Saturday, 28 February 2015

ኢህአዴግ 98 ቢሊዮን ብር ነጠፈበት!! – “ታላቅ ሥራ ተሰርቷል! እናመሰግናለን!” ኦባንግ

anuak woman abobo

ይህ ዘገባ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ዘገባ ነው
ኢህአዴግ በዓለም ባንክ በኩል ከእንግሊዝ የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤት ሊለግስለት ታቅዶ የነበረው 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) የገንዘብ ድጋፍ ነጠፈበት፡፡ አቶ ሬድዋን አልነጠፈብንም ይላሉ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው “የታላቅ ሥራ ውጤት ነው፤ እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጥቅምት 2፤2005 (October 12, 2012) “ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!! ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!” በሚል ርዕስ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ያካሂድ ስለነበረው ፕሮግራም በዘገበበት ወቅት የሚከተለውን ዜና አትሞ ነበር፡- “ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡”
ይህ ለመሠረታዊ ልማት እንዲውል በዓለም ባንክ በኩል የሚሰጠውን ገንዘብ የሚደጉሙት ምዕራባውያን አገራት ሲሆኑ አንዷ ተጠቃሽ አገር እንግሊዝ ናት፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ ከምዕራባውያን በዓለም ባንክ በኩል የሚያገኘውን ገንዘብ ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያነት እያዋለው መሆኑ ለዓለም ባንክ ተደጋጋሚ መረጃዎች ሲቀርቡ ቆይተዋል፡፡ በተለይ ሟቹ መለስ በቀጥታ በሰጡት ትዕዛዝ 424 የአኙዋክ ተወላጆች ከተገደሉ በኋላ ኢህአዴግ በቦታው ያሰማራው የመከላከያ ሠራዊት በሥፍራው የሚኖሩትን ከመኖሪያ ቀያቸው በማፈናቀል እምቢ ያሉትን በግድ በማስነሳት፣ በመግደል፣ አስገድዶ በመድፈር፣ በማሰቃየት፣ ወዘተ ግፍ ሲፈጽም መቆየቱ በተለያዩ ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና ባገኙ ዘገባዎች ሲነገር ቆይቷል፡፡ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ ልማት በማለት የሚሰጠው ገንዘብ ኢህአዴግ ወታደሮቹን የግፍ ሥራ ላይ በማሰማራት ደመወዝ የሚከፍልበት መሆኑን በመጥቀስ ወደ ኬኒያ የተሰደዱ የክልሉ ነዋሪዎች አቤቱታ አቅርበው እንደነበር ጎልጉል በወቅቱ የዘገበው ዜና ነበር፡፡ ““ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”፤ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል” በሚል ርዕስ የተጻፈውን ዜና ለማንበት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
money lost
ከዚሁ ጋር በተያያዘ “ሚስተር ኦ” በመባል የሚጠሩት አኙዋክ ተወላጅ ኢህአዴግ የዕርዳታ ገንዘብ ለሰብዓዊ መብት ረገጣና ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያነት እንዳዋለው በመጥቀስ የእንግሊዝ መንግሥት ከግብር ከፋይ ዜጎቹ የሚያገኘውን ገንዘብ አምባገነንነት እየደገፈበት መሆኑን በተለይም የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤቱ ተጠያቂ ስለሆነ ከዚህ እንዲታቀብ ክስ መመሥረታቸው ይታወቃል፡፡ የክሱ ሒደት እየተካሄደ ባለበት ባሁኑ ወቅት ሚስተር ኦ በተደጋሚ እንደመሰከሩት ኢህአዴግ ነዋሪዎችን በግዳጅ ከቀያቸው በማፈናቀል የሚያካሂደው የግዳጅ ሰፈራና የመንደር ምሥረታ ሕገወጥ መሆኑ በመቃወማቸው በተደጋጋሚ ከፍተኛ ድብደባ እንደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡ ብዙዎች ለአካላዊ ሥቃይ ደርሶባቸዋል፣ ሴቶች ክብረንጽህናቸው ተደፍሯል፣ አዛውንትና ህጻናት ለአሰቃቂ መከራ ተዳርገዋል፤ ይህንንም እርሳቸው እንዳዩ ሚስተር ኦ ይመሰክራሉ፡፡

