Friday, 27 February 2015

ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ፥ ልዩ መልዕክት ከጎንደር ሕብረት

 Ethiomedia

የጎንደር ክፍለ ሃገር በዚህ በያዝነዉ ዘመን የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር በተባለ ቡድን የጥቃት ሰለባ መሆኑን በተደጋጋሚ ተጽፏል፣ ነገር ግን ግፍ እና በደሉ ሰሚ ካጣ ብዙ ዓመታትን አስቆጥሯል። 


አሁንም መከራዉ እና ሰቆቃዉ ያላቆመዉ የጎንደር፤ የወልቃይት እና ጠገዴ፤ እንዲሁም የጠለምት ህዝብ በቁሙ እዬተቀበረ ነዉ። 
የዛሬዉ መግለጫችን የሚያተኩረዉ ለሚመለከታቸው የማህበረሰብ አካላት ሁሉ መልዕክታችን በማስተላለፍ ነዉ።




ክፍለ ሃገሩ ካሉት ሰባት አዉራጃወች የወገራና የደባርቅ አውራጃ ወረዳዎች አብዛኛወቹ በጉልበት ወደ ትግራይ አስተዳደር እንዲጠቃለሉ በመደረጉ ኗሪው ህዝብ የወገን ያለህ እያለ ነዉ። 

የጎንደር ህዝብ ትጥቅ የለዉምና መሬቱን ፈርቶ ይሰጣል በሚል ሥሌት አሁንም እንደገና የጭልጋን እና የጎንደር ዙሪያ ወረዳዎችን ለመቆጣጠር የትግራይ ህዝብ ነጻ አዉጭ ግንባር ከነበሩት አጥፊ እና ጠብ ጫሪ ሚሊሻዎቹ በተጨማሪ፤ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ አዲስ ሚሊሻዎችን በማሰልጠን የወልቃይት ወገኖቻችንን የጎንደሬነት ጥያቄም ሆነ የይሥሙላ ምርጫን በግፍ ለማፈን ተጨማሪ
ዝግጅት በማድረግ ላይ እንዳለ በተለያዩ የዜና አውታሮች ተዘግቧል። 


መልክታችን አንድ እና አንድ ነዉ። 


ድንበራችን ተከዜ ነዉ! እያለ ያለዉ የመላዉ የሰባቱ አዉራጃወች የጎንደር ሕህዝ ድምጽ መከበር አለበት ።


የወያኔ ወረዳዎችን የመንጠቅ በሽታ ጎንደርን ብሎም ኢትዮጵያን የመበታተን ዘመቻ በመሆኑ ይህንን ሴራ ለመቀልበስ በዬአዉራጃዉ እና በየወረዳዉ ሁሉም በየአካባቢው መሪዉን መርጦ ለመብቱና ለድንበሩ ዘብ የመቆም ታሪካዊ ግዴታ አለበት። 


ሙሉ መልክቱን ለማንበብ ሊንኩን ጫን በሉት፥


http://www.ethiomedia.com/10parts/gonder_hibret_022215.pdf

No comments:

Post a Comment