Eyerusalem Tesfaw
ደስ እሚል ውሎ ነው ያሳለፍኩት በጠዋት ነው "አሸባሪዎቹን" ለመጠየቅ ከጉዋደኞቼ ጋር ወደ ቂሊኒጦ የሄድነው ጀግኖቹን እያሰብን የመንገዱ ርቀት አልታወቀንም ᎓᎓
ዞን ሁለት ገባን የዞን ናይኖቹን በፍቄ እና አጥናፍ፣ የወያኔን የዘረኝነት ሰንሰለት የሰበረው አይናፋሩ አብርሃ የሰማያዊዎቹ በፍቃዱ እና ሲሳይ፣ አሰቃቂ ድብደባ የደረሰበት ጀግናው አበበ ካሴን አገኘናቸው ጠያቂው እና ተጠያቂው አይለይም ነበር አፅናኝ እና ጠያቂ ታሳሪዎቹ ነበሩ ለሰማያዊ ያላቸው ፍቅር ልዩ ነው ትልቅም ተስፋ አላቸው ያለውን አዲስ ነገር አወራናቸው ሁሉም ደህና ናቸው᎓᎓
ከአበበ ካሴ በስተቀር በፍቄ ነበር ከሌላ ሰው ጋር ደግፎ ያመጣው ዱላ ይዟል በጣም ተጎሳቅሏል የእጁም የእግሩም ጥፍር ተነቅሎ አዲስ እየበቀለለት ነው እጆቹ ይንቀጠቀጣሉ ብልቱን በጣም ስለጎዱት ሽንት መሽናት እንደሚቸገር ለዛም ፈሳሽ ነገር እንደማይወስድ ነገረኝ ግማሽ ጎኑ መንቀሳቀስ ይከብደዋል ኡፍፍ ምን ብዬ ልንገራቸሁ መፈጠርን ያስጠላል አሁንም ዱላው አልቀረለትም በቀን ከአምስት ጊዜ በላይ ለምርመራ ይወስዱታል ያንኑ አሰልቺ ጥያቄ ነው እሚጠይቁት አውጣ ማንነው የላከህ???? ህክምና እስካሁን አላገኘም ግን ምን አይነት ጀግና እንደሆነ!!!
እንደዚህ ሆኖ እኛን ነው እሚያበረታታን አይዟችሁ በርቱ ነፃ እንወጣለን እናንተ ብቻ በርቱ ይለናል በተደጋጋሚ እኔ ግን ህመሙ በጣም አሞኛል እምባ እየተናነቀኝ ነበር ተሰናብቼው የወጣሁት አይ ኢትዮጵያ በስንት ሰው ደም ይሆን ነፃ እምትወጪው?
No comments:
Post a Comment