Monday, 24 November 2014

በሰሜን የአገሪቱ ክፍል ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየታከሄደ ነው

ኀዳር ፲፭(አስራ አምስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ መንግስት ከማሃል አገር ሰፍረው የቆዩትን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ሁመራና ሌሎች የድንበር አካባቢዎች በስፋት እያሰማራ መሆኑን ወታደራዊ ምንጮች ገለጹ።

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከኤርትራ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየታየ መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ ምክንያቱ ደግሞ ኢህአዴግን በሃይል አስገድደው ለማውረድ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ የሚለው ስጋት እያየለ በመምጣቱ ሳይሆን እንደማይቀር ይገምታሉ። በአካባቢው ያለው የጸጥታ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆ መሄድ ገዢውን ፓርቲ እንዳሳሰበው የሚናገሩት ምንጮች፣ በተለይም በጠረፍ አካባቢ የሚኖረው ወጣት የተቃዋሚ ሃይሎችን ድንበር እያቋረጠ በስፋት እየተቀላቀለ መሆኑ፣ ሃይሉን እንዲያጠናክርና በድንበሩ አካባቢ ከፍተኛ ቁጥጥር ለማድረግ ሳያሰነሳሳው እንዳልቀረ ይናገራሉ።
መንግስት የተወሰነ ጦሩን ወደ ሱዳን በማስገባት የተቃዋሚ ሃይሎችን እንቅስቃሴ ለመግታት ከሱዳን ጋር ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment