ለወገን ደራሽ ወገን ነው ᎓᎓ ጦማሪያን ጋዘጠኞች ፖለቲከኛው ገበሬው መምህራኑ ሰራተኟውና ተማሪው በአጠቃላይ ከህፃናት እስከ ሽማግሌው ለኢትዮጵያ ለሃገራችን የወደፊት ተስፋ ይሆናሉ የተባሉትን በሙሉ በጅምላ ታፍነው ወደ እስር ቤት ሲጣሉና ሲበደሉ መከራ ሲደርስባቸው እና ሲገደሉ እያየንና እየሰማን ዝም ብሎ መኖሩ በጣም ከባድ የህሊና ህመም ነው᎓᎓ መቼም ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ አይነት የከፋ ስርዓት ይመጣልና ይኖራል ብሎ ያሰበ ብዙም ባይኖር የስርዓቱን ስር መሰረት ድብቅ አላማን የተረዱት ኢትዮጵያውያን በተለያየ መንገድ ሲገደሉና ታስረው ሲሰቃዩ የተረፉትም ሃገር ጥው ሲሰደዱ ይህው ሃያ ሶስት ዓመት ሞላን᎓᎓ በጣም ረጅም ዓመት ᎓᎓
በጥቂቶች መጥፎና ሸር በተሞላ አመለካከት እንዲሁም በጥቂቶች በግለሰብዓዊ ጥቅም በመለከፍና የህዝብንና የሃገር ህልውና ትርጉሙ በቅጡ ባልገባቸውና ባልተረዱ አምባገነንነትን እና አፓርታይድ መርህ አድርገው በሚጓዙ ሰዎች ይህን ያህል በደልና መከራ በህብረተሰቡ ላይ ሲፈፅሙ ዝም ብሎ ማየቱ በራሳችን ላይ አዚም እንደተደረገብን ወይም በፍላጎታችን ወይም ተገደን በወገባችን ላይ ከአቅማችን በላይ የሆነ ድንጋይ ተሸክሞ አንድ ባህር በዋና እንደማቋረጥ ነው የሚሰማኝ᎓᎓ ታዲያ ለዚህ መፍትሄው አዚምንም አዚም በሚያስወጣው ማስወጣት ድንጋዮንም ገፈትሮ ጥሎ በነፃነት ሆኖ የገባንበትን ባህር ቶሎ ዋኝቶ መውጣት የገባንበት አዚምና ባህር ውጦን ህዝባችንንና ሃገራችንን ሳያጠፋ ᎓᎓
በጣሙን የሚያሳዝነኝና ቅስሜን የሚነካው በዚህ በአለንበት በ 21 ኟው ክፍለ ዘመን ላይ ጭቆናና በደል እስራትና አፈና ሞትና ስደት እየደረሰበት ያለው የህብረተሰብ ክፍል ኢትዮጵያ ውስጥ ራሱን ዋሽቶና ሰብዓዊ ክብሩን ለግዚያዊ ጥቅም ሳይሸጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ባህሉንና እምነቱን ማንነቱንና ሰብዓዊ መብቱ ነፃነት እኩልነት ፍትህ እንዲሁም የህግ የበላይነት እንዲሰፍን በሚጥሩ መልካም ኢትዮጵያኖች ላይ መሆኑ ነው ᎓᎓
በራስህ ላይ እንዲደረግ ማትፈልገውን በሌላው ኢትዮጵያውያን ላይ ሲደረግ ዝም ብሎ ማየት ከባድ የህሊና ሸክም ነው ᎓᎓ ታዲያ በብሩስልስ ቤልጄም ከተለያየ የአውሮፓ ሃገራት ተሰባሰበው በተወለዱበትና ባደጉበት ሃገር ያጡትን ሰብዓዊ መብታቸው ተከብሮላቸው በህብረት በአንድ ላይ ሆነው ድምፁ ለታፈነው ወገኑ ድምፅ ሲሆንለት ልብን የሚነካና ለራሳችን ጥያቄ አቅርበን እኔስ በየትኟው መንገድ*(መስመር) ከወገኔ ጎን ልሰለፍ ብሎ ራስን የሚመረምሩበት አፋጣኝ ወቅት ላይ እንደደረስን እንረዳለን ᎓᎓ ህብረታችን የወያኔ ኢህዲግን አምባገነናዊ ስርዓት ያርበደብዳል ብሎም ህብረታችን የተሻለች ኢትዮጵያን በተፋጠነና በተመቻቸ መንገድ ህልውናዋን አስከብሮ ለሁላችንም በጥሩ ሁኔታ የምንኖርባት ሃገር እንድትሆን ያደረጋል ᎓᎓ ስለዚህ እያየንና እየሰማን ዝም አንበል᎓᎓ ትግሉ ለሁላችንም ነው ᎓᎓

No comments:
Post a Comment