Monday 4 May 2015

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እየታደኑ እየታሰሩ ነው እንዲሁም በየክፍለ ሀገሩ የሚገኙ አባላት ላይ የሚፈፀመው ድብደባ ቀጥሏል

• ‹‹የተጀመረውን የሀሰት ክስ እውነት ለማስመሰል የታቀደ ነው››
  
በየክፍለ ሀገሩ የሚገኙ አባላት ላይ የሚፈፀመው ድብደባ ቀጥሏል


የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ሰበብ እየታደኑ እየታሰሩ መሆኑን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ሀሙስ ሚያዝያ 22/2007 ዓ.ም ብሌን መስፍንና ተዋቸው ዳምጤ ከመስሪያ ቤት ተይዘው የታሰሩ ሲሆን ሚያዝያ 24/2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ‹‹ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተደረገውን አመጽ መርታችኋል፡፡›› በሚል ፖሊስ ክስ እንዳቀረበባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡


በተመሳሳይ ዛሬ ሚያዝያ 26/2007 ዓ.ም ማቲያስ መኩሪያ ቤቱ ውስጥ እያለ በፖሊስ ተይዞ ታስሯል፡፡ማቲያስ፣ ብሌንና ተዋቸው ወረዳ 10 (ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ) ታስረው ይገኛሉ፡፡ ይህንን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የሚደረገው እስርም ‹‹መንግስት በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የጀመረውን የሀሰት ክስ እውነት ለማስመሰል የታቀደ ነው፡፡ ፖሊስ ምርመራ ሳይጨርስ በሀሰት 20 አባላትንና 6 አመራሮችን አስረናል ብለው ነበር፡፡ እነሱ የፈለጉት ይህን ሚዲያ ላይ ወጥተው በሀሰት የፈፀሙትን ውንጀላ ማሰመሰል ነው፡፡›› ሲል አቶ ዮናታን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡


በሌላ ዜና በየክፍለ ሀገሩ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ደህንነትና ፖሊስ የሚፈፅመው ድብደባ አሁንም መቀጠሉ ተገልጾአል፡፡ በዛሬው ቀን የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪና የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነችው የሀሳብ ጌታቸው ‹‹ለሰማያዊ ፓርቲ ወረቀት በትነሻል›› በሚል ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀሙባት ተገልጾአል፡፡
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
 ተጨማሪ ዜና
የሰማያዊ ፓርቲ በብአዴን አህዮች የሚደርስባቸዉ ስቃይ ደ/ጎንደር..... የድርጅቱ ሰብሳቢ የሆነዉ አለማየሁ አደመ ሚያዚያ 20 ጧት አማን አዉለኝ ብሎ ሀገር ሰላም ይሁን እያለ ወደ ስራ ቦታዉ አመራ ።ሆዳሞች የገዛ ወንድማቸዉን በማረድ ደም በማፍሰስ የሚደሰቱ የህወሀት ገረድ ሆድ አደር ባለስልጣን በሸረቡት ሴራ እየተንቀሳቀሰ ወጣቱን በማደራጀት ስልጣናችን ያሳጣናል ብለዉ በመስጋት በእንሰሳ አስተሳሰባቸዉ ከጧቱ 3ሰአት ያለ ምንም ጥያቄ ወስደዉ አሰሩት።ቀጥሎም ከቀኑ11ሰአት ላይ አዉጥተዉ በሰዉ ልጅ እንዲህ ይሆናል ተብሎ በማይታሰብ ሁኔታ እጅግ ዘግናኝ በባህላችን ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ ተሰብስበዉ ቀጠቀጡት።በህይወትና በሞት መካከል እያለ የአካባቢዉን ነዋሪ በትእይንት እያሳዩ ሲመቱት ነዋሪዉም አስቀያሚን ድብደባ አስቁሞታል።እነዚህ የአካባቢ ታጣቂዎች ሳትገድሉ እንዳትለቁ ተብለናል ብለዉ ወደ ህዝቡም አፈሙዝ እንዳዞሩ ከስፍራዉ ያገኘነዉ መረጃ አመልክቷል። በአሁኑ ሰአት ይህ ጠንካራ ታጋይ የህይወቱ ነገር በጣም አሳሳቢ የሆነ ሲሆን ጎን አጥንቱ እግሩና እጁ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።




































No comments:

Post a Comment