Thursday 13 November 2014

ከቦሌ ለሚ ቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ታስረው ለስቃይ እየተዳረጉ ነው

ኀዳር (አራትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :- በቦሌ ለሚ በሚባለው አካባቢ የማሪያም ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ መደረጉን የተቃወሙ ነዋሪዎች ከፖሊሶች በደረሰባቸው ጥቃት በርካታ ሰዎች የተጎዱ ቢሆንም፣ ፖሊስ ሃይሉን አሰባስቦ በመምጣት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ይዞ አስሯል።

አብዛኞቹ ወጣቶች በኮብል ስቶን ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን፣ ፖሊስ ወደ ድርጅቶቹ በመሄድ ወጣቶችን በጅምላ ማሰሩን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ወንድሞቹ የታሰሩት አንድ ነዋሪ ለኢሳት ሲናገር በቦሌ ፖሊስ ጣቢያ ብቻ ከ1 ሺ ያላነሱ ወጣቶች ታስረው ውሃና ምግብ እንዳያገኙ ተከልክለው ሌሊቱን በብርድ አሳልፈዋል።
ጧት ውሃ ለማድረስ በሄደበት ጊዜ እጅግ የሚያሳዝን ትእይንት መመልከቱንም ነዋሪው ተናግሯል። ሌሎች ነዋሪዎች ደግሞ ወጣቶቹ በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች በመታሰራቸው ቁጥሩን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው ይላሉ።
በ7 መኪኖች ተጭነው ወደ አካባቢው የደረሱ የፌደራል ፖሊስ አባላት  በወሰዱት እርምጃ ብዙዎች እግራቸው አካባቢ ጉዳት እንደደረሰባቸው ኢሳት በትናንት ዘገባው አሰምቷል።
የማሪያም ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ እድትፈርስ የተደረገ ሲሆን፣ የቤተክርስቲያኑዋ እቃዎች በመኪና ተጭኖ ተወስዷል።

No comments:

Post a Comment