#Tariku_Desaleng
ከቤተሰብ ውጪ እንዳይጠየቅ ከቶም ህክምና እንዳያገኝ….. ይህ ተመስገን የሚባል ልጅ!!
ስለ ተመስገን ለዝዋይ እስር ቤት አዛዦች የተሰጠ ትእዛዝ
ለቤተሰብ ብቻ መታየት እንዲችል ከተፈቀደ ዛሬ 18 ቀናት የሆነውን ተሜን ለማየት ዝዋይ እስር ቤት በጠዋት ደርሼ የእስረኛና የጠያቂ መገናኛ ቦታ ላይ ተቀምጬያለሁ፡፡ ተሜ ሲመጣ አየሁት እንደለማዱ በወታደሮች ተከቦ ነው የመጣሁ፡፡ አዲሱ ነገር ተሜ አረማመዱ ቀስ እያለ አንዳንዴም እየቆመ ነው የሚመጣሁ፡፡ ወታደሮቹም ሲቆም እየቆሙ ቀስ ሲል ቀስ እያሉ ነው የሚሄዱት፡፡ አጠገቤ እስኪደርስ ሁኔታውን በዝምታ እየታዘብኩ ጠበቅኩት፡፡ እየሳቀ ሰላም አለኝ፡፡ እኔ ግን ሰላምታውን በመመለስ ፋንታ “እስካሁን ህክምና አላገኝህም?” አልኩት ቀስ ብሎ እንጨቱን ተደግፎ ሲቀመጥ የህመሙን መጠን አስተዋልኩ፡፡ “ህክምና እንድታገኝ አልተፈቀደልህም ተብያለሁ” አለኝ፡፡
ድሮንስ ተሜ መብቱን መቼ አስፈቅዶ ያውቅና ?! ወታደሮቹ ተኮሳትረው ይመለከቱናል ። ተሜ በፈገግታ እያናገረኝ ነው፡፡ ተሜ ህክምና ከልክለውት አይደለም ህይወቱን ሊነጥቁት ቢመጡ እንኳን በፈገግታ ነው የሚናገራቸው፡፡ “ህመሙ እንዴት ይዞሀል?” አልኩት ። “ ጆሮዬ ልውጥ የለውም፡፡ በጀርባዬ መተኛትም ሆነ መደገፍ አልችልም እብጠቱ ጨምሯል” አለኝ፡፡ የሀገርህ መታመም አሞህ እንደተነሳህ ይገባኛል ሆኖም ዛሬም ያንተ ህመም ከሀገር ህምም በታች እንጂ በላይ አይደለም፡፡
“እማዬ እንዴት ነች?” “ደህና ነች፡፡ ትላንት አባታችን ከሞተ 14ኛ አመቱ ነው”፡፡ አልኩት አይኑ እንባ አቀረረ፡፡ አባታችን በተሜ ህይዎት ውስጥ የነበረውን ቦታ አውቃለሁ፡፡ “እማዬ ለአባታችን የነብስ ይማርና የፍትሃት ፆሎት ላንተም የፍትህ ፆሎት አደርሳለች ” አልኩት ፡፡ ዝም ተባባልን፡፡ እኔ ይህን አሰብኩ ።
“ዝዋይ እስር ቤት መታከሚያም ማገገሚያም ቦታህ አይደለም ለሀገር መሰዋት እምታቀርብበት ቦታህ እንጂ፡፡ ላንተ አይነቱ ሰው ስቃይ ለዘላለም እንደማይኖር አይነገርም፡፡ በስቃይህ ግን ዘላለም ነፃነትህን እንደምታገኝ ታውቀዋለህ፡፡ ተሜ ህመምህ እንቅስቃሴህን እንጂ የመንፈስ ልዕልናህ ላይ ስላልደረሰና ስለማይደርስም ፤ ለእስሩም ህክምና ለከለክሉህም አለመበገርህን ስላየሁ ወንድሜ ከነ ኩራቴ ከዝዋይ እስር ቤት ዛሬም ተመልሻለሁ፡፡
ተሜ እግዚአብሔር ይማርህ፡፡
29/06/07

No comments:
Post a Comment