Saturday 10 January 2015

ምርጫ ቦርድ በአንድነት ጠቅላላ ጉባዔ አልገኝም አለ



የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አንድነት ፓርቲ በጠራው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንደማይገኝ ገለጸ። ምርጫ ቦርድ በአራት ቀናት ዉስጥ አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ አመራሮችን በሚስጥር አሰጣጥ መምረጥ እንዳለበት መናገሩ ይታወሳል። ሆኖም ትላንት አርብ በምርጫዉ ታዛቢ እንዲልክ በደብዳቤ የተጠየቀው ምርጫ ቦርድ “አየለ የሚባል ሰው ሌላ የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ይደረጋል የሚል ደብዳቤ ስላሰገባ፣ በሁለት ቦታ መገኘት አንችልም” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
አንድነት ፓርቲን የማይወክል አንድ ግለሰብ ደብዳቤ ስለጻፈ፣ ምርጫ ቦርድ በአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ አልገኝ ካለ፣ ችግሩ የምርጫ ቦርድ እንደሆነ በመግልጽ ፣ ምርጫ ቦርድ ተገኝም አልተገኝም ጠቅላላ ጉባኤው እንደሚካሄድ፣ አንድነት ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ አሳውቋል።
ምርጫ ቦርድ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ራሱን እያጋለጠና እርቃኑ እየወጣ ባለበት ወቅት፣ ከአገሪቷ ሁሉ የአንድነት አባላት በጠቅላላ ጉባኤው ለመገኘት እየተመሙ ነው። በአራት ቀናት ዉስጥ የጠቅላላ ጉባኤ አባላትን ሰብሰቦ ጠቅላላ ጉባኤ መጥራቱ የፓርቲዉን ድርጅታዊ ጥንካሬም የሚያሳይ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ።

No comments:

Post a Comment