የከምባታ ህዝቦች ኮንግረንስ እጩዎቹን አስመዝግቦ እያለ ምርጫ ቦርድ ትናንት የካቲት 4/2007 ዓ.ም በኢቢሲ በኩል ፓርቲው እጩዎቹን እንዳላስመዘገበ መግለጹ መራጮቹን ለማዘናጋት የተደረገና ሀሰተኛ መረጃ ነው ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርድሎ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡
አቶ ኤርጫፎ አክለውም ከምባታ ውስጥ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በተመዘገቡበት ወቅት የተሰጣቸው ደረሰኝ በእጃቸው እንደሚገኝ በመግለጽ ፓርቲያቸው እንዳልተመዘገበ በቴሊቪዥን መግለጫ መሰጠቱ ሆን ተብሎ ህዝቡን ተስፋ ለማስቆረጥ የተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ፓርቲው ዛሬ ጥር 5/2007 ዓ.ም ለምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤም በትናንትናው ዕለት የምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት አቶ ደምሰው በንቲ ለኢቢሲ የሰጡት መረጃና በቴሊቪዥን የተላለፈው ዘገባ ስህተት መሆኑን ገልጾ፤ ዜናው የተዛባ በመሆኑ ኢቢሲ ላጠፋው ጥፋት ይቅርታ ጠይቆ በዜና እወጃ ሰዓት ለዜናው ማረሚያ በማውጣት ለህዝብ ትክክለኛውን ዜና እንዲያደርስ ጠይቋል፡፡
ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment