Wednesday, 14 January 2015

ወያኔ ኢትዮጵያን አፍርሶ ወደ ጉሬው ለመግባት የመጨረሻ መሠናዶውን እያደረገ ነው

  • የትግሬ-ወያኔዎች ከተለያዩ ጎሣዎች እና ነገዶች ሰዎችን መልምለው እና አደራጅተው፣ እንዲሁም የወታደራዊ፣ የደህንነት፣ የአደረጃጀት፣ የአመራር እና የቁጥጥር ሥራ የሚሠሩ የትግሬ-ወያኔዎች መድበው በከፍተኛ ሚሥጢር ኢትዮጵያን የማፈራረስ ሤራ እየተዶለቱ መሆኑን በተጨባጭ መረጃዎች አረጋግጠናል።
የትግሬ-ወያኔ የመጨረሻ ግብ ኢትዮጵያን በመበታተን፣ የትግራይ ረፑብሊክ መመሥረት መሆኑን በ1968 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ፕሮግራሙ መሠረት ላለፉት ፵(አርባ) ዓመታት ያደረገው ጉዞ ያሣያል። በጉዞው የኢትዮጵያን የረጅም ዘመን ታሪክ ክዶ በመቶ ዓመት መገደቡን፣ የትግሬ-ወያኔ መሪዎች እና አባሎች በተደጋጋሚ በጻፉዋቸው መጻሕፍት እና በየአጋጣሚው ባደረጉዋቸው ንግግሮች ለሕዝብ ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል። «ኤርትራ በኢትዮጵያ በቅኝ ግዛትነት የተያዘች ናት፤ ስለሆነም ሻዕቢያ የሚያካሂደው የመገንጠል እና የነፃነት ጥያቄ ተገቢ እና ትክክል ነው።» ብለው፣ ከሻዕቢያ በላይ ሻቢያ ሆነው፣ የትግራይን ልጆች የጦር ማገዶ በማድረግ ኤርትራን ማስገንጠላቸው ማንም ሊያስተባብለው የማይችለው ሃቅ ነው። ኢትዮጵያውያንን እንደ አንድ ሕዝብ ያስተሳሰሩ የወል ዕሴቶችን፥ «የኢትዮጵያዊነት አገራዊ እና ብሔራዊ ስሜት የሁሉም በኢትዮጵያ የሚኖሩ ነገዶች እና ጎሣዎች ሳይሆኑ፣ የዐማራው ብቻ የማንነት መገለጫዎች ናቸው፤ ዐማራው ጨቋኝ እና በዝባዥ ነገድ ነው፤ እርሱን ሁሉም ነገዶች እና ጎሣዎች በወያኔ መሪነት ተባብረው ማጥፋት አለባቸው።» በማለት በከፈቱት የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ጦርነት፣ የኢትዮጵያዊነት የወል ዕሴቶችን፣ ተቋሞችን፣ ግንኙነቶችን፣ አሠራሮችን ወዘተርፈ በማጥፋታቸው ዛሬ አገሪቱ እና ሕዝቧ የሚገኙበት ሁኔታ በግልጽ ያሣያል። የአገሪቱ ዘመን-ጠገብ መልከዐ-ምድራዊ መለያ ስሞች እና ወሰኖች ተሽረው በተወሰኑ ነገዶች ማንነት ብቻ ላይ የተመሠረቱ ስሞች በመስጠት፣ የኢትዮጵያውያንን ተዘዋውሮ በፈለጉት ቦታ እና አካባቢ የመኖር እና የመሥራት ተፈጥሮአዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ሰብአዊ መብቶቻቸውን ገፍፈው፣ አንድነታቸውን አሣጥተው፣ አብሮነታቸውን ክደው፣ በጠላትነት እንዲተያዩ አድርገዋቸዋል። ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ከሕዝቡ ስሜት ፈጽሞ እንዲጠፉ መጠነ ሠፊ የሆነ የሥነልቦና ጦርነት ከፍተው አገሪቱን ከመጨረሻው የጥፋት ጠርዝ ላይ አድርሰዋት ይገኛሉ።
የትግሬ-ወያኔ እና ተከታዮቹ በኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅም፣ እንዲሁም በሕዝቧ ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ታሪክ፣ ትውልድ፣ ሕግ እና ማናቸውም ዓይነት ሥነ-ምግባር ይቅር ሊለው የማይችል የክህደት ተግባሮችን የፈጸሙ መሆኑን ከማንም ይበልጥ ራሣቸውም አይክዱም። ይህም በመሆኑ የኢትዮጵያ አንድነት ተጠብቆ ከዘለቀ በየትኛውም ጊዜ በአገር ክህደት ወንጀል ተጠያቂ እንደሚሆኑ ያውቃሉ። ከዚህ ተጠያቂነት ለመዳን እንችላለን ብለው የሚምኑት ሁለት ነገሮችን ጎን ለጎን ማከናወን ሲችሉ ብቻ  ነው። እነዚህም፦ አንደኛ የወያኔ ትውልድ ለሚቀጥሉት መቶ ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሕይዎት ላይ የወሳኝነቱን ሚና ይዞ የሚቀጥልበት አስተማማኝ ሁኔታ  ሲረጋገጥ፤ ይህ የመጀመሪያው ዕቅድ በተለያዩ ምክንያቶች ባይሣካ ሁለተኛው አማራጭ ዕቅድ ትግራይን ከኢትዮጵያ በመገንጠል የትግራይ ረፑብሊክ በመመሥረት ጎጆ መውጣት፤ የሚሉ ናቸው።
ሁለተኛውን ግብ ለማሣካት በኢትዮጵያ ላይ ሥልጣን ከተቆጣጠሩ ጊዜ ጀምሮ ለምትገነጠለው ትግራይ ቁሣዊ፣ ቴክኒካዊ እና ኅሊናዊ ሁኔታዎች እንዲሟሉ የሚያስችሉ ተግባሮችን ማከናወን እንዳለባቸው ታሣቢ አድርገው መንቀሣቀሣቸው ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው  ትግራይ ውስጥ አያሌ የመሠረተ ልማት ሥራዎች መሥራታቸው ይታወቃል። በዚህም መሠረት የትግራይ ክልል ከጎንደር እና ከወሎ ክፍለ ሀገሮች መሬት ነጥቀው በታሪክ የትግራይ አካል ሆነው የማያውቁ አካባቢዎችን አጠቃልለው ጥንተ-ነዋሪውን የዐማራ ነገድ አባላት የሚገድሉትን በመግደል፣ ቀሪውን በማሠር እና በማሰደድ ትግሬን አስፍረውበታል። ይህ የያዙት ግዛት ወደፊት ለምትገነጠለው ትግራይ ይጠብባል በማለት ከሰቲት ወደ ደቡብ ምዕራባዊ የጎንደር እና የጎጃምን የሱዳን አዋሳኝ ወረዳዎችን ከቤንሻጉል ጉምዝ እና ጋምቤላ ክልሎች ጋር በማገናኘት የታላቋ ትግራይን የመሥፋፋት ዓላማ ዕውን በማድረግ ላይ ይገኛሉ (አባሪ ካርታውን ይመልከቱ)።

Eth

በዚህም መሠረት ለወደፊቷ ትግራይ ለምትጠቀልለው ሠፊ ግዛት፣ ከውጭው ዓለም ጋር የሚያገናኙ የመገናኛ መሥመሮችን ዘርግተዋል፣ ተጨማሪ መሥመሮችንም በፍጥነትም በመገንባት ላይ ይገኛሉ። የትግራይን ምርት ወደ ውጭ ለመላክ እና ከውጭ የሚፈለጉ ሸቀጦችን ወደ ውስጥ ለማስገባት፣ ከጅቡቲ እስከ መቀሌ፣ ከሱዳን ጠረፍ እስከ መቀሌ የሚያገኛኙ የባቡር ሐዲድ ግንባታዎች በመፋጠን ላይ ናቸው። ሁለት ታላላቅ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ጣቢያዎች መቀሌ እና አክሱም ላይ ገንብተዋል። ቀበሌዎችን ከወረዳ ከተሞች፣ ወረዳዎችን ከአውራጃዎች (ዞኖች)፣ አውራጃዎችን ከዋና ከተማዋ ከመቀሌ ጋር የሚያገናኙ፣ ክረምት ከበጋ ያለምንም እንከን አገልግሎት የሚሠጡ መረብ-መሰል አውራ መንገዶች ተገንብተዋል። ድርቅን  ለመቋቋም የክረምት ዝናብን ለማቆር የሚያስችሉ በርካታ ግድቦችን ሠርተው አገልግሎት ላይ አውለዋል። የትግራይን አዲሱን ትውልድ ከኢትዮጵያዊነት ስሜት አውጥቶ የትግራዊነት ስሜት እንዲገነባ የሚያስችሉ፣ በተቀነባበረ ሁኔታ ቅስቀሣ እና ትምህርት በማያቋርጥ መልኩ የሚሰጡ ተቋሞች