Tuesday, 31 March 2015

Nigeria election: Muhammadu Buhari wins

Residents celebrate the anticipated victory of Presidential candidate Muhammadu Buhari in Kaduna, Nigeria 31 March 2015
Supporters of Gen Buhari celebrated as the results came in
Nigerian presidential poll has been won by Muhammadu Buhari, in the country's first election victory by the opposition.
His opponent, Goodluck Jonathan, has conceded defeat and called Gen Buhari to congratulate him on his victory.
Gen Buhari was ahead of Mr Jonathan by at least three million votes.
Observers have generally praised the election but there have been allegations of fraud, which some fear could lead to protests and violence.
However, a spokesman for Gen Buhari's All Progressives Congress (APC) party praised Mr Jonathan, saying: "He will remain a hero for this move. The tension will go down dramatically."
"Anyone who tries to foment trouble on the account that they have lost the election will be doing so purely on his own," the spokesman added in quotes carried by Reuters.
This is a hugely significant moment in Nigeria's history - never before has a sitting president lost an election, the BBC's Will Ross reports from Abuja.
For the first time, many Nigerians feel they have the power to vote out a government that is not performing well, our correspondent adds.
Nigeria has suffered from several attacks by the Islamist militant group Boko Haram, which has killed thousands of people in its drive to establish an Islamic state.
Many voters have said that they believe Gen Buhari is better positioned to defeat Boko Haram.

አውቀው ነው ስደተኞቹን የደበደቡት

በግሩም ተ/ሀይማኖት

ለሞቱት 46 ኢትዮጵያዊያ ሳዑዲ ተጠያቂ ናት…መደብደቧን አመነች

ትላንት ንጋት ላይ በሰሜናዊ ምስራቅ የመን ሀጃ አካባቢ በተደረገ የአየር ድብደባ አየር የ International Organization for Migration (IOM) ካምፕ ላይ ጥቃት ያደረሱት የሳዑዲ አረቢያ የቶር ጀቶች መሆናቸው ታወቀ፡፡ የሳዑዲ መንግስት ባለስልጣናትም ድብደባው በእነሱ ጀት መፈጸሙን አምነዋል፡፡ ድብደባው ግን ሆነጅ ተብሎ የተፈጸመ እንደሆነ የሚያሳይ ፍንጭ አለ፡፡ ቦታው የ UNHCR ካምፕ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ የ UNHCR አርማ ያለበት ድንኳን የተጣለበት መሆኑ እና የ UNHCR አርማ እየተውለበለበ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በእስከ አሁን ሁኔታ በጨለማ ሲደበድቡ ቅንጣት ስህተት አልነበረም፡፡ 


በሌላ በኩል ደግሞ አርማውን አላየንም አይባል ድብደባው የተፈጸው ንጋት ላይ ነው፡፡ አንዴ ሳይሆን በተደጋጋሚ ነው እየተመላለሱ የመቱት፡፡ ይሄ ምን ያሳያል እስኪ መንግስት ካለን መብታችንን የሚጠይቅልን ከሆነ ይሄን ይጠይቅ…..እባካችሁ ወገን እያለው ወገን እንደሌለው ሀገር እያለው ሀገር እንደሌለው የትም እየረገፈ ላለው ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ድምጽ እናሰማ፡፡ እባካችሁ የተኙትም ይንቁ ጠግበው ተገልብጠው እያደሩ ወገን እነሱ ባንኮራፉ ቁጥር እየረገፈ መሆኑን ይወቁት ይህን የሰው ልጅ ላይ የደረሰ አሰቃቂ እልቂት ያላየ ይይ ሼር አድርጉ……..በሁኑ ሰዓት የአየር ጥቃቱ ከወታደራዊ ተቋም ወደ ሲቪሉ ህዝብ እየወረደ ነው፡፡ በርካታ ሲቪሎች እየሞቱ ነው፡፡


በጣም የሚያሳዝንና ዘግናኝ አሟሟት ያዘለ ፎቶ ለመመልከት ይህን ይከፈቱ

Monday, 30 March 2015

በጋምቤላ ሌላ ዙር የጎሳ ግጭት አንዣቧል ሲሉ የጋምቤላ ኒሎትስ አንድነት ንቅናቄ አደራጅ ተናገሩ

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንቅናቄው መስራችና አደራጅ   ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት የህዝባዊ ወያን ሃርነት ትግራይ መንግስት በአካባቢው ያለውን መሬት ሙሉ በሙሉ ጠቅልሎ ለመውሰድ ባለው ፍላጎት በአኝዋኮችና በኑወር ብሄረሰቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ነው። ኑወሮችን በጦር መሳሪያ ከማስታጠቅ ጀምሮ ከደቡብ ሱዳን የሚፈናቀሉ ኑዌሮች በአኝዋኮች፣ መዠንገሮችና ሌሎች ብሄረሰቦች መካከል እንዲሰፍሩ በማድረግ እስከዛሬ የነበረውን የህዝብ አሰፋፈር በመቀየር አዲስ ግጭት ለምፍጠር ይቀሳቀል በማለት አቶ ኦኮክ ክስ አቅርበዋል።

