔ አመለካከት ከአይ. ኦ. ኤም ወይም ከቀይ መስቀል እርዳታ እስኪያገኙ እየጠበቁ ይመስለኛል፡፡ ዶክተሩ ግን ኤምባሲው ተመታ ብለው ሲዋሹ የመን ያለ ዝጋ ይታዘበኛል አይሉም? ወይ ምርጫ…ማን አለባቸው ሁሉ በእጃቸው ለምርጫ ብለው ይሄን ያህል መዋሸት?.አደን ከሚባለው ሁለተኛ ከተማ 30 ኢትዮጵያዊያን በባህር ወደ ጅቡቲ ገብተዋል፡፡

No comments:
Post a Comment