ተገንብተዋል። በርካታ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች፣ የቴክኒክ እና የሙያ ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርስቲዎች ተከፍተዋል። በኢንዱስትሪ ግንባታ ረገድ የነባሮቹን የኢትዮጵያ ፋብሪካዎች ሕልውና የሚያጠፉ የመድኃኒት፣ የጨርቃጨርቅ፣ የስሚንቶ፣ የመጠጥ እና የብረታ ብረት ፋብሪካዎች በሁሉም የትግራይ አውራጃዎች ተቋቁመዋል። ከእነዚህ መካከል፦ የአዲግራት መድኃኒት ፋብሪካ፣ እንዲሁም መቀሌ የተገነቡት የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ፣ የአልሜዳ የጨርቃጨር ፋብሪካ፤ የመሥፍን ኢንጂነሪንግ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ፣ ወዘተርፈ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው። አሽጎዳ አካባቢ በአፍሪቃ በግዙፍነቱ ቀዳሚ የሆነ እና በነፋስ ኃይል ኤሌክትሪክ የሚያመነጩ ተርባይኖች በብዛት ተገንብተዋል።
የአገሪቱ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መዋቅሮች ያላአንዳች ይሉኝታ በወያኔች የተያዙ ናቸው። የአገሪቱን የአየር እና የምድር ኃይል መከላከያ የማዘዣ ማዕከሎች ከአዲስ አበባ እና ከደብረዘይት በማስወጣት ማዕከላዊ ዕዛቸውን ትግራይ ላይ እንዲሆን በማድረግ ወሣኝ የሆኑት የመከላከያ መሣሪያዎች ትግራይ ውስጥ እንዲከማቹ ተደርጓል። የከባድ ሮኬቶች መተኮሻ መንኮራኩሮች ትግራይ ውስጥ ተገንብተዋል። የአገሪቱ የመከላከያ ኃይል ከጓድ እስከ ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ድረስ ያሉት ቁልፍ የአዛዥነት፣ የመገናኛ፣ የድርጅት፣ የሎጂስቲክ ኃላፊነቶችን በሙሉ በትግሬዎች በማስያዝ የወታደራዊ ተቋሙ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴው የትግራይን መገንጠል ዕውን በሚያደርግ መልኩ ወደፊት እየተባለ ይገኛል።
በአጠቃላይ የትግራይን ግንጠላ ዕውን መሆን ሂደቱ የተመቻቸ እንዲሆን፣ በ«ሽግግር ዘመን» ተብየው «ልማት ቅድሚያ በጦርነት ለተጎዱ ክልሎች» በሚል ስም የአገሪቱ  አጠቃላይ በጀት ለትግራይ ልማት ተመድቦ ለአምስት ዓመታት ከላይ ለተጠቀሱት ተግባሮች እንዲውል መደረጉ ይታወቃል። ከሽግግር መንግሥቱ ፍጻሜ በኋላም የተዘጋጀው «ሕገመንግሥት» ተብየው የሽግግር መንግሥቱ ቻርተር ተከታይ ሆኖ በመዘጋጀቱ፣ አጠቃላይ ያለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ሲሠራ የኖረው ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ሁለት ግቦች ለማሟላት፣ ማለትም፦ የትግሬ-ወያኔ ትውልድ ለመቶ ዓመታት በኢትዮጵያ ሥልጣን ላይ የሚቆይበትን ሁኔታ እያረጋገጡ መጓዝ፣ ይህ የማይሆን ከሆነ ለምትገነጠለው ትግራይ ቁሣዊ፣ ቴክኒካዊ እና ኅሊናዊ መሠረት ሊሆኑ የሚችሉ የሁለንተናዊ ግንባታ ተግባሮችን በተጓዳኝ ማከናወን የሚለው በተደጋጋፊ መልኩ ሲሠራ መቆየቱ ይታወቃል።
ይህ ሁሉ ሤራ ቢጎነጎንም፣ የትግሬ-ወያኔ ባልጠበቀው መልኩ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ከሕዝቡ ኅሊና ውስጥ ከመፋቅ እና ከመደብዘዝ በተቃራኒ፣ የበለጠ እየጠነከረ መሄዱ የአደባባይ ምሥጢር ነው። ለዚህ ማረጋገጫዎች በተከታታይ በሚነሱ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች እና በተቃዋሚ ኃይሎች መበራከት ናቸው። ስለዚህ የትግሬ-ወያኔ ቡድን «ለመቶ ዓመታት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥልጣን ላይ እቆያለሁ» የሚለው ዓላማው ሊሣካ የማይችል እንደሆነ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በ፲፱፻፺፯ (1997) ዓ.ም. ብሔራዊ ምርጫ በማረጋገጡ፣ አጠቃላይ እንቅስቃሴውን «ትግራይን ከቀሪዋ ኢትዮጵያ መገንጠል» በሚለው ሁለተኛ ግቡ ላይ እንዲያተኩር ሁኔታዎች እንዳስገደዱት ይታያል። ለዚህ የግንጠላ ዓላማው ያጸደቀው «ሕገመንግሥት» ተብየው ዋናው መሣሪያው መሆኑ ይታወቃል። አንቀፅ ፴፱(ሰላሣ ዘጠኝ) ለማንም ጥቅም ተብሎ ሣይሆን፣ የትግራይን ግንጠላ ለማሣሳካት የተቀረጸ አንቀፅ እንደሆነ ማንም ይስተዋል አይባልም። ዛሬም ቢሆን የትግሬ-ወያኔ የተመሠረተበትን ዋናውን ስሙን (ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ) ያለመቀየሩ የሚያረጋግጠው ሃቅ ትግራይን ከቀሪዋ ኢትዮጵያ መገነጠል በይደር የቆየ የማይቀር አጀንዳው መሆኑን ነው። ይህ ዕውነት እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ አንቀፅ ብቻ ትግራይን ገንጥሎ በሰላም መኖር እንደማይችል የትግሬ-ወያኔ ጠንቅቆ ያውቃል። የትግሬ-ወያኔ መሪዎች ከተጠያቂነት መዳን የሚችሉት፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን ንብረት መጠቀም የሚችሉት፣ የትግራይ መገንጠል ለጊዜውም ቢሆን ዕውን ሊሆን የሚመችለው፣ በቀሪዋ ኢትዮጵያ ነገዶች መካከል መበታተን ሲፈጠር፣ ከሁሉም በላይ ዐማራ የተሰኘውን ነገድ ሌሎች ነገዶች በጠላትነት ፈርጀው እርሱን ማዳከም ሲችሉ፣ እንዲሁም «ዐማራ» ሲል የከለለውን ክልል ከውጭ አገር ጋር እንዳይገናኝ ዝግ በማድረግ ብቻውን አቁሞ ኅልውናውን ማጥፋት ሲቻል እንደሆነ ብቻ መሆኑን ይህ ቡድን አቅዶ በተግባር ሲንቀሣቀስ ቆይቷል። ለዚህም ባለፉት ዓመታት ሁሉም በሚባልበት ደረጃ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙት ነገዶች ዐማራውን በአውራ ጠላትነት ፈርጀው የጥፋት እጃቸውን እንዲያነሱበት አድርጓል።