በመጋቢት ወር 2 አኝዋኮች መገደላቸውንና 3 ደግሞ መቁሰላቸውን  እንዲሁም በርካታ ሴቶች እና ህጻናት ከ ፒንዩዶ የስደቶች ካምፕ ታፍነው መወሰዳቸውን ፣ በየካቲት ወር ደግሞ 2 ህጻናት ታፍነው ሲወሰዱ፣ አንድ የአኝዋክ አርሶ አደር ደግሞ ተገድሏል።  በኩትቡዲ ፒንዩዶም እንዲሁ 4 አኝዋክ ህጻናት ታፍነው ሲወሰዱ፣ የኒዩም መንደር አዣዥ  ኦጉልም እንዲሁ ተገድለዋል።
ከአሁን በፊት በተቋቋሙት ቦንጋ፣ ዲማ፣ ፒኑዩዶ እና አኩላ ወይም ኢታንግ የሰፈራ ጣቢያዎች የገቡት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች አልበቃ ብሎ በአኝዋክ፣ መዠንገር፣ ኦፖ እና ኮሞ ጎሳዎች መሬቶች ላይ ቾላን፣ ፖኮንግ፣ ጃዊ፣ ኦቾም፣ ኮቦን፣ ካራሚ የተባሉ አዳዲስ የሰፈራ ጣቢያዎች መቋቋማቸው ሆን ተብሎ ግጭት ለመፍጠር መሆኑንና ምልክቶችም በመታየት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ዋናው አላማው በክልሉ የሚታየውን መሬት ለመቀራመት መሆኑን የሚገልጹት አቶ አኮክ ፣ ሁለቱ ብሄረሰቦች በሚጋጩበት ጊዜ ተጠቃሚዎቹ መሬቱን የሚዘርፉት የህወሃት ሰዎች ናቸው ብለዋል።
በቅርቡ ከ80 በላይ አኝዋኮችና 45 መዠንገሮች በማእከላዊ እስር ቤት ታስረው እንደሚገኙ፣  የቀድሞውን የክልሉን መሪ አቶ ኦኬሎ አኳይን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ በርካታ አኝዋኮች ከደቡብ ሱዳን ጁባ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸውን ገልጸዋል። በክልሉ እየደረሰ ያለው ጭፍጨፋ በአጼ ሃይለስላሴ እና ደርግ ከነበረው ጋር ሲተያይ አስከፊ መሆኑን የገለጹት ሃላፊው፣ በዚህ ቀጠለ ለዘመናት መስዋትነት የከፈልንላትን አገራችንን እንዳናጣት ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የሼክ አላሙዲን ሳውዲ ስታር ሳይቀር የመከላከያ ካምፕ መሆኑም አቶ ኦኮክ ገልጸዋል። ከአቶ አኮክ ጋር የተደረገው ቃልምልልስ ሰሞኑን ይቀርባል።

እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ፍርድ ቤት ቀረቡ

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በቁጥጥር ስር የዋሉትእና በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በእስር ላይ የሚገኙት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ ፍቅረማሪያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ፍርድ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ችሎት ከመግባታቸው በፊት በፈገግታ በፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ የነበሩትን ቤተሰቦቻቸውን፣ ጓደኞቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ሰላም ሲሉ መታየታቸውን ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በፌስ ቡክ ገጹ ዘግቧል።
ጠበቃ ዳዊት ከችሎት በኋላ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት መርማሪ ፖሊሶች ምርመራ አለመጨረሳቸውን፣ ተጠርጣሪዎች ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር ግንኙነት እንደነበራቸውና ይሄንንም በማጣራት ላይ እንደሚገኙ፣ የቴክኒክ መረጃዎች (የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔት፣ የስልክና የፌስ ቡክ) እንደሚቀራቸው፣ ለሽብር ተግባር ብር ሲቀበሉ እና ሲልኩ የነበረውን የባንክ ቤት መረጃ እየተከታተሉ መሆናቸውና ቢለቀቁ መረጃዎችን ሊያጠፉ ስለሚችሉ የተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡



መርማሪ ፖሊስም ‹‹የጦር መሳሪያ ተይዟል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በህቡዕ ነው የሚንቀሳቀሱት፡፡ ከእስር ቢለቀቁ ወደኤርትራ ሰው ወደመመልመል ስራቸው ይመለሳሉ›› የሚል ተቃውሞ በማሰማት፣  የጦር መሳሪያ የታጠቀ የሰው ምስል ለችሎት ማሳየቱንና መሳሪያ የያዘው ግለሰብ ማን እንደሆነ በግልጽ እንደማይታይ ጋዜጠኛ ኤልያስ ዘግቧል።
ፍቅረማርያም እና እየሩሳሌምም ቃላቸውን፣ የፌስ ቡክና ሌሎች መረጃዎችን በምርመራ ወቅት ለፖሊስ መስጠታቸውን፣ መሳሪያ ከተባለው ነገር ጋር የሚያገናኛቸው ነገር አለመኖሩንና ይሄም በግልጽ እንደሚታወቅ በመግለጽ ‹‹መረጃዎች ካሉ ክስ ይመስረትብን ካልሆነ ከእስር እንለቀቅ›› የሚል ሀሳባቸውን ለችሎቱ አቅርበዋል፡፡
ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ከተጠየቀባቸው በኋላ ብርሃኑ ተክለያሬድ  ወደ ችሎት መግባቱን፣ መርማሪ ፖሊሱ፣ ብርሃኑ ላይም ‹‹የጦር መሳሪያ ተገኝቷል›› የሚለውን ቃል ሳይደግም በሁለቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ያረቀበውን ሀሳብ ለችሎቱ ማስረዳቱን ጠበቃ ዳዊት ተናግረዋል።
ወጣት ብርሃኑ በበኩሉ ‹‹ቃላችንን ለፖሊስና ለፍርድ ቤቱ ሰጥተናል፡፡ የቀረ ነገር የለም፡፡ የእስር ሁኔታችን ከህግ አግባብ ውጪ ነው፡፡ ‹‹ጨለማ ክፍል›› በሚባለው እስር ቤት መብራት 24 ሰዓት ይበራል፡፡፡ እኔ የዓይን ችግር አለብኝ፡፡ በቀን ለ15 ደቂቃ ብቻ ነው ከታሰርኩበት ክፍል ወደ ደጅ የምወጣው፡፡ ቤተሰብና የህግ ጠበቃ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ከጠበቃ ጋር ሳልማከር ነው ቃሌን ለፖሊስ የሰጠሁት፡፡ የመብት ጥሰት አለ፡፡ ቤተሰቦቻችንን፣ ጠበቃና ጠያቂዎቻችንን መግኘት ይፈቀድልን፡፡ ሌሎች ከእኔ ጋር የታሰሩ እስረኞች ግን ቤተሰቦቻቸው ሲመጡ ለጥየቃ ይወጣሉ፡፡ በዚህ ላይ ትዕዛዝ ይሰጥበት፡፡ …መረጃዎች ካሉ ክስ ይመስረትብን ካልሆነ ከእስር እንለቀቅ›› ብሏል፡፡
የችሎቱ ሴት ዳኛም የተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ መብት መጠበቅ እንዳለበት ጠቁመው፣ ‹‹ተጠርጣሪዎቹ ከቤተሰብ፣ ከጠበቃ፣ ከሃይማኖት አባቶቻቸውና ከወዳጆቻቸው ጋር እንዲገናኙ የሚል ትዕዛዝ በቃል ሰጥተው በብርሃኑም ላይ የ28 ቀናት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ፈቅደዋል።