የሚስተር ኦ የፍርድቤት ጉዳይ ወደ ውሳኔ ሊደርስ ባለበት ወቅት የልማት መ/ቤቱ ይህንን ዓይነት ውሳኔ መውሰዱ ከፍርድ ቤቱ ጉዳይ ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ይናገራሉ፡፡ የልማት ተራድዖ መ/ቤቱ ቃል አቀባይ ግን የመ/ቤታቸው ውሳኔ ከሚስተር ኦ የፍርድቤት ጉዳይ ጋር ያልተያያዘ እንደሆነ መናገራቸውን የእንግሊዙ ዘጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ መ/ቤቱ ለዚህ ውሳኔ የደረሰው ኢትዮጵያ “የዕድገት ስኬት” እያስመዘገበች በመምጣቷ የመሠረታዊ ልማት አገልግሎት የገንዘብ ዕርዳታ የማያስፈልጋት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
ይህ መጠኑ እጅግ ከፍተኛ የተባለውና ለኢህአዴግ ንጹህ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የሚያስገኝ ገንዘብ እንደነጠፈበት መሰማቱን አስመልክቶ ጋዜጣው የኢህአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ የሆኑትን ሬድዋን ሁሴን በጠየቃቸው ወቅት የመለሱት አልነጠፈብንም የሚል እንድምታ ያለው ነው፡፡ “እነርሱ ያሉት ዕርዳታውን አንሰጥም ወይም እናቆማለን ሳይሆን ዕርዳታ አሰጣጡ እንደገና ይዋቀራል ነው” በማለት ሬድዋን ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሆኖም 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) ዕርዳታ ለመስጠት ከዓለምባንክ ጋር ስምምነት የነበረው የእንግሊዝ የልማት ተራድዖ መ/ቤት “ኢትዮጵያ አድጋለች” በማለት በ2015/2016 በፓውንድ 256ሚሊዮን ብቻ (5በመቶ) ዕርዳታ ለመስጠት መወሰኑን የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊው ሬድዋን ሁሴን አላብራሩም፡፡
ኢህአዴግ ለዕርዳታ የሚሰጠውን ገንዘብ ዜጎችን ለማሰቃየት፣ ወታደር ለመቀለብ፣ ወዘተ እንደሚጠቀምበት በተደጋጋሚ ዘገባዎች እና ማስረጃዎች ሲወጡበት የከረመ ቢሆንም ማስረጃዎቹን ተከትሎ የዓለም ባንክ በዕርዳታ አሠጣጡ ላይ አንዳች ውሳኔ እንዳያደርግ ብዙ ሲደክም ቆይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ጉዳዩ ውሳኔ ሳይሰጥበት እንዲስተጓጎል በማድረግ ለሁለት ዓመታት ያህል እንዲጓተት ማድረጉን ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይመሰክራሉ፡፡
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኦባንግ ሜቶ ጉዳዩን ገና ከጅምሩ የሚያውቁትና ድርጅታቸው ለዓመታት ሲሰራበት የነበረ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በመሆኑንም ይህንን የእንግሊዝ የልማት ተራድዖ መ/ቤት ውሳኔ የጋራ ንቅናቄያቸው ከደጋፊዎቹ ጋር በመሆን ያገኘው ድል እንደሆነ በፌስቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡ “ገና ከጅምሩ ከጋራ ንቅናቄያችን ጋር በመሆን ይህንን ሥራ በመደገፍ የተባበራችሁንን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፤ ታላቅ ሥራ ተሰርቷል፤ እናመሰግናለን” ብለዋል “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ ኦባንግ በተለይ ከጎልጉል ለቀረበላቸው አጭር ጥያቄ በሰጡት አስተያየት የጋራ ንቅናቄያቸው ደስታውን የገለጸው የልማት ገንዘብ በመቋረጡ ሳይሆን በልማት ስም የሚሰጠው ዕርዳታ ለሰብዓዊ መብት ረገጣ በመዋሉና ለዚህም ደግሞ ከበቂ በላይ ማስረጃ ድርጅታቸው ያለው በመሆኑ ነው፡፡ “አገር ብትለማ የሁሉም ደስታ ነው” ያሉት ኦባንግ አገርን በማልማት ሽፋን ደጋፊና ተቆርቋሪ የሌላቸውን ንጹሃን መበደልና የመኖር መብታቸውን መንፈግ ግን በየትኛውም መልኩ እርሳቸውም ሆነ አኢጋን የሚቀበለው እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
ኢህአዴግ በቅርቡ አካሂዳለው ለሚለው ምርጫ እንደ ዕቁብ ዕጣ በማውጣትና በማስወጣት “አልደረሳችሁም” እያለ የተቀናቃኝ ፓርቲ አመራሮችን ከምርጫ እያስወገደ ባለበት፤ ሌሎችንም ሕጋዊ አይደላችሁም እያለ በተለጣፊ ድርጅት በማስበት ኅልውናቸውን እያሳጣ ባለበት ባሁኑ ወቅት በዜጎቹ ላይ የሚያካሂደውን መረን የለቀቀ የመብት ገፈፋ ለሥልጣን ያበቁትን ምዕራባውያንን ያስደሰተ እንዳልሆነ ይነገራል፡፡ የአውሮጳ ኅብረት ምርጫውን አልታዘብም ከማለቱ በተጨማሪ በሚዲያ ላይ የተጫነው አፈና በዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ይፋ ከሆነ ወዲህ ማነቆው በኢህአዴግ ላይ እየከረረ መምጣቱን ያሳያል፡፡ ኢህአዴግን ለሥልጣን ከማብቃት አልፋ ነፍጥ አንጋቢዎቹን የህወሃት መሪዎች ጸጉርና ጺም ከርክማ፤ ልብስ አልብሳ፤ ቋንቋ አስተምራ፤ የከተማ አኗኗር እንዴት እንደሆነ አሠልጥና፣ ቶሎ ባይገባቸውም ፕሮቶኮል አስተምራ፣ እስካሁንም ተንከባክባ እዚህ ድረስ ያቆየቻቸው እንግሊዝ እንዲህ ያለውን የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ስታደርቅ “ቀጣዩስ ምን ይሆን?” የሚል ጥያቄ እንዲነሳ አድርጓል፡፡ “ምዕራባውያን መግደልም ማንሳትም ያውቁበታል” በማለት አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች እንደሚሉት ቀጣዩ የኢህአዴግ ጉዞ በከፍተኛ ሁኔታ ለህወሃት ሲቀጥል ለኢህአዴግ አስጊ ከመሆን ባሻገር በውጭ ምንዛሪ እጥረት በየጊዜው የሚፈጠረውን ግሽበት በዕርዳታ ገንዘብ የሚያስተካክለው ኢህአዴግ እንዲህ ያለው የገንዘብ ማዕቀብ ክፉኛ ያነጥፈዋል ሲሉ ግምታቸውን ይሰጣሉ፡፡ ሙስናው መረን በለቀቀባት አገር ከሕዝብ እየተዘረፈ በተለያዩ አገራት ባንኮች በውጭ ምንዛሪ የሚከማቸውን ገንዘብ በሚካፈሉትም ላይ የድርሻ ቅነሳ የማስከተሉ ጉዳይ አብሮ የሚታይ እንደሆነ ይነገራል፡፡
ከዚህ ዜና ጋር ተያያዥነት ያለውን ጥቅምት 2፤2005 (October 12, 2012) ያተምነውን ዜና ከዚህ በታች እንደሚከተለው እንደገና አትመነዋል፡፡

ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!!

ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!

ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ። ኢንስፔክሽን ፓናል (Inspection Panel – IP) የተሰኘ ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው ገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ታውቋል። ይፋ የሆነውን መረጃ አስመልክቶ ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም።
ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ ወንጀሎችን መረጃዎችን በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) ከሰለባዎቹ ውክልና ተሰጥቶታል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቋል።
የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርሰውን እስራት፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከመኖሪያ ቦታ ማፈናቀል፣ የግዳጅ ሰፈራ ወዘተ በማምለጥ ወደ ኬንያ የተሰደዱ የጋምቤላ ነዋሪዎች ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጽምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ስም ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የዕርዳታ ገንዘብ በመሆኑ ለባንኩ በላኩት የአቤቱታ ደብዳቤ አመልክተዋል።
አቤቱታውን መሠረት በማድረግ የሚደረገው ምርመራ ውጤት ይፋ ሲሆን፣ በሌሎች አገሮች እንደተደረገው በዕርዳታ ስም የሚገኝን ገንዘብ ኢህአዴግ ለፖለቲካ ተግባር መጠቀሙ ሲረጋገጥ፣ በመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ ከዓለም ባንክ ተፈቅዶ የነበረው 600ሚሊዮን ዶላር ሊከለከል ይችላል፡፡
የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ በሟቹ ጠ/ሚ/ርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በጋምቤላ ክልል በተለይ የተማሩ ወንዶች ላይ በማተኮር 424 ንጹሐን የአኙዋክ ተወላጆች በተገደሉበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩት ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክልሉ ሰላም የለም፡፡ በየጊዜውም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲካሄዱበት ቆይቷል፡፡ በተለይም ለም የሆነውን እጅግ ሰፋፊ መሬት ለውጪ ባለሃብቶች በሳንቲም በመሸጥ ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ አገዛዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀድሞው የደርግ ዘመን ሲካሄድ ከነበረው ባለፈ መልኩ እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ በመንደር ምስረታና አስገድዶ የማስፈር ፖሊሲ ከመኖሪያ ቀዬ የማፈናቀል ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የኦክላንድ ተቋም፣ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ … የመሳሰሉ ድርጅቶች ያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡
ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የባንኩ ድርሻ የሆነውን 600ሚሊዮን ዶላር ቦርዱ መስከረም 5ቀን 2005ዓም አጽድቋል፡፡
በአስገድዶ ማስፈር፣ መንደር ምስረታና ሌሎች በርካታ የሰብዓዊ መብቶቻቸው የተጣሱባቸው በኬንያ የሚገኙ ሦስት የአኙዋክ ስደተኞች ተወካይ ድርጅቶች በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ሌሎች የሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በመሆን ባንኩ ሊሰጥ የወሰነውን ገንዘብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ከመዋል ይልቅ ለኢህአዴግ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ እየዋለ መሆኑን በመጥቀስ ለባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጂም ዮንግ ኪም መስከረም 6፤ 2005ዓም ደብዳቤ ልከዋል፡፡ በጥያቄያቸውም መሠረት በዓለም ባንክ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚፈሰው ገንዘብ “በልማት ስም የኢትዮጵያ መንግሥት በጋምቤላ ክልል ለሚያካሂደው የመንደር ምስረታ እየዋለ ነው” በማለት ይከሳል፡፡ ሲቀጥልም የአኙዋክ ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት መንደር በማፈናቀል “የተሻለ አገልግሎት
 ይሰጣችኋል” በማለት በግድ የማስፈር ተግባር እየተፈጸመ ሲሆን “የተባለው አገልግሎትም ሆነ ለእርሻ የሚሆን በቂ ቦታ እንዲሁም ለከብቶች የሚበቃ የግጦሽና የውሃ ቦታ የላቸውም” በማለት ሰፈራውን የተቃወሙ ሁሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡ ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ደግሞ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) ስም ለልማት እንዲውል ከሚሰጠው የዕርዳታ ገንዘብ በመንግሥት ተቀጥረው ደመወዝ የሚከፈላቸው ሠራተኞች መሆናቸውን ገልጾዋል፡፡ ይህንን ጉዳይ ከዓለም ባንክ ጋር እንዲነጋገሩላቸው Inclusive Development International (IDI) የተባለውን ድርጅት መወከላቸውን አስታውቀዋል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)

