Tuesday, 9 December 2014

ኢሕአዴግ የማይሸነፍበት ምክንያት ምንም የለም

አቶ በላይ ፈቀደ የአንድነት ሊቀመንበር


አቶ በላይ ፍቅደ የአንድነት ሊቀመነበር አዉስትራሊያ ከሚገኘው የ ኤስ.ቢ.ሲ ራዲዮ ጋር ቃለ መጠይቅ አደርገዋል። በቃለ መጠይቁ ስለመጪው ምርጫና ከሌሎች ድርጅቶ ጋር አብሮ ስለምሰራት አቶ በላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከቃለ መጥይቁ የተወሰኑት እንሆ፡
Belay Fekadu (3)
አቶ በላይ ፍቃደ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመነበር
ኤስ.ቢኤስ 
የአንድነት ፓርቲ ዉስጥ እንደዚሁ በምርጫ መሳተፍ የለብንም የሚል ሐሳቦችም እንደሚንሸራሸሩ ይታወቃል። ፓርቲው በርግጠኝነት በ2007 ምርጫ ፤አይ ገብቶ በሰላማዊ ትግል ስልቱ እንደመሆኑ መጠን፣ ያንን ታግሎ የተወሰኑ ወንበሮችን ማግኘት ሲልም የስርዓት ለዉጥ አድርጎ ፣ በአብላጫ ድምጽ መንግስታዊ የፖለቲካ ስልጣንን ከመያዝ እችላለሁ ይላል ወይ ? ለዚያም ቅርጦ ተነስቷል ማለት ይቻላል ? በአሁኑ ወቅት በምን ሁኔታ አይ ነው የሚገኝው አንድነት ?
አቶ በላይ ፍቃደ 
አመሰግናለሁ። መጀመሪያ አንድነት ዉስጥ እኔ እስከማወቀው ድረስ ምርጫ መሳተፍ የለብንም የሚል አቋም አይቼ አላውቅም፣ ሠምቼም አላውቅም። በብሄራዊ ምክር ቤትም ደረጃ ይሁን በፓርቲው ሥራ አስፈጻምዊ ደረጃ ። ዋናው ክርክር ሁለት ነው። “እንደ ስልት ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠን፣ ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሟሉ ምርጫ አንገባም” የሚል አንድ የምርጫ ስትራቴጂ ያስፍልጋል የሚል አስተሳሰብ ሊኖር ይችላል። ሌላኛው “ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጥ ይሄን አገዛዝ ወደ ድርድር ማምጣት ፣ ካለው የጊዜ እጥረት አንጻር ፣ ከፍተኛ የፐብሊክ ሞቢላይዜሽን ከማድረግ አንጻር፣ በቂ ጊዜ ስለሌለ፣ አዋጪ ሊሆን ስለማይችል፣ ምርጫ ዉስጥ ገብተን፣ የተዘጋዉን የፖለቲካ ምህዳር ማስከፈት አለብን” የሚል ሌላኛው ክርክር ነው።
በኛ እምነት ሁለተኛው ክርክር የተሻለ ሚዛን ያነሳል የሚል እምነት አለን። አንድነት እንደ ፓርቲ እየተከተለ ያለው ስልት ፖለቲካ ምህዳሩን በአግባቡ ፈትሸነዋል። አይተነዋል። የተዘጉ መንገዶች ብዙ ናቸው። እነዚህን ለማስከፈት ትክክለኛው ስልት ምርጫው ዉስጥ መግባት ነው የሚል የጋራ ግንዛቤ አለን። እዚህ ላይ ተመሳሳይ አቋም ነው ያለን።
ሌላኛው የአንድነት የምርጫ ግብ ምንድን ነው የሚል ነው። በኛ እይታ ተቃዋሚው ተሰብስቦ በአንድ ሃይል ምርጫ ዉስጥ ከተሳተፈ፣ ኢሕአዴግ የማይሸነፍበት ምንም አይነት ምክንያት አይኖርም ብለን አናምንም። 2002 እና 2007 እጅግ በጣም የተለያዩ አመታት ናቸው የሚል እምነት ነው ያለን። በ2002 የነበረ የሕብረተሰቡ ፍርሃት ደረጃ ፣ የኢንተርርናሽናል፣ የአለም አቀፍ ኮሚኒቲው አቋም፣ የፓርቲዎች ሁኔታ፣ አሁን ካለው ሁኔታ ጋር ስናነጻጽር፣ እጅግ በጣም የተሻለ ነው የሚል እምነት አለን። ይብዛም ይነስም፣ የተወሰኑ በአሥር ሺሆች የሚቆጠር የሕብረ ተሰብ ክፍልን ማስንቀሳቀስ የተቻለበት ሁኔታ ነው ያለው።ባለፈው ሁለት ሶስት አመት እንደታየው። የህብረተሰቡ የፍርሃት ሁኔተ እየተሰበረ ለለዉጥ ያለው ፍላጎት ይበልጥ እያደገ የመጣበት ሁኔታ እንዳለ በግልጽ ግምገማ መረዳት ችለናል።
አሁን ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለው ችግር የለወጥ ፍላጎት ችግር አይደለም። የለወጥ ፍላጎት ከአንድ ገጠር ጀምረህ እዚህ አዲስ አበባ መሃል እስካለንበት ድረስ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው። አንድም ኢሕአዴግ ሊሄድበት ያለው መስመር ኢትዮጵያ የተሻለ ሊያደርግ እንደማይችል፣ ግንዛቤ ዉስጥ የወስዱ ሰዎች አሉ። ሁለተኛ ይሄ አይነት አፋኝ መንግስት ለኢትዮጵያ አይገባም የሚል አስተሳሰብ በስፋት ይንጸባርቃል።
ትልቁ ችግር ያለው የመደራጀት ጉዳይ ነው። ለማደራጀት ችግር ነው። የፖለቲካ ምህዳር ተዘግቷል ። ስለዚህ ክፍተቶች ሲመጡ እነዚህ ክፍተቶች ተጠቅሞ ሕብረተስቡን በስፋት ማደራጀት ያስፈልጋል። ተቃዋሚ በአንድ ቦታ ላይ ተደራርቦ መቅረብ የለበትም የሚል እምነት አለን። ያንን ኬሚስትሪ መፍጠር ከቻልን ኢሕአዴግ የማይሸነፍበት ምክንያት ምንም የለም። ይሄ ሊሆን የሚችለው ግን ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ኃይለ ማደራጀት ስንችል ነው የሚል እመነት አለን። የአንድነት ትልቁ ግብ ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ ኃይል ማደራጀት ፣ ድምጹን ማስከብበር፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ መምጣት ያለበትን የፖለቲካ ሪፎርም በተደራጀ ሁኔታ መጠየቅ መቻል ሲቻል ነው። አንድነት የትግል አቅጣጫው ይሄ ነው።ስለዚህ ይሄን ማድረግ ከቻልን በ2007 ትልቅ የዲሞክራሲ ለውጥ የምናመጣበት አመት ይሆናል ብለን ቀን ከሌሊት በአንድነት ደረጃ እየተረባረብን ነው።
ኤስ.ቢኤስ 
አሁን እንዳነሱት በተለይም ሁልጊዜ ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት ሲነገረን የነበሩ ጉዳዮች አሁን እየተነገሩ ያሉት፣ ተቃዋሚዎች ይተባበሩ ወይም ይሰባበሩ የሚል፣ የአንድነትና የሕብረት ጥሪ፣ በዉጭም ሆነ በአገር ዉስጥ ላሉ ፓርቲዎች ይቀርባል እንደሚያወቁት መኢአድ ቀዉስ ዉስጥ ይገኛል። የሰማያዊ ፓርቲ ሌሎች ዘጠኝ ትናንሽ ፓርቲዎች አሰባስቦ አንድ ላይ ቆሟል። አንድነት በዚህ በኩል አለ። ሌሎችም ተቃዋሚዎች ድርጅቶች እንደዚሁ በሌላ መስክ አሉ። የመድረክ አባላት የሆኑ ..ይሄንን በዚህ በአጭር ጊዜ ዉስጥ አሰባስቦ ለ24 አመታት ያለን ችግር በሚቀጥሉት ስድስት ወራት አንድ ላያ አድርጎ በጋራ ተደራጅቶ የመንቀሳቀስ ሁኔታዎች እዉን ሊሆኑ ይችላሉ የሚል እምነት አለ? ያ ካልሆነ በተቃዋሚዎች ዘንድ ያለፉት 24 አመታት አንድ ላይ ቆሞ በአንድ ድምጽ፡መናገር ያልተቻሉባቸው ዋነኛ ምክንያቶች ምንድን ናቸው ? ይላሉ።
አቶ በላይ ፍቃደ
ትልቅ ጥያቄ ነው ፣አስቸጋሪ ጥያቄ ነው የጠይከኝ። በተቃዋሚው ጎራ የሚታየው አብሮ ተናቦ ያለመስራት ችግር ለዉጥ እንዳይመጣ እንደ አንድ እንቅፋት እንደሆነ ነው የምናየው።ይሄ ለምን አልመጣም ብንል ብዙ ሊያከራክርን ሊያወያይ ይችላል።
