Wednesday 10 September 2014

ለአዲሱ አመት!

    ጳጉሜ  5 2006      10 09 2014  
                                                                            
እንኳን ለ2007 ለአዲሱ አመት አደረሰን !                                         
ከአብዩ ጌታቸው ስታቫንገር ኖሮዌ


አዲሱ አመት የጤና የሰላም  የነፃነት የፍትህ የእኩልነት የዲሞክራሲ እና የአንድነት ይሁንልን ! አሮጌውን ጨርቅ ጥለን አዲስ የምንለብስበት አመት ይሁን !

ሁላችንም እንደምናውቀው በአሁኑ ወቅት በሃገራችን በኢትዮጵያ በህዝቦቿ ላይ እየደረሰብን ያለው የፍትህ የህልውና የኑሮ ውድነት የነፃነትና የዲሞክራሲ  ችግርና መከራ ከአመት ወደ አመት እየጨመረ መጣ እንጂ ሲሻሻል እና ሲለወጥ አላየንም ምክንያቱም የጥሩ አስተዳደር አለመኖር ነው ᎓᎓

ታዲያ የተበላሸን አስተዳደር  ወደ ተሻለ አስተዳደር መለወጥ የሁላችንም ኢትዮጵያኖች የዜግነት አላፊነት ነው ᎓᎓ ያም ማለት አንድ ሃገር  ከሌላው ሃገር ተለይታ ስትጠራ ያላት የህዝብ ቁጥርም አንዱ ነውና  እኔም አንቺም አንተም ከቁጥሮቹ አንዱ መሆናችንን መገንዘባችንን መረዳት አለብን ᎓᎓ ታዲያ ነፍስ ካወቅን በኅላ እራሳችንን መጠየቅ ያለብን እኔ ቁጥር ብቻ ነኝ ወይስ እነደ አንድ ሰው እየኖርኩኝ ነው ብሎ እራስን መጠየቅና መልሱን አመዝናኖ እራስን እነደሰው መቁጠር አስፈላጊ ነው  ምክንያቱም አንድ ሰው እነደሰው ካሰበ ምን እንደሚያስፈልገው ያውቃልና᎓᎓ ከሚያስፈልገን ነገሮች ዋናው እነደ አንድ ሰው ካሰበ ጥሩ መስተዳድር ሰላም ፍትህ ነፃነትና እኩልነት  ዲሞክራሲ እና የህግ የበላይነት ነው᎓᎓ 

እነዚህ ደግሞ ወደ ተሻለ እና ወደ ተቻቻለ የኑሮ መስመር ይመሩናል᎓᎓ ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው በጣም አስከፊ የአገዛዝ ስርዓት ዝምታን መምረጥ መፍትሄ አይደለም ታዲያ እያንዳንዳንዳችን ይህን ከአተዳደር ተፅዕኖ የወረስነው አልያም ከአስተሳሰብ አለመብሰል የተነሳ ወይም ችግሩ በሬን አላንኳኳም  እያልን  ሰው ሆነን  የቁጥር ሟሟያ  ስለሆንን  እንደ ሰው በሃገራችን ለመኖር  ያልቻልንበት ምክንያት አንዱ ሲሆን  ዋናው ሚዲያውን የተቆጣጠረውን ክፍልን  ፈዞ ማዳመጥ እና አብሮ በመፍዘዝ ትክክል እንዳልሰራ እያወቅን እረ በቃ ይህስ አገዛዝ ይቀየር በተግባር  እንደማለት ዝምታን መመረጣችን አንዱም ምክንያት ነው᎓᎓

ሌላው ዋና ትልቁ እና ዋናው ነገር ደግሞ እንደ ሰው አሰበው ይህ ለኔም ለአንቺም ላንተም ለሃገራችንም ጥሩ አይደለም አገዛዙን መለወጥ አለብን ብለው ከተነሱት ጋር በህብረት ከመስራትና ከመተግበር ይልቅ ጥግ ጥጉን እርስበርስ መንሾካሾኩን ስለመረጥን ነው᎓᎓ይህም አንዱ ደካማ ጎን ነው᎓᎓ በዚህም የተነሳ ስንቱን  ሃገራችን ያፈራቻቸውን ጀግኖች  ልጆችዋን ለእስር ለመከራና ለስቃይ ለስደትና ለሞት አበቃን ?

ያም ሆነ ይህ በአዲሱ አመት ያለንን የተለያየ የእያንዳዳችንን ተስጥዖ በመጠቀም ለለውጥ ትግል መነሳት ይጠብቅብናል ᎓᎓ የትግል ዋና አላማ ትግሉ ተቀጣጥሎ ወደ እያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል ማድረስና  ህዝቡ በህብረት ሆኖ  ችግርክ ችግሬ ነው ብሎ በሃሳብና አላማ  በህብረት ተነስቶ የትግሉ ሰሚና ተመልካች ብቻ ሳይሆን ተሳታፊም ተገባሪም እንዲሆንና ከአለመበትና ከሚፈልገው ግብ በፅናት መድረስ መቻል ነው᎓᎓የታሰሩት ወገኖቻችን ለማን ብለው እንደሆነ መገንዘብ ይገባናል᎓᎓

ሌላው ደግሞ የስርዓት ለውጥን ትግልን በተናጠል መንገድ ማካሄድ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን መከራ ከማስፋትና እድሜ ከማራዘም ውጭ ለህዝባችንም ሆነ ለሃገራችን የፈጠረው አዲስ ነገር የለም᎓᎓ መስመር ባልያዘና በተበታተነ መንገድ የሚደረግ ትግል ለመጠቃትና ከአለመበት ዓላማ ሳይደርስ ለመጥፋት የተመቻቸ ይሆናል᎓᎓