ተመሳሳይ ጉዳዮችን በዓለምአቀፍ ደረጃ በመከታተልና በማስፈጸም የታወቀው IDI በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የመልሶ ማቋቋምና ልማት ዓለምአቀፍ ባንክና (International Bank for Reconstruction and Development (IBRD)) የዓለምአቀፍ ልማት ማኅበር (International Development Association (IDA)) ሥር ለሚገኘው የኢንስፔክተር ፓናል ባለ 18ገጽ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) ይህ የኢንስፔክተር ቡድን ከፍተኛ ሥልጣን ያለው መ/ቤት ሲሆን የዓለም ባንክ የሚሰጠውን ገንዘብ በትክክለኛ ቦታ ላይ አለመዋሉን በመጥቀስ ክስ የሚያቀርቡ ወገኖችን ጉዳይ በመከታተልና ቦታው ድረስ የራሱን ምርመራ በማካሄድ ውጤቱ ተግባራዊ እንዲሆን የባንኩን እጅ የማስጠምዘዝ ዓቅም ያለው እንደሆነ ከዚህ በፊት ያካሄዳቸው የምርመራ ውጤቶች ይጠቁማሉ፡፡
ይህ የመርማሪ ቡድን የቀረበለትን አቤቱታ መቀበሉንና በጉዳዩ ላይ የማንም ተጽዕኖ የማይደረግበትን የራሱን ምርመራ እንደሚያደርግ ከትላንት በስቲያ ባወጣው ባለ 8ገጽ መግለጫ ላይ አሳውቋል፡፡ ይህ የአቤቱታ ፋይል ቁጥር የተሰጠው ጉዳይ በግልባጭ ለባንኩ ፕሬዚዳንትና ለከሳሽ ተወካይ ድርጅት (IDI) እንዲደርስ ተደርጓል፡፡(የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
ጎልጉል የሰሜን አሜሪካ ዘጋቢ ባጠናከረው መረጃ መሠረት ቡድኑ ከያዝነው ዓመት የጥቅምት አጋማሽ በኋላ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ያቀናል። ቡድኑ ስደተኞቹ የሚገኙባቸውን፣ እንዲሁም ጉዳዩን በሚመለከት አስፈላጊ የሚላቸውን ቦታዎችና ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ያነጋግራል። ለስራው መሳካት የሚሆነውን ሁሉ በሚፈለግበት ቦታ በመገኘት በግንባር እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል።
በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግ የሚፈጽመውን ግፍና በደል በማደራጀት ሥርዓቱ ላይ ከትጥቅ የጠነከረ ትግል ማካሄድ እንደሚቻል አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል:: አያይዘውም በመላው አገሪቱ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣና የመብት ጥሰት በማሰባሰብ የኢህአዴግን የገንዘብ ምንጭ የማድረቅ፣ ብሎም በእርዳታ ገንዘብ የሚገነባቸውን የአፈና ተቋማት ማስለል እንደሚቻል አስታውቀዋል። ይህንን ታላቅ ስራ የሰሩትን አካላት ልምዳቸውን ለሌሎች በማካፈል አስፈላጊውን ስራ ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል። (የመግቢያው ፎቶ የተወሰደው: ዘጋርዲያን)

የወያኔ ሰላይ ከሆላንድ ተባረረ!


ሂሩት መለሰ – ከሮተርዳም

                                                
ሮተርዳም፣ ጥቅምት 28 ቀን 2015 – በስደት ስሙ አለማየሁ ስንታየው በመባል የሚታወቀው የህወሃት ሰላይ ከኔዘርላንድስ 
ተባረረ። አለማየሁ ስንታየሁ ቋሚ ነዋሪ ከነበረበት ከኔዘርላንድስ እንዲባረር የተደረገው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በከፈቱበት 
የስለላ ክስ መሆኑም ታውቋል።
የሮተርዳም ከተማ ፍርድ ቤት በአለማየሁ ላይ የተመሰረተውን የስለላ ክስና ማስራጃ ለረጅም ጊዜ ሲመረምር ከቆየ በኋላ የግለሰቡ 
የመኖርያ ፈቃድ እና ቤት እንዲነጠቅ፣ የሆላንድን ምድርም በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ አስተላልፏል። ከሆላንድ የምመራ 
ቡድን እንደተረዳነው ከሆነ – የግለሰቡ ቤት ሲፈተሽ ወያኔ የሰጠው እውነተኛ መታወቂያ እና በርካታ የስለላ ሰነዶች 
ተገኝተውበታል። በእርዳታ ስም የተቋቋመለት ድርጅትም ተፈትሾ ማስረጃዎች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል።

ይህ ሰው ትክክለኛ ስሙ ዘለቀ ፎላ ይባላል። በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባል ሆኖ ለረጅም አመታት አገልግሏል። ወያኔ 
ስልጣን ሲቆጣጠር ለፖለቲካ ተሃድሶ አዋሳ ደቡብ ጦር ቅጥር ግቢ ተላከ። በተሃድሶ በነበረበት ጊዜ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ 
የሰራዊቱ አባላትን ለወያኔ በማጋለጥ ታማኝነቱን ሲያሳይ እንደነበር የዚህ ዜና ዘጋቢ እማኝ ነው። የበርካታ ኢትዮጵያውያን ደም 
በእጁ ያለው አለማየሁ ከተሃድሶው ከወጣ በኋላ እስራኤል ገደቡ (የፓልቶክ ስሙ ኢዛና) ከተባለ ወታደር ጋር በመሆን የሰላም 
ተጓዥ ነኝ ብሎ በመገናኛ ብዙሃን ሲታይ ነበር። አለማየሁ እና ኢዛና በየሃገሩ እየዞሩ ስለ አዲሱ ስርዓት መልካምነት ሲሰብኩ 
ከረሙ። ከዚያም አስመራ ድረስ ተልከው የሻእቢያውን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂን በወታደሩ ስም ይቅርታ ጠይቀዋል።
አለማየሁ እና ኢዛና ለወያኔ በሰሩት ውለታ ሆላንድ ገብተው እንዲቀሩ ተደረገ። ይህም የተደረገበት ምክንያት በአውሮፓ የሚኖሩ 

ኢዮጵያውያንን ተቃዋሚ በመምሰልና በረቀቀ መንገድ እንዲያበጣብጡና እንዲሰልሉ ነው።
በሆላንድ ሃገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ ለወያኔ ቡድን የስለላ ስራ መስራት ወንጀል ነው። አለማየሁ የሆላንድ ዜግነት ቢኖረው ኖሮ ቅጣቱ የከፋ ይሆን እንደነበር ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉ የህግ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
የአለማየሁ መባረር በተሰማ ግዜ በሮተርዳም ያሉ የህወሃት ደጋፊዎች የአቤቱታ ደብዳቤ በመጻፍ ፊርማ ማሰባሰብ ቢጀምሩም ሊሳካላቸው አልቻለም። የአቤቱታ ደብዳቤው ግለሰቡ እዚህ የተወለዱ ሁለት ለጆቹን እየመጣ እንዲጎበኝ ይፈቀድለት የሚል ነበር።

አለማየሁ ስንታየሁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከሆላንድ ተባረረ። ኢዛና ግን አሁን የተቃዋሚ ጭንብሉን አውልቆ በግልጽ ወያኔ 
መሆኑን መናገር ጀምሯል። ኢዛና የሆላንድ ዜግነት ቢኖረውም በሆላንድ ሃገር ስራ ሰርቶ አያውቅም። የቀንና ማታ ስራው 
በፓልቶክ ላይ ነው። ባለፈው ወር ኢትዮጵያ የተጓዙ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮችን እየመራ በቴሌቭዥን መግለጫ ሲሰጥ አይተነዋል። 
ይህ ትርኢት የወያኔ ኢንቨስተሮች በጨበጣ እንደሚንቀሳቀሱም ያሳየናል።
ከመሃል ያለው ኢዛና (እስራኤል ገደቡ) ለ’ኢንቨስትመንት” አዲስ አበበ ያለፈው ወር

Friday, 27 February 2015

British support for Ethiopia scheme withdrawn amid abuse allegations

Department for International Development will no longer back $4.9bn project that critics claim has funded a brutal resettlement programme
E6T1GH Anuak Tribe Woman Cleaning The Ground In Abobo, The Former Anuak King Village, Gambela Region, Ethiopia
An Anuak woman at work in Abobo, a village in Ethiopia’s Gambella region. It has been claimed that UK money has funded abuses against Anuak people in the area. Photograph: Alamy
The UK has ended its financial support for a controversial development project alleged to have helped the Ethiopian government fund a brutal resettlement programme. Hundreds of people have been forced from their land as a result of the scheme, while there have also been reports of torture, rape and beatings.
Until last month, Britain’s Department for International Development (DfID) was the primary funder of the promotion of basic services (PBS) programme, a $4.9bn (£3.2bn) project run by the World Bank and designed to boost education, health and water services in Ethiopia.
On Thursday, DfID said it had ended its PBS contributions because of Ethiopia’s “growing success”, adding that financial decisions of this nature were routinely made after considering a recipient country’s “commitment to partnership principles”.
It has been alleged that programme funds have been used to bankroll the Ethiopian government’s push to move 1.5 million rural families from their land to new “model” villages across the country.
Opponents of the commune development programme (CDP) say it has been characterised by violence. One Ethiopian farmer is taking legal action against the British government, claiming UK money has funded abuses against Anuak peoplein the Gambella region. The man, an Anuak known as Mr O, says he was beaten and witnessed rapes and assaults as government soldiers cleared people off their land. DfID has always insisted it does not fund Ethiopia’s commune development programme.
scathing draft report from the World Bank’s internal watchdog recently concluded that inadequate oversight, bad audit practices, and a failure to follow the bank’s own rules had allowed operational links to form between the PBS programme and the Ethiopian government’s resettlement scheme.
Although the bank’s inspection panel found that funds could have been diverted to implement villagisation, it did not look into whether the resettlement programme had involved human rights abuses, claiming such questions were outside its remit.
DfID, which has contributed nearly £745m of UK taxpayer money to the PBS programme, said the decision to withdraw financial support was prompted in part by Ethiopia’s “impressive progress” towards the millennium development goals.
“The UK will now evolve its approach by transitioning support towards economic development to help generate jobs, income and growth that will enable self-sufficiency and ultimately end poverty,” it said.
“This will go alongside additional funding for specific health, education and water programmes – where impressive results are already being delivered – resourced by ending support for the promotion of basic Services programme.”
A DfID spokesman said the move had nothing to do with Mr O’s ongoing legal action or the World Bank’s internal report, but added: “Changes to programmes are based on a number of factors including, but not limited to, country context, progress to date and commitment to partnership principles.”
The department said its overall financial commitment to Ethiopia, one of the largest recipients of UK aid, would remain unchanged, with almost £256m due to be spent between 2015 and 2016.
The Ethiopian government said DfID’s decision was not a matter of concern.
“They have been discussing it with pertinent government bodies,” said the communications minister, Redwan Hussien.
“What they said is that the aid that they’re giving will not be refused or stopped, it will be reorganised.”
The World Bank’s executive board met on Thursday to discuss the internal report on the PBS programme and the management response.
In a statement released on Friday, the bank said that although its inspection panel had concluded that the seizing of land and use of violence and intimidation were not consequences of PBS, it had determined that the programme “did not fully assess and mitigate the risks arising from the government’s implementation of CDP, particularly in the delivery of agricultural services to the Anuaks”.
The World Bank Group president, Jim Yong Kim, said that one of the institution’s core principles was to do no harm to the poor, adding: “In this case, while the inspection panel found no violations, it did point out areas where we could have done more to help the Anuak people. We draw important lessons from this case to better anticipate ways to protect the poor and be more effective in fighting poverty.”
Opponents of the villagisation process have been vocal in their criticisms of the bank’s role. Jessica Evans, senior international financial institutions researcher atHuman Rights Watch, said the inspection panel’s report showed the bank had “largely ignored human rights risks evident in its projects in Ethiopia” and highlighted “the perils of unaccountable budget support” in the country.
Read more

ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ፥ ልዩ መልዕክት ከጎንደር ሕብረት

 Ethiomedia

የጎንደር ክፍለ ሃገር በዚህ በያዝነዉ ዘመን የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር በተባለ ቡድን የጥቃት ሰለባ መሆኑን በተደጋጋሚ ተጽፏል፣ ነገር ግን ግፍ እና በደሉ ሰሚ ካጣ ብዙ ዓመታትን አስቆጥሯል። 


አሁንም መከራዉ እና ሰቆቃዉ ያላቆመዉ የጎንደር፤ የወልቃይት እና ጠገዴ፤ እንዲሁም የጠለምት ህዝብ በቁሙ እዬተቀበረ ነዉ። 
የዛሬዉ መግለጫችን የሚያተኩረዉ ለሚመለከታቸው የማህበረሰብ አካላት ሁሉ መልዕክታችን በማስተላለፍ ነዉ።




ክፍለ ሃገሩ ካሉት ሰባት አዉራጃወች የወገራና የደባርቅ አውራጃ ወረዳዎች አብዛኛወቹ በጉልበት ወደ ትግራይ አስተዳደር እንዲጠቃለሉ በመደረጉ ኗሪው ህዝብ የወገን ያለህ እያለ ነዉ። 

የጎንደር ህዝብ ትጥቅ የለዉምና መሬቱን ፈርቶ ይሰጣል በሚል ሥሌት አሁንም እንደገና የጭልጋን እና የጎንደር ዙሪያ ወረዳዎችን ለመቆጣጠር የትግራይ ህዝብ ነጻ አዉጭ ግንባር ከነበሩት አጥፊ እና ጠብ ጫሪ ሚሊሻዎቹ በተጨማሪ፤ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ አዲስ ሚሊሻዎችን በማሰልጠን የወልቃይት ወገኖቻችንን የጎንደሬነት ጥያቄም ሆነ የይሥሙላ ምርጫን በግፍ ለማፈን ተጨማሪ
ዝግጅት በማድረግ ላይ እንዳለ በተለያዩ የዜና አውታሮች ተዘግቧል። 


መልክታችን አንድ እና አንድ ነዉ። 


ድንበራችን ተከዜ ነዉ! እያለ ያለዉ የመላዉ የሰባቱ አዉራጃወች የጎንደር ሕህዝ ድምጽ መከበር አለበት ።


የወያኔ ወረዳዎችን የመንጠቅ በሽታ ጎንደርን ብሎም ኢትዮጵያን የመበታተን ዘመቻ በመሆኑ ይህንን ሴራ ለመቀልበስ በዬአዉራጃዉ እና በየወረዳዉ ሁሉም በየአካባቢው መሪዉን መርጦ ለመብቱና ለድንበሩ ዘብ የመቆም ታሪካዊ ግዴታ አለበት። 


ሙሉ መልክቱን ለማንበብ ሊንኩን ጫን በሉት፥


http://www.ethiomedia.com/10parts/gonder_hibret_022215.pdf

በአዋሳ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሟቾች ቁጥር ከ20 በላይ ነው ሲሉ የቃጠለው ሰለባ የሆኑ ሰዎች ገለጹ


የካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል ዋና ከተማ በአዋሳ የካቲት 14 ቀን 2007 ዓም በደረሰው ከፍተኛ 
የእሳት ቃጠሎ የሟቾች ቁጥር በመንግስት እንደተገለጸው አንድ ሳይሆን ከ20 በላይ መሆኑን ተገጂዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

ከፍተኛ ንብረት ከወደመባቸውና እሳቱ ሲነሳ በስፍራው ከነበሩት መካከል አንዱ ለኢሳት ሲናገር፣ እርሱ የ6 ሰዎችን የተቃጠለ 
አስከሬን ማየቱን፣ በስፍራው የሚገኙ ጓደኞቹ ደግሞ በአጠቃላይ እስካሁን 27 አስከሬን ተፈልጎ መቀበሩን ተናገሩዋል።

አንድ ህጻነት እና አንዲት እናት ከ3 ልጆቿ ጋር ሞታ መመልከቱን፣ በማግስቱ ደግሞ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች ሞተው ማየቱን 
የሚናገረው ግለሰቡ፣ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች አካባቢውን ከነዋሪው በመከለል ማታ ማታ የተቃጠለ አስከሬን እየፈለጉ 
በመቅበር ላይ ናቸው ብሎአል። እናቶች አሁንም ድረስ ልጆቻቸውን እየጠየቁ ቢሆንም፣ በከንቲባው በኩል የሚሰጠው ምላሽ 
አሳዛኝ መሆኑን ግለሰቡ ገልጿል። ነዋሪዎቹ በመንግስት በኩል በቂ እርዳታ እንዳልተደረገላቸው በምሬት ተናግረዋል።

መንግስት የእሳቱን መነሻ እስካሁን ይፋ አላደረገም። ነዋሪዎች እንደሚሉት ግን መስተዳድሩ ቦታውን ለመሸጥ እሳቱን ሆን ብሎ 
አስነስቶታል። 
በጉዳዩ ዙሪያ የአዋሳን ከንቲባ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም።

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሰቆጣ አርሶደአሮች በረሃብ ምክንያት ተሰደዱ

ኢሳት 

ወኪላችን እንደዘገበው በሰቆጣ አካባቢ የተከሰተውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ አርሶደአሮቹ ወደ ምእራብ ጎጃምና ሌሎች የአማራ 
ክልል አካባቢዎች በመሰደድ ላይ ናቸው።

ተፈናቃዮቹ ከክልሉ ባለስልጣናትም ይሁን ከፌደራል መንግስቱ ምንም አይነት እርዳታ 
አለማግኘታቸውን ገልጸዋል።

ብዙዎቹ ተፋናቃዮች ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሲሆኑ፣ በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ስራ 
ሰርተው ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ እየጠየቁ ነው።

ተፈናቃዮቹ በዝናብ እጥረት ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ገልጸዋል።
መንግስት በአካባቢው ስለተከሰተው ድርቅ እስካሁን የሰጠው ምንም አይነት መልስ የለም።


Thursday, 26 February 2015

ኢትዮጵያ፥ኢትዮጵያዊነት እና አንቀፅ 39 (ክፍል 2)


አንቀፅ 39 ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ቻርተር አንቀፅ 78 ጋር ፊት ለፊት ይጋጫል። ይህ ማለት በአንቀፅ 

39 መሰረት መገንጠል የሚፈልግ ክልል ወይም ህዝብ እንደ ሃገር በተባበሩት መንግስታት እውቅና አይሰጠውም። እውቅና 

ካልተሰጠው ደግሞ ሃገር መሆን አይችልም። በድርቅና እና በድንቁርና የሚሆን ነገር የለም።በቃ! የዓለም አሰራር ይሄው ነው። 

የተመድ አንቀፅ 78 በውጭ ወረራ ቅኝ ግዛት ያልተገዙ ሃገራት አንድነታቸውን ማጠናከር ካልሆነ በቀር ተገንጥለው ሃገር መሆን 

እንደማይችሉ ይደነግጋል። በዚህ አንቀፅ መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ በውጭ ጠላት ተወረርኩ ብሎ መገንጠል የሚችል ህዝብ 

የለም። ኢሕአዴግ “ችግር የለም፤እኔ እገነጥላችኋለሁ!” ቢልም የተባበሩት መንግስታት እውቅናን አያገኝም።ይህ ማለት በዓለም 

ዓቀፍ ህግ ለሃገር ግንባታ የሚያስፈልጉ ተቋማትን እና መከላከያ ሰራዊት ጨምሮ እንዲኖረው አይፈቀድለትም ማለት ነው።

ይሄን የፃፍኩት በእኔ እድሜ ያሉ ወጣቶች የጎሳ ፖለቲካ ቁማር ማስፈፀሚያ እንዳይሆኑ ለማሳሰብ ነው። የተማሩ የምትሏቸው 

ሰዎች እዚያ ውስጥ የገቡት ከሌላው ነጥለው ለብቻ ሊረግጧችሁ እና እናንተን ከሌላው ጋር ተወዳድሮ በፖለቲካ ማሳመን 

ስለሚያቅታቸው ከሌላው የሚነጥላችሁን እና ለማሳመን ከጎሳ መመሳሰል በቀር ምንም እውቀት የማይጠየቅበትን አካሄድ 

ስለመረጡ ነው። በዚህ መንገድ ፖለቲካን የሚያራምዱት አብዛኞቹ ማለት ይቻላል የተማሩት በምዕራቡ ዓለም ቢሆንም በዚያ 

የነበረውን እና ስለ አንድነት የተደረገውን ጦርነት እንዲሁም ያን በማድረጋቸው ያገኙትን ጥቅም እና ዛሬ ላይ ከሌላው ዓለም 

በተሻለ ሃብታም መሆን የቻሉበትን መንገድ በጎሳ ለመነጠል ለሚፈልጉት ህዝብ አይነግሩትም። ምክንያቱም ይህ ህዝቡን 

ያነቃዋልና ነው። የነቃ ህዝብን ደግሞ እንደ ጭቃ በፈለከው ዓይነት ቅርፅ ባሻህ መንገድ አጠፈጥፈውም። ስለዚህ ይህን ማድረግ 

አይፈልጉም። በጎሳ ፖለቲካ የተረጋጋ ሃገር እና ሰላም እመሰርታለሁ ማለት ፈፅሞ የማይቻል ቢሆንም አንድ ህዝብ የመጨረሻ 

ፍላጎቱ ከሆነና ሌላ አማራጭ ከሌለ በግድ አብረህ ኑር ማለት እንደማይቻልም የታወቀ ነው። ይህን ለማድረግ አንቀፅ 39 

በህገመንግስቱ ኖረ አልኖረ ምንም የሚፈይደው ነገር የለም። በደለኝ በሚለው አካል የመገንጠል ‘መብት’ ተሰጥቶት በበዳዩ 

ፍላጎት ነፃ የወጣ ህዝብ የለም።

የአንድነትም ሆነ የጎሳ ፖለቲካ አቀንቃኞች አንዳንዶቹ ብዬ በጨዋ ደንብ ዲፕሎማሲያዊ ካላደረኩት በቀር አብዛኞቹ ፖለቲከኞች 

ያለውን እውነታ እና የዓለም አሰራር መናገር አይፈልጉም። ይህ በማወቅም ባለማወቅም ሊሆን ይችላል።የሚታየው ግን በሁለቱም 

ወገን የራሳቸውን ፍላጎት ብቻ የሚያስጠብቅ የተካረረ አካሄድ ነው። ይህ ለሁለቱም የሚጠቅም መንገድ አይደለም ብየ 

አምናለሁ። 

ቤንጃሚን ፍራንክሊን ባንድ ወቅት ለአሜሪካ ህዝብ “ለተኩላ ፖለቲከኞች በግ እንዳትሆን፤ይበሉሃልና!” ብሎ መልክት 

አስተላልፏል። እኛም ከመልክቱ ትምህርት መውሰድ ይኖርብናል። ከስሜት እና ከመፈክር ባሻገር እውነትን እንፈልጋት። 

ለጊዜው ፅሁፌን ከብላታን ጌታ ሎሬት ፀጋየ ገ/መድህን ቀዌሳ ‘ኢትዮጵያዊነት’ ላይ ይህችን ልቆንጥርና ልዝጋው። ፅሁፉ 

እንደሚቀጥል ተስፋ አአደርጋለሁ።

•••የኢትዮጵያዊነት ምስጢሩ

ወንድምህን መጥላት ሳይሆን፥ራስክን ማወቅ ነው ከስሩ።

ሰው በወንድሙ ሲሳለቅ፥ያው በራሱ እንደ መሳለቅ

ነውና ከቅድመ ታሪክ፥ “አስቀድመህ ራስክን እወቅ”

መባሉ በጥላቻ ዚቅ፥ታውረህ ወንድምክን ስትንቅ

ያው ራስህን ነው የናቅከው፥ከራስህ ጋር ነው ትንቅንቅ

የዘረኝነት በሽታ፥መልሶ ራስክን ስለሚያንቅ

መነሻውን ያላወቀ፥መድረሻ ግቡንም አያውቅ።•••

•••የካም ቤት ክብሯን ሳትለቅ፥ስትማጠቅ ከሌሎች ጋር

ኢትዮጵያዊነት ህብር ሆነ፥ባለብዙ ቀለም አውታር

ካም በሕዋው ጠረፍ ዳሱ፥በእምቅድመ ዓለም አድማሱ

ኦሮሞም፥አማራም፥ትግሬም በኢትዮጵያዊ ኩሩ ቅርሱ

ፅኑ ማተብ ነው መንፈሱ፥መልኮስኮስ አይፈቅድም ነፍሱ።

ኢትዮጵያዊነት ረቂቅ ነው በመናፍቅ የቀን እርካብ

ሊደርሱበት የማይቻል፥በትምክህተኝነት ዛብ

ወይ በጎሳ በላይነት፥በጎጠኝነት ልበ እባብ

የማይሞከር እሴት ነው፥በዘረኛና በጠባብ።•••

•••ይሄ ተለጉሞ መዳህ፥ተጨቁኖ መረጋጋት

አጎብድዶ ለአምባገነን፥እንደ መጋጃ መነዳት

ኢትዮጵያዊነት አይደለም!

ይሄ ሆድ አምላኩ ግሳት፥አጉል ማቀርሻት እንደ አራስ

እንደ ተኮላሸ ጥጃ፥የአምባገነን መዳፍ መላስ

ኢትዮጵያዊነት አይደለም!!!!

@Kidus Mehalu