Tuesday, 9 December 2014

መድረክ የተቃውሞ ሰልፍ ጠራ

ኀዳር ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና

የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ስብስብ የሆነው መድረክ የኢህአዴግ አገዛዝ በህዝባችን ህገመንግስታዊ ነጻ የመምረጥ መብት ላይ የሚፈጽማቸውን የመብት ረገጣዎች እንዲያቆም፣ በሃገራችን ነፃ ፣ ፍትሃዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ተአማኒነት ያለው ምርጫ እውን እንዲሆና የምርጫ ሜዳውም ለሁሉም እኩል የተመቻቸ እንዲሆን ለመጠየቅ ለታህሳስ 5 ቀን 2007 ዓም የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ መጥራቱን አስታውቋል።

መድረክ ለኢህአዴግ አገዛዝ የውይይትና የድርድር ጥያቄዎችን በተደጋጋሚ ቢያቀርብም፣ አገዛዙ አሻፈረን ማለቱን አስታውሶ ” ይህንኑ የኢህአዴግን ግትር አቋምና በተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና በህብረተሰቡ ላይ እያካሄደ የሚገኘውን እስራትና ወከባ ለመቃወም ወረዳ 8 በሚገኘው ኳስ ሜዳ ከጣቱ 3 ሰአት እስከ 7 ሰአት ለማካሄድ ማቀዱን አስታውቋል።
 በአሁኑ ሰአት ገዢው ፓርቲ በአንድ ለአምስት አደረጃጃት ሁሉንም ነገር ተቆጣጥሮ በሚገኝበት ሁኔታ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ እንደማይቻል የመድረክ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጥላሁን እንዳሻው ገልጸዋል። አገዛዙ ከህዝብ የሚቀርብለትን ጥያቄ ለመፍታት ፈቃደኛ ካልሆነ ተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎችም ሆኑ ሌሎች ሰላማዊና ህጋዊ የትግል ስልቶችን እንደሚጠቀሙ አቶ ጥላሁን ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment