Wednesday 22 April 2015

የህዝባችን ብሶት ይሰማን !

ኢትዮጵያዬ                     22 04 2015

በዛሬው ዕለተ እሮብ  በአዲስ አበባ በአራቱም አቅጣጫዎች  ተጠራርቶ በወገኖቻችን በኢትዮጵውያን ላይ በደቡብ አፍሪካ በህወታቸው ለተቃጠሉት ፣ በሊቢያ እስከ ነፍሳቸው ለታረዱት ፣ በየመን መውጪያና መሸሸጊያ አጥተው የሚደርስላቸው ወገን እና መንግስት ላጡት ወገኖቻችን ፣ በሜድትራንያን ባህር የሻርክ እራት ለሆኑብን ወገኖቻችን  የደረሰብንን ዘግናኝ እና አሰቃቂ ግድያንና አፈናን  ለማውገዝ በተሰበሰበው ህዝብ ላይ ወያኔ መራሹ የኢህዲግ ፖሊስ እና የፌዴራል ፖሊስ  ከህዝቡ ጎን በመቆም ማውገዝ ሲገባቻው በተቃራኒው በዚህ ወቅት በማይጠበቅና በማይታሰብ ሁኔታ በሰላማዊ መንገድ ብሶቱንና የወገኑን ሃዘን እና ጭንቀት ሊጋራ የተሰበሰውን የአዲስ አበባን ህዝብ ላይ ሲተኩሱበት ፣ በአስለቃሽ ጭስ ሲጎዱትና ሲበትኑት ፣ ሲደበድቡ ፣ ሲያፍኑና ሲያስሩ  መገኙታቸው እጅግ አሳዛኝ ድርጊትና ኢትዮጵያን መሆናቸው የሚያጠራጥር ነው ᎓᎓ ብዙ የአዲስ አበባ ህዝብ በደረሰበት ጉዳት በየመንገዱ ፣ በየቤቱ እና  በየሆስፒታሉ እነደሚገኝም ታውቃል ᎓᎓


 
 
 







የቆማችሁት ህዝብን እነደህዝብ በመሆን ለማገልገልና ለመጠበቅ ነው እንጂ  ላረጀና ለበሰበሰ አምባገነናዊ ስርዓት ግዚያዊ የመገልገያ መሳሪያ ለመሆን አይደለም ᎓᎓ ወቅቱ የለውጥ እነደሆነም ከህዝቡና በአገራችን ህልውና ላይ እየደረሰ ያለውንም እያንዳንዱን ሁኔታም ሳትገነዘቡት እንደማትቀሩ ህሊናችሁ ያውቀዋል ᎓᎓ እናንተ በመታደርሱበት በደል ተማሮ ስንቱ የተሻለ ሃገር ለመሄድ መንገድ ላይ እንደቀረ ቤት ይቁጠረው ᎓᎓ ዛሬም የኢትዮጵያ ህዝብ  በአንድነት ሆኖ ያሳያችሁ እና የነገራችሁ ጭቆናው ይብቃ ! ስደቱ ይብቃ ! የህዝባችን ደም በአሸባሪዎች በከንቱ ፈሶ አይቅር ! ቸነፈሩ ይብቃ ! ዘረኝነቱ ይብቃ ! መታሰሩ እና መገደሉ ይብቃ ! ነፃነትና እኩልነት ለሁሉም ! ሰብዓዊነት ይቅደም ! የመሰብሰብ ፣ የመናገርና የመፃፍ መብት ይከበር ! ሙስና ይብቃ ! መደብለ ፓርቲ ይኑረን ! ካለ አግባብ የታሰሩ የፖለቲካ አመራሮች እና አባላቶች ይፈቱ ! ጋዜጠኞችና ጦማሪያኖች ይፈቱ ! ህዝብ የመረጠው መንግስት ይኑረን ! በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ  በሃሰት የሚለጠፈው የሽብርተኝነት ፕሮፖጋንዳ ይቁም !  ለህዝቦች መሰደድና ስቃይ ተጠያቂው መንግስት ነው !  ፍትህ የበላይነት የሰፈነባት ሃገር ይኑረን !  ልዕልናዋ የተከበረ ዲሞክራሲያት ሃገር ይኑረን ! 

ወቅቱ የግድ የፖሊስ ሰራዊቱና የመከላኪያ ሰራዊቱ ከዘረኝነትና ከፖለቲካ ነፃ የሆነና ለህዝብ ዘብ የቆመ የሀገርን ህልውና የሚያስከብር  መሆኛው ግዜው አሁን ነው ᎓᎓ ህዝብን በማፈን የስልጣንን ግዜ ማራዘም ለአገራችን ኢትዮጵያና ህዝብ ጉዳት እንጂ  ምንም ጥቅም የለውም ! የአንድ ድርጅት ወይም ፓርቲ ጠበቃና አጃቢ መሆን  ይቁም ! መጪውን የለውጥ ግዜ እንደ አንድ ህዝብ እጅ ለእጅ ታያይዘን  የህዝባችንን ክብርና የአገራችንን ህልውና የምናስመልስበት ወቅት ነው !

ክብር ለኢትጵያውያን ! ሞት ለፀረ ኢትዮጵያውያን !

No comments:

Post a Comment