Thursday 2 April 2015

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል: የቅ/ሲኖዶስ አባላት ራሳቸውን በመስጠትና ወቅቱን በዋጀ አካሔድ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያድኑ ጥሪ አቀረቡ፤ስለ አስተዳደራዊ ችግሮችና የወደፊት ስጋቶች ተናግረዋል

His Grace Abune Samuel, Archbishop of DICAC copy
  • እኛ ዘንድ ቀኖና እና ሥርዐት ሲጣስ ‘No’ ማለት የለም፡፡ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን ማስፈጸም ከኹሉም የሥራ ሓላፊዎች የሚጠበቅ ኾኖ ሳለ በዝምታ ማየት ነው፡፡ ምእመናን ናቸው ሃይማኖታችን እያሉ የበለጠ መቆርቆር እያሳዩ ያሉት፡፡
  • መልካም አስተዳደር ባለመኖሩ በየጊዜው በሚፈጠረው ውዝግብ የተነሣ÷ የቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖናዊ ሥርዐት ይጣሳል፤ የእርስ በርስ ግጭት ይስፋፋል፤ ሙስናና ዝርፊያ ይንሰራፋል፤ ገጽታዋ ይዳከማል፤ ኢኮኖሚያዊ አቅሟ ይቀንሳል፤ የሕዝብ ድጋፍ እና የውጭ ዕውቅና ይጠፋል፤ የውስጥና የውጭ ጠላቶቿ ይበረታሉ፤ አንድነቷ ተናግቶ በየመንደሩ ልዩ ልዩ እምነቶች ይፈጠራሉ፤ በመጨረሻም መበታተን እና መከፋፈል ይከተላል፡፡
  • ልቅ ዝርፊያና ሙስና፣ መንፈሳዊነት እና ሰብአዊነት የሌለው መሥመር የለቀቀ ዘረኝነት፣ የፋይናንስ ሥርዐቱን እና የንብረት አያያዙን የሚያዘምን አስተዳደራዊ ሥርዐት እንዳይኖር ከሚቃወም የአመለካከትና የተግባር ድክመታችን መላቀቅ ይገባናል፡፡ ወቅቱን የዋጁ፣ በተግባር የሚተረጎሙ ሕገጋት እና ደንቦች ያስፈልጉናል፤ በረጅምና በአጭር ጊዜ ዕቅዶች መመራት ይኖርብናል፤ ዕውቀትን መሠረት ያደረገ፣ በተሰጠው ሓላፊነት የሚጠየቅ፣ በማያቋርጥ ሥልጠና አቅሙን የሚገነባ የሰው ኃይል ምደባና ሥምሪት ያስፈልገናል፡፡
  • በታሪካቸው ከእነሐርቫርድ የሚወዳደሩ እና የሚልቁ የአብነት ት/ቤቶቻችን ሥርዐተ ትምህርት ከወቅቱ አንጻር ማደራጀት እና በየክልሎቹ ማስፋፋት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችንን ምሩቃን እንደ የክህሎታቸው በሥልጠና ማብቃት፣ በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሊቃውንት እና ምሁራን በአግባቡ ማሳተፍና መጠቀም ይጠበቅብናል
  • haratewahido.wordpress.com

No comments:

Post a Comment