Saturday, 28 March 2015

በመላው አለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች



ከሁሉ አስቀድሜ በያላችሁበት የከበረ ሰላምታየን አቀርባለሁ በመቀጠል ቀደም ሲል በተለያዩ እስር ቤቶች የታሰሩብንን አባላት በተመለከተ በልዩ ልዩ የመገናኛ ዘዴዎች በተለይም በFacebook ባስተላለፍኩት መረጃ አንዳድ የወገን አለኝታ የሆኑ ወገኖች የእስረኞችን ቤተሰብ በተመለከተ ያስተላለፍኩትን መልክት አንብበው ልባቸው ተነክቶ የታሳሪ ቤተሰቦችን መርዳት የጀመሩ ወገኖች አሉ በዚህ በጣም ተደስተናል እነዚህ ወገኖች ላደረጉት መልካም ተግባር በምድርም በሰማይ ትልቅ ዋጋ አለው ።ለመጭው ትውልድም በታሪክ መዝገብ የምናስቀምጠው ይሆናል ።

ሀገገራችን ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ነገሮች እየተሻሻሉ ሳይሆን እየተባባሱ መጥተዋል ለዚህም ማሳየ የሚሆነን አገዛዙ ከጊዜ ወደ ጊዜ የብረት ቀንበሩን በጫንቃችን ላይ ጭኖ በየጊዜው አፋኝ ህጎችን በማውጣት በሰላማውይ መንገድ የምንታገል የፓለቲካ ፓርቲዎችን በማን አለብኝነት በመተዳደሪያ ደንባችን የመረጥናቸውን አመራሮች በፌደራል ፓሊስ ከፅ/ቤት በማስወጣት ለአገዛዙ ታማኝ የሆኑትን (የራሱ) ሎሌ የሆኑትን ሰዎች በመሾም የምታገልበትን ሜዳ በመቀማት አፈናውን ወደ ከፋ ደረጃ አድርሶታል ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ጥር 21/2007 ዓም ምርጫ ቦርድ በመኢአድና በአንድነት ፓርቲ ላይ የተወሰደውን እርምጃ ማስታወስ በቂ ይሆናል ።

በአባሎቻችን ላይ የሚደርሰው እስራት
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በአባላት የተመረጠውን አመራር አባሮ በመኢአድ ጠቅላላ ጉባላት ያልተመረጠውን አበባው መሀሪ የሚባል ግለሰብ ከሱ ጋር አብራችሁ ስሩ በሚል ማስፈራሪያ ሲደርሳቸው የፓርቲያቸውን ውሳኔ በማክበራቸው በመላ ሀገሪቱ ያሉ አባሎቻችን በሀገሪቱ ባሉ ልዩ ልዩ እስር ቤቶች ታስረው ይገኛሉ
ከዚህ በታች የቀረበውን ዝርዝር ይመልከቱ

አላማጣ ውህኒ ቤት የታሰሩ
1, ኢያሱ ሁሴን የመኢአድ ስራ አስፈፃሚና የማህበራውይ ጉዳይ ሀላፊ አላማጣ ውህኒ ቤት የሚገኝ
2, በላይ ዳኛው 4 ቦታ ተፈንክቶ
ፍርድ ያልቀረበ አላማጣ ፓሊስ ጣቢያ የሚገኝ አባል
3, ሞላ መለሰ አላማጣ ውህኒ ቤት የሚገኝ አባል
4, ጥጋቡ ሙላት አላማጣ ውህኒ ቤት የሚገን አባል
ከጎንደር ክ/ የታሰሩ
5, ዘመነ ምህረት የመኢአድ ም/ል ፕ/ት እና የሰሜን ቀጠና ሀላፊ ሰሜን ጎንደር አ᎐ አ᎐ ማዕከላዊ የሚገኝ
6, መ/ር ጥጋቡ ሀብቴ ሰሜን ጎንደር የዞኑ ሰብሳቢ ባህርዳር ውህኒ ቤት የሚገኝ
7, ጥላሁን አድማሴ የደቡብ ጎንደር ዋና ፀሀፊ
8, ስለሽ ጥጋቤ ሰሜን ጎንደር አባል
9, ጌትነት ደሴ ሰሜን ጎንደር አባል
10, መለሰ መንገሻ ሀገር አቀፍ የወጣች ድ/ት ጉዳይ ሰሜን ጎንደር አ᎐አ᎐ ማዕከላዊ
11. አቶ ጥላሁን አበበ/ደ.ጎንደር አባል
ሰሜን ሸዋ
12, ዓስራት እሸቴ አባል
ጎጃም ክ/ሀገር
ተስፋየ ታሪኩ አ᎐አ᎐ማዕከላዊ አባል
13, መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን አባል
14, ኢ/ር መለሰ ባህር ዳር አባል
15. አቶ አንጋው ተገኘ/ምዕ.ጎጃም አባል
16, አቶ አባይ ዘውዱ/ምዕ.ጎጃም አባል
17. አቶ እንግዳው ዋኘው/ ምዕ.ጎጃም አባል
18 አቶ አባይነህ ሲሳይ/ምዕ.ጎጃም አባል
19. አቶ አለባቸው ማሞ/ምዕ.ጎጃም አባል
20. ወጣት ታጀበ አለኸኝ/ ምዕ.ጎጃም አባል
21. አቶ ዮሐንስ ገደቡ/ምዕ.ጎጃም አባል
22 አቶ አዝመራው ከፋለ/ምዕ.ጎጃም አባል
23 ወጣት ተሥፋዬ አሥማረ/ንዕ.ጎጃም አባል
24, አቶ ችሎት ጎበዜ/ምዕ.ጎጃም አባል
የቤተሰባቸውን ሁኔታ
ከተራ ቁጥር 1— 24 የተዘረዘሩት አባላት የቤተሰብ ሁኔታ ምን እንደሚመስል ለማወቅ ባደረግነው የመረጃ አሰባሰብ ስራ የታሰሩት ሁሉም አባሎች የቤተሰብ ሀላፊዎች መሆናቸውን አረጋግጠናል የቤተሰቦቻቸውም የኑሮ ሁኔታ የተመሠረተው በነዚሁ እስረኛ ቤተሰቦቻቸው የገቢ ምንጭ በመሆኑ ልጆች ከት/ቤት ሊያቋርጡ ችለዋል እናቶቻቸውም ምንም አይነት ገቢ ስለሌላቸው በልጆቻቸው የወደፌት እጣ ፋንታ እንባቸውን በማፍሰስ የናንተን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን እርዳታ በጥብቅ ይሻሉ እኛም የመኢአድ አባላት የነዚህን ቆራጥ ታጋይ እስረኛ ቤተሰቦች ሁሉን አቀፍ እርዳታ ለማድረግ በቃላችን ፀንተን እንገኛለን ። 

