Sunday, 11 January 2015

ታሪካዊው ጣይቱ ሆተል ተቃጠለ



በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዘመናዊ ሆቴል የሆነውና ለሀገሪቱ እና ለሕዝቡ እንደ ታላቅ ቅርስ የሚታየው ጣይቱ ሆቴል ተቃጠለ። በቦታው የነበሩ የዓይን ምስክሮች እንዳሉት ሆቴሉ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ በእሳት ጋይቷል።






በሃገሪቱ ውስጥ የተከሰተው የፖለቲካ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ወያኔ በምርጫው ጉዳይ እና በተለያዩ የምእራባውያን ጫና የተወጠሩትና በህዝብ ጥያቄ የተጨነቁት የወያኔ ባለስልጣናት የህዝቡን የአስተሳሰብ አቅጣጫ ለማስቀየር እና ሃሳብ ለመስረቅና ለማስቀየስ ለማስደንገጥ እና አዲስ መወያያ ጉዳይ ለመፍጠር ያደረገው ተንኮል ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::


በዛሬው እለት የጣይቱ ሆቴል መቃጠልና የመውደሙ ነገር አስደንጋጭ ዜና ነው።ይህ ነገር ሆን ተብሎ ላለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለም።በርካታ ታሪካዊ ቅርሶችን ለልማት ያፈረሰው የወያኔ ኢህዲግ ዘረኟ አገዛዝ ይህን አያደርግም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። በውስጥ እና በውጭ የተከሰተበትን የፖለቲካ ውጥረት አቅጣጫ ማስቀየሪያ ነው:: የጣይቱ ሆቴል ባለቤት ፍፁምዘአብ አስገዶም ይባላል ᎓᎓ የእሳት አደጋው እዛው ፒያሳ ሆኖ በቶሎ ለመቆጣጠር ያለተቻለበት ምክንያት ታዲያ ምንድን ነው ???

No comments:

Post a Comment