Tuesday 28 October 2014

ቅዱስ ሲኖዶስ ተናወጠ ። የሲኖዶሱ ምልእተ ጉባዬ ሳይታሰብ እንዲቋረጥ ሆኗል።

‹‹ዓላማዎ ማኅበሩን መዝጋት ነው፤ አይደለም? አይዘጋም!›› - የምልአተ ጉባኤው አባላት
Minilik Salsawi


Image

በዛሬው እለት በተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ አቡነ ማትያስን ተጠሪነትዎ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ በቤተ ክርስቲያን ሕግ ቢመሩ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱን ቢያከብሩ ይሻልዎታል፤ ሕግ አይገዛኝም ካሉ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንሔዳለን፡፡ ሲል ማስጠንቀቁ እና ይህን ተከትሎ የሲኖዶሱ ምል አተ ጉባዬ ድንገት መቋረጡ ታውቋል።

ፓርትርያርኩ ብጹእ አቡነ ማትያስ በተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን ማህበርንም ይሁን ማንኛውንም አካል አክራሪና አሸባሪ በማለት አቋማቸው የሚቀጥሉ ከሆነ በውግዘት እንደሚለዩ ቅዱስ ሲኖዶሱ በጥብቅ አስጠንቅቋቸዋል። ፓርትርያርኩ በትላንትናው እለት የተጀመረውን አጀንዳ በመሰረዝ አዲስ አጀንዳ ይዘው የመጡ ሲሆን ከዚሁ ጋር አያይዘው ይህንን የተቃውሙትን የሲኖዶስ አባልት ለማስፈራራት እና ለማሸማቀቅ ሞክረው አልተሳካላቸውም በዚሁም መሰረት ቀጣይ አጀንዳዎች በድምጽ ብልጫ ለውይይት እንደሚቀርቡ ሲታወቅ ፓርትርያርኩ ስብሰባውን በህገ ስነ ስር አት መምራት ካልቻሉ ምልአተ ጉባኤው ሌላ ሰብሳቢ መርጦ እርሳቸውን ተሰብሳቢ በማድረግ ስራውን እንደሚቀጥል ታውቋል።

በቅ/ሲኖዶስ ከተወሰነው በተፃራሪ ማኅበሩ ለልዩ ጽ/ቤታቸው ሳያሳውቅ አንዳችም መርሐ ግብር እንዳያከናውንና ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ የሚወስዷቸውን ሕገ ወጥ ርምጃዎች መከላከልን በተመለከተ መመሪያ እንዲሰጥ ብፁዕ ዋና ጸሐፊው እና ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠይቀዋል፡፡ማኅበራት ገንዘባቸውን ወደ ማእከላዊ ካዝና ያስገቡ ይላሉ፤ የማኅበራት ዓላማ ገንዘብ ማሰባሰብ አይደለም፤ ገንዘብ አሰባሳቢ አይደሉም፤ ለተቋቋሙበት ዓላማ ያሰባሰቡትን ገንዘብ ግን እንዴት ሥራ ላይ እንዳዋሉት መቆጣጠር ይገባል፡፡ሲሉ የጉባዬው አባላት ተናግረዋል።የተቋረጥው ስብሰባ ነገ ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ  http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=88884

No comments:

Post a Comment