ሜሮን አየለ (ኖርዌይ)
ኢትዮጵያውያን ለነጻነታችን ዋጋ መክፈል የጀመርነው ከጥንት ጀምሮ መሆኑ ይታወቃል:: በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶየሚገኘው የዘረኛውና ቡድናዊው አገዛዝ በዜጎች ላይ ከፍተኛ በደል በማድረስ ላይ ይገኛል:: ከዚህ ጨቋኝ አገዛዝ ለመገላገልበአንድነትና በመተባበር ለነጻነታችን መታገል አለብን:: ላለፉት 24 አመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተቀመጠውንዘራፊውን እና ጨቋኙን የወያኔ ጁንታን ለመቅበር የአንድነት እና የለውጥ ሃይሎች ልዩነቶቻችንን በማቻቻል በጋራ ልንታገልየሚገባና ለውጥ ልናመጣ የሚገባ ችላ የማይባል ዋነኛ ጉዳይ ነው። በህዝባችን ላይ ከፍተኛ እንግልት፣ እስር፣ ሰቆቃ፣ ግድያወዘተ እየፈጸመ የሚገኘው የህዝባችንና የሃገራችን ጠላት ወያኔ እና ወያኔ ብቻ ነው::
ባሳለፍናቸው መራር የትግል አመታት ውስጥ በቅርቡ እንዳየነው የተቃዋሚዎች በመዋሃድና አንድነትን ከመፍጠር ይልቅ እርስበእርስ መፈራረጅና መወነጃጀል ለስልጣን መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ነው:: ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገርቢኖር ከጭቆና ወደ ባሰ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ፍጹም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም።የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባትተቻችሎ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ከግብ ለማድረስ ህብረ-ብሄር የሆኑት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና ግንቦት7 እንዳደረጉት ለአንድነትና ለትብብር ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል። በአሁኑ ወቅት ይህንን ዘረኛ ስርዓት ለማውረድ በውስጥምሆነ በውጭም ትግሉ በስፋት ቀጥሎ ይገኛል:: ወያኔ እስኪወድቅና ህዝባችን ድል እስኪቀዳጅ ድረስ ሊቀጥል የሚገባው ትግልእንደመሆኑ መጠን ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ የተያዘው ትግል በአሁኑ ሰአት ወያኔን እያፍረከረከ በፍርሃት እንዲሸበር አድርጎታል::
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል! የኛ የኢትዮጵያውያን ጥያቄ አብዮታዊ የለውጥ ጥያቄ ነው። የፖለቲካ አስተዳደር ለውጥ ፣የኑሮ ውድነት የሚያላቅቅ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ለውጥ፣ በጋራ ህብረተሰባዊነትና እኩልነት ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ወይንም መንግስትእንደምናገኝ የሚያረጋግጥልን ለውጥ እንፈልጋለን፡፡ የማህበራዊና ፍትህ እኩልነት ለውጥ፣ የነጻነት እና የመብት ማግኘት ጥያቄ፣ከመንግስት ነጻ የሆነ ፍርድ ቤት፣ በሃገራችን ተዘዋውረን በፈለግነው ቦታ የመስራት እና የመኖር ጥያቄ የሚያረጋግጥልን ለውጥእንፈልጋለን፡፡ በሃገራችን ላይ የሃገራችን ባለቤቶች ስንሆን የሚገኘው ብልጽግና እና እድገት ባለቤት መሆናችንን የሚያረጋግጥልንለውጥ እንፈልጋለን፡፡ ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። ሰብአዊ መብቶች ለዲሞክሪያሲያዊስርአት ግንባታና ለአንድ ሀገር ልማትና ብልፅግና መሰረታዊ ነገሮች ተደርገው የሚወሰዱ ናቸው፡፡ ዜጎች የሃገራቸው ሃብትባለቤትና የመጠቀምም መብት እንዲሁም ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብት ሊኖረን ይገባል::
በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውንም በመቅረፍእንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከሁላችንም ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
Meron Ayele
No comments:
Post a Comment