Sunday, 7 December 2014

ኢ/ር ይልቃልን ከመኪና ገፍትረው ሊጥሏቸው ነበር

ነገረ ኢትዮጵያ

አመራሮቹ ጨለማ ቤት ታስረዋል

• ኢ/ር ይልቃልን ከመኪና ገፍትረው ሊጥሏቸው ነበር



ህዳር 27/2007 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ታፍሰው ከታሰሩት መካከል አብዛኛዎቹ ጨለማ ቤት መታሰራቸው ታወቀ፡፡ ከሰማያዊ ጽ/ቤት አካባቢ በጀመረው ሰልፍ ላይ ታፍሰው አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) ታስረው የሚገኙት መካከል ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፣ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬና ሌሎቹም ለየ ብቻቸው ጨለማ ቤት መታሰራቸው ታውቋል፡፡ ታሳሪዎቹ ትናንት ህዳር 27/2997 ዓ.ም ምሽት ላይ ከጨርቆስ ፖፖላሬ እስር ቤት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) የተዛወሩ ሲሆን ‹‹ምርመራ ላይ ናቸው፡፡›› በሚል እንዳይጠየቁ ተደርገዋል፡፡ 

በሌላ በኩል ከሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ የተነሳው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል አብዛኛዎቹ እግርና እጃቸውን እንደተሰበሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም ባሻገር የታፈሱት አመራሮች በፒክ አፕ መኪና ተጭነው በሚወሰዱበት ወቅት ደህንነቶች ኢንጅነር ይልቃል ጌትነትን ከመኪናው ላይ ገፍተው ለመጣል ሙከራ አድርገው እንደነበርና አብረው የተጫኑት ታሳሪዎች ይዘው እንዳስቀሯቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡


No comments:

Post a Comment