በአንድነት እይታ፣ ዉህደት በጣም ጥቃሚ ነው ከሚል ግንዛቤ፣ ላለፉት ሶስት አራት አመታት፣ ከመኢአድ ጋር ዉህደት ለመፍጠር ትልቅ እንቅስቃሴ አድርገናል። አብረን ተዋህደን ተጠናክረን መውጣት አለብን ብለን መዋህድ አለብን በሚል ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያደረግንበት ሁኔታ አለ።የመኢአዱ መስመር ይዞ፣ ያለመታድል ሆኖ፣ በምርጫ ቦርድ በኩል በመጣ እንቅፋት የመኢአድ እና የአንድነት ዉህደት ሳይሳክካ ቀርቷል። ይሄ ማለት ግን አብሮ መሰባሰብ ፣ በአንድ ወቅት ዉደቅት ስለመጣ፣ ይቆማል ማለት አይደለም። ቅንጅት አብሮ ተቀናጅቶ በመምጣቱ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ዉስጥ እጅግ የሚገርም የሆነ የሕዝብ መነሳሳትና መነቃቃት ያመጣ ፓርቲ ነው። እግርጥ ነው በወቅቱ የነበረውን ቅንጅት በብስለት ወደፊት ማራመድ ባለመቻሉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ትልቅ የሆነ ጠባሳ ጥሎ አልፈል። ያ ማለት ግን መተባበር አይጠቅምም ማለት አይደለም። መማር ያለብን ትምህርት ተምረን፣ መተባበር፣ መዋሃድ አስፈላጊ ነው። ተከትሎ የሚመጡ ችግሮችን ግን፣ በጥሞና ትምህርት ወስዶ መፍታት ያስፈልጋል የሚል ትክክለኛ ግንዛቤና መስመር ነው የሚል እምነት አለን።
ስለዚህ አንደኛ በተለይም አንድነት፣ ሰማያዊና መኢአድ በምንም አይነት ሁኔት በተናጥል መሄድ አለባቸው ብለን አናምንም። ምክንያቱም እነዚህ ፓርቲዎች የሚመሩበት የፖለቲካ አስተሳሰብም ሆነ የፖለቲካ አስተምህሮዋቸው ተመሳሳይ ነው። ተመሳሳይ ነው ብቻ ሳይሆን አንድ አይነት ነው። ምንም አይነት ትርጉም አይሰጥም። የአንድነት ፣ መኢአድ ሰምያዊጋር ሄዶ የማይታገልበት ምንም አይነት ምክንያት የለም። የመኢአድ እና የሰማያዊ ሰው አንድነት መጥቶ አባል ሆኖ የማይታገሉበት ምንም አይነት ምክንያት የለም። ችግሩ ምንድን ነው ተብሎ መጠየቅ ያለበት ይመስለኛል።
አንዱ ምናልባት እኔ የሚታየኝ የድርጅት ባህል ችግር ይመስለኛል። በየፓርቲዎች ዉስጥ የተለያዩ ድርጅታዊ ባህል አለ። ዴሞርካሲያው ባህል ያላቸው ፓርቲዎች አሉ። አንዳንድ ቦታ ምናልባት ወደፊት የተራመደ የፖለቲካ ባህል የሌለበት ቤት አለ። አንጻራዊ ነው ይሄ።
በሌላ በኩል በተወሰነ ሁኔታ፣ በዋነኝነት እንደዉም የኢጎ ስሜት አለ። የአገርን ጥቅም ከራስ ስልጣን አስበልጦ መመልከት ሲገባ ያ አልተቻለም የሚል ግንዛቤ አለ። ስለዚህ እነዚህ ችግሮች በአግባቡ ፈቶ ፣ የትግሉ መዓከል በአንድ ሁኔታ፣ በአንድ ማጠንጠኛ ዉስጥ ማስገባት ያስፈልጋል የሚል እምነት አለ። እና በዚህ አንጻር አንድነት ከዚህ ቀደምም ሰፋፊ ስራዎች ሰርቷል። አሁንም ይሰርል የሚል እምነት ነው ያለኝ።
በዚህ ምርጫ ግን ዉህድት አይቻልም። ምክንያቱም ኦልሬዲ የምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ በግልጽ በይፋ አሳውቀዋል።ዉሀደት ካልተቻለ፣ ከዉህደት መለስ የሆኑ አሰላለፎችን እንዴት አድርገን መፍጠር እንችላለን የሚለውን፣ በአግባቡ መመርመር አለበት ። ይሄ ኬሚስትሪ ሄዶ ሄዶ ሕብረተሰባችንን፣ ሕዝቡን ለድል ማብቃት መቻል አለበት የሚል እምነት ነው ያለን። እኛ ቢያን ቢያንስ ፓርቲዎች በአንድ ወንበር ላይ ተደራርበው መወዳደር የለባቸውም የሚል እምነት ነው ያለን። ይሄን ለማሳካት የሚይስፈልገው በፖለትካ ፓርቲዎች መሃል ሆደ ሰፊነት ብቻ ነው የሚል እምነት ነው ያለን።
ሌሎችን ምናልባት እዚህ ጋር መግጽል አስፈላጊ አይደለም። አንድነት ያቀዳቸው ነገሮች አሉ።ከተቃዋሚዎች ጋር በ2007 እንዴት አብረን እንሰራለን የሚለው፤ እንደ ትልቅ ስልት ነው ያስቀመጥነው። ምናልባት ከተሳከ ለወደፊቱ ከየፓርቲዎች ጋር ዉይይት ተደርጎ በአጭር ጊዜ ዉስጥ የምናሳወቀው ይሆናል።

No comments:

Post a Comment