Friday, 23 January 2015

አራት ወታደራዊ መኮንኖች ታሰሩ

የደቡብ ምስራቅ እዝ የመከላከያ ሰራዊት ካልደፈረሰ አይጠራም እያለ ነው
ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው:-
ጨፍጫፊው ሌ/ጄነራል አብረሃ ወልደ ማርያም (ኩዋተር) የሚመራው ለሶማሌ ክልል ሰላም በሚል በአከባቢው የሰፈረው የደቡብ ምስራቅ እዝ የሕወሃት የጦር አዛዦች በራሳቸው የሚወሥዱት ውሳኔ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የሚያደርሱት ጫና እና እንዲሁም ሰራዊቱ ያቀረበውን ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ ወደ አመጽ ማምራቱ ተሰምቷል::በጎዴ ከሚገኙ የመከላከያ ደህንነት ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ካልደፈረሰ አይጠራም በሚል የተነሳውን አመጽ የተመለከቱ የሕወሓት የጦር አዛዦች የመከላከያ ሰራዊት ጥያቄ እና አመጻ ተከትሎ አነሳስተዋል የተባሉ አራት ወታደራዊ መኮንኖች መታሰራቸው ታውቋል::
በዚህም መሰረት
ሌተናት ኮሎኔል ተክለአረጋይ ዳኘው
ሻለቃ አበባየሁ አቡኑ
ሻለቃ ደምወዜ የኔአለም
የም/መቶ አለቃ ላቀው ልኬየለህ በጎዴ ወታደራዊ እስር ቤት መታሰራቸው ታውቋል::

በጅጅጋ ከተማ በተከታታይ የሚሰበሰበው የሕወሓት ጄኔራሎች ቡድን በደቡብ ምስራቅ እዝ ውስጥ የተነሳውን አለመተማመን እና ግርግር መቅረፍ እንዳልተቻለ እና አመጾች ሳይስፋፉ እና ስር ሳይሰዱ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ሁሉ እንዲወሰዱ ሲል ተስማምቷል::በሶማሊ ክልል የሚገኘው የሕወሓት ጀሌዎች የሆኑ መኮንኖች በኦጋዴን ክልል ማህበረሰብ ላይ ይህ ነው የማይባል ከባድ ግፍ እና ግድያ እስር ሰቆቃ የሚፈጽሙ ሲሆን በሕገወጥ ንግድ ላይ በመሰማራት የሃገሪቷን አንጡረ ሓብት በመዝረፍ እና በማሳጣት ስራ ላይ መሰማራታቸው የአደባባይ ሃቅ ነው::ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው የሕወሓት የጦር መኮንኖች እንዲሁም በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ሴቶችን በመድፈር በዘረፋ ከአከባቢው ሲቭል ባለስልጣናት ጋር የተመሳጠረ ሙስና በመስራት የሚከሰሱ ሲሆን ስርኣቱ በስልጣን እንዲቆይ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በአከባቢው እንደሚፈስ ምንጮቹ የተናገሩ ሲሆን የዚህ ገንዘብ ፍሰት የሙስና ተግባራት በሕወሓት የጦር መኮንኖች ይፈጸማል ሲሉ ይናገራል::

No comments:

Post a Comment