Saturday, 28 March 2015

በመላው አለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች



ከሁሉ አስቀድሜ በያላችሁበት የከበረ ሰላምታየን አቀርባለሁ በመቀጠል ቀደም ሲል በተለያዩ እስር ቤቶች የታሰሩብንን አባላት በተመለከተ በልዩ ልዩ የመገናኛ ዘዴዎች በተለይም በFacebook ባስተላለፍኩት መረጃ አንዳድ የወገን አለኝታ የሆኑ ወገኖች የእስረኞችን ቤተሰብ በተመለከተ ያስተላለፍኩትን መልክት አንብበው ልባቸው ተነክቶ የታሳሪ ቤተሰቦችን መርዳት የጀመሩ ወገኖች አሉ በዚህ በጣም ተደስተናል እነዚህ ወገኖች ላደረጉት መልካም ተግባር በምድርም በሰማይ ትልቅ ዋጋ አለው ።ለመጭው ትውልድም በታሪክ መዝገብ የምናስቀምጠው ይሆናል ።

ሀገገራችን ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ነገሮች እየተሻሻሉ ሳይሆን እየተባባሱ መጥተዋል ለዚህም ማሳየ የሚሆነን አገዛዙ ከጊዜ ወደ ጊዜ የብረት ቀንበሩን በጫንቃችን ላይ ጭኖ በየጊዜው አፋኝ ህጎችን በማውጣት በሰላማውይ መንገድ የምንታገል የፓለቲካ ፓርቲዎችን በማን አለብኝነት በመተዳደሪያ ደንባችን የመረጥናቸውን አመራሮች በፌደራል ፓሊስ ከፅ/ቤት በማስወጣት ለአገዛዙ ታማኝ የሆኑትን (የራሱ) ሎሌ የሆኑትን ሰዎች በመሾም የምታገልበትን ሜዳ በመቀማት አፈናውን ወደ ከፋ ደረጃ አድርሶታል ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ጥር 21/2007 ዓም ምርጫ ቦርድ በመኢአድና በአንድነት ፓርቲ ላይ የተወሰደውን እርምጃ ማስታወስ በቂ ይሆናል ።

በአባሎቻችን ላይ የሚደርሰው እስራት
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በአባላት የተመረጠውን አመራር አባሮ በመኢአድ ጠቅላላ ጉባላት ያልተመረጠውን አበባው መሀሪ የሚባል ግለሰብ ከሱ ጋር አብራችሁ ስሩ በሚል ማስፈራሪያ ሲደርሳቸው የፓርቲያቸውን ውሳኔ በማክበራቸው በመላ ሀገሪቱ ያሉ አባሎቻችን በሀገሪቱ ባሉ ልዩ ልዩ እስር ቤቶች ታስረው ይገኛሉ
ከዚህ በታች የቀረበውን ዝርዝር ይመልከቱ

አላማጣ ውህኒ ቤት የታሰሩ
1, ኢያሱ ሁሴን የመኢአድ ስራ አስፈፃሚና የማህበራውይ ጉዳይ ሀላፊ አላማጣ ውህኒ ቤት የሚገኝ
2, በላይ ዳኛው 4 ቦታ ተፈንክቶ
ፍርድ ያልቀረበ አላማጣ ፓሊስ ጣቢያ የሚገኝ አባል
3, ሞላ መለሰ አላማጣ ውህኒ ቤት የሚገኝ አባል
4, ጥጋቡ ሙላት አላማጣ ውህኒ ቤት የሚገን አባል
ከጎንደር ክ/ የታሰሩ
5, ዘመነ ምህረት የመኢአድ ም/ል ፕ/ት እና የሰሜን ቀጠና ሀላፊ ሰሜን ጎንደር አ᎐ አ᎐ ማዕከላዊ የሚገኝ
6, መ/ር ጥጋቡ ሀብቴ ሰሜን ጎንደር የዞኑ ሰብሳቢ ባህርዳር ውህኒ ቤት የሚገኝ
7, ጥላሁን አድማሴ የደቡብ ጎንደር ዋና ፀሀፊ
8, ስለሽ ጥጋቤ ሰሜን ጎንደር አባል
9, ጌትነት ደሴ ሰሜን ጎንደር አባል
10, መለሰ መንገሻ ሀገር አቀፍ የወጣች ድ/ት ጉዳይ ሰሜን ጎንደር አ᎐አ᎐ ማዕከላዊ
11. አቶ ጥላሁን አበበ/ደ.ጎንደር አባል
ሰሜን ሸዋ
12, ዓስራት እሸቴ አባል
ጎጃም ክ/ሀገር
ተስፋየ ታሪኩ አ᎐አ᎐ማዕከላዊ አባል
13, መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን አባል
14, ኢ/ር መለሰ ባህር ዳር አባል
15. አቶ አንጋው ተገኘ/ምዕ.ጎጃም አባል
16, አቶ አባይ ዘውዱ/ምዕ.ጎጃም አባል
17. አቶ እንግዳው ዋኘው/ ምዕ.ጎጃም አባል
18 አቶ አባይነህ ሲሳይ/ምዕ.ጎጃም አባል
19. አቶ አለባቸው ማሞ/ምዕ.ጎጃም አባል
20. ወጣት ታጀበ አለኸኝ/ ምዕ.ጎጃም አባል
21. አቶ ዮሐንስ ገደቡ/ምዕ.ጎጃም አባል
22 አቶ አዝመራው ከፋለ/ምዕ.ጎጃም አባል
23 ወጣት ተሥፋዬ አሥማረ/ንዕ.ጎጃም አባል
24, አቶ ችሎት ጎበዜ/ምዕ.ጎጃም አባል
የቤተሰባቸውን ሁኔታ
ከተራ ቁጥር 1— 24 የተዘረዘሩት አባላት የቤተሰብ ሁኔታ ምን እንደሚመስል ለማወቅ ባደረግነው የመረጃ አሰባሰብ ስራ የታሰሩት ሁሉም አባሎች የቤተሰብ ሀላፊዎች መሆናቸውን አረጋግጠናል የቤተሰቦቻቸውም የኑሮ ሁኔታ የተመሠረተው በነዚሁ እስረኛ ቤተሰቦቻቸው የገቢ ምንጭ በመሆኑ ልጆች ከት/ቤት ሊያቋርጡ ችለዋል እናቶቻቸውም ምንም አይነት ገቢ ስለሌላቸው በልጆቻቸው የወደፌት እጣ ፋንታ እንባቸውን በማፍሰስ የናንተን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን እርዳታ በጥብቅ ይሻሉ እኛም የመኢአድ አባላት የነዚህን ቆራጥ ታጋይ እስረኛ ቤተሰቦች ሁሉን አቀፍ እርዳታ ለማድረግ በቃላችን ፀንተን እንገኛለን ። 

በእስር ላይ የሚገኙ ታጋዮቻችን ከኛ ምን ይሻሉ ?
ከላይ የቤተሰባቸውን ሁኔታ ለማየት እንደሞከርነው በእስር ላይ ከሚገኙ ልጆቻቸውና ወላጆቻው የእነሱን (የታሳሪዎቹን) እርዳታ የሚፈልጉ በመሆናቸውና ከሚኖሩበት እርቀት አንፃር ሊረዷቸው የሚችሉ አይደሉም በዚህ ምክንያት በቤተሰብ የመጠየቅ እድል አያገኙም
እስረኞቹ ምን ያስፈልጋቸዋል ?
ከላይ የቤተሰባቸውን ሁኔታ እንዳየነው በእስር ላይ ያሉ አባሎቻችን መሠረታዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ይፈልጋል እነዚህን አቅም በፈቀደ ለማድረግ እየሞከር ነው ።

ከአቅም በላይ የሆነብን ነገር

ከላይ በዝርዝር ያየናቸው ታጋዮች ለአንደኛቸውም የህግ አማካሪ (ጠበቃ) ማቆም አልቻልንም በርካታ የህግ ባለሙና ለማነጋገር ብንሞክር ፈፅሞ የምንችለው አልሆነም ለአንድ ታሳሪ ዝቅተኛ ክፍያ 50, 000 (ሀምሳ ሽህ ብር) ጠይቀውናል በዚህ ስሌት ለአንድ እስረኛ 50,000 ሀምሳ ሽህ ብር ከተጠየቅን ለ24 ሰው 1,200,000 ( አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሽህ ብር) ያስፈልገናል ማለት ይህ ገንዘብ እንኳን በኛ አቅም በብዙ ሠው የሚሸፈን አይደለም ይህንን ያክል ገንዘብ ተገኝቶ ለሁሉ ጠበቃ ማቆም የማይቻል ነው
ለህግ ባለሙያዎች
እኛ ወንድሞቻችሁ ኢትዮጵያውያን የምንደርገው ሰላማዊ የፓለቲካ ትግል በሀገራችን የጠፋውን የህግ የበላይነት በፅኑ መሰረት ላይ ለማቆም ነው ።
በመሆኑም ዛሬ በእስር ላይ የሚማቅቁት ወንድሞቻችሁ በዚህ ስርዓት ካድሬዎች የሚቀርብባቸውን የፈጠራ ክስ በህግ ግንዛቤ ማጣት መከላከል አልቻሉም ።
አንዳንዶቻችሁ ከዚህ ፍርድ ቤት ምን ፍትህ ይገኛል ልትሉ ትችላላችሁ ። እውነት አላችሁ ዳኛውም ፣አቃቤ ህጉም ፣ፓሊሱም ፣በቀጭን ትእዛዝ የሚታዘዙ የባለ ጊዜ አገልጋዮች ናቸው ።ነገር ግን ይህ ለዘላለም አይቀጥልም ። ለትውልድ ታሪካዊ ሰነድ ለፍርደኞች ማቆየት ከኛ ፍትህ ጠባቂዎች ይጠበቃል ባለጊዜዎችንም ተረኛ መሆናቸውንም ማሳየት ተገቢ ነው ብለን እናምናለን ። ስለዚህ የህግ ባለሙያዎች የድርሻችሁን ታበረክቱ ዘንድ ሙያዊ ጥሪ ቀርቦላችኋል ።

ኢትዮጵያ ወድቃ አትቀርም አሁን የዋጣት ጨለማ በማያቋርጥ ብርሀን ይለወጣል !!!!

No comments:

Post a Comment