በእስር ላይ የሚገኙ ታጋዮቻችን ከኛ ምን ይሻሉ ?
ከላይ የቤተሰባቸውን ሁኔታ ለማየት እንደሞከርነው በእስር ላይ ከሚገኙ ልጆቻቸውና ወላጆቻው የእነሱን (የታሳሪዎቹን) እርዳታ የሚፈልጉ በመሆናቸውና ከሚኖሩበት እርቀት አንፃር ሊረዷቸው የሚችሉ አይደሉም በዚህ ምክንያት በቤተሰብ የመጠየቅ እድል አያገኙም
እስረኞቹ ምን ያስፈልጋቸዋል ?
ከላይ የቤተሰባቸውን ሁኔታ እንዳየነው በእስር ላይ ያሉ አባሎቻችን መሠረታዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ይፈልጋል እነዚህን አቅም በፈቀደ ለማድረግ እየሞከር ነው ።

ከአቅም በላይ የሆነብን ነገር

ከላይ በዝርዝር ያየናቸው ታጋዮች ለአንደኛቸውም የህግ አማካሪ (ጠበቃ) ማቆም አልቻልንም በርካታ የህግ ባለሙና ለማነጋገር ብንሞክር ፈፅሞ የምንችለው አልሆነም ለአንድ ታሳሪ ዝቅተኛ ክፍያ 50, 000 (ሀምሳ ሽህ ብር) ጠይቀውናል በዚህ ስሌት ለአንድ እስረኛ 50,000 ሀምሳ ሽህ ብር ከተጠየቅን ለ24 ሰው 1,200,000 ( አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሽህ ብር) ያስፈልገናል ማለት ይህ ገንዘብ እንኳን በኛ አቅም በብዙ ሠው የሚሸፈን አይደለም ይህንን ያክል ገንዘብ ተገኝቶ ለሁሉ ጠበቃ ማቆም የማይቻል ነው
ለህግ ባለሙያዎች
እኛ ወንድሞቻችሁ ኢትዮጵያውያን የምንደርገው ሰላማዊ የፓለቲካ ትግል በሀገራችን የጠፋውን የህግ የበላይነት በፅኑ መሰረት ላይ ለማቆም ነው ።
በመሆኑም ዛሬ በእስር ላይ የሚማቅቁት ወንድሞቻችሁ በዚህ ስርዓት ካድሬዎች የሚቀርብባቸውን የፈጠራ ክስ በህግ ግንዛቤ ማጣት መከላከል አልቻሉም ።
አንዳንዶቻችሁ ከዚህ ፍርድ ቤት ምን ፍትህ ይገኛል ልትሉ ትችላላችሁ ። እውነት አላችሁ ዳኛውም ፣አቃቤ ህጉም ፣ፓሊሱም ፣በቀጭን ትእዛዝ የሚታዘዙ የባለ ጊዜ አገልጋዮች ናቸው ።ነገር ግን ይህ ለዘላለም አይቀጥልም ። ለትውልድ ታሪካዊ ሰነድ ለፍርደኞች ማቆየት ከኛ ፍትህ ጠባቂዎች ይጠበቃል ባለጊዜዎችንም ተረኛ መሆናቸውንም ማሳየት ተገቢ ነው ብለን እናምናለን ። ስለዚህ የህግ ባለሙያዎች የድርሻችሁን ታበረክቱ ዘንድ ሙያዊ ጥሪ ቀርቦላችኋል ።

ኢትዮጵያ ወድቃ አትቀርም አሁን የዋጣት ጨለማ በማያቋርጥ ብርሀን ይለወጣል !!!!

Friday, 27 March 2015

የአዋሳ ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ቁሳቁሶችን ቀማ

• ‹‹የባጃጅ ሾፌሮችን አድማ የመራው ሰማያዊ ነው›› ባለስልጣናቱ
የአዋሳ ፖሊስ መጋቢት 20/2007 ዓ.ም ለሚደረገው ሰልፍ የተዘጋጁትን የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ቁሳቁሶች መቀማቱን በአዋሳ ከተማ የሰልፉ አስተባባሪ አቶ ዮናስ ከድር ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ከአዲስ አበባ ሰልፉን ለማስተባበር ወደ አዋሳ ያቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች አዋሳ በደረሱበት ወቅት የፀጥታ ኃላፊው እና የከንቲባው አማካሪ አስተባባሪዎቹን አስጠርተው በሚያወያዩበት ወቅት ፖሊስ የቅስቀሳ ቁሳቁሶችን ከተቀመጡበት ቦታ ቀምቶ እንደወሰደ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአዋሳ ከተማ የፀጥታ ኃላፊ እና የከንቲባው አማካሪ የሰልፉን አስተባባሪዎች በመጥራት ‹‹በከተማችን በሚገኙ አደባባዮች ባዛሮች አሉ፡፡ በተጨማሪም ለህዳሴው ግድብ ከ18-30 የህዝባዊ ስብሰባዊና ህዝባዊ ንቅናቄዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚህም ምክንያት የፀጥታ ኃይል ስለሌለን እስከ መጋቢት 30 ድረስ ሰልፍ ማድረግ አትችሉም፡፡›› እንዳሏቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የሰልፉ አስተባባሪዎች ከከተማው ባለስልጣናት ጋር በሚወያዩበት ወቅት ፖሊስ ቲሸርትና በረሪ ወረቀቶች ቀምቶ የወሰደ ሲሆን ቁሳቁሶቹ አሁንም ድረስ በፖሊስ እጅ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ፖሊስ ‹‹እቃ አልወሰድንም፣ የምናውቀን ነገር የለም›› ብሎ እንደካዳቸው አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ዜና በሲዳማ ዞን ቡርች ወረዳ የደህኢዴን /ኢህአዴግ ካድሬዎች ህዝቡ እሁድ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጣ በሜጋ ፎን እየቀሰቀሱ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡ ካድሬዎቹ ‹‹በእሁዱ ሰልፍ የወጣ ሰው ይታሰራል›› እያሉ እንደቀሰቀሱም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሌላ ዜና በአዋሳ ከተማ የተከሰተውን የነዳጅ እጥረትና የዋጋ ታሪፍ ተከትሎ ትናንት መጋቢት 17/2007 ዓ.ም የባጃጅ ሾፌሮች የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉ ሲሆን የከተማው ባለስልጣናት አድማውን የመራው ሰማያዊ ፓርቲ ነው የሚል ውንጀላ እያቀረቡ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

‹‹የአዋሳ ፖሊስ ለእሁዱ ሰልፍ የተዘጋጁትን የቅስቀሳ ቁሳቁሶች በመቀማት እና የተለያዩ ወከባዎችን በመፍጠር
ሰልፉን ለማደናቀፍ እየሰራ ቢሆንም እኛ ህጋዊ ግዴታችን ተወጥተናል፡፡ በመሆኑ ሰልፉ በታቀደለት ወቅት
ይካሄዳል›› ሲሉ የሰልፉ አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡

Thursday, 26 March 2015

ጉዞአችን ወደ ነፃነት ነው!! መዳረሻችንም የነፃነት አደባባይ ብቻ ነው!!

pg7-logoአለማችን አንባገነን ስታስተናግድ ወያኔ የመጀመሪያው አይደለም። ዘረኛንም እንዲሁ …….. እኛም ስለነፃነት ብለን ለትግል ሰንነሳ የመጀመሪያዎቹ አይደለንም …… አለማችን እንደየዘመኑና እንደ የወቅቱ አንባገነኖች ያለ የሌለ የመሳሪያና ወታደራዊ ሀይላቸውን በመጠቀም ህዝብን በፍርሀት አሸማቀውና ረግጠው ለመግዛት ሲውተረተሩ በተደጋጋሚ ታይተዋል። በዚያው ልክ ህዝባዊ ሀይልና መመከት ተስኗቸው ሲንኮታኮቱ በተደጋጋሚ የታየ ወደፊትም አናባገነኖች እስከተከሰቱ ድረስ በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገው መቀመቅ ሲወርዱ መታየቱ አይቀሬ ነው ። ህዝብ የወደደውን አስተዳዳሪ እንጂ ረግጦ ሊገዛው የሚፈልገውና አንባገነን ተቀብሎ አያውቅም ፤ዛሬም አልተቀበለም ፤ ነገም አይቀበልም ። ይህን በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ በተደጋጋሚና በጉልህ የሚታይ ግዙፍ እውነት መቼም ተቀብለውና ከታሪክ ተምረው ስለማያውቁ አሳፋሪው ውድቀታቸው በተደጋጋሚ ሲታይ አለ።
ሀገራችን የአለማችን አካል እንደመሆኗ አንባገነኖች ተፈራርቀውባታል። አንባገነኖችም በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገውባታል። ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ትልቅ ወታደራዊ ሀይል የነበረው የትናንቱ ደርግ እንደ እንቧይ ካብ ሲናድ ተመልክተናል። አንባገነኖች መናገር እንጂ መስማት የማይችሉ፤ ማየት እንጂ ማስተዋል የተሳናቸው በመሆናቸው እነሆ ዛሬም የወያኔ ዘረኛው ቡድን ህዝብ ላነሳው የነፃነትና የፍትህ ጥያቄ ያለ የሌለውን ወታደራዊ ሀይል በጠራራ ጸሀይ በማሰለፍ መቼውንም ያልተቻለውን ህዝብን በሀይል አሸማቆ ለመግዛት መከራውን ሲያይ ይስተዋላል። ለዚህም ነው ….. ከሌላው የሀገራችን ክልሎች ከፍ ባለ ሁኔታ የህዝባዊ እንቢተኝነት እየታየ ባለበት ጎንደርና አካባቢው በሰራዊት ማጥለቅለቅ የተያያዘው።
ለሚነሱ ህዝባዊ ተቃውሞዎችና ህዝባዊ የመብት ጥያቄዎች የሚሰጡት ምላሾች እስር፤ አፈናና ግድያ ከሆነ ህዝባዊ እንቢተኝነትን ማስከተሉ አይቀሬ ነው። በእስር ፤በአፈናና በግድያ እንዲሁም በሰራዊት ሀይል ህዝብን በማሸማቀቅ በስልጣን መቆየት የሚቻል ቢሆን ደርግም ከቤተ-መንግስት ባልወጣ፤ ወያኔም ዛሬ ከቤተ-መንግስቱ ባልተንፈልለሰሰ ነበር። ይህ ደግሞ ሊያስተምር በተገባ ነበር።
እስከ ዛሬ የትኛውም አንባገነን ስርአት በሚተማመንበት የወታደራዊ ሀይል አማካይነት የመንኮታኮቻቸውን ሰአት በአንድ ሰኮንድ ማዘግየት የቻለ እንደሌለ ሁሉ ወያኔም ያለ የሌለውን ወታደራዊ ሀይል ሲያርመሰምስ ውሎ ቢያድር ውድ ቀቱን በአንድ ሰኮንድ ማዘግየት እንደማይችል በተለይ እንቢ ለነፃነቴ፤ እንቢ ለሀገሬ… ብለን ለትግል የተነሳን ሀይሎች በመረ ዳት፤ ይበልጡኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተቀጣጠለ ያለውን ህዝባዊ እንቢተኝነት ይበልጥ እያሰፋን የጀመርነውን የነፃነት ጉዞ ከነፃነታችን አደባባይ ለማድረስ ሌት ተቀን የመስራት ሀላፊነታችናና መወጣት ይገባናል።
በጎንደር የሚታየውን የአልገዛም ባይነት ትንቅንቅ በሌሎች ክልሎችም በማቀጣጠል፤ በደብረወርቅ የታየውን የመምህራን የስራ ማቆም አድማ ወደ ሌሎች አካባቢዎች በማስፋት፤ እንደ ድምፃችን ይሰማ ሁሉ ተቃውሞን ወደ እንቢተኝነት በማሸጋ ገር …… ወዘተ የነፃነታችንን ቀን ለማቅረብ መከፈል የሚገባውን መክፈል ይገባናል።
በደርግ  የተነሳው እንቢተኝነት እያየለ ሲመጣ ያሰለፈው ሰራዊት ወያኔን አጅቦ የደርግን ቀብር እንደቆፈረለት ሁሉ ዛሬም በወያኔ ላይ እየተቀጣጠለ የሚገኘው ህዝባዊ እንቢተኝነት እየጠነከረ በመጣ ቁጥር የደረደረው ሰራዊት የወያኔን ቀብር ቆፋሪ ከመሆኑ እንደማይመለስ ከቅርብ ጊዜ ታሪካችን በመማር ነፃነታችንን ለማስከበር የጀመርነውን የእንቢተኝነት ትግል በመላው የሀገራችን ክፍሎች በማስፋትና በማቀጣጠል አይቀሬውን የወ ያኔ ቀብር ለማቅረብ በአንድነት የነፃነት ጉዞውን እንቀላቀል። የጀመርነው የነፃነት ጉዞ መቆሚያው የነፃነታችን አደባባይ መሆኑን በተግባር ከምናሳይበት ወቅት ላይ እንገኛለንና በአንድነት እንነሳ!!!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!

9 ፓርቲዎች የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ በመጪው እሁድ ሊካሄድ ነው

መጋቢት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት የተሰባሰቡትና ምርጫ ቦርድ ዕውቅና አልሰጠሁም በሚል ትብብራቸውን እንዲያቆሙ

ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው ዘጠኝ ፓርቲዎች በትብብር የጠሩት ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የፊታችን እሁድ የአዲስአበባ እና የድሬዳዋ ከተሞችን ጨምሮ በአስራአምስት ዋና ዋና ከተሞች ይካሄዳል፡፡
ሆኖም አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከወዲሁ ሰልፉ በመንግስት በኩል ያልተፈቀደ ነው በሚል ለማጨናገፍ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በባህርዳር መጋቢት 20 ሊካሄድ የታቀደው ሰልፍ እንደማይካሄድ መስተዳድሩ ደብዳቤ ጽፏል። በደብዳቤው ላይ እንደተመለከተው ሰልፉ በከተማዋ በመካሄድ ላይ ባለው አገራቀፍ የስፖርት ውድድርና በእለቱ የአባይ ቦንድ ግዢ ዝግጅት በመኖሩ ነው።
የምእራብ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ የሰልፉ ጊዜያዊ አስተባባሪ ወጣት አዲሱ ጌታነህ  እንደሚለው በምርጫ ወቅት ምንም አይነት ውድድር ቢኖር ቅድሚያ ለምርጫ ዝግጅቶች እንደሚሰጥ ገልጾ፣ ሰልፉ የሚካሄደው ስፖርታዊ ውድድር ከሚካሄድበት
ስታዲየም ራቅ ባለ ቦታ በመሆኑና ለተማሪዎች ውድድር የጸጥታ ሃይሎች አስፈላጊነት አናሳ በመሆኑ፣ መስተዳድሩ ሰልፉን ሆን ብሎ መከልከሉን ተናግሯል።
ገዢው ፓርቲ ሰልፉን ለመከልከል የፈለገበት ሌላ ምክንያት ይኖር ይሆን ተብሎ ለተጠየቀው ደግሞ ” ህዝቡ በስርአቱ ላይ ሊያሰማ የሚችለው ተቃውሞ ገዢውን ፓርቲ ስጋት ላይ ስለጣለው ነው በማለት መልሷል
የሰልፉ ዋና አስተባባሪ የሆኑት አቶ ግርማ በቀለ እንደተናገሩት እስካሁን ድረስ ከአዲስ አበባም ሆነ ከሌሎች አካባቢዎች ሰልፉ እንዳይካሄድ የሚያግድ ደብዳቤ አለመቅረቡን ገልጸው፣ ሰልፎቹ በ15 ከተሞች በታቀደላቸው መሰረት ይካሄዳሉ ብለዋል።
አቶ ግርማ እንደሚሉት በምርጫ ቅስቀሳ ወቀት መስተዳድሮች የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያካሂዱዋቸውን ሰልፎች መከልከል እንደማይችልና ሰልፎቹ በማንኛውም መንገድ እንደሚካሄዱ ገልጸዋል
«ነጻነት ለፍትሐዊ ምርጫ» በሚል የታሰበው ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ የሚካሄድ ከሆነ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ ድጋፉን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የአዲስ አበባው ዘጋቢ አስተያየቱን ሰጥቷል።
በግንቦት ወር ከሚካሄደው ምርጫ ጋር ተያይዞ ጠንከር ያሉ መልዕክቶችን ያዘሉና ገዥውን ፓርቲ የሚተቹ የምርጫ ቅስቀሳዎች በመንግስትና እንደራዲዮ ፋና ባሉ የፓርቲ ልሳናት እየታገዱ ሲሆን ፣ በየመንገዱ የሚሰቀሉና የሚለጠፉ የቅስቀሳ መልዕክቶች
ኢህአዴግ ከፍሎ ባሰማራቸው  ወጣቶች አማካይነት በጠራራ ጸሐይ እየተቀደዱ መሆኑን ፓርቲዎቹ በተናጠል በሚያቀርቡዋቸው ተደጋጋሚ ቅሬታዎች  እያሳወቁ ነው፡፡
በአንዳንድ አካባቢዎች ተወዳዳሪ ዕጩዎች ሳይቀር ምክንያት እየተፈለገ በመታሰር ላይ ናቸው።
በሌላ በኩል ደግሞ በአዲስ አበባ ስጋቶች ላይ የመከረው የአዲስ አበባ ካቢኔ የዋጋ ንረት ፤ የገንዘብ ግሽበት ፤ የስኳር እና ዘይት እጥረቶችን በቀዳሚነት አንስቷል።  በመጭው ምርጫ ለስርአቱ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ነው  ሲል ገምግሟል።
ሙስሊሙ ከፖለቲካው ጋር በፈጠረው ኩርፊያ ፤ ለኢህአዴግ ድምፁን የመንፈግ እና አመፅ የማቀጣጠል እድል እንዳለው ስጋት በሚለው የመጀመሪያ መስመር ላይ ተቀመምጧል፡፡ ምርጫውን ለማሸነፍ የ1ለ 5 አደረጃጀት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሰተያየት ተሰጥቷል።
ካቢኔው በቅርቡ የተከፋፈሉት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ህዝቡ ለኢህአዴግ ድጋፍ እንዲሰጠው እንደሚያግዘው ገምግመዋል።  ብዙዎችን ያስገረመው  የኮምፒዩተር እጣ አወጣጡን ሶፍት ዌር አዘጋጀው ለተባለው ለመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ወይም ኢንሳ 11 ሚሊዮን ብር መከፈሉ ነው።