በተለያየ መንገድ ተሰልፈው አላማቸውና ራያቸው አንድ የሆነና የሚመሳሰል ከሆነ በጋራ በህብረት በመሆን ትግላቸውን ቢያካሄዱ መረሳት የሌለበት  ነገር የትግሉን እድሜ የሚያሳጥር እና ለህዝቡም ከጎኑ ቶሎ ተደራሽነት የሚያመጣ የሂደት ጉዞ ያደርጋል᎓᎓ ዓላማው የህዝቡን ፍላጎትን ለሟሟላትና  የህዝቡን የመብትና የስልጣን ባለቤትነት እንዲሆን ለማድረግ እስከሆነ ድረስ᎓᎓

እንዲህም ሆኖ የህዝቡን ፍላጎትና ዓላማ ለማግኘት ቀላል ሆኖ ባይገኝም መሆን ያለበት የሁላችንም አዕምሮ አይንና ጆሮ ትኩረት መስጠትና ማስተዋል ያለበት ህዝባችንና ሃገራችንን ኢትዮጵያ ለዚህ አስከፊ ወደር የለሽ የአስተዳደር  የፍትህ እና የኑሮ አዘቅት ውስጥ እንድትገባና ለዚህ መፍትሔ በህብረት ሆነን  እንዳንታገል እንቅፋት የሆነውን የወያኔ ኢህዲግ ስርዓት ላይ መሆን አለበት᎓᎓

ስለዚህ በዚህ በመጣው በ 2007 አዲስ ዓመት የሁላችንም ዓላማ ህዝባችን ከመቼውም ግዜ በበለጠ ለፍትህ ለነፃነት ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በተነሳበት ወቅት እንዴትና በምን መንገድ በህብረት ሆነን የደረሰብንና የሚደርስብንን እንቅፋቶች እየተረማመድን  ትግሉን ከአለምንበት ዓላማ ማድረስ እና ፍትህ እና ሰላም ለተጠማው ህዝብ በተቻለው መንገድ ሁሉ ከጎኑ ቶሎ እንዲደርስ አጋርነታችንን በተግባር ማሳየት የሁላችንም  የዜግነት አላፊነት ነው᎓᎓ 

 መርሳት የሌለበት ሃገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ በ 21ኟው  ክፍለ ዘመን  ከሌሎች በአለም ዙሪያ ከሚገኙ ሃገራት ጋር ስትነፃፀር   በሰብአዊ መብት እረገጣ ᎓ ጋዘጠኞችን ነፃ ፕሬሶችን በማፈን  ᎓ በኢፍትሃዊ አሰራር ᎓በኑሮ ውድነት ድህነት  ᎓ ትምህርት በጨረሰው ወጣት ላይ ያለ የስራ ማጣት ችግር ᎓የባለስልጣናት በወንጀልና በሙስና መጨማለቅ ᎓ በአንድ ድርጅት አምባገነንነት᎓ እኔን ብቻ ስሙ አካሄድ ᎓የእምነት ነፃነት የሌለባት᎓ጀግኖችና እውነትን ይዘው የሚቆረቆሩላት የህሊና እስረኞች ወደ እስር ቤት የሚጣሉቧት ᎓የሴቶች እህቶቻችን በአረብ ሃገርም ሆነ በጎረቤት ሃገር የሚደርስባቸው ስቃይ᎓ ገበሬው መሬቱ ላይ ለሌላ ባሪያ ሆኖ መኖሩ እና የዘር መርዝ  በህብረተሰቡ ላይ መርጨት ᎓ ማፈናቀል᎓ ከመቼውም ግዜ በበለጠ የተማረው ክፍል በፍትህ እጦት ሃገር ጥለው የሚሰደዱባት ተሰደውም እንደሌላው ዜጋ  በተሰደዱበት ሃገር የማይከበሩበት  የሲቪክ ድርጅቶች ሃገሩን ትተው የወጡበት  በምስኪኑ ህዝብ  በተማሪው በሰራተኟው በሰራዊቱ ላይ ያለው የዘር በድሎ᎓በአጋዚ በሚባሉ ሠላማዊ ህዝብን ማስጨረስ ᎓ በአጠቃላይ  ያለንበትን ወቅትና የወያኔን ኢህዲግ አገዛዝ ስናየው  ከአለም መጨረሻ ከተመደቡት ሃገራት ጋር ኢትዮጵያም አብራ ናት ስለዚህ  የግድ ለውጥ ያስፈልገናል᎓᎓ የወያኔ ኢህዲግ  አገዛዝ ከግዜው ጋር አብሮ የማይሄድ ስርዓት ነው᎓᎓

በስተመጨረሻ አዲሱ አመት 2007  የነፃነት  የፍትህ  የዜጎች እኩልነት እና የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለውጥ የሰፈነባት ኢትዮጵያ እንድትሆንልን ሁላችንም በቻልነው መንገድ በሰላማዊ መንገድም ሆነ   በሁለገብ ትግል  የዚህን መጥፎ ስርአት ለመጣል ከሚታገሉት ወገኖቻችን ጋር በመሆን  እንደ ሰው የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል በማለት የትግሉ ተካፋይ በመሆንና  በትግላችን  ለውጥ የሚመጣበትና የምናይበት አዲስ ዓመት ይሁንልን !!!



ኢትዮጵያ ለዘላለም በልጆችሽ ተከብረሽ ኑሪ !



No comments:

Post a Comment