Sunday 25 January 2015

በህወሃት/ኢህአዴግ ፖሊሶች አንድነት ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ ለመበተን ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ

በዛሬው ዕለት በህወሃት/ኢህአዴግ ፖሊሶች አንድነት ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ ለመበተን ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ፡፡ ድብደባው የአካል ማጉደልንም ያካተተ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ስለሺ ሐጎስና አቶ ዳግማዊ ተሰማ ራሳቸውን ስተዋል፡፡ ዳግማዊ አይኑ ማየት አልቻለም፡፡ በአንባገነኑ ስርዓት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈፀመባቸው አመራር አባላትና አባላት መካከል፡-
1. አቶ አስራት አብርሃም (የህዝብ ግንኙነት ተጠባባቂ ሃላፊ)
2. አቶ ዳንኤል ተፈራ (የውጭ ጉዳይ ሃላፊ)
3. አቶ ብሩ ብርመጅ (የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ ፀጋየ አላምረው (ምክትል አፈ-ጉባኤ)
5. አቶ አሻግሬ መሸሻ (የሰሜን ቀጠና ሃላፊ)
6. አቶ ሰለሞን ስዩም (የኤዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢ)
7. ወ/ት ልዕልና ጉግሳ (የም/ቤት አባል)
8. አቶ ዳግማዊ ተሰማ (የም/ቤት አባል)
9. ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ
10. አቶ ስንታየሁ ቸኮል (የአዲስ አበባ የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ)
11. አቶ አሸናፊ አሳምረው (የወረዳ አመራር)
12. አቶ ኢሳያስ ቱሉ (አባል)
13. ወ/ት መስከረም ያረጋል (አባል)
14. አቶ ሃይሉ ግዛው (የወረዳ ሰብሳቢ)
15. አቶ አዲሱ መኮንን (የወረዳ ሰብሳቢ)
16. አቶ ሲሳይ ካሴ (አባል)
17. አቶ ወጋየሁ አድማሴ (አባል)
18. አቶ ክብረት ሃይሉ (የም/ቤት አባል)
19. አቶ ስለሺ ደቻሳ (አባል)
20. አቶ ማሩ አካሉ (አባል)
21. አቶ ክፍሉ በዳኔ (አባል)
22. አቶ ፋሲካ አዱኛ (የወረዳ አመራር)
23. ወ/ሮ ገነት ግርማ (የወረዳ አመራር)
24. ተስፋየ ብዙነህ (አባል) ሲሆኑ በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም፡፡ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ሪፖርት እየተከታተልን እናቀርባለን፡፡



*** ጉዳት የደረሰባችው የተቃውሞ ሰልፈኞች ህክምና እየተከታተሉ ነው፡፡ የወያኔ ፖሊሶች ቀበና መዳህኔዓለም ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባት የ70 አመት አሮጊት ላይም ጉዳት አድርሰዋል *** 
በማጠቃሊያ በአንድነት ሰልፍ የተገኙ ዲፕሎማቶች በሆነው ነገር በጣም አዝነዋል። የተጎዱትን ሁኔታ ለመከታተል ወደ ሆስፒታልም ሄደዋል።የተጎዱ ወገኖቻችን ፣ «ከዚህም የበለጠ ዋጋ ለነጻነታች እንከፍላለን። እነርሱ ያላቸውን የመጨረሻ ዱላ ነው የተጠቀሙት፣ እርሱም ኃይል" ያሉት ተጎጂዎች ይህ የትግል ወኔያቸውን የበለጠ የሚያጠናከር እንጂ የሚቀንሰው እንዳልሆነ እያረጋገጡ ነው። ታጣቂዎቹ በተለይም በአቶ ስለሺ ሐጎስ እና በአቶ አሰራት አብርሃ ላይ፣ ከሌሎች በተለየ መልኩ ከፍተኛ ድብደባ ፈጽመዉባቸዋል። የሰባት ወር ነፍሰ ጡር ሴት ሆዷ ላይ ተመታለች። የሰባ አመት እናት፣ አባት ሽማግሌ ተደብደበዋል።







ቪዲዮውን ይመልከቱ 

    እስከመቼ ለወያኔ ኢህዲግ በሰላማዊ መንገድ ለሚቀርብላቸው ጥያቄ  በጭፍጨፋ እና በማሰር ይዘልቁታል ? በዛሬው እለት ድብደባና መቁሰል እስር መንገላታት የደረሰበት የኢትዮጵያ ህዝብ ለማንስ ብሎ ይመስለናል ? ባለፈው በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ተመሳሳይ ግፍ ደረሶባቸው ነበር ዛሬ ደግሞ  በአንድነት ላይ እንዲህ  አይነት ግፍ ደረሰ ᎓᎓ ተነጣጥሎ በሚደረግ ትግል በደሉን መከረውና ጭቆናው በህዝባችን ላይ እየጨመረ ነው የሚያስኬደውና ችግራችን አንድ አይነት እስከሆነ ድረስ በህብረት የችግራችንን ስር ከስሩ ለመንቀል በመተባበር መስራት ነው የሚያዋጣን ᎓᎓ 


















No comments:

Post a Comment