Sunday 19 April 2015

ISIS በመባል የሚጠራው የአረመኔዎች ጥርቅም 28 ኢትዮጵያውያንን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ ገደለ

  የእስላም አክራሪ ድርጅት የሆነው ISIS በመባል የሚጠራው  የአረመኔዎች ጥርቅም  28 ኢትዮጵያውያን ን በሊቢያ  በአሰቃቂ ሁኔታ ገደለ ᎓᎓ 

ዛሬ አልጄዚራ እነደዘገበው የ12ቱ አንገት በባህር ዳርቻው በካራ ሲቀላ የ16ቱ ጭንቅላት ደግሞ በበረሀው መሀል በጥይት ተነድሏል። 

በስደት አለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ኢ ሰብዓዊ ግፍ እና ግድያ ከዕለት ወደ እለት ከመቼውም ግዜ 

እየጨመረ መጥቶአል ᎓᎓ በአረብ ሃገራት  በሳውዲ ፣ በየመን ፣ በቤሩት ፣ እና በሌሎች ሃገራት እንዲሁም በአፍሪካ በኬንያ ፣ 

በሱዳን ፣ በደቡብ አፍሪካ ፣ በሊቢያና በሌሎችም የአረብና የአፍሪካ ሃገሮች ኢትዮጵያውያን በተሰደዱበት ሃገራት እየተገደሉ 

እየታፈኑና በየእስር ቤቱ እየተንገላቱ ሰብዓዊ ክብራቸው ተጥሶ  በሞትና በስቃይ ላይ ይገኟሉ ᎓᎓ 



ኢትዮጵዊ በዚህ መልኩ በአለም ፊት  ሲዋረድና  ሲገደል  እኛ ኢትዮጵያውን ከንፈር በመምጠጥ ብቻ ዝም ብለን ማለፍ የሚገባን ነገር አይደለም ᎓᎓ ኢትዮጵያ መንግስ አልባ ሃገር መሆናን በሚገባ እየተመለከትን  እንገኟለን ᎓᎓ ህዝባችን የችግሩ መፍትሄ በእጁ ነው ያለው በስደት ያተረፍነው መከራና ሞት ነው ᎓᎓ በስደት አገር እንዲህ ሆኖ ከመሞት  ለአገራችን በሚደረገው ለፍትህ ለነፃነት ለእኩልነት  ትግል በመሳተፍ መሞት የበለጠ ክብር ነው ᎓᎓ ለአገራችን ህልውና እና ለህዝባችን  ክብር ዘላቂ መፍትሄው በጋራ በመቆም ለዚህ ያበቃንን ችግር በመተባበር በማስወገድ ዘለቄታ ያለው  የችግራችንን መፍትሄ አሁኑኑ  ከተግባር ጋር መወሰን ይኖርብናል ᎓᎓

በግፍ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያንን  ነፍስ በገነት ያኑርልን !

እነዚህን ሊንኮች በመክፈት መመልከት ይችላሉ᎓᎓

http://www.aljazeera.com/news/middleeast/2015/04/isil-claims-massacre-ethiopian-christians-libya-150419104309814.html

ቪዲዮ http://www.vocativ.com/world/isis-2/isis-video-shows-mass-beheading-of-ethiopian-christians-in-libya/?fb_action_ids=848501618548970&fb_action_types=og.shares
http://www.jpost.com/Middle-East/New-Islamic-State-video-shows-shooting-beheading-of-Ethiopian-Christians-398563


No comments:

Post a Comment