ቀን ጥር 27/ 2007
አመሰግናለሁ
ክብርት ምክትል አፈጉባኤ
ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰትር
ዛሬ እንደወትሮ በቀረበው ሪፖርት ላይ ዝርዝር ጉዳዮች የኤኮኖሚ የፖለቲካ እያልኩ ማብራሪያ እንዲሰጡኝ እንደማልጠይቅ የሚያውቁ ይመስለኛል፡፡ ይህንን ዝርዝር በህዝብ ፊት አቅርበን እንዳንዳኝ በሩን ዘግታችኋል፡፡ በሪፖርቱ ውስጥ ገፅ 13 የመጨረሻ ፓራግራፍ ስለምርጫ ያነሱት ላይ ብቻ ማተኮር እፈልጋለሁ፡፡ በዘንድሮ ዓመት ከሚሰተናገዱት ኩነቶችና ዋነኛው የምርጫ ስራ እንደሆነ ገልፀው ሰላማዊና እና በህዝባችን ዘንድ አመኔታ ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሰት በሁሉም መስክ አስፈላጊውን ዝግጅት ያደረገና በቀጣይነትም ሂደቱን በንቃት በመከታተል መንግሰታዊ ግዴታውን ይወጣል፡፡ የሚል ነው፡
የመንግሰት ግዴታ መወጣት ያሉት፤
· ምርጫ ቦርድ ከመቼ ጀምሮ ነው ለፓርቲዎች መሪ መምረጥ የጀመረው?
· ፍርድ ቤቶች ፓርቲዎች የሚያቀርቡትን ክስ አልቀበልም የማለት መብት አላቸው ወይ?
· የምርጫ ቦርድ ህገ ወጥ አስተዳደራዊ ውሳኔ ለማሰፈፀም የፖሊስ ሀይል ማስማራትና ቢሮ የመዝረፍ መብት ማን ነው የሰጠው? ይህ የመንግሰት ግዴታ አካል መሆኑ ነው?
· ገለልተኛ ምርጫ ቦርድ በሌለበት እና ፍርድ ቤት በሌለበት ሀገር በሪፖርት ውስጥ የገለፁት ዓይነት ምርጫ ከየት ነው የሚመጣው?
አንድነት ፓርቲ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ከግብ ግብ ነፃ የሆነ ፖለቲካ ለማራመድ ቁርጠኛ ሲሆን በጉልበት ድንክ ማድረጋችሁ ገዢው ፓርቲም ሆነ መንግሰቶ የዚህ ዓይነት ፖለቲካ ለመቋቋም አቅም እንዳነሰው ማሳያ አድርገን እንወሰደዋለን፡፡ ከዚህ ውጭ ሊሰጡኝ የሚችሉት ማብራሪያ የሚኖር አይመሰለኝም!!!
በዚህ የፖለቲካ ውሳኔ በሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ በእረሶ የአመራር ዘመን የተፈፀመ አሳዛኝ ታሪክ ሆኖ ይመዘገባል፡፡ ይህ ያሰመዘገባችሁት ታሪክ ለእኔም ለእናንተም ልጆች ታሪክ ፍርድ ይቀመጣል፡፡
እንኳን ደስ ያላችሁ!!!!!
እንኳን ደስ ያለዎት!!!!!
አመሰግናለሁ!!!!
ግርማ ሠይፉ ማሩ
No comments:
Post a Comment