(አዲስ ቮይስ)የአሜሪካን ድምጽ ዳይሬክተር ዴቪድ አንሶር የአፍሪካ ቀንድ የበላይ ሃላፊ የነበረው ፒተር ሃይንላይን ከሃላፊነቱ መነሳቱን አሳወቁ። ዳይሬክተሩ ባለፈው አርብ የክፍሉን ሰራተኞች በድንገት ሰብስብስበው እንዳስታወቁት ሃይንላይን ከሃላፊነቱ ተነስቶ በምትኩ የርሳቸው ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ዊሊያም ማርሽ በግዚያዊነት መሾማቸውን ገልጸዋል።
በቅርቡ በአሱዛ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ተሰጥቶ የነበረ ክብር መሰረዙ ጋር በተያየዘ ከሄኖክ ሰማእግዜር ጋር በመተባበር የተዛባ ዘጋባ አቅርቧል የሚል ክስ ቀርቦበት የነበረው ፒተር ሃይንላይን የአስተዳደር በደል አቤቱታም በተጨማሪ በስሩ ያስተዳድራቸው ከነበሩ ሰራተኞች ቀርቦበት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
የአሜሪካ ድምጽ የበላይ ሃላፊዎች በሃይንላይን ላይ የቀረቡትን አቤቱታዎች መመርመራቸውንና ከፍተኛ የአሰራር ጉድለቶች እንደነበር ማረጋገጣቸው ታውቋል። በጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላው አቤቱታ የቀረበበትን ዘገባ በተመለከተ የአሜሪካን ድምጽ የበላይ አስተዳደር (Board of Broadcasting Governors) ጉዳዩን በጥልቀት መርምሮ ዘገባው ያለተሟላና ከአሜሪካ ድምጽ ደረጃ በታች የወረደ ነበር ሲል መግለጹ ይታወሳል።
ይሁንና የአሜሪካን ድምጽ የአማርኛ ክፍል ግዜውን በጠበቀ መልኩ አግባብ ያለው እርምትና ማስተካከየ ሳያደርግ መቅረቱና ስህትቱን ከማረም ይልቅ መሸፋፈን በመምረጡ ተጨማሪ አቤቱታ ለቪኦኤ የበላይ ሃላፊዎች ቀርቦ እንደነበር አበበ ገላው ገልጿል።
አበበ በተለይ ፒተር ሃይንላይን እንደ ባለስልጣን ሃላፊነት በተሞላበት መልኩ ማስተካከያ ከማድረግ ይልቅ አደናጋሪና የተዛቡ ዘገባዎችን በተደጋጋሚ እንዲቀርቡ ማድረጉ ለእርምጃው መወሰድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው የውስጥ አዋቂዎችን በመጥቀስ አስረድቷል።
አዲሱ የአፍሪካ ቀንድ ሃላፊ ሆነው የተሾሙት ማርሽ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሃላፊነት ለሶስት አመታት ማገልገላቸው የታወቀ ሲሆን በሰራተኞች የተከበሩና ለሙያቸው ትልቅ ከበሬታ ያላቸው መሆኑን ለማወቅ ተችላሏል። ፒተር ሃይንላይን ከሃልፊነት ቦታው ወርዶ ያልምንም አስተዳደራዊ ሃላፊንት ወደ አፍሪካ ክፍል መዛወሩ ለመረዳት ተችሏል።

No comments:
Post a Comment