12 02 2015
☞ ሁለት ኮሎኔሎች ታስረዋል።
በሰራዊቱ ውስጥ የዘረኝነት ጥቃት እየተፈጸመ ነው። የሰራዊቱ ተቃውሞ እንዳይስፋፋ ወያኔ ሰግቷል። በምስራቅ ኢትዮጵያ የሰፈረው የደቡብ ምስራቅ እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባልት ከአለቆቻቸው ጋር የፈጠሩት አለመግባባት እየተካረረ መምጣቱን በቦታው የሚገኙ ወታደራዊ ደህንነቶች ያደረሱት መረጃ ጠቅሷል።
ከቀድሞ በተለየ ሁኔታ የመከላከያ ሰራዊቱን እየሰበሰቡ መገምገም ማሰር የቀጠለ ሲሆን ከመሃል አገር ተመድበው የመጡ አዳዲስ አባላት በሰራዊቱ መካከል ገብተው ውጥረቱን ለማርገብ እና ለማዘናጋት ቢያስተባብሩን እንዳልተሳካ ታውቋል።
በሕገመንግስቱ በማዕረግ እድገት እንዲሁም በጥቅማጥቅሞች ዙሪያ የተነሳው ጥያቄ ከወር በፊት አራት ወታደራዊ መኮንኖች መታሰራቸው ሲታወስ ከሁለት ቀን በፊት በተደረገው ግምገማ ኮሎኔል አብደላ ጫልቺሳ እና ኮሎኔል ተከተላቸው በወጉ የተባሉ ወታደራዊ መኮንኖች ወደ እስር ቤት መወርወራቸው ታውቋል።
የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ሕገመንግስቱ መሰረት ያደረገ አስተዳደር በኢትዮጵያ የለም ሕዝቡ በፖለቲካ በኢኮኖሚ ተጎዳ የሚል ጉዳዮችን በውይይት መድረካቸው ጊዜ አንስተው ቢወያዩበትም ጉዳዩ ተስፋፍቶ ከውይይት መድረክ ወደ ክርክር እና ተቃውሞ የተቀየረ መሆኑን እና በእዙ ውስጥ ውጥረት እንዲነግስ ማድረጉን የጠቀሱት ምንጮች የማዕረግ እድገትን በተመለከተ ለአንድ ብሄር ብቻ እንደሚሰጥ እና ሃገሪቱን በጋራ እስካገለገልን ድረስ የእንጀራ ልጅ የሚባል ነገር የለም አድልዎ እየተደረገ ነው የሚል ተቃውሞ የተፈጠረ ሲሆን በጥቅማ ጥቅም ዙሪያ እንዲሁ እንደ ማዕረግ እድገቱ የዘረኝነት ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑን በመግለጽ አቤቱታ እያሰሙ መሆኑን ምንጮቹ ተናግረዋል።
መከላከያ ሰራዊቱ ያነሳው ጥያቄ/ተቃውሞ ወደ ሰሜን እና ምእራብ እዝ እንዳይስፋፋ በጥንቃቄ የተያዘ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል።
~~ምንሊክ ሳልሳዊ~~
No comments:
Post a Comment