Tuesday, 9 December 2014

ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አቋም መግለጫ

DCESON
DCESON
ዴሞክራሲያዊ ውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ  ከተቋቋመበት አላማዎች አንዱና ዋነኛው በሃገራችን  በኢትዮጲያ ያለውን ኢፍትሃዊ የአንድ ዘር የበላይነት የሰፈነበትን አምባገነን  ስርሃት በማውገዝ እንዲሁም በመታገል ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጲያን ማለትም  የዜጎችን እኩልነት የተረጋገጠባት፣  የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት ፣ የዜጎች ሰብአዊ መብት የተከበረባት ፣  የህግ የበላይነት የሰፈነባት፣ እንዲሁም  ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በኩል አይን የሚታይባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጲያን ለመገንባት የሚደረገውን ህዝባዊ ትግል መደገፍና ብሎም በአጋርነት ሞቆም ነው፡፡
ስለሆነም ባሳለፍነው ሳምንት ማለትም ህዳር 27/28 የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የሃገሪቱ ህገ- መንግስት በሚፈቅደው መሰረት  ለሃያ አራት ሰአት የሚቆይ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተው እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ሆኖም በማን አለብኝ ሃገሪቱን እንዳሻው የሚያደርግ ህውሃት(ኢህአዴግ)አሁን በህብረተሰቡ ዘንድ የተፈጠረውን የለውጥ ስሜት እንዲሁም ለዚህ ክስተት ምክኒያት ናቸው ያላቸውን የ9ኑ ፖርቲዎች ትብብር ከመቼውም በላይ ስላሰጋው ከላይ  በተጠቀሰው ቀን የአደባባይ የ24 ሰአት ሰልፍ እንዳይካሄድ የትብብሩን አምራሮችና አባላትን በማዋከብ ስራ በዝቶበት ሰንብቷል፡፡
በመጨረሻም በሰልፉ ላይ የተገኙ የ9ኙ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮችና አባሎችን እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ፍርሃት ባሸበረው ህውሃት (ኢህአዴግ)በጭካኔ ተደብድበዋል፣ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ ተግዘው ታስረዋል፡፡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ  በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በመገኝታቸው ብቻ ከጎዳና ታፍሰው የአገዛዙ አረመኔዊ እርምጃ ሰለባ ሆነዋል፡፡ እስካሁንም በዚሁ ዘረኛና አረመኔያዊ አገዛዝ ቁጥራቸው ከ300 የሚበልጡ  ሰላማዊ ታጋዮች በእስር ቤት ታፍነውከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸዋል ፡፡
ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ  አምባገነኑ ህውሃት(ኢህአዴግ) በሰላማዊ ታጋዮች እንዲሁም በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ሊያሰሙ በወጡ ዜጎች ላይ የወሰደውን አረመኔያዊ እርምጃ በጥብቅ እያወገዘ የ9ኙ ፖርቲዎች ትብብር እያደረገ ያለውን እልህ አስጨራሽ ትግል በንቃት የሚከታተልና ከጎናችሁ መቆሙን እየገለጸ ለተጀመረው የነጻነት ትግል አጋርነቱን ይገልጻል፡፡
ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ!!!!!
ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ !!

No comments:

Post a Comment