የትግሬ-ወያኔ ምዕራባዊውን «የዐማራውን ክልል» ለም እና ድንግል መሬቶች ለሱዳን በገጸበረከት ሰጥቷል። በቀረው ምዕራባዊ ዳርቻ የትግራይን ግዛት በማስፋት ከቦ፣ ከቤንሻጉል ጉምዝ እናከጋምቤላ ክልሎች ጋር አገናኝቷል (አባሪ ካርታውን ይመልከቱ)። ከ5 ሚሊዮን የማያንስ ዐማራ ከምድረ ኢትዮጵያ አጥፍቷል። አያሌ ዐማሮች በአገር ውስጥ ሠርቶ የመኖር መብታቸውን በመገፈፋቸው ለስደት ሕይዎት ተዳርገዋል። በስደት በዓለም ዙሪያ ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ መካከል ከመቶ ፷(ስድሣ) እጁ በላይ ዐማራ መሆኑ የሚያመለክተው፣ ዐማራው በገዛ አገሩ ሠርቶ የመኖር መብቱን የተገፈፈ መሆኑን ብቻ ሣይሆን፣ ዐማራው በመጥፋት ሂደት ላይ መሆኑን የሚያሣይ ነው።
ሰሞኑን ለሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ከደረሱት እጅግ አስተማማኝ መረጃዎች መካከል፣ ወያኔ በኢትዮጵያ ፖለቲካ አናት ላይ የመቆየት ዓላማው የማይሣካ መሆኑን ተገንዝቦ፣ ወደ ሁለተኛው እና የመጨረሻ ግቡ፣ ማለትም፦ ትግራይን ለመገንጠል በከፍተኛ ሚስጢር እየሠራ መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው። ይህም የትግራይ ግንጠላ ዕቅድ ለማሣካት እንዲቻል፣ ከአገር ውስጥ ተቃዋሚ ኃይል እንዳይነሣ፣ ኢትዮጵያን በሽግግር ዘመኑ ከፋፍለዋት በነበረው ፲፬(አሥራ አራት) እና ከዚያም በላይ የሆኑ የክልል ወሰኖችን የሚያመለክቱ ካርታዎችን አዘጋጅተው፣ ከየጎሣው ሰዎችን መልምለውና አደራጅተው፣ ለነዚህ ሰዎች የወታደራዊ፣ የደህንነት፣ የአደረጃጀት፣ የአመራር እና የቁጥጥር ሥራ የሚሠሩ የትግሬ-ወያኔዎች ተመድበው በከፍተኛ ሚሥጢር ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ እየተዶለተ መሆኑን አረጋግጠናል። ይህም ከ1997 የምርጫ ሽንፈታቸው ማግሥት ጀምሮ በመከናወን ላይ ያለ ተግባር እንደሆነ የመረጃ ምንጮቻን ገልፀውልናል። «ይህ አይሆንም፣ አይደረግም፣ አይታሰብም» ሊባል የማይችል እንደሆነ የወያኔ ጉዞ እና ተግባር ከጥርጣሬ ውጭ በሆነ መንገድ ያስረዳናል። ለዚህ ሤራቸው ማረጋገጫዎቹ በነባር ኢትዮጵያዊ እምነቶች መካከል እየሰራ ያለው የማጥፋት ሥራ፤ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባ፣ በሶማሌ፣ እየተካሄዱ ያሉት የጥፋት እርምጃዎች የዚህ ዕቅድ አካሎች መሆናቸውን ልብ ሊባል ይገባዋል።
ሌላው የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ተልዕኮው የማይቀር እና የፍጻሜው የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረሱን ማሣያው፣ የምዕራቡ ዓለም የመረጃ እና የስትራቴጂክ ጥናቶች ተቋም ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት አጋማሽ ላይ በ2030 እ.አ.አ. ከዓለም ካርታ ላይ ከሚጠፉ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ይፋ ማድረጉን እናስታውሳለን። በተመሣሣይ ሁኔታ በኅዳር ወር ፪ሺህ፯ ዓ.