በኦሮሚያ እና ሌሎች አካባቢዎች የመጠጥ ውሃ ችግር ት/ቤቶችን ከማዘጋት አልፎ ለስደት እየዳረገ ነው

መጋቢት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በመቶ ሚሊየን በሚገመት ወጪ በታላቅ ፌሽታ እያከበረ የሚገኘው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) አመራር በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን እስከ ማዘጋት የደረሰውን የመጠጥ ውሃ ችግር ሊታደግ ያልቻለ መሆኑን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡

ከግብርና ሚኒስቴር የወጣ አዲስ መረጃ እንደሚያሳየው፣ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው የመጠጥ ውሃ ችግር ሕዝብን ለከፍተኛ ችግር ከመዳረጉም አልፎ የመማር ማስተማር ስራ በማደናቀፍ ትምህርት ቤቶችን እስከማዘጋት ደርሷል።

የመጠጥ ውሃ ችግር ከገጠማቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች መካከል በአርሲ ዞን በጎሎልቻ፣ መርቲ፣ .ዝዋይ፣ ዱግዳ፣ ሴሩና ደጁ ወረዳዎች፣ በምዕራብ አርሲ ዞን በሻላ ሲራሮና ሻሸመኔ ወረዳዎች፣ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በሚደጋ፣ ቁምቢያ መዩ ወረዳዎች፣ በምስራቅ ሸዋ ዞን በቦሰት ወረዳ እና በጉጂ ዞን በሊበንና ሰባቦሩ ወረዳዎች አስከፊ የተባለ የመጠጥ ውሃ ችግር ማጋጠሙን ሚኒስቴሩ አጋልጦአል፡፡
የመጠጥ ውሃ ችግሩ በተለይ በአርሲ ዞን በዝዋይ ዱግዳና በሴሩ ወረዳዎች፣ በጉጂ ዞን በሊበን ወረዳ ት/ቤቶችን እስከማዘጋት የደረሰ ችግር መከሰቱ ተረጋግጦአል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የተከሰተውን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ ሚኒስቴሩ ከአጋር ድርጅቶች ባገኘው ድጋፍ ውሃ በቦቴ የማደል ስራ እያከናወነ መሆኑ ታውቋል፡፡
በቦረና ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ማለትም በአሬሮ፣ ድሬ፣ ዲሎ፣ ዳስ የእንስሳት መዳከምና ሞት መከሰት የጀመረ ሲሆን በአርሲና ምዕ/ሐረርጌ ዞኖች የእንስሳቱ አቋም እየተዳከመ መሆኑ፣ የእንስሳት እንቅስቃሴም ተጀምሮ በምዕ/ሐረርጌ ዞን ከቡርቃ ዲምቱና ሃዊ ጉዲና ወደ ዱንገታና ዋቤ ወንዝ፣ በቦረና ዞን ከተልተሌ ወደ ገራንና ኮንሶ፤ ከድሬ፤ ሚዮና ሞያሌ ወደ ኬንያ (አዋሳኝ ቦታዎች) በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው በሪፖርቱ ተመልክቷል።
የኦሮሚያ ክልል ገዥ ፓርቲ ኦህዴድ/ኢህአዴግ  እንዲህ ዓይነቱን የህዝብ ችግር ሳይፈታ ለክብረበአል በመቶ ሚሊየን ብሮችን ሲያፈስ መታየቱ አሳዛኝ መሆኑን ዘጋቢያችን ያነጋገርናቸው የኦሮሞ ተወላጆች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Wednesday, 25 March 2015

የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ለ8ኛ ጊዜ ተመለሰ


• ኢብኮና የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት መልሰዋል
• ‹‹አማራጫችን እንዳናቀርብ እየተከለከልን ነው›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ‹‹አናስተላልፍም›› ብለው መመለሳቸውን ድርጅቶቹ ለፓርቲው በላኳቸው ደብዳቤዎች ገልጸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ መጋቢት 16/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የብሔራዊ ራዲዮ በአማርኛ ስርጭት የሚተላለፍ ‹‹መንግስታዊ አወቃቀር›› የሚል የቅስቀሳ መልዕክት ልኮ የነበር ሲሆን ባለፉት 24 አመታት ተግባራዊ የሆነው የጎሳ ፌደራሊዝም ለግጭት መንስኤ መሆኑን በመረጃ ዘርዝሮ ማቅረቡን የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
ይሁንና ኢብኮ ይህን የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹በተለያዩ ጊዜያት በብሔር ብሔረሰቦች መካከል ተከሰቱ ያሉትን ግጭቶች በመዘርዘር በህዝቦች መካከል ሌላ ግጭት እንዲቀሰቀስና እንዲባባስ የሚያደርጉና ግጭት የሚያራግቡ፣ አንዱን ብሔር ከሌላ ብሔር የሚያገጩ ናቸው፡፡›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡ ከዚህም ባሻገር በመልዕክቶቹ ውስጥ ‹የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት›፣ እንዲሁም ‹የህወሓት/ኢህአዴግ ስርዓት› የሚለው አገላለጽ የፓርቲውን ህጋዊ መጠሪያ የማይወክል በመሆኑ›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡
በሌላ በኩል እነዚህ ግጭቶች በአሁኑ ወቅትም የቀጠሉና የጎሳ ፌደራሊዝሙ እስካለ ድረስ ብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉ መሆናቸውን የገለጸው የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ መልዕክቶቹ ከፓርቲው ማንፌስቶ የወጡ፣ ኢብኮ እንዳለው ለግጭት ሳይሆን ከግጭቶቹ መማር እንዲቻልና አሁን ያለው የጎሳ ፌደራሊዝም ከተስተካከለ ችግሮቹ እልባት እንደሚያገኙ በሚያሳይ መልኩ የተላለፈ መልዕክት ነው ብሎአል፡፡ ‹‹እኛ ያቀረብነው አማራጫችን ነው፡፡ አማራጫችን ስናቀርብ ደግሞ የጎሳ ፌደራሊዝም የፈጠረውም ቀውስም በማሳያነት ማቅረብ አለብን፡፡ ይህን እውነታ የአገር ውስጥና የውጭ ተቋማት ዘግበውታል፡፡ አብዛኛዎቹ መንግስትም ያመነባቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን ስርዓቱ የሰራቸው ጥፋቶች ይፋ አውጥተን እንዳናቀርብ ስለተፈለገ መልዕክቱን መልሰውታል፡፡ በግልጽ አማራጫችን እንዳናቀርብ ተከልክለናል›› ሲል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
በተመሳሳይ የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹ከሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ጋር የሚጻረር፣ ብሔር ብሄረሰቦችን ወደ አላስፈላጊ ግጭት እንዲያመሩ የሚገፋፋ፣ የሌላ ፖለቲካ ፓርቲን ስም የሚያጎድፍ ይዘት የተካተተባቸው›› ናቸው በሚል መልሷል፡፡ ይህ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ሲመለስ ለ8ኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡



