Tuesday, 4 November 2014

የእስር ዜና...!




አቶ አግባው ሰጠኝ በህወሓት አገዛዝ መራሹ ቡድን ለእስራት ተዳረጉ !
=======================================

የቀድሞ የቅንጅት አባል እና የፓርላማ ተመራጭ የነበሩ፤እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ መስራች እና የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ፣የሰሜን ጎንደር የዞን አስተባባሪ ዋና ሰብሰቢ አቶ አግባወ ሰጠኝ ታሰሩ፡፡ዛሬ ከቀጥር በኋላ 10፡00 ሰዓት አካባቢ ሲንቀሳቀሱበት ከነበረው ቦታ፣ በሁለት ፒካፕ መኪና የተጫኑ የጦር መሣሪያ በታጠቁ የፊዴራል ፖሊሶች ከበባ በመፈፀም የያዦቸው ሲሆን፡፡ወደመኖሪያ ቤታቸው በመውሰድ ከ 1 ሰዓት ተኩል በላይ ፍተሻ እና ብርበራ በማካሄድ ስፍራው ወደልታወቅ ቦታ ይዣቸው እንዴዱ ለማወቅ ተችሎአል፡፡
ፍተሻ እና ብርበራ ፖሊሶች ሲያካሂዱ ከፍርድ ቤት ትህዛዝ የያዙ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን፣በማዘዣው ላይ “በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ በመሆናቸው አስፈላጊውን ፍተሻ ማካሄድ እንዲችሉ” የሚል በፍረድ ቤት ትዕዛዙ ላይ ተገልፆ እንደሚገኝ በቅርበት ጉዳዩን ሲከታተል የነበረ የቅርብ ጓደኛው ገልፀዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ መረጃው ከደረስ ሰዓት ጀምሮ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነና ለማወቅ ተችሎአል፡፡

የዓረና ሁለት ኣመራሮች በሑመራ ታሰሩ።
========================

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሑመራ ወረዳ ዳንሻ ከተማ ኣቶ ዘነበ ሲሳይ የዓረና ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባል ዛሬ ማከሰኞ 25 / 02 / 2007 ዓ/ም ከቀኑ 7 ሰዓት ፖሊሶቸ ፖሊሰ ጣበያ ተፈለጋለህ በለው ከመኖርያ ቤቱ ዳንሻ ከተማ ወሰደው ኣሰረውታል።

በሌላ ዜና ኣቶ ኣማረ ተወልደ የዓረና ቁጥጥር ኮሚቴ በሑመራ ከተማ ዛሬ ማከሰኖ 25 / 02 / 2007 ዓ/ም ከቀኑ 10 ሰዓት በፖሊሰ ታስሬዋለ። ኣቶ ኣማረ ተወልደ ከሳምንት በፊትም ታሰረው በ3000ብር ዋሰ ተለቀው ነበር።
ከትናንት በስተያም በማይካድራ ከተማ የዓረና ስራ ኣስፈፃሚ ኣባሉ ኣቶ መሰለ ገብረ ሚካኤል ታስረው እንደነበሩ የሚታወስ ነው።
የህወሓት መንግስት የዓረና ኣባላተ በየቀኑ ማሰር፣ ማነገላታትና መደንደብ እቅድ ኣወጥቶ የጥላቶች ክትትል ቡድን በማደራጀት እየፈፀመው ይገኛል።
ኣብራሃ ደስታ፣ ኣያሌው በየነ፣ ኣድሃና ንጉሰ፣ ገብረዋህድ ሮምሃ በጠላትነት ፈርጆ በእስር እያማቀቃቸው ይገኛል። ኣብራሃ ደስታ ነገ እሮብ 26 /02 / 2007 ዓ/ም በልደታ ፍርድ ቤት ይቀርባል።የሸገር ኑዋሪዎቸ በልደታ ፍርድ ቤት ተገኝታቹ እንደተለመደው ደጋፋቹ እንድትለግሱላቸው እንላለን።
በነገራችን ላይ እነ ኣብራሃ ደስታ ከማእከላዊ እስር ቤት ወደ ቂሊንጦ ተዘዋውረዋል። ማንኛውም ዜጋ እነ ኣብራሃ ደስታ ቂሊንጦ በመሄድ መጠየቅ ይችላል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው....!
IT IS SO..!

No comments:

Post a Comment