Friday 20 March 2015

ወያኔን በብዕር ሳይሆን በጠብመንጃ

ወያኔ ኢህአዴግ 24 አመታት ሊሞላው እነሆ የሁለት ወራት ገደማ አድሜ ብቻ ቀረው፡፡
በእነዚ 24 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ከላይ ለተዘረዘረው ችግር ሁሉ ምንጭ የሆነው ወያኔ-ኢህአዴግ በጉልበቱ የቀማውን ሉኣላዊ የስልጣን ባለቤትነቱን ለማስመለስ ትግል አካሂዷል፡፡ በዚህም ምክንያት እልፍ አዕላፎች ወደ ወህኒ ተግዘዋል፤ በርካቶች የሚወዷት አገራቸውን ጥለው ተሰድደዋል፤ ብዙዎች ከቀያቸውና ቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፤ ስፍር ቁጥ የሌላቸው አካላቸው ጎድሏል መንፈሳቸው ተመርዟል፤ አለፍ ሲልም ህልቆ መሳፍርቶች ውድ ህይወታቸውን ከፍለዋል…
ከወያኔ-ኢህአዴግ ጋር የተደረጉት ልዩ ልዩ ትግሎች በአብዛኛው በሰላማዊ ትግል ስልቶች ማዕቀፍ ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉ ብቻ ናቸው፡፡ በተጨሚሪም ተመጣጣኝ ባለመሆናቸው የሚፈለገውን ስር ነቀል ለውጥ በሚፈለገው ጊዜ ለማምጣት የሚያስችሉ አልነበሩም፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያን ህዝብ ዋጋ ብቻ እያስከፈሉ ኢትዮጵያ ልትወጣው ትችል ከማትመስልበት በእሳተ ገሞራ የቀለጠ አለት ከሚፈልቅበት የፖለቲካዊ፡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሸለቆ ውስጥ ተወርውራ ከገባችበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡
አዎ ብዕራቸውን አንስተው በነፃው ፕረስ ትግል ሜዳ ገብተው የተፋለሙ የዘላለም ጀግኖች ናቸው፤ ነገር ግን ወያኔ በብዕር ሳይሆን በጠብመንጃ አረር ሲያነዳቸው ሳይወዱ በግድ በረሃ ወርደዋል፡፡
አዎ ፓርቲ መስርተው ወደምኒልክ ቤተ መንግስተ በታንክ የገባውን ወያኔ በካርድ አናስወጣዋለን ብለው የታገሉ ዛሬም የሚታገሉ ብፁዓን ናቸው፤ ነገር ግን ወያኔ በካርድ ሳይሆን በክላሽን ኮቭ የእሳት ሰደድ ሲያራውጣቸው የታሰሩት ታስረው የሞቱት ሞተው የቀሩት ደግሞ ጫካ ገብተዋል፡፡
ማህበር አቋቁመው ባንድነት ለመታገል የቆረጡ እጅግ ፅኑዎች ናቸው፤ ነገር ግን ወያኔ በመርዛም አስለቃሽ ጭስ በታትኗቸው ዛሬ ተራሮችን እየማሱ ዋሻ ውስጥ ሆኗል ቤታቸው፡፡
አዎ እውነት ነው! ዛሬ ሁሉም የሰላማዊ ትግል አማራጭ በሮች በታላቅ የብረት በር ክርችም ብለው ተዘግተው በጉዋጉንቸር መቆለፋቸው ለሁሉም ሰው ግልፅ ነው፤ ነገር ግን ሁሉም የሰላማዊ ትግል መንገዶች የመጨረሻ መዳረሻቸው በረሃ መሆኑን ሁሉም ሰው በጊዜ ሊገነዘበው ይገባል፡፡
ደግነቱ ዘውዱ አበባው

No comments:

Post a Comment