Thursday 15 January 2015

ከፍተኛ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ጀኔራሎች ስርዓቱ በላያቸው ላይ የሚፈፀመውን ተግባር በመቃወም ወደ ጠቅላይ ሚኒስተር ደብዳቤ መላካቸው ተገለፀ

generals of ethiopia
ከመከላከያ እስታፍ አፈትልኮ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በከፍተኛው የመከላከያ ሰራዊት እርከን ሲሰሩ የቆዩ ከፍተኛ መኮነኖች ሌተናል ጀኔራል አበባው ታደሰ፥ ሌተናል ጀኔራል ሰዓረ መኮነን፥ ሜጀር ጀኔራል ሞላ ሃይለማሪያም፥ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በላያቸው ላይ እየፈፀመው ያለውን ተግባር ትክክል አይደለም በማለት በዚህ ሳምንት ወደ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማሪያም ደሳለኝ የቅሬታ ደብዳቤ እንደፃፉ ለማወቅ ተችሏል፣
በግላቸው ከፃፏቸው ደብዳቤዎች የተወሰኑትን ለመጥቀስ አበባው ታደሰ ለምን በዚህ አገባብ ከተባረርኩ የጡረታ መብቴ ለምን አይከበርልኝም የሚል ሲሆን ሰዓረ መኮነን ደግሞ ከዚህ ቀደም ከነበርኩበት የስራ ቦታ ለምን ተነሳሁ መመለስ አለብኝ አሁን ባለሁበት የስራ ቦታ ላይ በነፃነት መስራት አልቻልኩም የሚሉና ሌሎችም የሚገኙበት ሲሆን፤ ሞላ ሃይለማሪያም በበኩሉም እኔ ምን አጥፍቼ ነው እያሰራችሁ የምታሰቃዩኝ የሚል ቅሬታ የያዘ ደብዳብቤ እንደሆነ ታውቋል፣
ሃይለማሪያም ደሳለኝ በወገኑ እኔ የህይወት ታሪካችሁን አላውቅም በማለት አባይ ፀሃየንና በረከት ስምዖንን ጠርቶ ባቀረቡት አቤቱታ ጉዳይ እንደተወያዩ የገለፀው መረጃው፤ አንዳንዶቹ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸው ስለተበላሸ መባረራችሁ የግድ ነው ሲሏቸው ለአንዳንዶቹ ደግሞ ገንዘብ አጠፋፍታችሁ ችግር እየተፈታተናችሁ በመሆኑ በተመደባችሁበት ዘርፍ ስሩ እንዳሏቸው ሊታወቅ ተችሏል᎓᎓
source: TPDM

No comments:

Post a Comment