January9,2014
ዳዊት ከበደ ወየሳ
በሰሜን ጎንደር, አርማጭሆ አውራጃ ልዩ ስሙ "ገ'ጨው" በተባለው ስፍራ የመከላከያ ሰራዊት ከትላንት ጀምሮ እንዲሰፍር ተደርጓል:: ማዶ እና ማዶ ሆነው እየተዋጉ ባሉት የትግራይ ወታደሮች እና በአማራ ህዝብ መካከል መከላከያ ሰራዊት ከሰፈረ በኋላ ጦርነቱ አሁን ለጊዜው ጋብ ብሏል:: የቀድሞ የህወሃት ወታደሮችን ሁመራ ላይ በማስፈር አካባቢውን ለራሱ ያደረገው ህወሃት - አሁን ደግሞ በአርማጭሆ መስፋፋት በመጀመሩ ነው - በአካባቢው ከሚኖረው የአማራ ህዝብ ጋር ግጭቱ የተቀሰቀሰው::
ሰሞኑን ግጭቱ ከመባባሱ በፊት የአማራው ህዝብ ተዋጊዎች - ህወሃት በአጭር ጊዜ ውስጥ አካባቢውን ለቅቆ እንዲወጣ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር:: ሆኖም የህወሃት ወታደሮች አካባቢውን ለቅቀው ባለመሄዳቸው በተለይ በማይ'እምቧ በርካታ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ - ህወሃት አባላት ሞተዋል:: በወያኔዎቹ ላይ የደረሰው አደጋ ያስደነገጣቸው እና ወደ አርማጭሆ ያመሩት ሌሎች የህወሃት አባላት - ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ጦርነት ሲያደርጉ ነበር የከረሙት:: በዚህ ጦርነት የሞቱት ሰዎች ቁጥር በትክክል ባይታወቅም የተኩስ ልውውጡ ከፍተኛ ነበር:: አሁን የመከላከያ ሰራዊት በሁለቱ ወገኖች መካከል ከሰፈረ በኋላ ግን ጦርነቱ ለጊዜው ጋብ ብሏል:: ሆኖም ሁለቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች - ማለትም የህወሃት እና ብአዴን አመራሮች ውስጥ ውስጡን እየተናቆሩ ናቸው::
ህወሃት በድንበር ጉዳይ ካደረጋቸው የአገር ውስጥ ጦርነቶች ይሄኛው ጠንከር ያለ ነው:: ከዚህ ቀደም የህወሃት ወይም የትግራይ ታጣቂዎች የአማራውን መሬት ሲወስዱ - ህዝቡ "በህግ አምላክ" ብሎ እየጮኸ ከመሞት ውጪ ብዙ ምርጫ አልነበረውም:: አሁን ግን እየጮኸ ሳይሆን ጥይት እያጮኸ መሞትን የመረጠበትን አጋጣሚ ለማየት እየበቃን ነው:: አሁን የደረንበትን የቅርቡን ታሪክ እንዳየነው ከሆነ - ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) የአማራውን ህዝብ ከሁመራ እና ጠለምት: ከበየዳ, ከወልቃይት, ከድብ ባህር, ከአብደራፌ, ከብራ ዋድያ, ከሻግኔ እና ላሄን እያፈናቀሉ መሬቱን ለቀድሞ የወያኔ ወታደሮች ሲሰጡ ቆይተዋል:: በአካባቢው የአማራው መሬት ብቻ አይደለም ተወሰደው:: ወንዶቹን እያፈናቀሉ: ያንገራገረውን እየገደሉ ሚስቶቻቸውን እና ሴት ልጆቻቸውን በሙሉ ነው ነጥቀው የወሰዱት:: [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]
No comments:
Post a Comment