# የሕወሓት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች 40 አመታቸውን ተከትሎ ፍትጊያ ጀምረዋል::
# አለመተማመኑ እና ክፍፍሉ እየሰፋ መቷል::የእርስ በርስ መወነጃጀሉም ተጧጡፏል::
# በሰላም አስከባሪ ስም የተባበሩ መንግስታት ድርጅት በሚሊዮቾች ዶላሮች በኢትዮጵያ የጦር አለቆች ተጭበርብሬአለሁ የሚል ስሞታ አሰምቷል::
ሕወሓት በራሱ መልክ እና ቅርጽ የፈጠረው የመከላከያ ሚኒስቴር ስር ካለው ከጦር ሃይሎች መኮንኖች የተገኘው መረጃ እንደጠቆመው የወያኔ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እርስ በራሳቸው መወነጃጀላቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ቀውስ ውስጥ በመግባት በግምገማ እየተፋተጉ መሆኑን ታውቋል::በዘረፋ እና መረጃ በመሸጥ:አሳልፎ ለጠላት ወገን በማስተላለፍ ወንጀል መፈራረጅ የጀመሩት የጦር መኮንኖቹ አብዛኛዎቹ የመንደር ጎጥ ለይተው ሲጠቋቆሙ እና ሲመሰካከሩ የታየ ሲሆን ለእረፍት ከሃገር ውጪ ያሉ ከፍተኛ መኮንኖች በአስቸኳይ ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ ተጠይቋል::
በሕወሓት መራሹ መንግስት ላይ ከንፈራቸውን የነከሱ በርካታ ከኮሎኔል በታች ያሉ የጦር መኮንኖች በቀጥዩ ግምገማ ላይ በመንግስት ላይ ያላቸውን ቅሬታ የሚገልጹበት መድረክ እንደሚዘጋጅ የተነገረ ሲሆን ላለፉት ሁለት ቀናት የተደረገው እና አሁንም በቀጣይነት በመኮንኖች ክበብ እና በተለያዩ የመምሪያ አደራሾች ውስጥ በከፍተኛ መኮንኖች እና የጦር መምሪያ ሃላፊዎች ላይ የቀጠለው ግምገማ ውጠቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የጦር ሃይሎች ኢታማጆር ሹም የሆነው ሌ/ጄ. ሳሞራ የኑስ ዋናው አትኩሮ ሲናገር የነበረው በሙስና እና በመረጃ ንግድ ላይ የተሰማራችሁ የጦር መኮንኖች ምስጢራችንን አሳልፋችሁ ሸጣችኋል እና ብትጠነቀቁ መልካም ነው ካልሆነ እርምጃ እንወስዳለን ሲል የዛተ ሲሆን እርምጃ የሚወሰድባቸው ሊኖሩ ይችላሉ ሲል ተናግሯል::
ከጦር ሰራዊቱ ውስጥ ከአስረአምስት ቢሊዮን ብር በላይ አላግባብ ባክኗል የተባለው የሙስና ግምገማ በመኮንኖቹ መካከል ከፍተኛ የሆነ የቃላት አተካሮ እና አለመግባባት እየፈጠረ መሆኑን ምንጮቹ ለምንልክ ሳልሳዊ ተናግረዋል:: ይህንን ተከትሎ አንዳንድ አደገኛ የተባሉ የጦር መኮንኖችን ለማባረር በጡረታ ለማሰናበት እና ለማሰር የታቀደ ሲሆን አትኩሮት የሚደረግባቸው በሰራዊቱ ውስጥ ተከስቶ ያለውን አለመተማመን እና ክፍፍል ተከትለው ከስርአቱ በተጻራሪ ወገን ቆመዋል ጥያቄ ያበዛሉ የተባሉ የመለየት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል ምንጮቹ አክለው::
ተጨማሪ መረጃ (EDIT) : የሃገሪቱን አንጡረ ሃብት ዘርፈው ሃገሪቱን በውጪ ብድር ዪመራሉ ብድሩም ከዘረፋ አልተረፈም:: የሚገርመው እያንዳንዱ የጦር መኮንን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከመዝረፉም ባሻገር ለውጪ ሃይሎች መረጃ በመሸጥ ወያኔንን እርቃኑን አስቀርቶታል የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሰላም አስከባሪ ስም የተባበሩ መንግስታት ድርጅት በሚሊዮቾች ዶላሮች በኢትዮጵያ የጦር አለቆች ተጭበርብሬአለሁ የሚል ስሞታ አሰምቷል::
No comments:
Post a Comment