Thursday, 20 November 2014

በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች የዋስትና መብታቸውን ተከለከሉ

ኀዳር ፲፩(አስራ አንድቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የአንድነት ፓርቲዎቹ ሃብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲው የሽዋስ አሰፋ፣ የአረና ፓርቲው መምህር አብረሃ ደስታ እና ሌሎች 6 የመብት ተሟጋቾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ በፍርድ ቤት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።

በአቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ መዝገብ የተከሰሱት አስሩ ፖለቲከኞችና የመብት ተሟጋቾች፣ ህገመንግስቱን ጠቅሰው የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም።
ሁሉም እስረኞች በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው ይታወቃል። አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ክሱ ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ ነው በማለት ውድቅ ያደርጉታል። ፍርድ ቤት ለህዳር 17 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠጡም ታውቋል፤፡
በሌላ ዜና ደግሞ በትግራይ የታሰሩት ወጣት ሽሻይ አዘናው እና አማረ ተወልደ እስካሁን የታሰሩበት ቦታ አለመታወቁን አቶ አስገደ ገብረስላሴ ገልጸዋል።
ግለሰቦቹ በህወሃት የደህንነት ሃይሎች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ የት እንደገቡ ባለመታወቁ፣ ከክልሉ ፕሬዚዳንት ጀምሮ ላሉ ባለስልጣናት አቤት ቢባልም መልስ የሚሰጥ መጥፋቱን አቶ አስገደ ገልጸዋል።
ኢህአዴግ ባለፈው ወር በተለያዩ ክልሎች ባደረገው አፈና በርካታ የዞንና የወረዳ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እየተያዙ ታስረዋል።በቅርቡ ከታሰሩት መካከል ዘነበ ሲሳይ፣ ጥላሁን አበበ፣ አግባው ሰጠኝ፣ ዘሪሁን ብሬ፣ ታስፋየ ታሪኩ፣ አንጋው ተገኝ፣ አባይ ዘውዱ ይገኙበታል።

No comments:

Post a Comment