ም. ሞስኮ ውስጥ የተካሄደ የዓለም አቀፍ ቀውሶች ጥናት ተቋም ባዘጋጀው ስብሰባ፣ በምሥራቅ አፍሪካ የሚታየውን ብጥብጥ ለዘለቄታው ለማስወገድ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ኮንፌደሬሽን መመሥረት እንዳለበት ግፊት የሚያደርግ ጥናት ቀርቧል። የኮንፈደሬስሽኑ አባል አገሮች ጥንት እንግሊዝ «ከኢትትዮጵያ ተቆርሶ ወደ ሱዳን ይካተት» ትለው የነበረው የኤርትራ ምዕራባዊ ክፍል ወደ ሱዳን ተካልሎ ሱዳን ከሦስት እንድትከፈል፣ የኤርትራ ደጋማው ክፍል ከትግራይ ጋር ተቀላቅሎ ትግራይ ትግርኝ የተሰኘ ግዛት እንዲፈጠር፣ የአፋርኛ ተናጋሪዎች በአንድ ግዛት ተጠቃለው አንድ ግዛት እንዲሆኑ፣ በአምስቱ ዓመት የአርበኛነት ዘመን ፋሽስት ጣሊያን «ዐማራ» ብሎ ሰይሞት የነበረው ክልል አንድ የዐማራ ግዛት እንዲሆን፣ የቀሩት አካባቢዎች የፋሽስት ጣሊያንን ክፍፍል መሠረት አድርገው የየራሳቸውን ግዛቶች እንዲመሠረቱ እና በነዚህ አገሮች መካከል ኮንፌደሬሽን ይመሥረት የሚል ነው። የእነዚህ ጥናቶች ግብም ከወዲሁ ኢትዮጵያዊው የኢትዮጵያን መፍረስ አይቀሬነት እንዲለማመደውና «ድሮም ተብሎ ነበር» በማለት የአገሩን መፍረስ በፀጋ እንዲቀበል የሥነ- ልቦና ሰለባ ከወዲሁ መሠራቱን የሚያመለክቱ ናቸው።

ካርታ፦ ለወደፊቱ «የትግራይ ሪፑብሊክ» ተብሎ በትግሬ-ወያኔ የሚገነጠለው የኢትዮጵያ አካል በአረንጓዴ ቀለም የተቀለመው ነው።
 
የትግሬ-ወያኔ እና ዕኩይ ዓላማው ኅልው ሆነው የሚዘልቁት ኢትዮጵያውያን ሠፊውን ለቀን ጠባቡን፣ ኢትዮጵያዊነትን ትተን ጎሣዊ ማንነትን ስንላበስ፣ ዕውነትን ከድተን ከውሸት ጎራ ስንሰለፍ፣ ዘላቂውን ትተን አላቂውን እና ጠፊውን ስንይዝ፣ አኩሪውን ትተን  ነገ የሚያሳፍረውን ስንከተል፣ ለኅሊና ሳይሆን ለጥቅም ስንገዛ ነው። እስካሁን የትግሬ-ወያኔ ያለ ልጓም የጋለበን በነዚህ ምክንያቶች ብቻ ነው። አሁን ግን የትግሬ-ወያኔ አጥፍቶን ሊጠፋ ከመጨረሻው ጠርዝ ላይ ቆሟል። የመጥፋቱም ያለመጥፋቱም ጉዳይ የሚወሰነው በእኛ ብቸኛ ምርጫ ነው። ምርጫችን በኢትዮጵያዊነታችን መቀጠል ከሆነ፣ ወያኔ ያጠመደልንን የመነጣጠል መንገድ ትተን በአንድነት በመቆም ኢትዮጵያን ከመጥፋት ለመታደግ ቁርጠኛ አቋም ልንይዝ ይገባል። ቢመሽም፣ እጅግ ብንዘገይም፣ ፈጽሞ ከመቅረት ይሻላል እና እጅ ለጅ ተያይዘን አገራችን እንድናድን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።
ከሁሉም በላይ የትግሬ-ወያኔ ወደ መጨረሻ እርምጃው ሲያመራ አጥፍቶ የሚጓዘው፣ ከጽንሱ ጀምሮ በአውራ ጠላትነት ፈርጆ ላለፉት ፵(አርባ) ዓመታት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲገድለው፣ ሲያስረው፣ ሲያሰቃየው እና ሲያሳድደው የኖረውን ዐማራ እስትንፋስ ሳያቋርቋጥ ከጉሬው እንደማይገባ አውቀን፣ ከተደገሰልን ጥፋት እራሳችን መከላከል እንድንችል ከምንጊዜውም በላይ ነቅተንና ተደራጅተን ኅልውናችን ለማስጠበቅ ቁርጠኛ ሆነን እንድንቆም ሞረሽ-ወገኔ አደራ ይላል።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ በጀግና እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራ እና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

No comments:

Post a Comment