Saturday, 20 December 2014

ኢህአዴግ በባህር ዳር ግድያ ፈጸመ! በባህርዳር ዋይታ ሆነ!


bahirdar


በእምነት ቦታ ይገባኛል ነዋሪዎች ባሰሙት ጥያቄ ኢህአዴግ የጥይት መልስ ሰጠ፡፡ ድርጊቱን በምስል በማያያዝ በተለያዩ ማኅበራዊ ገጾች ያሰራጩት ክፍሎች አዛውንትና መነኮሳት ሳይቀሩ መደብደባቸውንና መቁሰላቸውን በምስል አስደግፈው አመልክተዋል፡፡
አኻዙ በትክክለኛው ባይታወቅም አምስት የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ በማኅበራዊ ገጾች የተበተኑት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ አንዳንድ የድረገጽ ዜናዎችም በአኻዝ ከመለያየት በስተቀር የግድያውንና የድብደባውን መጠን በመግለጽ ዜናቸውን አስፍረዋል፡፡
ድርጊቱን የፈጸመው ኢህአዴግ ስለሞቱትና ስለተደበደቡት መነኮሳትና አዛውንት እንዲሁም ሌሎች ወገኖች ይህንን መረጃ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ይፋዊ ማስተባበያ አልሰጠም፡፡ ይልቁንም ከሁለት ሳምንት በፊት ኢህአዴግ የፌዴራል ምክት ሚ/ሩን በፖሊስ ፕሮግራም በማቅረብ የፌስቡክ ዜናዎችን አትመኑ በማለት ማሳሰቢያ ሲሰጥ ነበር፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ” የተሰኘው የፌስቡክ ገጽ ቀበሌ፣ ወሰንና የምክርቤት ስም ጠቅሶ የተፈጠረውን ሁኔታ ከዚህ እንደሚከተለው አስፍሮታል፡፡
“የአማራ ክልል አስተዳደር የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን የታቦት ማደሪያ ለመንገድና ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች መስሪያ እንዲነጠቅ ማዘዙን ተከትሎ በቤተ ክርስቲያን የተጠራው ተቃውሞ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከታቦት ማደሪያው 9 ሜትር ገብቶ መንገድ እንዲሰራ እንዲሁም ቀሪው ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች እንዲሰጥ አስተዳደሩ ማዘዙን ተከትሎ ታቦት ማደሪያውን ከነገ ህዳር 10/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሊፈርስ እንደነበር መረጃው የደረሳት ቤተ ክርስቲያን ለህዝበ ክርስቲያኑ አስቸኳይ ጥሪ ማስተላለፏ ታውቋል፡፡ ህዝቡም “በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተገናኝተን በእግዚያብሄር ስም በአስቸኳይ ጠርተንዎታል” በሚል በቀረበለት ጥሪ መሰረት ዛሬ ጠዋት ተቃውሞውን የጀመረ ሲሆን አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ተገልጾአል፡፡ ህዝቡ ቀበሌ 10 በሚገኘው አዲሱ ምክር ቤት እንዲሁም በዚሁ ቀበሌ በሚገኘው የቀድሞው ምክር ቤት በመገኘት ተቃውሞውን እየገለጸ ይገኛል፡፡ በተለይ በአዲሱ ምክር ቤት ተገኝቶ ተቃውሞውን እያሰማ የሚገኘውን ህዝብ በኃይል ለመበተን ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡”
ግድያውንና ድብደባውን በተመለከተ “የክልሉ መስተዳድር ድርጊቱን እንደፈጸመ አድርገው የሚወጡት ዘገባዎች ትክክል አይደሉም፤ መስመርም ያስታሉ፤ ዋንኞቹን ወንጀለኞች ከደሙ የነጹ ያደርጋቸዋል” በማለት ቅሬታቸውን ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የሰጡ ወገኖች “በየትኛውም የአገሪቱ ክልሎችም ሆነ ከተሞች ለሚፈሰው ደምና ለሚጠፋው ሕይወት ግምባር ቀደም ተጠያቂው ህወሃት/ኢህአዴግ እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል” ሲሉማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ “በቁጥጥር ሥር ውሏል” የተባለው የሙስሊሙ ተቃውሞ በድንገት መካሄዱ ታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ኑር መስጊድ የተካሄደውን ተቃውሞ አስመልክቶ የተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች በተለይም የሙስሊሙን ጉዳይ በመከታተል ይፋ የሚያደርጉ መገናኛዎች እንዳስታወቁት ተቃውሞው የተካሄደው ኢህአዴግ ከሚጠብቀውና ከሚገምተው ውጪ ነበር፡፡ እንደወትሮውም የጥሪ ማስታወቂያና ቅስቀሳ አስቀድሞ አልተካሄደም በማለት ዘግበዋል፡፡ ተቃውሞው ውጤታማ፣ ግቡን የመታና የተጠናከረ ቅንብር እንደነበረው የታዘቡ ይናገራሉ፡፡
ኢህአዴግ በእሁድ የፖሊስ ፕሮግራሙ የሚሰጠው “ልማት ተኮር” የፖሊስ ማስተባበያ “ምርመራ ውጤት በተስፋ” ይጠበቃል፡፡ ከተለያዩ የማህበራዊ ገጾች ያገኘናችው ምስሎች ከዚህ በታች ሰፍረዋል::
bahirdar3bahirdar5bahirdar10bahirdar11bahirdar7bahirdar15bahirdar16bahirdar17bahirdar14bahirdar6bahirdar8bahirdar9nur mesjid addisbahirdar1bahirdar13

No comments:

Post a Comment