መጋቢት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሶስት አመታት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች በመወከል ድምጹ እንዲሰማለት ጠይቆ፣ መለስ የተነፈገው ድምጻችን ይሰማ አመራሮቹን ለማስፈታትና ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ግፊት ለማድረግ እስካሁን ሲከተለው ከነበረው የትግል ስልት አንድ ደረጃ ከፍ ያለ የትግል ስልት ይፋ እንደሚያድርግ አስታውቋል።
ድምጻችን ይሰማ ” መብቴን ካላከበርክ እኔም..” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ ህዝብ ሲመረው መብቴ ይከበርልኝ ከሚል ጩኸት መብቴን ካላከበርክ እኔም ወደ ሚል ዛቻ መሄዱ አይቀሬ ነው ብሎአል።
ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ “መብቴን ካላከበርክማ” ወደሚል የትግል ምእራፍ መሸጋገሩን የሚገልጸው ድምጻችን ይሰማ፣ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች ዝርዝር መግለጫ ከመስጠት ተቆጥቧል። ይሁን እንጅ ሰሞኑን ስለሚወሰዱት እርምጃዎች መግለጫ እንደሚያወጣ አስታውቋል።
የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት አሁንም በፍትህ እጦት በእስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ ይገኛሉ።
******************************************************************************************************
No comments:
Post a Comment