
ልጆችን በተናጠል እያስጠሩ አልጋ በያዙበት ሆቴል ፎርም ሲያስሞሉና ብር ሲዘርፉ አድረዋል። በቀጣዩ ቀን እሁድ ጠዋትም አንድ ኤፍሬም በሚባል ግለሰብ ለጥቅም አድሮ ህዝቡን ለመንግስት ወንበዴዎች በሚያዘርፍ የአበሻ ምግብ ቤት ወስጥ መኖራቸውን መረጃ ያገኙ የተቃዋሚ ሀይሎችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጲያውያን በነቂስ በመገኘት የተለያዩ መፎክር በማሰማት ተቃውማቸውን አሰምተዋል። ተቃውመው እየጠነከረ መሄዱን የተረዱት እነዚሁ የወያኔ ጉጅሌዋች ከአበሻው ምግብ ቤት ወጥተው በመኪናቸው ገብተው ለማምለጥ ሲሉ መኪናቸው በእንቁላልና በድንጋይ ተደብድቧል። ከወያኔዎችም ከመኪና ውስጥ ተጎትቶ ቦክስ የቀመሰም እንደነበር ታዝበናል
የህዝቡ ቁጣ ከፍተኛ በመሆኑ መኪናቸውን አስነስተው በፍጥነት ባይሸሹ ኑሮ ከዚያ የበለጠ አደጋና ውርደት ይገጥማቸው ነበር።
ወያኔን በሔደበት ማዋረድ ይቀጥላል።
No comments:
Post a Comment