Saturday, 13 December 2014

ETV የአረቡ አለም አብዮት ግቡን እንዲስት ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ ነገር ፌስ ቡክ ነው ᎓᎓

የአረቡ አለም አብዮት ግቡን እንዲመታ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ  ነገር ፌስ ቡክ ትልቅ ድርሻ እንደነበረው ይታወቃል   ᎓᎓ የአለም ህዝብም ያውቀዋል ᎓᎓

ETV  በቅዳሜ 13 12 2014 ዜናው ሲመዘግብ  http://www.ethiopian.tv/ethiopian-news-saturday-december-13-2014/   ስለ ፌስ ቡክ

የአረቡ አለም አብዮት ግቡን እንዲስት  ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ  ነገር ፌስ ቡክ ትልቅ ድርሻ እንደነበረው ይታወቃል   ᎓᎓
 (ግቡን እዲመታ  የሚለውን ግቡን እንዲስት ብሎ መናገር ህዝብን መዋሸት ነው ᎓᎓) 

ደግሞም በተዘዋዋሪ መንገድ የአምባገኖችን የጋዳፊንና የሁስኒ ሙባረክን መወደቅ መቃወም እንደሆነም እረስተውት  ነው᎓᎓

በተጨማሪም እደዘገበው  *** ፌስ ቡክን የሚቆጣጠረው አካል ባለመኖሩ ለሁሉም ሰው መረጃ የመስጠት እድል ስለሚኖረው አጠቃቀሙ በጥንቃቄ እንዲያዝ ባለሙያዎች ይመክራሉ ᎓᎓ ****

በዘገባው የህዝብን ቀልብ የሚስቡ እና የሚያሳስቱ ምክሮች አለበት ለምሳሌ እረዠም ሰዓታት ካለ እረፍት መጠቀም እና በስራ ሰዓትና በትምህርት ሰዓት ከሰማንያ ዘጠኝ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን በሚኖርባት ሃገር  ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጋ  ህዝብ ኢንተርኔት በሞባይል(በካርድ) ተጠቃሚ በመሆኑ  የስራ ሰዓቱንና የትምህርት ሰዓቱን እንዳያባክን በሚል የህዝብን አስተሰሳሰብ የመስረቅ አካሄድና በስተጀርባው ግን  የያዘው ዋና አላማ  ህዝባችን የነፃ ሚዲያ እና የግል መፅሔት ተጠቃሚነቱ የታፈነ እና የቀረ ነገር  ሆኖ ሳለ ጥቂቱ  የቀረችውን ፌስ ቡክን ለማሸማቀቅ የቀረበች ዜና ናት ᎓᎓ እስቲ ይህን ያንብቡት ፍሪደም ሃውስ  ስለሃገራችን ምን ይለናል ?     https://freedomhouse.org/report/freedom-net/2014/ethiopia

 ግብፅ ውስጥ የሁስኒ ሙባረክ የ 30 ዓመት የአምባገነን ስርዓት እንዲወድቅ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገው  የተማረውና በስደት ሀገር የሚኖሩት ምሁራን በማህበራዊ ገፅ ላይ ተሳትፈውና ከህዝቡ ጎን በመቆም ስርዓቱን በመቃወም ለውጥ እንዲመጣ ትልቅ ስራ በፌስ ቡክ  ሰርተውበታል ᎓᎓  የሁስኒ ሙባረክ መንግስት ማህበራዊ ሚዲያውን ቢዘጋውም ከውድቀት አላመለጠም ᎓᎓
የአለም ሚዲያዎችም መዝግበውታል ᎓᎓

 **After widespread protests were organised via social media, the Egyptian government of Hosni Mubarak has shut down social networks in the country. **ABC NEWS.  
https://www.youtube.com/watch?v=i3-m1HDfJ30

 ቢቢሲም የአሜሪካን ፕሬዝዳት ኦባማን ንግግር እንዲህ አቅርቦታል

   http://www.bbc.co.uk/news/world-middle-east-12433045

US President Barack Obama said that Egypt must now move to civilian and democratic rule.
"The people of Egypt have spoken, their voices have been heard," Mr Obama said. "Egypt will never be the same again." ይህም ማለት የውጭ ሃገሮች ለጥቅማቸው ሲሉ ብቻ አምባገነኖች በአንድ ሃገር ህዝብ ላይ  የሚያደርሱትን መጥፎ ስራ ዝም ብለው እያዩ አብረው እያጨበጨቡ ኖረውአንድ ቀን ግን የህዝብ የብሶት ድምፅ በአየለ ወቅት ፊታቸውን ከመቀፅበት እንደሚያዞሩ ነው᎓᎓ ስለዚህ ሙባረክ የወሰደው የመጨረሻ ሚዲያን የማፈን ስራ እንኳን ከመፈጥፈጥ አላዳነውም᎓᎓ ታዲያ የሃገራችን አዲሱ ትውልድ ሚዲያ በአግባቡ ነፃ ሆኖ ካልተጠቀመና ለጥቂት ግለሰቦች ጥቅምና ለስልጣን እርዝማኔ  ሲባል ሃገራችንና ህዝባችንን ከዘመናዊ  ስልጣኔ ማራቅ ህዝብም አይወደውም እግዝአብሔርም አይወደውም᎓᎓

  ህዝብ  በትክክለኟው  መንገድ  በኢንፎርሜሽን ከተገነባ የጥሩ እውቀት ባለቤትና ለሃገር የሚቆረቆር ትውልድ ሃገራችን ኢትዮጵያም በብዛት እያፈራች ትሄዳለች ከወቅቱም ጋር ትራመዳለች ᎓᎓ ነገር ግን  በተለይ በስልጣን ላይ የተቀመጡ የሚሰጡት አስተያየት በውሸት የተሞላና  እንኪያ ሰላምታ የሚያበዙ ከሆነና የወረደ ከሆነ  አፋቸው ሲከፈት ጭንቅላታቸውን  እንደሚታይ ማይገነዘቡ ከሆነ ደግሞ  ህዝባችን አይቶ አይቶ  በዚህ በ 21 ኟው ክፍለ ዘመን  የሚበጀውን እና ለወደፊት ለመራመድ የተሻለውን እንደሚመርጥ መገንዘብ ይኖርባቸዋል ታዲያ መቀበልም አለባቸው᎓᎓  በማሰር ፣በመግረፍ ፣ በማፈን፣ በመግደል  በአጠቃላይ ስልጣንን ተገን አድርጎ ወንጀል በመስራት ስልጣንን ማራዘም የማይበጅና አንድ ባልታሰበ ቀን ግዜው ጠብቆ   ህዝብ ከህዝብ ጎን ለጎን ቆሞ  እጅ ለእጅ ተያይዞ በትክክል እነደሚፈርድባቸው መገንዘብ አለባቸው ᎓᎓ 

ቸር ያሰማን !
አብዩ ጌታቸው

1 comment: