Monday, 17 November 2014

ሾልኮ የወጣው ደብዳቤ እና የአቤ መረጃውን በስልክ የማጣራት ሙከራ

Health official orders the burning of Ebola patients in western Ethiopia, secret letter reveals


===================================================================

ከአቤ ቶክቻው *Abe Tokichaw facebook ገፅ ላይ የተወሰደውን  ደግሞ ከስር አንብቡት 

===============================================17 11 2014


በስንት መከራ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ጤና ቢሮ ደውዬ ስለ ኢቦላው ጉዳይ ለማጣራት ባደረኩት ሙከራ...

አወዛጋቢው ደብዳቤ ስር የፈረሙ አቶ አለሙ ጅራታ በበዙ ስቃይ አገኝቼ አነጋግሬያቸዋለሁ። አቶ አለሙ በመጀመሪያ ላረጋግጥልህ የምፈልገው ነገር.... ብለው የነገሩኝ፤ በክልሉ ቤኒሻንጉል ጉምዝም ሆነ በአሶሳ ኢቦላ አለመከሰቱን ነው።
ታድያ እንዲህ ያለ ደብዳቤ ከየት መጣ... ብዬ የጠየኳቸው አቶ አየለ ጅራታ ደብዳቤውን እርሳቸውም እንዳዩት እና ምንጩ ከየት እንደሆነ ለማወቅ አለመቻላቸውን አስረድተውኛል። እርሳቸው እንደሚሉት በተሰራጨው ደብዳቤ ላይ ግልባጭ የተጻፈላቸው አቶ አማኑኤል በረደድ ከዚህ በፊት ''ክሊራንስ'' ጠይቀው የነበረ ሲሆን ከክሊራንሱ ጉዳይ ጋር በተያያዘም ደብዳቤ ተጽፎ ግልባጭ ተድርጎላቸው እንደነበር ጠቁመውኛል። በተሰራጨው ደብዳቤ ላይ የሚገኘው ማህተም አቀማመጥ ከክሊራንሱ ደብዳቤ ጋር እንደሚመሳሰል፤ ነገር ግን የተጻፈው ቀን እና የደብዳቤ ቁጥሩ ከክሊራንሱ ደብዳቤ ጋር እንደማይመሳሰል ነገረውኛል።

(እንግዲህ የዚህን ሰው ደብዳቤ ማን ለዚህ አላማ ተጠቀመው ወይስ አቶ አየለ እየዋሹኝ ነው የሚለውን የሚያወቅ አንድ ሰው እና አንድ ፈጣሪ ይኖራሉ...) እነርሱ ሌላ ማብራሪያ እስኪሰጡን ድረስ ግን... በአሶሳም በቤኒሻንጉል ጉምዝም ኢቦላ ገብቷል የሚለውን የሚያረጋግጥ ነገር ስላላገኘን ሰላም ነው የሚለውን በማስታወሻችን ይዘን እንቆያለን!

አቶ አየለ ጅራታ እከሌ ነኝ ሳልላቸው ከጨነቀው ምን ጨነቀኝ ብለው በቅጡ ስላናገሩኝ አመሰግናለሁ።

''ሽልም ከሆነ ይገፋል ቦርጭም ከሆነ ይጠፋል'' እኒዲሉ፤ ወደፊት ደግሞ እወነቱ እየጠራ እንደሚመጣ ተስፋ እናደርጋለን!

/////////////

በነገራችን ላይ ሀገራችን ውስጥ አንዳች ነገር ሲሰማ ቶሎ ብለን ለወዳጆች እንዲደርስ የምናደርገው ስለሚያገባን ነው። እንጂ፤ ኢህአዴግን ስለምንጠላ የሚመስላችሁ ወዳጆች ያገናችሁት ኤክስ.... በጣም ግድንድግድ ነው። እና እንደምንም አጥንታችሁ ድጋሚ ለመፈተን መሞከር አለባችሁ!
በበኩሌ ኢህአዴግዬ ራሷ ትጠላኝ እንደሁ እንጃ እንጂ እኔ የተለየ ጥላቻ የለኝም። ህመምተኛ ናት ትታከም። ሞቅታ ውስጥ ናት አልኮል ትቀንስ... ማለት ለራሷ ጤና በማሰብ ነው። እንጂ ከጥላቻ የሚመነጭ አይደለም።

እና በተረፈ እንዴት ናችሁ...

በያላችሁበት ይመቻችሁ!

No comments:

Post a Comment