Sunday 7 December 2014

በርግጠኝነት የምናገረው ነገር ያልታሰረ እና ያልተሰደደ ፍትህ ናፋቂ በሙሉ በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ይገኛል!

መድረክ ታህሳስ አምስት ሊያደርግ ያሰበው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ተሰጠው። ይህ የሪፖርተር ዜና ነው... ርግጥ ሪፖርተር ''ተፈቀደለት'' ብሎ ነው የዘገበው እኔ ግን በሀገ መንግስቱ ውስጥ ለሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ ሰጪ እና ከልካይ የሚባል ነገር ባለመኖሩ ከህገ መንግስቱ ጋር ላለመጋጨት ብዬ እውቅና ተሰጠው በሚል አስተካⷌዋለሁ... (የቢሮው ስም ራሱ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ጽህፈት ቤት ነው የሚለው!)


መድረክ በታህሳስ አምስቱ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያነሳው ያሰበው ጥያቄ ብዙ ፓርቲዎች የሚጋሩት ነው። እንደውም የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር ''አታድርግም'' ተብሎ በህገ ወጥ መልኩ የተከለከለው ሰልፍ ራሱ አንግቦ የተነሳው ዛሬ መድረክ ሊጠይቅ የተነሳው አይነት ጥያቄ ነው። ማሳወቂያ ጽፈት ቤቱ ለአንዱ እውቅና ሰጥቶ ሌላውን አይናችሁን አያሳየኝ የሚለው ለምን ይመስልሃል... ብላችሁ ብትጠይቁኝ ይቺ የኢህአዴግዬ ስራ ናት ብዬ ድንጋይ ነክሼ እምላለሁ።

እንደምታውቁት እና እንደማታውቁት ኢህአዴግዬ ከሁሉ ከሁሉ የመከፋፈል ስራ በደንብ አድርጋ ነው የምትችልበት። በርሷ ቤት እነ ሰማያዊ ተከልክለው እነ መድረክ ሲፈቅድላቸው መድረክን በጥርጣሬ እንድናየው ፈልጋ ነው። (ሳስበው ተቃዋሚዎችን ለመከፋፈል ተብሎ የተመደብ የስራ ክፍል ሳይኖራት አይቀርም፤ እንደውም ስሙ ''የተቃዋሚዎች ከፋፋይ ዋና ስራ ሂደት...'' የሚባል ይመስለኛል)

ተባኖብሻል..... ብሉልኝ!

በርግጠኝነት የምናገረው ነገር ያልታሰረ እና ያልተሰደደ ፍትህ ናፋቂ በሙሉ በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ይገኛል!

አቤ ቶክቻው
ምንጭ  ከአቤ ፌስ ቡክ  
ምስል ከጉግል

No comments:

Post a Comment