አንድ ወቅት ሎሬት ጸጋዬ አንድ ስብሰባ ላይ የተጠየቁት ጥያቄ ትዝ ይለኛል። <<ስለ አፄ ቴዎድሮስ ሁል ጊዜ እያሞገሱ ለምን ይጽፋሉ?>> ተብለው ሲጠየቁ <<አይ ሌላውንማ የኢትዮጵያ ጠላቶች ይጽፉታል>> ነበር ያሉት። ስሞኑን ሎሬት የተነበዩትን በገሃዱ ሕይወታችን እያነበብን ይሆን?
የህወሓት መስራቾች ለትግል በረሃ ከወጡበት ዘመን ጀምሮ፣ ቂም ቋጥረው ደም የተቃቡት ከደርግ አገዛዝ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሐገሪቱ ታሪክም ጋር እስኪመስል ድረስ በአፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ላይ ተጠምደው እንደነበር ይታወሳል፤ በተለይም ለአፄ ምኒሊክ ስምና ስራ ያላቸው ጥላቻ ወሰን አልባ ነው። የድርጅቱ ‘ማኔፌስቶ’ የተዋቀረበት ጭቃና ማገርም በሐገሪቱ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ቡድን የበላይነት (ጭቆና) መኖሩን አውስቶ የአንድነትና የዘመናዊት ኢትዮጵያ አባት ዳግማዊ ምኒሊክን አንኳሶና አጠልሽቶ አዲስ ታሪክ መፍጠሩ የትላንት ትዝብት ነው።
የህወሓት አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ትኩረት ያደረገው፣ ምኒልክ ገር ከማቅናት አኳያ በኦሮሚያና ደቡብ አካባቢ የፈፀማቸውን የኃይል እርምጃዎች በማጎን ቅዋሜውን ‘ህዝባዊ’ ማስመሰሉ ላይ ነው (በኃይለሥላሴ ዘመን የታነፀውን የዳግማዊ ምኒልክ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልት ይፍረስ እስከማለት ደርሶ እንደ ነበር አይዘነጋም) በእኔ እምነት ንጉሡን አስመልክቶ የሚነሱ መከራከሪያዎች ‘ወሰን በማፅናቱ ዘመን የተከሰቱ ጥፋቶችን መቀነስ ይቻል ነበር’ የሚሉ ናቸው ካልተባለ በቀር ‘ዘመቻው አያስፈልግም ነበር’ ማለቱ ‘ዛሬ መረከብ የነበረብን የአማራ፣ የትግሬ፣ የኦሮሞ፣ የወላይታ…. ተብለው በብሔር የተከፋፈሉ ገራት መሆን ነበረበት’ እንደማለት ይመስለኛል።
የሆነው ሆኖ የምኒልክ ወሰን የማፅናት ዘመቻ አሁን ያለችዋን ኢትዮጵያ እንዲያካትት የሄደበት መንገድ፣ ዘመኑ የፈቀደው ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ይሰማኛል፤ እናም በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ያሉ የ ገረ-መንግስት (NATION State) ህልዮቶችን መቶ ዓመት ወደ ኋላ ወስዶ የምኒሊክን ኢትዮጵያ ለመመዘን መሞከሩ ቢያንስ ምሁራዊ ታማኝነት ይኖረዋል ብዬ አላምንም። ርግጥ ነው አማርኛ ቋንቋ አፍ መፍቻቸው ካልሆኑ የጦር አበጋዞቹ ጭምር ወደ ደቡባዊቷ ኢትዮጵያ ሲዘምት፣ የተከሰተው ዕልቂት ዘግናኝ እንደነበረ፣ የተናዱት ‘ወጥ ማንነቶች’ ብዙ እንደነበሩ ባይካድም፣ በተጨማሪም እርሱን የምንወቅስባቸው ተጨባጭ በደም የተፃፉ ሁነቶች ቢኖሩም፣ ያንን ክቡድ የነፃነት መንፈስ ለማቆሸሽ መምረጡ የዛሬይቱንም ሆነ የነገይቱን ኢትዮጵያ መከራዎች ከማባባስ ያለፈ ፋይዳ ይኖረዋል ብዬ አላስብም።
በአናቱም በግራም በቀኝም ያሉ የ ገሬ የተቃውሞ ልሂቃን፣ በዚህ ንጉስ አገር ገንቢነት ላይ ያላቸው አረዳድ ጠርዝ ለጠርዝ የሚያቆማቸው መሆኑ ስለነገይቱ ኢትዮጵያ በጋራ እንዳያልሙ እንቅፋት መፍጠሩን እረዳለሁ። ይሁንና የታሪክ መሰረቶች ላይ የሚቆሙ መተናነቆችን መሻገሪያው ብቸኛው መፍትሄ ጉዳዩን ለታሪክ ባለሙያዎች መተው ብቻ ይመስለኛል። ከዚያም የአፄውን በጎ ምግባሮች በጋራ እያወደሱ፣ የተሻለች ገር ትኖረን ዘንድ በህብረት መትጋት ቢያንስ ከቀጣይ ትውልዶች ከሳሽነት ነፃ ያደርጋል።
በመጨረሻም ምንም እንኳ ዛሬ ዕውቅና የመንሳቱ አዝማሚያ እየጠነከረ ቢመጣም፣ ገሬ በአፄ ምኒልክና ሕዝባቸው ግንነትና መስዋዕትነት በምድራችን ታሪክ በነጭ ወራሪ ኃይል ላይ የመ መሪያውን የበላይነት ከመቀዳ ት አልፋ፣ ለመላው አፍሪካውያን የነፃነት መገለጫ የመሆኗን ጉዳይ ለጊዜው ማደብዘዙ የተሳካ ቢመስልም፣ ከታሪክ መዝገብ የሚፋቅ ባለመሆኑ ‘ቪቫ ምኒልክ’ እያልኩ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማዬን ከፍ አደርግለታለሁ።
ክብር ለአድዋ ጀግኖቻችን
No comments:
Post a Comment