Tuesday, 24 March 2015

Muslim Brotherhood: Coup Regime Nile Water Agreement With Ethiopia Null and Void

Muslim Brotherhood: Coup Regime Nile Water Agreement With 

Ethiopia Null and Void

Muslim Brotherhood: Coup Regime Nile Water Agreement With Ethiopia Null and Void
Mohamed Montaser, Muslim Brotherhood Media spokesman, says Al-Sisi's signing of the Grand Ethiopian Renaissance Dam Accord is another treacherous act against the people of Egypt.

Tuesday, March 24,2015 05:09

The heinous coup commander Abdel-Fattah Al-Sisi has illegitimately signed on behalf of Egypt the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) agreement, without any knowledge of its terms and conditions or the essential details of GERD and its storage capacity, according to experts and specialists. Al-Sisi has thus sold the Egyptian people's long-established rights to Nile water for a few billion dollars more from foreign powers, straight to his own and his junta's pockets.

Today (Monday), the coup commander signed an agreement which would not fool even a half-witted child, and which lacks the ABCs of international agreements and international law, to prove his gullibility, failure and treachery. For one thing, according to this agreement, the Ethiopians do not have to guarantee or safeguard any Egyptian rights to Nile waters. The traitor Al-Sisi knows full well that he has no legitimacy, and so rushes to enter into any agreements, even they deprive Egypt of its rights.

The putschists are not concerned with Egypt or its people. They do not care if Egyptians go hungry or thirsty.

In any event, we assure the whole world that the Egyptian people's Revolution will triumph and that any agreement entered into by the coup regime, or the junta, will not be recognized, but regarded as null and void.

The people of this homeland will not be brought to their knees. They will certainly not go thirsty. The Revolution will not only topple this illegitimate coup regime, it will also cancel all treaties, agreements and contracts the junta and the coup regime will have signed illegally in the name of the Egyptian people.

Cairo: Saturday – March 21, 2015

Mohamed Montaser

Muslim Brotherhood Media spokesman

ኢህዴድ በሐረርጌ በጨለንቆ ከተማ ያስገነባው የሰማዕታት ሐውልት የፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናት ባልተገኙበት መመረቁን ምንጮች ጠቆሙ፡፡

መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅዳሜው የሐውልት ምረቃው ላይ ያልተገኙት ጠ/ሚኒስትሩ፣  በማግስቱ በጅማ ከተማ በተካሄደው የስታዲየም ሰልፍ ላይ ተገኝተው ኦህዴድን የሚያወድስ ንግግር ቢያደርጉም እርሳቸውም ሆኑ የህወሃት ባለስልጣናት በሃውልቱ ምርቃት ላይ አልተገኙም።

የህወሃት ከፍተኛ አዛዦች በሐውልት ምረቃው ላይ ያልተገኙት “ኦህዴድን  የፈጠርነው እኛ ነን” ከሚለው የህወሃቶች ትምክህት ወይም  ኦህዴድ ሰማዕታት አሉኝ በማለት የሚናገረውን ላለመቀበልና ዕውቅና ላለመስጠት ሊሆን እንደሚችል ምንጮች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።
የሐውልት ምረቃው በቴሌቭዥንና በራዲዮ ጭምር በዕለቱ ሽፋን ሳይሰጠው ቀርቶ ሰኞ  በትንሽ የዜና ሽፋን እንዲያገኝ መደረጉን የህወሃት ባለስልጣኖችን አለመደሰት ያሳያል ሲሉ አስተያየታቸውን አክለዋል።
በትግራይና በአማራ ክልሎች የሰማአታት ሃውሎቶች ሲመረቁ የህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተው መልእክቶችን አስተላልፈው ነበር። ከዚህ ጋር ተያይዞ ኦህዴድ ለኣመታት የተጓተተውን የባህል ማዕከል ረቡዕ ለማስመረቅ አቅዶአል፡፡
አዲስ አበባ ስታዲየም አካባቢ የተገነባው የኦሮሞ የባህል ማዕከል መጠናቀቅ ከነበረበት ከሶስት ዓመት በላይ መዘግየቱን ምንጮች ይገልጻሉ።
የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ከሚያገኛቸው ጥቅሞች መካከል ት/ቤቶችን መገንባት፣ የባህል ማዕከላትን  ማቋቋም የሚሉት ጉዳዮች የሚገኝበት ሲሆን በአዲስአበባ በአስሩም ክፍለከተሞች አንድ የኦሮሞ ት/ቤት ለመገንባት ተይዞ የነበረው ዕቅድ ባልታወቀ ምክንያት ሊተገበር አልቻለም፡፡ ኦህዴድ  በህገመንግስቱ ላይ የሰፈሩ ጥቅሞችን ሆን ብሎ እንዳይፈጸሙ ያደናቅፋል በሚል በራሱ አባላት ጭምር ጠንካራ ትችቶች እንደሚደርስበት ይታወቃል፡፡
በሐረር፣ በጅማ፣ በነቀምቴ፣ በሻሸመኔ፣ በአምቦ፣ በአዳማ ከተሞች በመቶ ሚሊየን ብር ወጪ በማፍሰስ በኣሉን ሲያከብር የቆየው ኦህዴድ ፣ የፊታችን ሐሙስ በሸራተን እና በሚሌኒየም አዳራሽ በሚያካሂደው ፌሽታ በኣሉን ይፈጽማል።
ሕወሃትም  40ኛ ዓመት በአሉን ከመንግስት ካዝና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ  በማውጣት በፌሽታ አክብሮአል።